No summary available.
ሐምል 8 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ኤሉያስ ታምራት - ጠበቃ መኮንን ኪዲነ ጋር - ቀረቡ ተጠሪ፡-
አንደኛ ተከሳሽ ባለሁለት ፍቅ ህንፃ ለመገንባት ከክፍለ አስተዲደር የግንባታ ፈቃድ ሲወስደ እኔም ስምምነቴን ተጠይቄ ከድንበሩ 0.70 ሣንቲ ሜትር በመራቅ ህንፃውን እንዱገነባ ተስማምቸ ፉርሜያለሁ። ሆኖም አንደኛ ተከሳሽ የከሳሽን የአጥር ግንብ ግድግዲ በማድረግ የቤቱን ፍሳሽ ወደ ከሳሽ እንዱፈስ በማድረግ ግንባታ በመገንባት ጉዲት እያደረሰብኝ ይገኛል።
ስለዚህ አንደኛ ተከሳሽ በከሳሽ አጥር ግንብ ላይ የገነባውን ግንባታ እንዱያፈርስና የፈጠረው ሁከት እንዱወገድ ውሣኔ ይስጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች።
አመልካች በበኩለ በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ በመሆን ቀርቦ ህንፃውን የገነባሁት በራሴ ይዞታና በተሰጠኝ የግንባታ ፈቃድ መሰረት ነው። ከከሳሽ አጥር ላይ የሰራሁት ግንባታ የለም። የከሳሽን ይዞታ አልገፊሁም በከሳሽ ላይ የፈጠርኩት ሁከት የለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችና አንደኛ ተጠሪ ክርክራችንን ይደግፈልናል በማለት በተለያየ ጊዜ በቀድሞው አሰራር ቀበላ 01/09 አስተዲደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዲደር የሚመለከተው ክፍል የፃፊቸውን የተለያየ ይዘት ያላቸውን ደብዲቤዎች በማስረጃነት የያዙ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውሣኔው አስፍሮታል።
የሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ከተሰጠው የግንባታ ፈቃድ ውጭ ህንፃ በመሥራት በከሳሽ ይዞታ ላይ ሁከት የፈጠረ መሆኑ ተጣርቶ እንዱቀርብለት ትዕዛዝ ሰጥቶ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የይዞታና አስተዲደር የሽግግር ጊዜ ፕሮግራም ጽ/ቤት ሀምላ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የባለሙያዎች ቡድን ከቦታው ድረስ በመላክ ባደረገው ማጣራት አንደኛ ተከሳሽ /አመልካች/ በከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ/ ይዞታ ውስጥ አልገቡም። አንደኛ ተከሳሽ ከመንግስት ይዞታ 26 ካሬ ሜትር የገቡ መሆኑ ተረጋግጧል የሚል መግለጫ ለሥር ፍርድ ቤት በመላኩ አንደኛ ተከሳሽ በከሳሽ ይዞታ ላይ የፈጠረው ሁከት የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ አንደኛ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርባለች። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት አጣርቶ ውጤቱን እንዱልክ ትዕዛዝ ሰጥቶ ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል። የክፍለ ከተማው ግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ጽ/ቤት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው መልስ አመልካች ከዋናው ቤት በስተጀርባ የገነባው ሰርቪስ ኳርተር በስተቀኝ ያለው ግድግዲ ገፅ በይግባኝ ባይና በመልስ ሰጭ መካከል ባለው አጥር ላይ የተገነባ መሆኑን አይተናል የሚል የፅሐፍ መግለጫ ልኳል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ማስረጃ መሰረት በማድረግ አመልካች በአጥሩ ላይ የገነባውን ኳርተር ሰርቪስ ግንባታ ይፍረስ በአንደኛ ተጠሪ ይዞታ ላይ የፈጠረው ሁከት ይወገድ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኃላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በድምፅ ብልጫ አጽንቶታል።
አመልካችና ተጠሪ የተስማሙበት ሰነድ ዋናው ህንፃ የሚገነባበትንና ከዋናው መንገድ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን አጥር እንጂ ሰርቪስ ክፍለ ተደግፍ የተሰራበትን አጥር የሚመለከት አይደለም። ሰርቪስ ክፍለ ተደግፍ የተሰራበትን አጥር ያጠርኩት አመልካች 1984 ዓ.ም ሲሆን የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር አስቀምጨበት እኖር ነበር። የውሃ ታንከሩን በማውረድ ግንባታ አካሄጀበታለሁ። ይህንን በተመለከተ አንደኛ ተጠሪ ያቀረበችው ክስ ሳይኖርና የአጥሩን ባለቤት በተመለከተ በጭብጥነት ተይዞ የግራ ቀኛችን ማስረጃ ተሰምቶ ውሣኔ አልተሰጠም ስለሆነም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ ክስ ካቀረበበት ጭብጥ ውጭ በመውጣት የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 329 (1) በሚቃረን ሁኔታ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልክቷል።
