No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች- አፍሮ ፅዮን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነ/ፈ ዘላለም ብሩክ ቀረቡ ተጠሪዎች- 1ኛ. አቶ ያሬድ ተሾመ 2ኛ. አቶ አድማሱ መርሻ አልቀረቡም 3ኛ. አቶ ገረመው አሰፊ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአጭር ሁኔታ የሚወሰኑ ክርክሮች በሚታዩበት ስርዓት ታይቶ እንዱወሰን ባቀረቡት አቤቱታ ነው።
የተጠሪዎች ክስ ይዘት ባጭሩ ተከሳሹ ከ1ኛ ተጠሪ ላይ የውሃ ቦቴ ተሸከርካሪ ፤ ከ2ኛ ተጠሪ ልደር ተሸከርካሪ እና ከ3ኛ ተጠሪ ግሪደር እና ልደር ተሽከርካሪ በመከራየት የኪራይ ዋጋ እንደ ቅደም ተከተላቸው ብር 34,757.21 (ሰላሳ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሰባት ከ21/100) ፤ ብር 21,555.00 (ሃያ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ አምስት) እና ብር 302,201.42 (ሶስት መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ አንድ ከ42/100) ስላልከፈላቸው ይህን ገንዘብ ከነወለደ ወጪና ኪሳራ ጨምሮ እንዱከፍል እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ቀርቦ ክሱን ለመከላከል እንዱፈቀድለት በ09/02/2008 ዓ.ም በተፃፈ ጠይቆ ተፈቅድለት መልስ አቅርቧል። ነገር ግን አመልካች በ22/03/2008 ዓ.ም በተፃፈ ባቀረበው መልስ የተከሰሰበት ገንዘብ ያለበት መሆኑን አምኖ መልስ ሰጥቷል ተብል ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የተከሰሰበትን ገንዘብ ከነወለደ፤ ወጪና ኪሳራ ጨምሮ ለተጠሪዎች እንዱከፍል ተወስኗል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።
የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክስ ባላስረደበት አግባብ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ፤
እንዱሁም የአመልካች ጠበቃ ከቅን ልቦና ውጭ ክሱን ማመኑን ተከትል በተጨማሪ ማስረጃ ሉረጋገጥ ሲገባው በማመን ብቻ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው እንዱሻርልን በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ታዞ በሰጡት መልስ በኪራይ ውለ መሰረት በሚመለከታቸው የድርጅቱ ኃላፉዎች ድርጅቱ ባዘጋጀው የክፍያ ማዘዣ ፍርም ላይ ተፈርሞ በተሰጣቸው የገንዘብ አለብኝ መተማመኛ ሰነድ ተደግፍ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 284(ሀ) መሰረት የቀረበ ክስ በመሆኑ፤
እንዱሁም ጠበቃው የሰጠውን መልስ ከመድገም ውጭ የአሁኑ የአመልካች ጠበቃ ለቀረበው ክስ መከላከያ መልሱ በእንዱህ አይነት መልኩ መሰጠት ይገባው ነበር ባላለበት ሁኔታ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሚዛን የሚደፊ ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም ተብል እንዱፀና ጠይቀዋል።
አመልካች በሰጠው የመልስ መልስ በተጠሪዎች የክፍያ ማዘዣ ላይ የገንዘብ መጠኑን በመጥቀስ ሰነድ የሰጣቸው መሆኑን እና ይህንኑም ሰነድ ለክሱ በማስረጃነት አያይዘው ማቅረባቸውን በመግለፅ ሆኖም ግን የስር ፍርድ ቤት ክሱን ከማስረጃው አንፃር ትክክለኛነቱን እና ተገቢነቱን ሳይመረምር የአመልካች ጠበቃ አላግባብ በማመኑ ብቻ ተቀብል ውሳኔ ማስተላለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚለውን ክርክር በማጠናከር አቅርቧል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ እና ግራ ቀኙ በሰበር ያደረጉትን ክርክር ሲሆን በበኩላችን ክርክሩን ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች አንፃር መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው አመልካች ለተጠቀመባቸው የተጠሪዎች ማሽነሪዎች የሚጠበቅበትን ክፍያ አልከፈለም በሚል የገንዘቡን መጠን በመጥቀስ እንዱከፈላቸው ተጠሪዎች ክስ አቅርበዋል። ክሱም ውልን እና የገንዘብ አለብኝ ሰነድን መሰረት በማድረግ በአጭር ሁኔታ እንዱወሰን የቀረበ ነው። የአመልካች (ሥር ተከሳሽ) ጠበቃ በተወካይነቱ ቀርቦ ለመከላከል ፈቃድ ጠይቆ ቢፈቀድለትም በሰጠው መልስ ‘…. ከሳሾች በክሳቸው ላይ ከተከሳሽ ጋር የስራ ውል በመዋዋል ስራ መስራታቸው የሚካድ አለመሆኑን፤ ከሳሾች ክፍያው እንዱከፈላቸው ያቀረቡት የክፍያ ጥያቄ አዱስ አበባ የሚገኘው የበላይ አካል መልስ እስኪሰጥ ድረስ እንዱጠብቁ ተነግሯቸው ትዕግስት በማጣት ክስ አቀረቡ እንጂ ተከሳሽ ክፍያውን ለመፈፀም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም፤ ስለዚህ ተከሳሽ ድርጅት አሁንም ለከሳሾቹ ክፍያ ለመክፈል አዱስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፤ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ይገንዘብልን …..’ በማለት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የሥር ፍ/ቤት እንደተጠሪዎች ጥያቄ ገንዘቡ እንዱከፈል የወሰነው ተከሳሽ የሰጠው መልስ ገንዘቡ የላለበት መሆኑን አልካደም፤ እንዱያውም አምኖ መከራከሩን ያሳያል በሚል ነው።
No topics extracted.
የአመልካች መሰረታዊ ቅሬታ ክርክሩ የተመራበትን እና ውሳኔ የተሰጠበትን አግባብ በተመለከተ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ክርክሩን የመራበት እና ውሳኔ ላይ የደረሰበት አካሄድ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል። የፍትሃብሄር ሥነ ሥርዓት ህጉ በቁ 235 እና 83 ስር የሚደነግገው በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል በሚል ሲሆን ይህ ሥነ ሥርዓታዊ ድንጋጌ እንደተያዘው ጉዲይ በልዩ ስርዓት የሚመሩና ማስፈቀጃ ተጠይቆበት በፈቃድ ለቀረበ መልስም ተፈፃሚ ነው። ከዚህም ላላ ተከሳሽ ካመነ በአመነው መሰረት ውሳኔ ለመስጠት የሚከለክል በቂ የህግ ምክንያት እስከላለ ድረስ ውሳኔ መስጠት የሚገባ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች የጠየቁት ልኩ የታወቀ ገንዘብ መሆኑንና ክሱም የተመሰረተው በውል እንዱሁም በገንዘብ አለብኝ ደረሰኝ ምክንያት መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዲዩ በተፊጠነ ሥነ ሥርዓት እንዱቀርብ መፍቀደ፤ አመልካች ቀርቦ ለመከላከል ያቀረበውን ማመልከቻ መቀበለ እና በቀረበው መልስ መሰረት ውሳኔ መስጠቱን ከተደረገው ክርክር መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ከሥነ ሥርዓት ህጉ የሙግት አመራር መርህ አኳያ ጉድለት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ባሳለፈት ውሳኔ እና ትዕዛዝ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ የአመልካችን ቅሬታ ባለመቀበል ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ24/03/08 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በ13/04/2008 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ፤ እንዱሁም የክልለ ሰበር ችልት በፊ/ በ15/04/2008 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ በመ/ የተጀመረው አፈፃፀም ታግድ እንዱቆይ ከዚህ ፍርድ ቤት ታህሳስ 22/2008 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ሩ/ለ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት።