ሑሳብ አስተሣሣቢ የመመደብ ሥልጣን ያለው ዋናው ጉዲይ በዲኝነት አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለውና የግራ ቀኙን ክርክር የሰጠው ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ አንድን ጉዲይ ለመወሰን የቀረቡት /የተሰጡት/ የሙያ አስተያየቶች ተቃራኒ ይዘት ባለበት ሁኔታ የአንድን ባለሙያ አስተያየት ብቻ በመቀበል መወሰን ተገቢ ስላለመሆኑ፣ ( የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136፣145/1/፣246፣248 እና 264
No summary available.
ህዲር 19 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኸሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጰውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አምሣለ ወርቁ ኮንስትራክሽን ድርጅት ተጠሪ፡- ትድሃር ኤስካቬሽንና ኤርዝ ሙቪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
1.ጉዲዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍትብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 188 መሰረት በመዝገብ ያጣራውን የገንዘብ መጠን ውድቅ በማድረግ፣ በራሱ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና ተገቢውን ማጣሪያ በማድረግ፣ ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለው ብር 1,500,144/አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር/ ብቻ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ ይግባኝ ሰሚል ችልት ማፅናቱ በህግ አግባብ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ነሐሴ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ተቆጣጣሪ መሃንዱሱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ጥልኝ ሄዶል እኔም ካለተቆጣጣሪ መሃንዱሱ መሥራት ስለማልችል 10 ቀናት ያህል ማሽነሪዎችን ያቆምኩ ሲሆን ተከሳሹን ስጠይቀው ከዋናው ኮንተራክተር ጋር ያደረገው ንዐስ የሥራ ውል የተቋረጠ መሆኑን ገልጿል። ስለሆነም ተከሳሽ ከሳሽ ለ30 ቀናት ሰርቼ 54,000 ሜትር ኪዩብ ያነሳሁበትንና ለአስር ቀናት ማሽኖች የቆሙበት በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጣራው መሰረት ብር 5,800,000 ማሽኖች ከቆሙበትና ከቫት ጋር የነዲጅ ወጪ በመቀነስ ተከሳሽ እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
በውላችን መሰረት ከሳሽ በቂ ማሽነሪ በማሰማራት በቀን 5,500 ኪዩብ ድንጋይና አፈር ለማንሳት ተስማምቷል። ሆኖም ከሳሽ በውለ የተገለፀውን ስልሣ ቀን ለማጠናቀቅ ስድስት ቀናት ሲቀረው የውል ግዳታውን ለመፈፅም ባለመቻለ ውለ እንዱቋረጥ ተደርጓል። ከሳሽ በክሱ የገለፀውን 54,000 ሜትር ኪዩብ አፈርና ድንጋይ አላነሳም። ዋናው ኮንትራክተር ሲሲሲሲ ከተከሳሽ ጋር የነበረውን የሥራ ውል አቋርጦ ከሳሽ የሰራውን ሥራ ሲረከብ የተሰራው ጠቅላላ የእስካቬሽን ሥራ 8997 ሜትር ኪዩብ መሆኑንና ከዚህ ውስጥ ከሳሽ የሰራው 2416.79 ሜትር ኪዩብ መሆኑ ተረጋግጧል።ከሳሽ ይህንን ሥራ ለመምራት የወሰደው 5021 ሉተር ነዲጅ ሲሆን ከሳሽ ከሰራው ሥራ የወሰደው የነዲጅ ዋጋ ሲቀነስ ቀሪው ብር 195,660.50/አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሸህ ስድስት መቶ ስልሳ ብር ከሃምሣ ሣንቲም/ ነው። ስለዚህ ተከሳሽ ያቀረቡት ገንዘብ የላለ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልን በማለት መልስ ሰጥቷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር በገባው የሥራ ውል መሰረት ለሥራ ያሰማራቸው ማሽነሪዎች በቀን ሥምንት ሰዓት ሰርተው ምን ያህል መጠን ያለው የኢስካቬሽን ሥራ መሥራት እንደሚችለ ከሙያ አንፃር መርመረው አሰተያየት እንዱሰጡበት ለአራት የተለያዩ ድርጅቶች ትእዛዝ ሰጥቷል። የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ከደረሳቸው መካከል የኦሮሚያ ክልል ከተማና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ለመገመት እንደማይችል ገልፆ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ ሳፍኮን ኮንስትራክሽን የተባለው ድርጅት በቀን ከ320 ሜትር ኪዩብ እስከ 384 ሜትር ኪዩብ ይሆናል በማለት በፅሐፍ መልስ ሰጥቷል። አረጋ አባተ ኮንሰትራክሽን የተበለ ድርጅት በቀን 1400 ሜትር ኪዩብ ሉያነሱ ይችላለ በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን የምስራቅ ሸዋ ኢንደስትሪና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በቀን 1120 ሜትር ኪዩብ ማንሳት ይችላለ በማለት በጽሐፍ መልስ የሰጠ መሆኑን የክልል ጠቅለይ ፍ/ቤት በውሣኔው በግልፅ አስፍሮታል።
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳፍኮን የተባለው ድርጅት ማሽነሪዎች በቀን 320 ሜትር ኪዩብ ያነሳለ በማለት የሰጠውን መግለጫ በመወሰድ አመልካች በአርባ ስድስት ሜትር ኪዩብ ድንጋይና አፈር ለማንሳት የሚችል በመሆኑ የአንድ ሜትር በብር 102 /አንድ መቶ ሁለት ብር/ ሑሳበ ተከሳሽ ለከሳሽ ብር 1,500,144/አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር/ ተከሳሽ ለከሳሽ ይክፈል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ ባቀረበው ይግባኝ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቷል። አመልካች በይግባኝ ሰሚው ችልት በመልስ ሰጭነት ቀርቦ ለይግባኝ ባይ /ተጠሪ/ ይግባኝ ቅሬታ መልስ ከመስጠቱ በተጨማሪ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 340 መሰረት መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን መስቀለኛ ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። በልላ በኩል ይግባኝ ሰሚው ችልት የተጠሪን ይግባኝ በመቀበልና ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር በመመርመር ይግባኝ ባይ /ተጠሪ/ ለመልስ ሰጭ የምከፍለው ብር 195,660.05 /አንድ መቶ ዘጠና አምሰት ሺ ስድስት መቶ ስልሣ ብር ከዜሮ አምስት ሣንቲም / ብቻ ከዚህ ውስጥ መልስ ሰጪ /አመልካች /ከይግባኝ ባይ /ተጠሪ/ የወሰደው /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ቅድመ ክፍያ ያለ በመሆኑ መልስ ሰጪ /አመልካች/ ከይግባኝ ባይ ከሰራው ስራ በላይ ገንዘብ የወሰደ በመሆኑ ይግባኝ ባይ ለመልስ ሰጪ የሚከፍለው ገንዘብ የለም በማለት ሰጥቷል።
አመልካች መስከረም 10 ቀን 2007 ዓ.ም ፅፍ ባቀረባቸው የሰበር አቤቱታ የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኦዱተሮች መድቦ፣ አመልካች ከተጠሪ የሚጠይቀው ብር 5,828,590/አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ብር/ ያለው መሆኑን በማረጋገጥ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሰ ያቀረብኩት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 188 መሰረት ሑሳብ አስተሳስቦ የተሰጠውን ውሣኔ በማስረጀነት በማያያዝ ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ማስረጃ ውድቅ በማድረግ ላላ የባለሙያ አስተያየት መጠየቅና ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ የሰጠው የቻይና መንገድ ሥራ ኩባንያ /CCCC/ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፃፈውን ደብዲቤ ነው። ሆኖም የቻይና መንገድ ሥራ ኩባንያ ደብዲቤውን የፃፈው ከተጠሪ ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ መሆኑን በደብዲቤ የገለፀውን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሣያገናዝብ ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሮ የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባፀደቀውና ተጠሪ በይግባኝ ያላሻረው ብር 5,828,509.76 /አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ዘጠኝ ብር ከሰባ ስድስት ሣንቲም/ እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ባቀረበው መልስ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና ስህተት የፈፀመበት መሆኑን በሰፉው በመግለፅ ነው። የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና ስህተት በዚህ ሰበር ችልት የሚታይና የማይታረም በመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ያሰናብተን፣ አመልካች የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሑሳብ ባለሙያዎችን በመመደብ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ተጠሪ የመክፈል ሃላፉነት ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። በመሰረቱ አመልካችና ተጠሪ የምንከራከርበት ጉዲይ የፋዳራል ጉዲይ ነው። የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጠኑ በአመልካች ክስ ማመልከቻ የተገለፀውን የፋዳራል ጉዲይ የመዲኘት ሥልጣን የለውም። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዲኘነት የማየት ስልጣን በላለው ጉዲይ ሑሳብ ታስቦ እንዱቀርብ ለኦዱተሮች የሰጠው ትአዛዝም ሆነ ኦዱተሮች ያቀረቡለትን ሪፖርት በማፅደቅ የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሣኔ ምንም አይነት የህግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኘ። አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችልት የቻይና መንገድ ሥራ ድርጅት የፃፈውን ደብዲቤ በአግባቡ ያልመዘነ መሆኑን በመግለፅ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የማስረጃ ምዘና ስህተት ክርክር ነው ይህም የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ ላደረግልኝ ይገባል በማለት ተከራክሯል።አመልካች መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን ጉዲይ ለመወሰን፣ የሚከተለትን የህግ ጭብጦች በዝርዝር ማየትና መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በዝርዝር መታየት ያለባቸው ጭብጦችም የሚከተለት ናቸው።
ሀ/የአሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የሑሳብ ማስተሳሰብ ጥያቄ ተቀብል ኦዱተሮች በመመደብና ኦዱተሮች አጣርተው ያቀረቡለትን ሪፖርት በመዝገብ ታህሳስ 24 ቀን 2005 ዓ.ም በማፅደቅ የሰጠውን ውሣኔ እንደማናቸውም የሰነድ ማስረጃ መዝነው ውድቅ ማድረጋቸው ህጋዊ አሰራርን የተከተለ ነው ወይስ አይደለም? አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ሪፖርቱን በማፅደቅ የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ያልተሻረ በመሆን ሙለ በሙለ ክሱን ለማስረዲት ተቀበይነት ያለው ማስረጃ ተደርጏ መወሰድ አለበት በማለት ያቀረበው ክርክር የሕግ መሰረት አለው ወይስ የለውም?
ለ/ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የቻይና መንገድ ሥራ ኩባንያ CCCC የፃፈውን ደብዲቤ ተቀበይነትና የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ ነው በማለት ለውሣኔው መሰረት ማድረግ የማስረጃ አመዛዘን መርሆዎችን የተከተለ ነው ወይስ አይደለም? ይግባኝ ሰሚው ችልት ደብዲቤውን የማስረጃ አቀባበልና አመዛዘን ሥርዓትና መርህ ተከትል አልመዘነም ቢባል ውጤቱ ምን ይሆናል?