አንደኛ ተጠሪ ጥር 23 ቀን 2008 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች በአጥሬ ላይ ግንባታ የገነባ መሆኑን በመግለፅ ክስ አቅርቤያለሁ። አመልካች ይህንን ክስ በግልፅ ክድ ካለመከራከሩም በላይ የክፍለ ከተማው የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የባለሙያ ቡድን በመመደብ አመልካች አንደኛ ተጠሪ አጥር ላይ ግንባታ የፈጸመ መሆኑን ማረጋገጫ አቅርበዋል። ስለዚህ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያላነሳውን የአጥር ባለሀብትነት ክርክር አቅርቧል። ስለዚህ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥታለች። በሥር ፍርድ ቤትና ጉዲዩ በይግባኝ በሚታይበት ጊዜ ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት የታየው ሁለተኛ ተጠሪ አመልካች ከተሰጣቸው የግንባታ ፈቃድ ውጭ የገነባ በመሆኑ የፈጠረው ሁከት እንዱወገድ የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው በማለት ጥር 23 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ሰጥቷል። አመልካች መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የክፍለ ከተማው ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ እቦታው ድረስ በመሄድ አንድ ጊዜ አመልካች ግንባታውን የገነባው ተሻሽል በተሰጠው የግንባታ ፈቃድ መሰረት ነው የሚል መግለጫ የሰጡ መሆኑንና በልላ ጊዜ ደግሞ አመልካች ከግንባታ ፈቃድ ውጭ ህንፃውን በመሥራት ከአንደኛ ተጠሪን መብት እንደተጋፊ የሚገልጽ መግለጫ ያቀረቡ መሆኑን አመልካችና አንደኛ ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቧቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ይዘትና ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመረዲት ችለናል።
ከዚህ በተጨማሪ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የይዞታ አስተዲደርና የሽግግር ፕሮግራም ጽ/ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በባለሙያ አጣርቶ እንዱልክለት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የባለሙያ ቡድን መድቤ አድርጌዋለሁ ባለው ማጣራት አመልካች የተጠሪን ይዞታ ያልተጋፊ መሆኑን በመግለጽ ሀምላ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ ሰጥቷል።
በአንፃሩ ጉዲዩ በይግባኝ በሚታይበት ጊዜ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የባለሙያ ቡድን መድቤ ጉዲዩን አጣርቻለሁ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም የፅሐፍ መግለጫ የሰጠው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት አመልካች የሰርቪስ ኳርተር የአንደኛ ተጠሪን አጥር አስደግፍ ገንብቷል የሚል መግለጫ ያቀረበ መሆኑን ተረድተናል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ የክፍለ ከተማው የተለያዩ አካላት የአንደኛ ተጠሪና የአመልካችን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባለሙያ መድበው ባደረጉት ማጣራት የደረሱበት መደምደሚያና የሰጧቸው ደብዲቤዎች ዕርስበርሳቸው የሚቃረን ይዘት ያላቸው መሆናቸውን ከበታች ፍርድ ቤቶች ተረድተናል። ከዚህ በተጨማሪ የክፍለ ከተማው የአስተዲደር አካላት ለፋዳራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ለሰጠው ትዕዛዝ የባለሙያ ቡድን መድበውና አጣርተው ሀምላ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው መግለጫና በተመሣሣይ ጭብጥ ላይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ ከቦታው ድረስ ሄደው አጣርተዋል የተባለ ባለሙያዎች ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ያቀረቡት መግለጫ ዕርስ በርሱ የሚቃረን ይዘት ያለው መሆኑ ሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሣኔ ይዘት ለመረዲት ችለናል።
የክፍለ ከተማው የተለያዩ አካላት በተለያዩ ጊዜ የመደቧቸው ባለሙያዎች የተለያየ ውጤት ያለው ሙያዊ መግለጫ የሚያቀርቡት በመጀመሪያ ደረጃ የሥር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በጭብጥነት ሉያዙና ሉጣሩ የሚገቡ የፍሬ ጉዲይና የህግ ጭብጦች ሣይመሰርቱና የባለሙያዎች ቡድን አጣርቶ መግለጫ ሉያቀርብባቸው የሚገቡትን አከራካሪ ፍሬ ነገሮች ማለትም፡- (ሀ) አመልካች ከአንደኛ ተጠሪ ይዞታ 70 ሣንቲ ሜትር ርቆ ለመገንባት የተስማማው ባለሁለት ፍቅ ህንፃውን ብቻ ነው ወይስ ሰርቪስ ቤቱን ከአጥሩ 70 ሣንቲ ሜትር ርቆ ለመገንባት ተስማምቷል? ወይስ አልተስማማም?
