ፍ/ቤቶች እውነትን ለማውጣት ማስረጃ አስቀርበው መስማት አለባቸው ሲባል በቀረበው ማስረጃ እውነት እስከተረጋገጠ ድረስ የግድ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱያቀርቡ የሚገደድበት ምክንያት የላለ ስለመሆኑ፣ የፍትሐብሕር ክርክር ማስረጃ የሚሰማውና ፍሬ ነገር እንዱጣራ የሚደረገው በማስረጃ የሚገኘው ፍሬ ለዲኝነት አሰጣጡ እጅጉን አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝ እነ አሰፊ መንግስቱ ኮንስትራክሽን ኪራይ /ሁለት ሰዎች/ እና ግልባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር
No summary available.
ሕዲር 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ተመልክቶ ይግባኙ ተቀባይነት የለውም በማለት መሰረዙ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ሉታረምልን ይገባል በማለት 1ኛ አመልካች ጥር 29 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ፤ 2ኛው አመልካች ደግሞ ጥር 22 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የየራሳቸውን የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ክርክሩ በመኪና አደጋ ለደረሰ ጉዲት ካሳን ለማስከፈል በመዲረግ የቀረበ ክስን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ አመልካች ተከሳሽ 2ኛ አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ለጉዲዩ መነሻ ምክንያት የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ጥቅምት 27 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ ክስ በ1ኛው አመልካች ላይ በማቅረባቸው ሲሆን የክሱም ይዘት በአጭሩ፡-ንብረትነቱ የ1ኛ አመልካች የሆነው የሰላዲ ቁጥሩ 3-31175 ኢት. መኪና ንብረትነቱ የተጠሪ ደንበኛ አቶ ሙላት ሳጃ የሆነውን የሰላዲ ቁጥሩ 3-14981 የሆነ መኪና በመግጨት ላደረሰው ጉዲት ተጠሪው ለደንበኛቸው የከፈለትን ብር 159,626.68 /አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከስልሳ ስምንት ሳንቲም/ የጉዲት አድራሹ መኪና ባለቤት የሆኑት 1ኛ አመልካች ለክርክሩ ከሚወጣ ወጭና ኪሳራ ጋር እንዱተኩላቸው ለማስወሰን የቀረበ ነበር።
1ኛ አመልካችም ክሱ ደርሷቸው ህዲር 18 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ሰላዲ ቁጥሩ 3-31175 ኢት. የሆነው መኪና የ1ኛ አመልካች ንብረት ስለመሆኑ አምነው አደጋው የደረሰው በ1ኛ አመልካች መኪና ጥፊት ሳይሆን በተጠሪ ደንበኛ መኪና ጥፊት መሆኑን፤ከፖሉስ የቀረበው ማስረጃ የሚታመን አለመሆኑን፤ በ1ኛ አመልካች መኪና ላይ ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ከገለፁ በኋላ ተጠሪ ጥፊተኛውን በአግባብ ሳይለዩ ለደንበኛቸው የከፈለትን ገንዘብ 1ኛ አመልካች የመተካት ኃላፉነት የላለባቸው መሆናቸውን በመከራከሪያነት ካቀረቡ በኋላ ለጉዲቱ ኃላፉ የሚባለበት ምክንያት ካለም ለ1ኛ አመልካች መኪና የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠው የአሁን 2ኛ አመልካች ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክስዮን ማህበር ወደ ክርከሩ ገብቶ እንዱከራከር እንዱታዘዝላቸው አመልክተዋል።
የአሁን 2ኛ አመልካች የሆነው ኒያላ ኢንሹራንስ አክስዮን ማህበር ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎ በሰጠው መልስ በማስረጃነት የቀረበው የፖሉስ ሪፖርት ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም የ1ኛ አመልካች መኪና የቀኝ መስመሩን ይዞ አሸዋ ሲጭን የተጠሪ ደንበኛ መኪና ከላላ አቅጣጫ በፍጥነት መጥቶ የ1ኛ አመልካችን መኪና በመግጨቱ የደረሰ ጉዲት ነው። ይህ ሆኖ እያለ የፖሉስ ሪፖርቱ በመርማሪው ባለሙያ ሳይዘጋጅ ያላግባብ የቀረበ ነው። በምርመራ ሂደቱ ላይ የተሳተፈው የፖሉስ አባል ቀርቦ ምስክርነት እንዱሰጥ ይደረግልን ካለ በኋላ የኢንሹራንስ ሽፊን መጠኑም ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ መሆኑን በመግለፅ ክርክር አቅርቧል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራቀኙን ወገኖች የቃል ክርክር እና ማስረጃዎች በመስማት፤በጉዲዩ ላይ ቅሬታ ቀርቦበት ድጋሚ ምርመራ ተደርጓል የተባለ በመሆኑ ይኸው የፖሉስ የምርመራ መዝገብ እንዱቀርብ፤እንዱሁም ስለ ሁኔታው ያውቃለ የተባለት የፖሉስ አባል ቀርበው ምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ በማድረግ ካጣራ በኋላ አደጋው የደረሰው በ1ኛ አመልካች መኪና ጥፊት ለመሆኑ በቀረበው ምስክሮች ቃል ከፖሉስ መምሪያ በተጻፈ ደብዲቤ እንዱሁም ፍርድ ቤቱ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ያመች ዘንድ አስቀርቦ ከሰማው ምስክር ቃል መገንዘብ መቻለን ገልፆ የመኪናው ባለቤት የሆኑት 1ኛ አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ያለባቸው በመሆኑ፤ 2ኛው አመልካች በበኩላቸው ለ1ኛው አመልካች ተሽከርካሪ በሰጡት የኢንሹራንስ ሽፊን መነሻነት ኃላፉ ሆነው በመገኘታቸው ሁለቱም አመልካቾች በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ የደረሰውን ጉዲት ብር 159,626.68/አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስደስት ብር ከስልሳ ስምንት ሳንቲም/ ጉዲዩ ውሳኔ ካገኘበት ከጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ክፍያው ተፈፅሞ እስኪጠናቀቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ እና ከክርክር ወጭ ብር 1,000/አንድ ሺህ ብር/ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ይክፈለ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ የአሁን አመልካቾች ቅር በመሰኘት የየራሳቸውን የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት ይግባኙን ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንን ዲኝነት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የስር ፍ/ቤቶች ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል ሲሆን 1ኛ አመልካች በዚህ የሰበር መዝገብ እንዱሁም 2ኛ አመልካች በሰበር መዝገብ ላይ የየራሳቸውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። የ1ኛው አመልካች የሰበር አቤቱታ በአጭሩ፡- የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ማስረጃን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን፤ለውሳኔው መሰረት የሆነው የፖሉስ ሪፖርትም በሀሰት የተዘጋጀ መሆኑን፤ለደረሰው አደጋ ጥፊተኛው የተጠሪ ደንበኛ መኪና ስለመሆኑ የተረጋገጠ ማስረጃ አቅረበው በበቂ ሁኔታ ክሱን ማስተባበላቸውን፤ በድጋሚ የተሰራው የትራፉክ ምርምራ ለውሳኔው መሰረት መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን፤የ1ኛ አመልካች ማስረጃዎች የታለፈበት ምክንያት በግልፅ አለመጠቀሱን፤ ኒያላ ኢንሹራንስ ወደ ክርክሩ ገብቶ እስከ ብር 100,000 ለ1ኛ አመልካች የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠ መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሮ እያለ የ1ኛ አመልካች ኃላፉነት እስከ ብር 159,626.68 በአንድነትና በነጠላ መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ እንዱታረምላቸው ያቀረቡት ነው። 2ኛው አመልካች በመዝገብ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ደግሞ በይዘቱ ከ1ኛው አመልካች ቅሬታ ጋር የሚመሳሰል ሆኖ በአጭሩ፡- የሥር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ አለመወሰኑን፤የአመልካቾች ማስረጃ ውድቅ የተደረገው በተገቢው ምክንያት ላይ ተመስርቶ አለመሆኑን፤ተጨማሪ ማስረጃ ለማቅረብ የጠየቁበት የማስፈቀጃ ጥያቄ ያላግባብ ውድቅ መደረጉን የሚመለከት ነው።
