የይግባኝ መዝገብ በድሀ ደንብ እንዱከፈት የሚቀርብ ጥያቄን ለመወሰን አመልካች ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ( ንብረት በመታገደ ፣ገንዘብ ማንቀሳቀስ የማይችል እና የሚከፍለው ገንዘብ የላለ እንደሆነ) ለዲኝነት የሚከፈለው ገንዘብ ያለው ወይም የላለው መሆኑ መጣራት እና መረጋገጥ ያለበት ሰለመሆኑ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 567 ፣ፍ/ሕ/ቁ 1793/ለ/ እና አክሰስ ሪል እስቴት እና ጋቢኢንቨስትመንትኃ/የተ/የ ግ/ማ 8/10/ 2008 ዓ.ም 66 VI 37(1) 16. መብቴን የሚነካ ፍርድ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያን ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይቅርብ በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ መቃወሚያ መቅረብ ያለበት ክርክሩን ሰምቶ ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት ሰለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418
No summary available.
ሐምል 4 ቀን 2008ዓ.ም ዳኞች፡ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ መሰረት አንዲርጌ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ያቀረበችውን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ለመቀበልና ጉዲዩን በዲኝነት አይቶ ለመወሰን የሚያስችለኝ የዲኝነት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠውን ብይን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማጽናቱ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። አመልካችና ላልች የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅራቢዎች፣ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ያቀረቡት የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 13904 አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ከሳሽ ሶስተኛው ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረው መጋቢት 16 ቀን 2001ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንን በማሻሻል የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ነው።
በመዝገብ ቁ. 13904 አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ቀርበው ተከሳሽ (3ኛ ተጠሪ) የወላጅ አባታችን አቶ ስመኝ ባይህ የውርስ ንብረት የሆነ ንብረት በመያዝ ጠቅላላ ግምቱ ብር 2,856.000 /ሁለት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺ ብር/ የወሰደ በመሆኑ፣ ይህንን ገንዘብ ከነወለደ ድርሻችንን እንዱያካፍለን ይወሰንልን በማለት ክስ አቅርበዋል። ተከሳሽ ያቀረቡትን ክስ በመቃወምና በመከላከል መልስ አቅርቧል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሹ (ሶስተኛ ተጠሪ) ግምቱ ብር 1,867,728 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር/ የሟችን የውርስ ንብረት የያዙ በመሆኑ የከሳሾችን /አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪን/ ድርሻ ከነወለደ እንዱከፍል በማለት መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት የሶስተኛ ተጠሪንና የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪን የይግባኝ ክርክር በይግባኝ መዝገብ ቁ. 24731 ከሰማ በኋላ፣ የከሳሾች (የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ) የውርስ ንብረት ክፍያ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ሚያዚያ 11 ቀን 2002 ዓ.ም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 11 ቀን 2002ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ የሰበር አመልካች ሶስተኛ ተጠሪ የሰበር ተጠሪ በመሆን ያቀረቡትን ክርክር በሰበር መዝገብ ቁ. 09914 ከሰማ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ችልት የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የውርስ ንብረት ለመካፈል ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ሽሮ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ወደ ፍሬ ጉዲዩ ገብቶ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ውሳኔ ይስጥበት በማለት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሶለታል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቀደም ሲል ዘግቶት የነበረውን የይግባኝ መዝገብ ቁ. 24731 ካንቀሳቀሰ በኋላ (የይግባኝ ባዩን/ ሶስተኛ ተጠሪንና) የመልስ ሰጭዎችን /አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች/ ክርከር ከሰማ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ባዩ /ሶስተኛ ተጠሪ/ ለመልስ ሰጭዎች (አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ) ግምቱ ብር 1,867,728 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር/ ከሆነው የውርስ ንብረት ድርሻቸውን ያካፍላቸው በማለት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል አፅንቶ፣ ሶስተኛ ተጠሪ ወለድ ሉከፍል ይገባል በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ በመሻር ሶስተኛ ተጠሪ የውርስ ንብረት ወለድ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት በይግባኝ መዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሳኔ ሰጥቷል።
ሶስተኛ ተጠሪ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወለድን በተመለከተ የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር አጣሪ ችልት አቅርቦ፣ የክልለ የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። ሶስተኛ ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ሰበር ችልት አቅርቦ፣ ይኽ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ቁ. 96715 የሶስተኛ ተጠሪንና /የአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች/ ክርክር ከሰማ በኋላ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 13904 መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ.
24731 ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም እንደተሻሻለ አፅንቶታል። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለኝም በማለቱ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታ ለዚህ ሰበር ችልት አቅርበዋል።
ይህ ሰበር ችልት በአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች አመልካችነት መነሻ በሰበር መዝገብ ቁ.