(ለ) ለአመልካች የተሰጠው የግንባታ ፈቃድ ህጋዊ ሥልጣን ባለው አካል ተጠንቶ ተሻሽሎል ወይስ አልተሻሻለም?
(ሐ) አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ከተገነባው አጥር ላይ አስደግፍ ሰርቪስ ቤት የማይሰራ መሆኑን ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ተስማምቷል ቢባል አመልካች ሰርቪስ ኳርተር አሰጠግቶ የገነባበትን የአጥር ክፍል የገነባችው አንደኛ ተጠሪ ናት ወይስ አመልካች?
(መ) አመልካች ሰርቪስ ኳርተሩ የተገነባበትን የአጥር ክፍል አመልካች የገነባው መሆኑ ሲረጋገጥ አንደኛ ተጠሪ አመልካች አጥሩን አስደግፍ የገነባውን ሰርቪስ ኳርተር እንዱያፈርስ ለመጠየቅ የሚያስችላት የህግ መሰረት አለ ወይስ የለም?
(ሰ) አመልካች ሰርቪስ ኳርተሩን የገነባበትን የአጥር ክፍል የሰራችው አንደኛ ተጠሪ መሆኗ ቢረጋገጥ አመልካች አጥሩን አስደግፍ የሰራውን ሰርቪስ ኳርተር እንዱያፈርስ አንደኛ ተጠሪ ለመጠየቅ የሚያስችላት የህግ መሰረት አለ ወይስ የለም?
(ረ) አመልካች ባከናወነው ግንባታ የአንደኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም የሚጎዲ ህገ ወጥ ተግባር በመፈፀም በአንደኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት በማድረስ የሁከት ድርጊት ፈፅሟል ወይስ አልፈፀመም?
(ሰ) በአጠቃላይ አመልካች ህጋዊ ሥልጣን ባለው አካል ከተሰጠው የግንባታ ፈቃድ ውጭ ፈፅሟል ወይስ አልፈፀመም? አመልካች ከግንባታ ፈቃድ ውጭ ገንብቷል ቢባል በዚህ ግንባታ አንደኛ ተጠሪ መብትና ጥቅሟ ተነክቷል። ከግንባታ ፈቃድ ውጭ በተሰራው ግንባታ የአንደኛ ተጠሪ መብትና ጥቅም አልተነካም ቢባል ውጤቱ ምን ይሆናል? ከግንባታ ፈቃድ ውጭ በተሰራው ግንባታ የአንደኛ ተጠሪ መብትና ጥቅም ተነክቷል ቢባል ውጤቱ ምን ይሆናል? የሚለትን ጭብጦች በግልፅ በመያዝ ባለሙያዎች ቦታው ሄደው በማጣራት በተለያየ ጊዜ ለአመልካችና ለአንደኛ ተጠሪ በተለያዩ የክፍለ ከተማው የተለያዩ አካላት የተሰጣቸውን ሰነድ ማስረጃዎች ይዘት፡አግባብነት ካለው የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት በማድረግ አጣርተው እንዱያቀርቡ ግልፅ ትዕዛዝ ባለመስጠታቸው ልዩነት የተፈጠረ መሆኑን ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዲደር የሽግግር ጊዜ ፕሮግራም ጽ/ቤት ሀምላ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በባለሙያ አጣርቶ የሰጠውን መግለጫና ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክፍለ ከተማው የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ጽ/ቤት ባለሙያ ቡድን አጣርቶ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በጽሁፍ የሰጠውን መግለጫ ይዘት በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
