በክርክር ወቅት ጣልቃ እንዱገባ የተፈቀደለት ተከራካሪ በመጀመሪያ ሉያቀርብ የሚፈልገውን መቃወሚያ እንዲያቀርብ የሚከለክለው ህግ የላለ ስለመሆኑ፣ ( የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 ፣234/1/ VIII
No summary available.
የሰ/መ/ ሕዲር 15 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሀ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ ወርቂቱ ገመዲ -አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ደመቀች ብርሃኑ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ውርስ እንዱጣራ በማለት የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪ አመልካች በዚህ የሰበር ክርክር የላለ አቶ ሳህለ ብርሀኑ እና ወ/ት አባይነሽ ብርሃኑ እንደ ቅደም ተከተላቸው ተጠሪዎች፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ጣልቃገብ በመሆን ተከራክረዋል። የአመልካቾች ክስ ይዘት በአጭሩ ከሟች አባታቸው መቶ አለቃ ብርሃኑ አያኖ በውርስ የተላለፈላቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 ቤ.ቁ 389 የሆነው ቤት ከሥር ተጠሪዎች ጋር በጋራ ይዘው በአላባው እየተጠቀሙበት መሆኑን፤ድርሻቸው ሳይለይ ቢቀጥል ችግር ሉገጥማቸው የሚችል መሆኑን በመጥቀስ ውርስ አጣሪ ተሹሞ ውርሱ እንዱጣራ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የሥር 1ኛ ተጠሪ ድርሻቸውን በስምምነት ይዘው እየተጠቀሙበት መሆኑን በመግለጽ ውርሱ ሉጣራ አይገባም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የሥር 2ኛ ተጠሪም የይርጋ መቃወሚያ በማንሳት ውርሱ ሉጣራ አይገባም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የአሁን አመልካች ተጠቃሹን ቤት ይዘው የሚያስተዲድሩት እና ተጠሪ በንብረቱ የማይጠቀሙ መሆኑን በመጥቀስ የተጠሪ ጥያቄ በይርጋ ይታገዲል በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤት አመልካች ወደ ክርክሩ ጣልቃ የገቡት ፈልገው ነው፤ በውርስ ማጣራቱ ሂደት የሚስትነት ድርሻ ካላቸው ለአጣሪው ማስረጃቸውን ከሚያቀርቡ በቀር የውርስ ሀብቱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም፤ ያነሱት የይርጋ ጥያቄም ከውርስ ማጣራት ጋር የሚገናኝ አይደለም በማለት አመልካች ያቀረቡትን የይርጋ መቃወሚያ በብይን ውድቅ በማድረግ የሟች መቶ አለቃ ብርሃኑ አያኖን የውርስ ሀብት የሚያጣራ ውርስ አጣሪ እንዱሾም አድርጓል፤ ውርስ አጣሪው ያቀረበውን ሪፖርት ከመረመረም በኃላ አመልካች የሟች ሚስት በመሆናቸው አከራካሪው ቤት የሟች እና የአመልካች የጋራ ሀብት እንደሆነ ይገመታል፤ የተጠሪ ምስክሮች ቤቱ የተሰራበትን ትክክለኛ ጊዜ አላስረደም፤ ቤቱ በውርስ ወይም በልላ መንገድ ለሟች የተላለፈ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም፤ የስጦታ ውል ነው በማለት የቀረበው ሰነድም ቦታ እንጂ ቤቱ ለሟች የተላለፈ መሆኑን አያሳይም፤ የሟች አባት አቶ አያኖ አደራ ለሟች አቶ ብርሃኑ አያኖ ቤት መስራታቸውን ያሳያል የተባለው ሰነድም አዋሳኙን ያልገለጸ እና አከራካሪውን ቤት የሚመለከት ነው ልባል የማይችል በመሆኑ ክርክር የቀረበበት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 ቤ.ቁ 389 የሆነው ቤት የሟች መቶ አለቃ ብርሃኑ አያኖ እና የአመልካች የጋራ ሀብት ነው፤ ቤቱን ተከፊፍለው በመኖሪያ ቤትነት እና በማከራየት ሲጠቀሙበት የነበረ በመሆኑ የቤት ኪራይን በተመለከተ በውርስ አጣሪው ሪፖርት ላይ የተዘረዘሩት ነገሮች ተሰርዘዋል፤ ለበር ማሰሪያ ተጠሪ ያወጡትን ወጪ ድርሻቸው ተቀንሶ አመልካች እና የሥር ተጠሪዎች ሉከፍሎቸው ይገባል በማለት ውርስ አጣሪው ያቀረበውን ሪፖርት በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በተጠሪ በኩል ቀርበው የተሰሙት ምስክሮች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ሟች መቶ አለቃ ብርሃኑ አያኖ አመልካችን ከማግባታቸው በፉት በአባታቸው አቶ አያኖ አደራ ተሰርቶ የገቡበት እና እየኖሩበት የነበረ መሆኑን ያስረደ በመሆኑ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 ውስጥ የሚገኘው ቁጥሩ 389 የሆነው ቤት ሟች አቶ ብርሃኑ አያኖ አመልካችን ከማግባታቸው በፉት በግላቸው የነበራቸው ቤት ነው በማለት ተጠቃሹ ቤት የሟች አቶ ብርሃኑ አያኖ የውርስ ሀብት ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጓል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር በፍ/ቤት የተፈቀደለት ወገን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንስቶ እንዲይከራከር የሚከለክል ሕግ በላለበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት አመልካች ያቀረብኩትን የይርጋ መቃወሚያ በብይን ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም፤ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ሟች አባታቸው ከወላጅ እናታቸው በውርስ የተላለፈላቸው ይዞታ ላይ ቤት ሰርተው በስጦታ የተላለፈላቸው ነው በማለት ከሚከራከሩ በቀር አቶ አያኖ አደራ ቤቱን ሰርተው ለሟች አባታቸው የሰጡ መሆኑን በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር በላለበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ ካቀረቡት ክርክር ውጪ በመውጣት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱቱታ ተመርምሮ አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉን እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪ ካቀረቡት የክርክር መሥመር ውጪ በመውጣት አከራካሪው ቤት የአመልካች እና የሟች የጋራ ሀብት ነው በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ የመሻሩን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎ የጽሐፍ መልስ ሰጥተዋል።
ተጠሪ በሰጡት መልስ ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን የይርጋ መቃወሚያ በብይን ውድቅ ካደረገው በኋላ በብይኑ ላይ በይግባኝም ሆነ በመስቀለኛ ይግባኝ አቤቱታ ቀርቦበት ይርጋውን በተመለከተ የተወሰነ ነገር ስለላለ ይህ ችልት በይርጋው ላይ የተያዘውን ጭብጥ የመመርመር ስልጣን የለውም፤አመልካች እና ተጠሪ በአከራካሪው ቤት ውስጥ የራሳችንን ክፍል ይዘን የምንኖርበት በመሆኑ ቤቱ በአመልካች እጅ ብቻ አይደለም፤ አመልካች መብታቸው በማይነካበት ሁኔታ የራሳቸውን መብት ለማስከበር ጣልቃ በገቡበት ክርክር የይርጋ መቃወሚያን ሉያነሱ አይችለም፤ሟች የውርስ ሀብቱን ያገኙት ከማነው የሚለው ነጥብ የፍሬነገር ክርክር እና የማስረጃ ምዘና በመሆኑ ችልቱ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተመለከተው ነው። ይህ ችልትም ወደ ዋናው ጉዲይ ከመገባቱ በፉት ጉደዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች ወደ ክርክሩ ጣልቃ የገቡት ፈልገው በመሆኑ በውርስ ማጣራቱ ሂደት የሚስትነት ድርሻ ካላቸው ለአጣሪው ማስረጃቸውን ከሚያቀርቡ በስተቀር የውርስ ሀብቱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ በአግባቡ ነው?ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
ጉዲዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች ውርሱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም ከሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርስ የቻለው አመልካች ወደ ክርክሩ የገቡት ፈልገው ነው፤ በውርስ ማጣራቱ ሂደት የሚስትነት ድርሻ ካላቸው ለአጣሪው ማስረጃቸውን ከሚያቀርቡ በስተቀር የውርስ ሀብቱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም በሚል መሆኑን ከሰጠው ብይን መገንዘብ ይቻላል። የሥር ፍ/ቤቱ የደረሰበት ይህ ድምዲሜ ተገቢ መሆን አለመሆኑ ከጉዲዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ድንጋጌዎች ይዘት ጋር በማገናዘብ ሉመረመር ይገባል።በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የሙግት ተካፊይ ስለመሆን አስመልክቶ ከተደነገጉት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ድንጋጌዎች ውስጥ ሦስተኛ ወገኖች በጣልቃ ገብነት የክርክር ተካፊይ መሆን ስለሚችለበት ሥርዓት የተደነገገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 ድንጋጌ ተጠቃሽ ነው።
ይህ ድንጋጌ በአንድ ክርክር ያገባኛል የሚል ማናቸውም ሦስተኛ ወገን ከፍርድ ውሳኔ በፉት ጣልቃገብ ሆኖ ለመከራከር እንዱችል እንዱፈቀድለት ማመልከት ስለሚችልበት እና በክርክሩ ተካፊይ ለመሆን ሉፈቀድለት ስለሚችልበት ሥርዓት የሚደነግግ ነው።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ዓላማ ክርክርን በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ በመምራት ፍትሀዊ ውሳኔ መስጠት ነው። ተጠቃሹ ድንጋጌም ይህን ዓላማ የማሳካት ዓይነተኛ ሚና ያለው በመሆኑ የድንጋጌው አተገባበርም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ዓላማ ጋር በማገናዘብ ላሆን ይገባል። የሥነሥርዓት ሕጉ ዓላማም ሉሳካ የሚችለው በድንጋጌው መሰረት ጣልቃ እንዱገባ የተፈቀደለት ተከራካሪ ወገን አለኝ የሚለውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያም ሆነ የፍሬነገር ክርክር ማቅረብ ሲችል ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች በዚህ ድንጋጌ መሰረት ጣልቃ ገብተው እንዱከራከሩ ጠይቀው ተፈቅድላቸው የክርክሩ ተካፊይ እንደሆኑ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ያሳያል። አመልካች በክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ ከተፈቀደላቸው በኋላ ያላቸው መብት ለጉዲዩ ይጠቅመኛል ያለትን መከራከሪያ ማቅረብ እንደሆነ ከድንጋጌው ይዘት እና ዓላማ መገንዘብ ይቻላል። አከራካሪው ጉዲይ አመልካች ጣልቃገብ ተከራካሪ ወገን በመሆናቸው በሚያቀርቡት መከራከሪያ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ማቅረብ ይችላለ? ወይስ አይችለም? የሚለው ነው።
