No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ክፍለጽዬን ማሞ ጰውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ተወካይ አልቀረበም ተጠሪ፡- ሚ/ር አቤቻንድ ፖፖትላል ሜታ ወራሽ ጠበቃ አቶ ታደሰ መንገሻ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የጀመረው በፕራይቬታዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ነው። የአሁን ተጠሪ ያቀረቡት አቤቱታ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በቀድሞ ወረዲ 2 ቀበላ 11 በአሁኑ አራዲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 1 የቤት ቁጥር 271 የሆነ የቡና ማጠቢያና ማከማቻ መጋዘን ከነቢሮዎቹ ከአዋጅ ውጭ ስለተወሰደብን ይመለስልን የሚል ነው።
ኤጀንሲውም ጉዲዩን አጣርቶ በአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀጽ2(3) ድንጋጌ መሰረት ከአዋጅ ውጭ በቀላጤ የተወሰደ ንብረት በሚለው ትርጓሜ ስለሚሸፈን አቤቱታ የቀረበበት መጋዘን ከነቢሮዎቹ በመርህ ደረጃ እንዱመለስላቸው ሲወስን ንብረቱን ግን ተጠሪ የሚረከበው በተጨማሪነት ለተሰሩት ክፍልች የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በሚያቀርበው ወጪ መሰረት ክፍያውን ሲፈጽም ነው በማለት መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ወስኗል። የኤጀንሲው ዋና ዲይሬክተርም መጋቢት 28 ቀን 2004 ዓ/ም የውሳኔውን ትክክለኛነት አረጋግጦ ለመንግሥት ቤቶች አጄንሲ ጽፎል። የመንግሥት ቤቶች አጄንሲ ይግባኝ ለፕራይቤታይዜሽን ቦርድ አቅርቦ ቦርደም የአጄንሲውን ውሳኔ የሚያስለውጥ ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም በማለት ግንቦት 30 ቀን 2004 ዓ/ም አጽንቷል።
አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበው አቤቱታ ለክርክሩ መነሻ የሆነው የቤት ቁጥር 271 የቡና ማጠቢያና ማከማቻ መጋዘን ከነቢሮዎቹ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሰው ከጥቅምት 1 ቀን 1972 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት /ጅንአድ/በማከራየት አመልካች እያስተዲደረ የሚገኘውን ለተጠሪ ይመለስ በማለት የተወሰነው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልን የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታው ከተመረመረ በኌላ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲም ሆነ ቦርደ አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ እንዱመልስ የወሰኑት አመልካች በከርክሩ ተጠርቶ በአግባቡ ተከራክሮ መሆን ያለመሆኑን እና በቤቶች ኤጀንሲ ስር ሆኖ የቆዬው የድርጅት ቤትና መጋዘን ለተጠሪ ይመለስ ተብል የተወሰነው በአግባቡ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 193/92 አንቀጽ 7 አንጻር ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ ተቃውሞና መልስ ያቀረበ ሲሆን ተቃውሞውም የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈ በመሆኑ ክርክሩ ሉቀጥል አይገባም የሚል ነው።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለውን የውሳኔ ይዘት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ከመመርመሩ በፉት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ አልፎል ወይስ አላለፈም? የሚለውን በቅድሚያ ተመልክተናል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፕራይቤታይዜሽን ቦርድ ውሳኔ የሰጠው ግንቦት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ነው። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው በ8/9/2006 ዓ.ም ነው። ይህም የይግባኝ ውሳኔ ከተሰጠ ከአንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወር ከሰባት ቀን በኋላ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው። አመልካች ግን የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንስ ለፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈጻጸም ውክልና ታግድ እንዱቆይ ካደረገ በኃላ የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ/ም እግደን ያነሳ በመሆኑ የይግባኝ ጊዜው ሉቆጠር የሚገባው ከዚህ ቀን ጀምሮ ነው በማለት ተከራክሯል፡ ይህ ችልት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ አፈጻጸሙን አግዶል የተባለውን ለማጣራት ማኅደሩን በትዕዛዝ አስቀርቦ ተመልክቷል።
ኤጀንሲው ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ/ም ለአራዲ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጻፈው ደብዲቤ በኤጀንሲው ውሳኔ የተጠቀሰውን ቁጥር 271 የሆነውን መጋዘንና ቢሮዎች በአፈጻጸሙ መሰረት እንዱረከቡ በማድረግ ጅንአድ ለማስረከብ ፈቃደኛ ያልሆነባቸውን ቁጥር 006፣008/1 እና 008/2 የሆኑትን መጋዘኖች በሚመለከት በተለዋጭ ደብዲቤ ለፍርድ ቤቱ እስከምናሳውቅ ድረስ አፈጻጸሙ ለጊዜው ታግድ እንዱቆይ የሚል ነው።በዚህ ደብዲቤ መሰረት መጀመሪያ ውሳኔ ያረፈበት ቤት አፈጻጸም አልታገደም። ይልቁንም ደብዲቤው ውሳኔ የተሰጠውን ቤት የፍርድ ባለመብት እንዱረከብ ፍርድ ቤቱ እንዱያደርግ የሚል ይዘት ያለው ነው። የአመልካች የይግባኝ ጊዜ ሉቆጠር የሚገባው ከ8/9/2006 ዓ/ም ጀምሮ ነው የሚለው ክርክር ከዚህ አንጻር ሲታይ ተቀባይነት ያለው አይደለም። በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 22(4) እንደተደነገገው ለሰበር ሰሚ ችልት የሚቀርበው አቤቱታ ውሳኔ በተሰጠ 90 ቀን ውስጥ መቅረብ አለበት። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሰበር አቤቱታውን ለማቅረብ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካጋጠመ የሰበር አቤቱታው ከመቅረቡ በፉት በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 324 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የይግባኝ ማስፈቀጃ ማመልከቻ ቀርቦ ሉወሰን ይገባል። ይህ ባልተደረገበት ሁኔታ አመልካች ጊዜ ያለፈበትን የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ጭብጥ ተይዞ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የመልስ ልውውጥ ያደረጉ ቢሆንም የሰበር አቤቱታው የስነ ሥርዓት ግድፈት የተፈጸመበት በመሆኑ የክርክሩን ይዘት መመርመር ሳያስፈልግ የሰበር አቤቱታውን ሰርዘናል። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
አመልካች በህግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሰበር አቤቱታውን ያላቀረበ በመሆኑ የሰበር አቤቱታውን ውድቅ አድርገነዋል።
የሰበር አቤቱታው መሰረዙን እንዱያውቅ የፍርደ ግልባጭ ለፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ይላክ።
የዚህን ችልት ወጪና ኪሳራ በተመለከተ የግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
በዚህ ፍርድ ቤት ጥር 28 ቀን 2007 የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ።
ለሚመለከተው ይፃፍ።
No topics extracted.