ሐ/የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትና የፋራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አስገዲጅ የሆኑ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ድንጋጌዎችን በመከተል መጣራት የሚገባቸው አከራካሪ ጭብጦች በአግባቡ እንዱጣሩ በማድረግ ውሣኔ ሰጥተዋል ወይስ አልሰጡም?የሚለትን ጭብጦች አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መመርመር የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ የሚፈለግበት ገንዘብ ተጣርቶ ቀርቦ እንዱከፈል ውሣኔ ይሰጥልኝ የሚል ይዘት ያለው አይደለም። አመልካች ያቀረበው ጥያቄ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኦዱተሮች በመመደብ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 188 መሰረት ሑሳብ ያስተሳስበኝ የሚል ይዘት ያለው ነው። ይህም አመልካች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ጥያቄ ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 300 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 306 በተደነገገው ሥርዓት ወይም ከፍትሐበሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 307 እስከ ፍታብሓር ሕግ ቁጥር 314 በተደነገጉት ልዩ ሁኔታዎች የማይሸፈንና በተፊጠነ ሥነ ሥርዓት /Accelerated procedures/ ታይቶ ውሣኔ የሚሰጥበት ጉዲይ እንዲልሆነ ከህጉ ድንጋጌዎች ዝርዝር ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
10.የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪን ሑሳብ የሚያስተሳስቡ ኦዱተሮች የመደበውና የኦዱተሮች ሪፖርት ያፀደቀው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ቁጥር 188 መሰረት እንደሆነ በመዝገብ ታህሳስ 24 ቀን 2005 ዓ.ም የኦዱተሮችን ሪፖርት ባፀደቀበት ውሣኔ ጠቅሷል። ይህም በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 188 ሑሳብ አስተሳሳቢ የመመደብ ሥልጣን ያለው ዋናው ጉዲይ በዲኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለውና የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤት ነው ወይስ ዋናው ጉዲይ በዲኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን የላለው ጥያቄ የቀረበለት ማናቸውም ፍርድ ቤት የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 188 በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ በምዕራፍ ስድሰት ስለ ፍርድና ስለ ትእዛዝ በሚለው ርዕስ ውስጥ የተደነገገ ድንጋጌ ነው።
ስለ ፍርድና ስለ ትእዛዝ የተደነገጉት ድንጋጌዎች በክፍል አንድና በክፍል ሁለት የተከፈለ ሲሆን በክፍል አንድ ሥር አጠቃላይ ድንጋጌዎች ከፍትሐበሓር ሥነ ሥርዓት ቁጥር 180 እስከ ፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ 184 የተደነጉትን ድንጋጌዎች የሚያካተት ነው።
የምዕራፍ ስድሰት ክፍል 2 በአንድ አንድ ውሣኔ ስለሚሰጥ የተለየ መመሪያ የሚደነገግበት ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 188 እስከ ፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር191 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች የያዘ ነው፡ 11.ከላይ የገለፅነው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ምዕራፍ ስድስት በክፍል አንድና በክፍል ሁለት ሥር የተደነገጉት ድንጋጌዎች፣ ጉዲዩ በዲኝነት አይቶ፣ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ፍርድ ሲሰጥ ሉከተላቸው የሚገቡ ሥነ ሥርዓቶችንና በዋናው አከራካሪ ጭብጥ ላይ ፍርድ ከሰጠ በኋላ በቀጣይነት ሉሰጣቸው የሚገቡ የተለያዩ ትእዛዞችን የሚያሳዩ ድንጋጌዎች ናቸው።ከዚህ አንፃር በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ምዕራፍ ስድስት በጠቅላላውና ተከራከሪዎቹ ሑሳብ ተሰርቶ እንዱቀርብ በፍትሐብሕር ሥነ ሥዓርዓት ሕግ ቁጥር 188 መሰረት ልዩ ተፈፃሚነት ያለው ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ከሳሽና ተከሳሽ ያቀረቡትን የተሟላ ክርክር ለማሰማትና ማስረጃ በመቀበልና በመመዘን ከሳሽና ተከሳሽ በሚከራከሩበት ጉዲይ ላይ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 3 መሰረት ፍርድ ለሚለው ቃልና ትአዛዝ ለሚለው ቃል በተሰጠው ትርጉምና ከፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 280 እስከ ፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 291 የተደነገጉትን ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ጉዲዩን በዲኝነት አይቶ ፍርድ እና ልዩ ተፈፃሚነት ያለው ትእዛዝ የመስጠት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የሚመለከት ሥርዓት ነው።
12 ከዚህ አንፃር የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 188 አንድ ሰው ጉዲዩን በዲኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ለላለው ማናቸውም ፍርድ ቤት ከተከሳሽ ጋር ሑሳብ እንድተሳሰብ ትእዛዝ ይሰጥልኝ የሚለውን ጥያቄ ተቀብል ለማስተናገድ የሚያገለግል የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ አይደለም።የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 188 ድንጋጌ ይዘትም ሆነ መሰረታዊ ዓላማ አንድ ሰው ከላላ ሰው አለኝ የሚለውን ሑሳብ በባለሙያ ተጣርቶ እንዱቀብር ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን ለላለው ለማናቸውም ፍርድ ቤት ጥያቄ እንዱያቀርብ ለመፍቀድ የተደነገገ የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌ አይደለም። በአንጻሩ ጉዲዩን በዲኝነት የማየት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ፍርድ ከሰጠ በኃላ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ገንዘብ መተሳስብን የሚጠይቅ ሲሆን፣ ሑሳቡ ተሰልቶ እንዱቀርብ ቀጣይ ትዕዛዝ ላሰጥ ስለሚችልበት ሁኔታ የሚደነግግ ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበትን ጉዲዩ በዲኝነት አይቶ የመወሰን ስልጣን የላለው መሆኑ ህገ መንግስቱን አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 4 እና የአዋጅ ቁጥር 25/1988 ድንጋጌ በማየት ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዲኝነት አይቶ ለመወሰን በማይችለው ጉዲይ ላይ የሑሳብ ባለሙያዎች የአመልካችንና የተጠሪን ሑሳብ ሰርተው ሪፖርት እንዱያቀርቡለት የሰጠው ትዕዛዝና ሪፖርት ከቀረበለት በኋላ ሪፖርቱን በማጽደቅ የሰጠው ውሳኔ የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 188 ደንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ ውጭ የሰጠውና በፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር ‛ፍርድ“ ‛ውሳኔ“ እና ትዕዛዝ ለሚለት ቃላት የተሰጠውን ህጋዊ ትርጉም የማያሟላ መሆኑን ተረድተናል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ኦዱተሮችን መድቦ፣ ኦዱተሮች አጣርተው ያመጡለትን ሪፖርት በማጽደቅ የሰጠው ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ፣ ህጋዊ አስገዲጅነትና ተፈጻሚነት እንዲለው የፍርድ ቤት ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ለማየት የሚያስችል ባህሪም ሆነ ይዘት የለውም። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድምዲሜ ህጋዊ ስርዓትን የተከተለ አይደለም። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድምዲሜ የሚነጻጸረው ጉዲዩን የማየት ስልጣን የላለው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ከሰጠው ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ጋር ሳይሆን፣ ከፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 132 እስከ ፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 135 በተዘረጋው ስርዓት መሰረት አከራካሪ ፍሬ ጉዲይ በምትክ ዲኛ ተጣርቶ እንዱቀርብ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ምትክ ዳኞች በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 134 መሰረት ከሚያቀርቡት የሑሳብ ምርመራ ውጤት ጋር ነው።