ሰበር አጣሪው ችልቱም ሁለቱንም መዝገቦች መርምሮ በዚህ ጉዲይ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች አንፃር አመልካቾች የደረሰውን ጉዲት የመተካት ኃላፉነት አለባቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት ይህ የሚታለፍ ከሆነ የኃላፉነት መጠኑን አስመልክቶ በአንድትና በነጠላ ይክፈለ የተባለበትን አግባብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪ መልሳቸውን አመልካቾችም የመልስ መልሳቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል።
ክርክሩ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ተጠናቋል። እኛም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንፃር ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም አመልካቾች የሚከራከሩት ጉዲት መድረሱን ሳይክደ ጉዲቱ በተጠሪ ደንበኛ መኪና አሽከርካሪ ጥፊት የደረሰ በመሆኑ 1ኛው አመልካችም ሆነ ለእርሱ የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠው 2ኛው አመልካች ጉዲቱን ለመካስ ኃፉነት የለብንም፤ በዚህ ረገድ በማስረጃ ያረጋገጥነው ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ባግባቡ ታይቶ የተወሰነ አይደለም የሚል የጋራ ክርክር ያቀረቡ ሲሆን 1ኛው አመልካች ኃላፉነት አለብህ የምባል ቢሆን እንኳን ብር 100,000 በ2ኛው አመልካች ተሸፍኖ ቀሪውን 2ኛው አመልካች እንዱከፍል ሉወሰን ይገባል እንጂ ሁለቱ አመልካቾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ሙለን ጉዲት እንድንክስ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የለውም በሚል አቅርበዋል። 2ኛው አመልካችም ተጨማሪ ማስረጃ እንድናቀርብ ጠይቀን ሳይፈቀድ ቀርቷል የሚል ቅሬታ አቅርበዋል። ስለሆነም ከግራቀኙ ወገኖች ክርክር አንፃር ሲታይ የሥር ፍርድ ቤት ኃላፉነት ያለበትን ወገን በመለየት ረገድ የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራርና በማስረጃ የማጣራት ስህተት አለ ወይስ የለም? 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ሙለውን የካሳ መጠን ለተጠሪ እንዱከፍለ መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? በአጠቃላይ የሥር ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት አለ ወይስ የለም? የሚለት ነጥቦች ምላሽ ማግኘት ያለባቸው መሆናቸውን ተገንዝበናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ ስንመለከት ከመዝገቡ እንደተረዲነው ንብረትነቱ የ1ኛው አመልካች የሆነው ሰላዲ ቁጥሩ 3-31175 እና ንብረትነቱ የተጠሪ ደንበኛ አቶ ሙላት ሳጃ በሆነው የሰላዲ ቁጥሩ 3-14981 በሆነው ተሸከርካሪ መካከል በተፈጠረ የግጭት አደጋ በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ጉዲት መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን በአመልካቾች በኩልም ቢሆን የቀረበው ክርክር የተጠሪ ደንበኛ መኪና አልተጎዲም የሚል ሳይሆን የ1ኛ አመልካች ተሸከርካሪ ጥፊት የላለበት በመሆኑ ካሳውን ለመክፈል ኃላፉነት የለብንም በማለት መከራከራቸውን ተገንዝበናል። ከሁለቱም አመልካቾች ክርክር መረዲት እንደተቻለው የተጠሪ ደንበኛ መኪና በፍጥነት መጥቶ ቆሞ አሸዋ ሲጭን የነበረውን የ1ኛ አመልካች መኪና በመግጨት የደረሰ ጉዲት ለመሆኑ ይከራከራለ። በጉዲዩ ላይ በወቅቱ ፕላን የማንሳትና የምርመራ ሥራ ተከናውኖ እንደነበርና ይህ የትራፉክ ፕላን አነሳስ እና የምርመራ ተግባር ችግር እንዲለበት ለሚመለከተው የኦሮሚያ ክልል ፖሉስ ኮሚሽን አቤቱታ ቀርቦ ላላ ጉዲዩን በድጋሚ የሚያጣራ አምስት አባላት ያለት ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ ተደርጎ እንደነበር አመልካቾች ሳይክደ አቅርበን ያሰማናቸው የመጀመሪውን ምርመራ ያከናወኑ አባላትን በማስረጃነት አቅርበን አሰምተን እያለን ማስረጃችን ያለ ምክንያት ተቀባይነት አጥቷል በሚል ይከራከራለ። ተጠሪ በበኩላቸው አስቀድሞ የተደረገው ምርመራ ችግር እንዲለበት ታምኖበት እንደገና እንዱጣራ በመደረጉ ምክንያት የኋለኛው መርማሪ ቡድን ያገኛቸውን ማስረጃዎች መሰረት አድርገው የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት ይከራከራለ።