ይህም የሥር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በባለሙያ ተጣርተው ሉቀርቡ የሚገባቸው አከራካሪ የፍሬ ጉዲይ ጭብጦች በግልጽ ሣይመሰርቱና መጣራት የሚገባቸውን ፍሬ ጉዲዮች በውል ሣይለዩና በግልጽ ሣይዘረዝሩ ባለሙያዎች አጣርተው ያቅርቡ የሚል ጥልቅ ትዕዛዝ በመስጠታቸው ተቃራኒ ይዘት ያላቸው ማስረጃዎች (Contradictory Evidence) ከክፍለ ከተማው የተለያዩ አካላት በተለያየ ጊዜ ቦታው ድረስ ሄደው አይተው የሰጡ መሆኑን ያሳያል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 246፣ አንቀጽ 247 እና አንቀጽ 248 መሰረት አከራካሪ ጉዲዮችንና ጭብጦችን በአግባቡ ሣይመሰርቱና ሣያጣሩ ውሣኔ በመስጠት መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀሙ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ የክፍለ ከተማው ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ ከቦታው ድረስ በመሄድና የሥር ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሰጡት ትዕዛዝ ተቃራኒ ይዘት ያለው አስተያየት ካቀረቡ ተቃራኒ ይዘት ካላቸው አስተያየቶች አንደኛውን ተቀብል ላላውን ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ግልፅ መስፈርትና ምክንያት ሉኖር ይገባል።
በተመሣሣይ የሙያ ብቃትና ልምድ ትይዩ የሆነ ሥልጣን ያላቸው የክፍለ ከተማው የተለያዩ አካላትና ባለሙያዎች አንድ መሰረታዊ ፍሬ ጉዲይ ላይ ያቀረቡት መግለጫ ዕርስ በርሱ የሚቃረን ሆኖ ዕውነታውን ለመለየት የማያስችል በሚሆንበት ጊዜ ተቃራኒ መግለጫውን ያየው ፍርድ ቤት ጉዲዩ በክፍለ ከተማው ካለ ባለሙያዎች የተሻለ ዕውቀትና የሥራ ልምድ ባላቸው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሚመለከተው ቢሮ ባለሙያዎች ተጣርቶ እንዱቀርብና ዕውነታው እንዱረጋገጥ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 250 እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136 (1) መሰረት ትዕዛዝ ሣይሰጥ አንደኛውን መግለጫ ተቀብል ላላውን ዕውነት ነው ብል ውሣኔ ለመስጠት የሚቻልበት የህግ መሰረት የለም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዚህ ፍርድ ተራ ቁጥር 8 የተገለፁት ጭብጦች በግልጽ ሣይዙና እንዱጣሩ ሣያደርጉና የክፍለ ከተማው ባለሙያዎች ከሰጡት ዕርስበርሱ የሚቃረን ሙያዊ ምስክርነትና መግለጫ ዕውነታው የትኛው እንደሆነ የተሻለ ሙያ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደር ባለሙያዎች ተጣርቶ እንዱቀርብላቸው ሣያደርጉ የሰጡት ውሣኔ ከላይ የገለፅናቸውን የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 246፣ አንቀጽ 247፣ አንቀጽ 248 አንቀጽ 250 እና አንቀጽ 136 (1) ድንጋጌዎች ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ፍርድ በተራ ቁጥር 9 የተገለፁትን ጭብጦች በመያዝና እነዚህ አከራካሪ የፍሬ ነገር ጭብጦች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሚመለከተው አካል የካበተ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች መድቦ አጣርቶ ውጤቱን እንዱያሳውቀው በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136 (1) መሰረት በማድረግና ዕውነታውን ለማረጋገጥ ይጠቅማለ ያላቸውን ሰነድች በማስቀረብና የምስክሮችን ቃል በመስማት ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ፡ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.