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሑሳብ አጣርተው እንዱቀርቡ የተመደቡ ኦዱተሮች በመጀመሪያ ደረጃ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተመደቡ ምትክ ዳኞች ወይም ባለሙያዎች አይደለም። አመልካችንና ተጠሪን የሚያከራክራቸው መሰረታዊ ጭብጥ አመልካች ከተጠሪ ጋር በገባው የኮንስትራክሽን ስራ ውል መሰረት፣ መንገድ ከሚሰራበት ስፍራ ቆፍሮ ያነሳው ድንጋይና አፈር ምን ያህል ኪዩብክ ሜትር ነው የሚለው የምህንድስና ሙያ የሚጠይቅ ሆኖ እያለ በሑሳብ ባለሙያዎች የኦዱት ምርመራ ውጤት የቀረበበት በመሆኑ፣ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ እና በይግባኝ የማየት ስልጣን ያላቸው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በላለው የዲኝነት ስልጣንና በህግ ከተደነገገው ስርዓት ውጭ ኦዱተሮች (ምትክ ዳኞች) መድቦ ያጸደቀውን ሪፖርት እንደማኛውም የሰነድ ማስረጃ ህጋዊ ተቀባይነት (legal admissibility) ያለውና ተዓማኒነት ያለው መሆኑን መዝነው ውድቅ በማድረግ ጉዲዩን በልላ መንገድ የማጣራትና ላላ ማስረጃን መሰረት በማድረግ ለመወሰን የተከተለት ስርዓት የፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 135 እና ላልች የማስረጃ አቀባበልና አመዛዘን መርሆችን የተከተለ ምንም አይነት የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) የተጻፈው ደብዲቤ በተመለከተ፣ አመልካችና ተጠሪ አመልካች በሰራው ስራና ጨርሶ ባነሳው ድንጋይና አፈር መጠንና ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍል በሚገባው የገንዘብ መጠን ላይ ሰፉ ልዩነት ያላቸው በመሆኑ ግራ ቀኙ የሚካካደበትን ጭብጥ ለመወሰን በጉዲዩ ገለልተኛ ሆኖ ትክክለኛ ማስረጃ ላሰጥ ይችላል ተብል የተሰጠው የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ፣ አከራካሪውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች የሰራው የኢስካቬሸን ስራ መጠን አጣርቶ እንዱያሳውቀው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሰው የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) በቁጥር CCCC(E) AA/2013/56 እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ህዲር 11 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መልስ ሰጥቷል።
የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ ከላይ ቁጥሩ በተገለጸው ደብዲቤ ለፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ ሜትር ኩዩብ ትልቅ ደንጋይና 283 ሜትር ኩዩብ ቀላል ድንጋይ አነስቶ ገንዘቡ ተከፍልት እንደተሰናበት ከገለጸ በኃላ በደብዲቤው መደምደሚያ ላይ ‛በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ከኢትዮጵያ መንገድች ስራ ጋር ኩባንያችን CCCC አንድ ላይ በመሆን እንዲንለካ ቦታው በሰብቤዝና በአስፓልት ተሸፍኗል። ስለሆነም የመርመርነው ከመልስ ሰጭው በተገኘው የጽሁፍ ማስረጃ ነው“ በማለት ግልጽ አድርጓል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቻይና መንገድ ስራ ካንፓኒ በደብዲቤው የገለጻቸውን ፍሬ ነገሮች የራሱን የሰነድ ማስረጃዎች መነሻ በማድረግ ሳይሆን የስር ተከሳሽ (ተጠሪ) የቀረበለትን የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ የሰጠው መረጃ መሆኑን በመገንዘብ ውድቅ አድርጎታል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግን፣ የደብዲቤውን ሙለ ይዘት ሳይመረምር በተለይም CCCC በደብዲቤው የገለጻቸውን ፍሬ ነገሮች ያገኘው የስር ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ የቀረበለትን የሰነድ ማስረጃ በመመልከት እንደሆነ የገለጸው መደምደሚያ ህጋዊ ውጤት ሳያገናዝብ ደብዲቤው የአሰረጅነት ብቃት ያለው የሰነድ ማስረጃ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ይህ የይግባኝ ሰሚው ችልት አሰራር አንድ ማስረጃ ሉመዘን የሚገባው ከማስረጃው ውስጥ ከሳሽን ወይም ተከሳሽን የሚጠቅመውን ክፍል ነጥል በመወሰድ ሳይሆን የማስረጃውን