በክርክር ሂደት ላይ ፤ የቀረቡት የባለሙያ አሰተያየቶች ተቃራኒ ይዘት ካላቸው ፤ ግልፅ መሰፈረት እና ምክንያት በላለበት አንደኛውን ተቀብል ላላውን ውድቅ ማደረግ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 እና 136(1) 115963 አቶ ኤልያስታምራት እና እነ ወ/ሮ አሰቴር መከተ (ሁለት ሰዎች) 8/11/ 2008 ዓ.ም 75 18. የሰበር አቤቱታ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሳይቀርብ ጊዜው ካለፈ የሰበር አቤቱታ ከመቅረቡ በፉት የይግባኝ ማስፈቅጃ ማመልከቻ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 22(4) ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 324 101277 የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ እና ሚ/ር አቤንቻንድ ፓፓትላል 23/1/ 2009 ዓ.ም 81 19. በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር አፍሮ ፅዩን 26/1 /2009 ዓ.ም 84 VII ይቆጠራል የሚለው ድንጋጌ በልዩ ስርዓት( በአጭር ሁኔታ) ለሚመሩ ክርክሮች ላይ ጭምር ለቀረበ መልስ ላይም ተፈፃሚ የሚሆን ስለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 284 (ሀ) ኮ/ኃ/የተ/የግ/ማህ እና እነ አቶ ያሬድ ተሾመ ( ሦስት ሰዎች ) 20. ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽል እንዱቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 90(1) 122249 አቶ በላይ አየለ እና በአ/አ/ከ/አ/ከ/ፅ/ቤት አዱስ ዙ ፓርክ ማዕከል 26/1 /2009 ዓ.ም 87 21. አንድ የዲኝነት አካል የሥረ - ነገር ስልጣን ባይኖረውም እንኳን የሰጠው ውሳኔ ሥርዓቱን ተከትል እስካልተሻረ ድረስ የፀናና የመጨረሻ በመሆኑ አዱስ ክስ በተመሳሳይ ጉዲይ ማቅረብ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/1/ እና 212
No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- . አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ በላይ አየለ - ከጠበቃ ዮሴፍ አስምሮ ጋር - ቀረቡ ተጠሪ፡- በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ከንቲባ ጽ/ቤት አዱስ ዙ ፓርክ ማዕከል - ነ.ፈጅ አብይ አስናቀ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ሁከት እንዱወገድ እና በሁከት ምክንያት የተቋረጠ ጥቅም ይከፈለኝ በማለት የቀረበን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአመልካች ክስ ይዘት በአንበሳ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ቦታ ገንዘብ እና ንብረት በማፍሰስ የተለያየ የልጆች መጫወቻ የተከለበት መሆኑን፤ ስራውን ሲሰሩ የነበረው ብር 3300 /ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መሆኑን፤
ተከሳሹ በጨረታ አከራያለሁ በማለት ጨረታውን ያሸነፈ ግለሰቦች ባሸነፈበት ዋጋ መቀጠል ስላልቻለ አመልካች በሰጡት የጨረታ ዋጋ /አሥር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሐያ አንድ ብር/ እየከፈለ እንዱቀጥለ እና የውል ቆይታ ጊዜውም በ6 ኪል የሚገኘው ጽ/ቤት አዱስ እያሰራ ወዲለው የፒኮክ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እስከሚዛወር ድረስ መሆኑን በመግለጽ ተከሳሹ የጻፈላቸው መሆኑን፤ ሆኖም ተከሳሹ የውለታው ጊዜ ሳያልቅ ግቢ ለቀህ ውጣ በማለት የጻፈላቸው መሆኑን፤
በመግለጽ ተከሳሽ የፈጠረው ሁከት እንዱወገድ እና በሁከቱ ምክንያት የተቋረጠባቸው ጥቅም እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት የጠየቁ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ አስቀድሞ ለአመልካች የተጻፈው ደብዲቤ በሚመለከተው አካል የተጻፈ አይደለም። ተጻፈ የተባለው ደብዲቤም በልላ ደብዲቤ ተሽሯል። አመልካች ቀርበው ውል እንዱያድሱ ጥሪ ቢደረግላቸውም ቀርበው ውል አላደሱም። እንደውል ያቀረቡት ደብዲቤም የውል ሰነድ ተደርጎ ሉቆጠር አይችልም። ንብረቱን በተሻለ ገንዘብ ለማከራየት ለአመልካች ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለ እንዱቋረጥ መደረጉ የሁከት ተግባር አይደለም። የተቋረጠ ጥቅም በማለት የቀረበው ጥያቄም በማስረጃ የተደገፈ ስላልሆነ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ.ም ለአመልካች የጻፈው ደብዲቤ እንደውል ማሻሻያ የሚታይ እንጂ ተራ ደብዲቤ አይደለም። ደብዲቤው የኪራይ ማሻሻያን የሚመለከት እና የውል ቆይታ ጊዜውም በስድስት ኪል የሚገኘው የአዱስ ዙ ፕሮጀክት በመሰራት ላይ ወዲለው ፒኮክ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እስኪዛወር የሚገልጽ ነው። በመሆኑም የውል ጊዜው ሳይጠናቀቅ አመልካች እንዱለቅ መደረጉ የሁከት ተግባር ነው በማለት ተጠሪ ሁከቱን አስወግድ አመልካች ሥራውን እስኪጀምር ድረስ ከጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ አንዱከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤትም ለአመልካች መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ.ም የተጻፈ ደብዲቤ በአንድ ወገን የቀረበ ጥያቄ እንጂ አስቀድሞ የነበረውን ውል ያራዘመ አይደለም። ተጠሪው ጥር 9 2006 ዓ.ም በጻፈው ደብዲቤም አስቀድሞ የጻፈውን ደብዲቤ ሽሮታል። በመሆኑም ተጠሪ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመልካች ለቀው እንዱወጡ ማድረጉ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው የነበረ ቢሆንም አቤቱታቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዟል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አመልካች በአዱስ አበባ አስተዲደር ከንቲባ ጽ/ቤት መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈው የውል ማሻሻያ ሰነድ ተቀብዬ በሰነደ ላይ የተገለጸውን የዋጋ ማሻሻያ ስከፍል ቆይቻለሁ፤ በሰነደ ላይ የኪራይ ውለ ቆይታ ጊዜ በስድስት ኪል የሚገኘው የአዱስ ዙ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አዱስ እያሰራ ወዲለው ፒኮክ ፕሮጀክት ጽ/ቤት እስኪዛወር ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተመልክቷል፤ በድጋሚ ተጽፎል የተባለው ደብዲቤም የጸና ውል እያለኝ ድጋሚ የኪራይ ውል ለማድረግ የሚያስገድደኝ አይደለም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይህን በማለፍ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው የሚል ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ በመሆኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም በሰበር የተያዘው ጭብጥ ከመወሰኑ በፉት ከመነሻውም ቢሆን የሥር ፍ/ቤቶች ክርክሩን ሁከት ይወገድልኝ በማለት በተጠየቀው ዲኝነት መምራት ነበረባቸው? ወይስ አልነበረባቸውም? የሚለውን ጭብጥ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ርዕስ ሁከት እንዱወገድ እና በሁከቱ ምክንያት የተቋረጠ ጥቅም ለማስከፈል በሚል የቀረበ ቢሆንም ዝርዝር ይዘቱ ሲታይ ከኪራይ ውል አፈፃፀም ጋር የተገናኘ ነው። በግራ ቀኝ ወገኖች የሚቀርብ የክርክር ይዘት ፍ/ቤቱ ለሚይዘው ጭብጥ መሰረት ነው። በአግባቡ ያልቀረበን ክስ መነሻ በማድረግ በፍ/ቤቶች የሚሰጥ ፍርድም ፍትሐዊ ላሆን አይችልም። በተያዘው ጉዲይ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች ያቀረቡትን ክስ በመቀበል የተጠሪ ተግባር ሁከት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ውሳኔ ከመስጠቱ ውጪ የክሱን ዝርዝር ይዘት በማየት ክርክሩ ከኪራይ ውል አፈጻጸም ጋር የተገናኘ መሆኑን ተገንዝቦ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 91/1 በሚፈቅደው መሰረት ክሱ እንዱሻሻል አላደረገም።
የፍ/ቤቶች ዋነኛ ሚና ክርክሮች በተገቢው የሕግ ሥርዓት እንዱመሩ ማድረግ ነው። ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት በክርክሩ ላይ ባለው የመሪነት ሚና ክሱ እንዱሻሻል ማድረግ ሲገባው የቀረበውን ክስ አከራክሮ ውሳኔ መስጠቱ እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
182/2 በሚደነግገው መሰረት ጉዲዩ የሚመራበትን ሂደት ማረም ሲገባው ይህንኑ ሳያርም ተጠሪ የፈጠረው ሁከት የለም በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 46548 ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 166197 ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ. 120477 ታህሳስ 05 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረቡት ክስ በሁከት ይወገድልኝ የሚታይ ሳይሆን ከውል አፈጻጸም ጋር የተገናኘ መሆኑን አውቆ አመልካች ክሱን እንዱያሻሽለ እና ተገቢውን ዲኝነት እንዱከፍለ በማድረግ ግራ ቀኙን አከራክሮ የመሰለውን እንዱወስን ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1 መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.