በመሰረቱ ፍርድ ቤቶች ተገቢውን የክርክር አመራር መከተል እንዲለባቸው፤ጉዲዩን ባግባቡ በማጣራት የግራቀኙን ወገኖች ማስረጃ በማስማትና ለፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ በሆነም ጊዜ ተጨማሪ ማስረጃ አስቀርበው በመስማትና በማጣራት ውሳኔ ሉሰጡ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ህ/ቁ 145፤264፤266፤267፤345 እና በላልችም በግልፅ ተመልክቶ የሚገኝ ቢሆንም በፍትሐብሕር ክርክር ማስረጃ የሚሰማውና ፍሬ ነገሩ እንዱነጥር የሚደረገውም በማስረጃ የሚነጥረው ፍሬ ነገር ለዲኝነት አሰጣጡ እጅጉን አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ፍርድ ቤቶች እውነትን ለማውጣት ማስረጃ አስቀርበው መስማት አለባቸው ሲባል በቀረበው ማስረጃ እውነቱ እስከተረጋገጠ ድረስ የግድ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱያስቀረቡ የሚገደደበት ምክንያት ይኖራል ማለት አይደለም። ስለሆነም ተጨማሪ ማስረጃ ለማቅረብ ማስፈቀጃ አቅርበን መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በሚል 2ኛው አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
አመልካቾች ያቀረብነው ማስረጃ በምክንያት ውድቅ አልተደረገም በሚል የሚያቀርቡትን ክርክር በተመለከተ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይዘት የሚያመለክተው በአመልካቾች በኩል የቀረበው ክርክርና ማስረጃ ከተጠሪ ክርክርና ማስረጃ በተሻለ ሁኔታ ሉታመን የማይችል መሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ውድቅ የተደረገ መሆኑን ነው። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ ማስረጃን የማጣራት የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን ያለው የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተገቢውን ጭብጥ ይዞ ጉዲዩን በማስረጃ ለማጣራት የግራቀኙን ወገኖች ማስረጃ ሰምቷል።
አስፈላጊ ነው ብል ያመነበትንና ሰነድና የሰው ምስክርም አስቀርቦ ሰምቷል። በአስፈላጊነቱ ላይ ያላመነበትን ማስረጃ ሳያስቀርብ ቀርቷል። ከዚህ በመነሳትም ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበትን ወገን ለመለየት በግራቀኙ ወገኖች የቀረቡትንና ለፍትህ አስጣጥ አመችነት ፍርድ ቤቱ ያስቀረባቸውን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ እንዱሁም የራሱን ምክንያት በመሰጠት አደጋው ለመድረሱ ከማረጋገጡም በላይ አደጋውንም ያደረሰው የ1ኛ አመልካች መኪና የሆነው አሸዋ ሲጭን የነበረው የሰላዲ ቁጥሩ 3-31175 ኢት. የሆነው መኪና ለመሆኑ አረጋግጧል። ከዚህ በመነሳትም በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 2081(1) መሰረት የመኪናው ባለቤት የሆነው 1ኛው አመልካች ካሳውን ለመክፈል ኃላፉ መሆናቸውን ሲወስን 2ኛው አመልካች ከ1ኛው አመልካች ጋር የኢንሹራንስ ውል ያላቸው ለመሆኑ ስላልተካደ ኃላፉነት ያለባቸው ለመሆኑ ወስኗል።
ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤት ተገቢውን ጭብጥ በመመስረት በግራቀኙ ወገኖች የቀረቡትን ማስረጃዎች እንዱሁም አስፈላጊ ነው ብል ያመነበትን ማስረጃ አስቀርቦ በመስማትና በመመርመር መወሰኑን መዝገቡ ስለሚያስረዲ በሥር ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካቾች ኃላፉ መሆናቸው ከተረጋገጠ የኃላፉነት መጠናቸውን መመልከቱ ተገቢነት ያለው ይሆናል። ተጠሪ ለደንበኛቸው የከፈለትን ብር 159,626.68/አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከስልሳ ስምንት ሳንቲም/ 1ኛ አመልካች እንዱተኩላቸው ዲኝነት ጠይቀው ላቀረቡት ክስ በ1ኛው አመልካች በኩል የቀረበ የካሳ መጠንን የሚመለከት ክርክር የለም። 