98329 ከሰማ በኋላ የአንደኛና የሁለተኛ ተጠሪ የሰበር አቤቱታ በሰበር ለመታየት ብቁ አይደለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካችና በዚህ ክርክር ተሳታፉ ያልሆኑት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅራቢዎች የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ከሳሽ ሶስተኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው በተከራከሩበት በመዝገብ ቁ. 13904 መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠበት የውርስ ንብረት ላይ እኛም ድርሻ ያለን በመሆኑ ወደ ክርክሩ ገብተን ድርሻችን ተረጋግጦ እንዱወሰንልን በማለት ያመለከቱ ሲሆን አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የመቃወም አመልካችዎች የውርስ ንብረት ድርሻ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚልና ላልች መከራከሪያዎችን አቅርበዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዲዩ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ውሳኔ የሰጠበት በመሆኑ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻው መቅረብ ያለበት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ነው በማለት የአመልካችንና የላልቹን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ይህንን ብይን በመቃወም ያቀረበችውን የይግባኝ ቅሬታ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በይግባኝ መዝገብ ቁ. 40822 ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም አይቶ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች የሟች አቶ ስመኝ ባይህን የውርስ ንብረት በተመለከተ የሟች ተተኪ ወራሽ የሆንኩት አመልካች በክርክሩ ተሳታፉ ሳልሆን፣ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ከሳሽ ሶስተኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረው የውርሱን ንብረት እንዱካፈለ ውሳኔ የሰጠበት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ወለድን በተመለከተ ብቻ ከማሻሻል ውጭ የዞኑን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቶታል። ስለዚህ የፍርድ መቃወሚያው መታየት የሚገባው የውርስ ንብረቱን በተመለከተ አከራክሮ ውሳኔ ለሰጠው ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆን ሲገባው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን ስህተት አለበት በማለት ያመለከተች ሲሆን ተጠሪዎች ጉዲዩ እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት ድረስ ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን ገልጸው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ የፍርድ መቃወሚያ የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
ከላይ በዝርዝር እንደተገለጸው፣ አመልካች መብቴና ጥቅሜ በክርክሩ ተካፊይ ሳልሆን ውሳኔ ተሰጥቶበታል የምትለውን የሟች ስመኝ ባይህን የውርስ ንብረት በተመለከተ የአንደኛና የሁለተኛ ተጠሪን ክስና ማስረጃ የሶስተኛ ተጠሪን የመከላከያ መልስና ማስረጃ ሰምቶና የሟች ውርስ ብር 1,867,728 /አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሃያ ስምንት ብር/ እንደሆነ በመግለጽ፣ ይንን ገንዘብ ከነ ወለደ ሶስተኛ ተጠሪ ለአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ድርሻቸውን እንዱያካፍል በማለት ውሳኔ የሰጠው የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 13904 መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ነው። የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ የወለድ ክፍያን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 24731 ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔም ሆነ ይህ የሰበር ችልት በመዝገብ ቁ. 96715 እና በሰበር መዝገብ ቁ. 98329 በሰጠው ውሳኔ አልተለወጠም።
ይህም የሚያሳየው አመልካች አጠቃላይ ግምቱ ብር 2,801,592 /ሁለት ሚሉዮን ስምንት መቶ አንድ ሺ አምስት መቶ ዘጠና ስምንት ብር/ በሆነው የሟች ስመኝ ባይህ የውርስ ንብረት ላይ ድርሻ እያለኝ የክርክሩ ተሳታፉ ሳልሆን መብትና ጥቅሜን የሚጎዲ ውሳኔ ተሰጥቶብኛል በማለት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ላይ መሰረታዊ የሆነ ውሳኔ የሰጠበት የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ያሳያል። ይህንን ፍርድ በመቃወም አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የምታቀርበውን የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ተቀብልና የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ቀደም ሲል የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360(2) መሰረት የማፅናት፣ የማሻሻል፣ የመሰረዝ ወይም የመሻር ስልጣን ያለው አመልካች በውሳኔው መብትና ጥቅሜ ተነክቷል የምትለው የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የፍርድ መቃወሚያዋን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ታቅርብ በማለት የሰጠው ውሳኔ በጉዲዩ በየደረጃው ያለ ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ይዘትና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘትና ተግባራዊ አፈጻጸም ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን በትእዛዝ ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 13904 ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ብይንና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ. 40822 ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ተቀብልና የግራቀኙን ክርክር ሰምቶ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን አለው በማለት ወስነናል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበችውን የፍርድ መቃወሚያና ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341 መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.