አንድ ተከራካሪ ወገን አለኝ የሚለውን መከራከሪያ ሳያቀርብ የሚሰጠው ውሳኔ ፍትሐዊ ላሆን አይችልም። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234/1/ሐ ተከሳሽ በሚያቀርበው መከላከያ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካለው በመከላከያ መልሱ መግለጽ እንዲለበት ይደነግጋል። አመልካች የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ እስከተፈቀደላቸው ድረስ ይህ ድንጋጌ በሚፈቅደው መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካላቸው ዘርዝረው የማቅረብ መብት ያላቸው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ጉዲዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች ጣልቃገብ ተከራካሪ ወገን ስለሆኑ ውርሱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት ወደ ዋናው ጉዲይ በመግባት ውሳኔ መስጠቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 ድንጋጌን ትክክለኛ አተገባበር ያልተከተለ ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል ተጠሪ የሥር ፍ/ቤት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ በሰጠው ብይን ላይ በይግባኝ ወይም በመስቀለኛ ይግባኝ ቅሬታ ቀርቦበት ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ይህ ችልት በይርጋው ላይ የተያዘውን ጭብጥ የመመርመር ሥልጣን የለውም በማለት መከራከሪያ አቅርበዋል። ሆኖም ጉዲዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት ከመነሻውም ቢሆን አመልካች ውርሱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት የአመልካችን መቃወሚያ ያልተቀበለው እና ጉዲዩ በይርጋ ይታገዲል? ወይስ አይታገድም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ብይን ያልሰጠበት በመሆኑ አመልካች የይርጋ መቃወሚያውን መሰረት በማድረግ ይግባኝ ወይም መስቀለኛ ይግባኝ ማቅረብ ነበረባቸው የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ ተጠሪ በዚህ አግባብ ያቀረቡትን መከራከሪያ አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ ጉዲዩ በቀጥታ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች ውርሱ እንዲይጣራ ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት ብይን መስጠቱ፤ በየደረጃው ያለ ፍ/ቤቶችም ይህንኑ ሳያርሙ ማለፊቸው መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ147733 ጥቅምት 03 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ. ታሕሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
በውርስ ማጣራቱ ሂደት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 41 መሰረት ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር የተፈቀደለት ተከራካሪ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ መሰረት አለኝ የሚለውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንስቶ መከራከር ይችላል ብለናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ላይ በጉዲዩ ተከራካሪ የነበሩት ወገኖች የሚያቀርቡትን ክርክር በመስማት እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ ተገቢ የሆነ ብይን እንዱሰጥበት፤
የሚሰጠው ብይን የአመልካችን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የሚሰጥ ከሆነ በዋናው ጉዲይ ላይ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሰረት ተመልሶለታል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመ. የሆነው መዝገብ ወደመጣበት ይመለስ።
No topics extracted.