2ኛው አመልካች በሰጡት መልስ ለ1ኛው አመልካች መኪና የሰጡት የኢንሹራንስ ሽፊን እስከ ብር 100,000/አንድ መቶ ሸህ ብር/ እንደሆነ ገልፀው መልስ አቅርበዋል። የ2ኛው አመልካች ኃላፉነት ለ1ኛው አመልካች ከሰጡት የኢንሹራንስ ውል የሚመነጭ ከመሆኑም በላይ መጠኑም በውለ ልክ የሚወሰን ነው። ይህ ከሆነ የሁለቱ አመልካቾች ኃላፉነት መጠን የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት ተብል የመወሰኑን አግባብነት መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። ከዚህ አንፃር 2ኛው አመልካች ለተጠሪ እስከ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሸህ ብር/ የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠ መሆኑ እስካልካደ ድረስ ከተወሰነው የካሳ መጠን በዚሁ ገንዘብ ልክ ሉከፍለ የሚገባቸው ይሆናል። 1ኛው አመልካች ደግሞ ቀሪውን የውሳኔ መጠን ሉከፍለ ይገባል ማለት ነው። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ የደረሰውን ጉዲት መጠን ብር 159,626.68/አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከስልሳ ሳንቲም/ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ሁለቱም አመልካቾች በአንድነትና በነጠላ ይህንኑ ገንዘብ ከጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድና ከብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ የክርክር ወጭ ጋር ይክፈለ የተባለበት አግባብ የ1ኛ አመልካችንና የ2ኛ አመልካችን የኢንሹራንስ ውል ግንኙነትና 1ኛ አመልካች 2ኛውን አመልካች ወደ ክርክሩ እንዱገቡላቸው የጠየቁበትን ዓላማ ያላገናዘበ በመሆኑ በመጠኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ ማስረጃ የመመርመር፤ የማጣራትና መመዘን ሥልጣን የተሰጣቸው የሥር ፍርድ ቤቶች በግራቀኙ ተከራካሪ ወገኖች በኩል የቀረቡ ክርክሮችን መሰረት በማድረግ ተገቢውን ጭብጥ ይዘውና አጣርተው ከፍትሐ ብሓር ጉዲዮች ማስረጃ ምዘና አንፃር በመመልከት አመልካቾች ያቀረቡት ክርክርና ማስረጃ የሚያሳምን አለመሆኑን ጠቅሰው ውድቅ በማድረግ የተጠሪን ማስረጃ በመቀበል አመልካቾች የደረሰውን ጉዲት የመካስ ኃላፉነት ያለባቸው በመሆኑ ላይ የደረሱበት ድምዲሜ የሚነቀፍበት ምክንያት አልተገኘም። በልላ በኩል 2ኛው አመልካች ለ1ኛው አመልካች እስከ ብር 100,000 ኢንሹራን ሽፊን የሰጡ ለመሆናቸው በመልሳቸው አምነው አቅርበው እያለ ከተወሰነው የካሳ መጠን ውስጥ ብር 100,000 ከነወለደ በ2ኛው አመልካች እንዱሸፈን ሆኖ ቀሪውን 1ኛው አመልካች እንዱከፍለ መወሰን ሲገባው ሁለቱም አመልካቾች ሙለውን ካሳ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ የተሰጠው ውሳኔ ክፍል ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም የሚከተለውን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሕዲር 01 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካቾች በተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለባቸው መባለና በዚህ ጉዲት ምክንያት የመጣ ካሳ ብር 159,626.68 ከጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍል እስኪያልቅ የሚታሰብ በዓመት 9% ህጋዊ ወለድና ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ የክርክር ወጭ ለተጠሪ ሉከፈል ይገባል መባለ ባግባቡ ነው ብለናል።
አከፊፈለን በተመለከተ ከዚሁ የካሳ መጠን ውስጥ ብር 100‚000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከጥቅምት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፊል እስኪያልቅ ድረስ ከሚታሰብ በአመት 9% ወለድ ጨምሮ በ2ኛው አመልካች የሚሸፈን ሆኖ ቀሪው የካሳ መጠን ከነወለደና የክርክር ወጭ በ1ኛው አመልካች እንዱከፈል ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ችልት ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈፅም ተወስኗል፤ ይጻፍ።
በዚህ ችልት ክርክር ለወጣ ወጭና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ የሰበር መዝገብ አካል ይሁን ብለናል።
No topics extracted.