ሙለ ይዘት በመመርመርና በመመዘን መሆን ይኖርበታል የሚለውን መሰረታዊ የማስረጃ አመዛዘን መርህ የሚጥስ ነው። የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) በደብዲቤው የገለጻቸውና ፍሬ ነገሮች ያገኛቸው ተከሳሽ (ተጠሪ) ከቀረበለት የሰነድ ማስረጃ መሆኑን እንደገለጸ ሳያገናዝብና CCCC የሰጠው መረጃ የተከሳሽን (ተጠሪን) የቀረበበት ሰነድ ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑ በራሱ የተከሳሽን ማስረጃ በቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) በኩል ተጽፍ ቁጥር ተሰጥቶና ደብዲቤው የተጻፈበት ቀን ተገልጾና በማህተም ተረጋግጦ እንዱቀርብ ከማድረግ ውጭ የተለየ ህጋዊ ውጤት የላለው መሆኑን ሳያገናዝብ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ደብዲቤውን ለውሳኔው መሰረት አድርጎ መጠቀሙ ከላይ የገለጸነውን የማስረጃ አመዛዘን መርህ ያልተከተለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) የጻፈው ደብዲቤ ተጠሪ በመከራከሪያነት ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች በልላ መንገድ የሚገልጽና የሚደግም ሰነድ እንጅ ስለአከራካሪው ጭብጥ በቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) ወይም በልላ ሶስተኛ ወገን (ኢትዮጵያ መንገድች ባለስልጣን) እጅ ያለትን፣ ሰነድች መሰረት በማድረግ የተጻፈ ደብዲቤ ባለመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ችልት ይህንን ደብዲቤ መነሻ በማድረግ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
መጣራት የሚገባቸው ፍሬ ጉዲዩች ስለመጣራቸው፣ ከላይ እንደተገለጸው የቻይና መንገድ ስራ ድርጅት (CCCC) ተጠሪ የቀረበለትን ሰነድ መሰረት በማድረግ የጻፈውን ደብዲቤ ሙለ ይዘት ሳይመዘን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ የማስረጃ አመዛዘን መሰረታዊ መርህ ያልተከተለ ነው። ይህም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠው መጣራት የሚገባቸውን አከረካሪ ፍሬ ጉዲዬች በአግባቡ በማጣራት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ እንድንመረምር የሚያስገደድ ነው። የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሑሳብ ባለሙያዎች መድቦ ያገኘውን የኦዱት ሪፖርትም ሆነ የቻይና የመንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) የጻፈውን ደብዲቤ አከራካሪውን ጭብጥ ለማስረዲት ተቀባይነትና የአስረጅነት ብቃት ያላቸው ማስረጃዎች አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አከራካሪውን ጭብጥ ላልች ባለሙያዎች የመንግስትና የግል ድርጅቶች በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብለት የሰጠው ትዕዛዝ የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 250 እና የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 136(1) ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
አከራካሪው የህግ ጭብጥ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ከተጠሪ ጋር በተዋዋለው ውል መሰረት የሰራው የኢስካቬሽን ስራ መጠንና ለዚህ ስራው ሉከፈለው የሚገባው ገንዘብ ምን ያህል ነው የሚለውን አጣርተው መግለጫ እንዱያቀርቡለት ያዘዛቸው አራት ድርጅቶች የተለያየና ተቃራኒ ይዘት ያለው አስተያያት አቅርበውለት እያለ የአንደኛውን ‛ሳፍኮን“ የተባለው ድርጅት የሰጠውን የሙያ አስተያየት ተቀብልና የላልቹን የሙያ አስተያየት ውድቅ አድርጎ ውሳኔ የሰጠበት ህጋዊ ምክንያት ምንድን ነው የሚለው ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስለጉዲዩ አጥንተው የሙያ አስተያየት እንዱሰጥ ትዕዛዝ ከሰጣቸው ድርጅቶች አንደኛው ማለትም የኦሮሚያ ከተማና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ፣ ለመገመት እንደማይቻል የገለጸለት ሲሆን ሳፍኮን ኮንስትራክሽን የተባለው አመልካች በቀን 320 ኩዩቢክ ሜትር ያነሳል በማለት የገልጸ ሲሆን አርጋ አባተ ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት አመልካች በቀን 1400 ኪዩብክ ሜትር አፈርና ድንጋይ ያነሳል በማለት ገልጿል። የምስራቅ ሸዋ ዞን ኢንዱስትና ከተማ ጽ/ቤት በበኩል አመልካች በቀን 1120 ኩዩቢክ ሜትር ያነሳል በማለት ጽፊል።
ከላይ የገለጽነው ተቃራኒ ይዘትና የተለያየ የሙያ አስተያየት በተሰጠበት ሁኔታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያለምንም ህጋዊ ምክንያትና መነሻ ሳፍኮን የተባለው ድርጅት የሰጠውን የሙያ አስተያየት በመቀበል አመልካች በቀን 320 ኩብቢክ ሜትር ስራ ይሰራል በማለት የሰጠውን አስተያየት በመቀበልና በላልች ድርጅቶች የሰጡትን የሙያ አስተያየቶች ውድቅ በማድረግ መወሰኑ ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ አንጻር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የሚሰሩ በጉዲዩ ላይ በቂ ዕውቀትና ክህልት ያላቸውን ባለሙያዎች በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 136(1) መሰረት በመመደብ የተመደቡት ባለሙያዎች፡ሀ. አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው ውል መሰረት የኤስካቬሸን ስራ ሲሰራ የተጠሪ አማካሪ ማህንዱስ ስራውን ሲቆጣጠርበት የነበረውን ሳይት ቡክ፣ ለ. አመልካችና ተጠሪ ማሽነሪዎች በየቀኑ ለምን ያህል ሰዓት እንደሰሩ የመዘገቡበትን ሰነድ፣ ሐ. አመልካች የተጠቀመው ነዲጅ 5021 (አምስት ሺ ሃያ አንድ ሉትር) ነዲጅ አመልካች ለስራ ባሰማራቸው ማሸነሪዎች ምን ያህል የኢስካቬሸን ስራ ሉያሰራ እንደሚችል በመገመት፣ መ. ተጠሪ ከቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) በአመልካችና በራሱ አቅም ለሰራው የኢስካቬሸን ስራ ምን ያህል ክፍያ እንደተከፈል በማጣራትና፣ ሰ. የተጠሪ አማካሪ መሀንዱስ፣ ስራው ከሚሰራበት ቦታ ለቅቆ ከመሄደ በፉት፣ አመልካች ምን ያህል ኩዩብክ ሜትር አፈርና ድንጋይ እንዲነሳ አስፈላጊ የሆኑ ሰነድችን ይዞ በመቅረብ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 246(1) መሰረት ትዕዛዝ በመሰጠትና ላልች አከራካሪውን ፍሬ ጉዲይ ለመወሰን የሚጠቅሙ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በትዕዛዝ በማቅረብና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ አንቀጽ 246፣ አንቀጽ 247፣ አንቀጽ 248፣ አንቀጽ 145(1) አንቀጽ 136(1) እና አንቀጽ 264(1) መሰረት አጣርቶ መወሰን ሲገባው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከላይ በገለጽነው ሁኔታ ጉዲዩን በማጣራት ሳይሆን ተቃራኒ ይዘት ካላቸው ሙያዊ አስተያየቶች የአንደኛውን ድርጅት አስተያየት መርጦ በመውሰድ መወሰኑ ከላይ የጠቀሰናቸውን የህግ ድንጋጌዎች ያልተከተለና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፈጸመውን ስህተት ሳያርም አመልካች ያቀረበውን መስቀልኛ ይግባኝ ውድቅ ማድረጉና የቻይና መንገድ ስራ ኩባንያ (CCCC) የጻፈውን ደብዲቤ ብቻ መሰረት በማድረግ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 9 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሀምላ 28 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሙያው በቂ ዕወቀትና ክህልት ያላቸውን ባለሙያዎች በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 136(1) መሰረት መመደብና በዚህ ፍርድ በተራ ቁጥር 20 ከ ‛ሀ እስከ ሰ“ የተዘረዘሩ መሰረታዊ ጉዲዮች መነሻ በማድረግ አጣርተው እንዱያቀርበለት በማደረግ ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችለ የሰነድ ማስረጃዎች በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
145(1) መሰረት በትዕዛዝ በማሰቀረብና ተጠሪን በመወከል ስራውን ሲያሰራ የነበረውን አማካሪ መሃንድስና ላልች ጠቃሚ የምስክርነት ቃል ሉሰጡ የሚችለ ሰዎች በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 264(1) መሰረት በምስክርነት ቀርበው ቃላቸውን እንዱሰጡ በማድረግ፣ አመልካች ከተጠሪ ጋር በተዋዋለው ውል መሰረት የሰራው የኢስካቬሽን ስራ መጠኑ ምን ያህል ነው? ተጠሪ ለአመልካች መክፈል የሚገባው ክፍያ (ገንዘብ) ምን ያህል ላሆን ይገባል የሚለትን ጭብጦች አጣርቶ ውሳኔ እንዱሰጥባቸው ጉዲዩን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
343(1) መሰረት መልስን ልከንለታል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.