No summary available.
ሐምል 8 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አክሰስ ሪል ስቴት (አ.ማ) ተጠሪ፡- ጋቢ ኢንቨስትመንት ኃ/የተ/የግል ማህበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት በስሙ የላለው መሆኑ አልተረጋገጠም። በአንፃሩ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ድርጅቱ በቂ የገንዘብ አቅም ያለው መሆኑንና ለቤት ገዥዎች ቤታቸውን አጠናቅቆ ሉያስረክባቸው እንዱችል የከፈለት ገንዘብ እንዱመለስላቸው የሚጠይቁ የቤቱ ገዥዎች ገንዘባቸው የሚመለስላቸው መሆኑን ግልፅ የሆነ መግለጫ ሰጥተዋል ስለዚህ አክሲዮን ማህበሩ ደሃ ነው ለማለት ስለማይችል ይግባኙ በድሃ ደንብ ሉከፈትለት አይገባም የሚል ክርክር አቅርቧል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ አመልካች ይግባኝ ባይ /አመልካች/ ካለው ካፒታል 3/4ኛው የጠፊ ስለመሆኑ በገለልተኛ ባለሙያ ተጣርቶ ያልቀረበ በመሆኑ በድሃ ደንብ ይግባኙ እንዱከፈትለት ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ያለኝን ንብረት ሽጬ ወይም አከራይቼ ለዲኝነት እንዲልከፍል በተለያዩ አካላት በተሰጠ የዕግድ ትዕዛዝ ምክንያት የማልችል መሆኔን በገለፅኩበት ሁኔታ ፍትህ የማግኘት መብቴን የሚያሳጣ ብይን መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚል የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረት የላለው መሆኑን በመዘርዘርና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያቀረባቸውን መከራከሪያ ነጥቦች በማጠናከር መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የፍተሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 467 የዲኝነት የሚከፍለው ገንዘብ የላለውና ለማግኘት የማይችል ሰው በነፃ ፊይል ማስከፈት እንደሚችል በንዐስ አንቀጽ 1 ደንግጓል። አመልካች የይግባኝ መዝገብ በነፃ እንዱከፈትለት ጥያቄ ያቀረበው ያለውን ንብረት እንዲይሸጥ፣ እንዲይለውጥና እንዲያከራይ በተለያዩ የመንግስት አካላት ለጊዜው የተላለፈ የዕግድ ትዕዛዞች ስላለ ያለኝን ሀብት ሸጬ የባንክ ሑሳቤን አንቀሳቅሼ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መክፈል የሚገባኝን የዲኝነት ገንዘብ ለጊዜው ላገኝ አልቻልኩም በማለት ነው። ይህም በመንግስት አካላት በተሰጠ ትዕዛዝ አመልካች ያለትን የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲይሸጥ፣ እንዲይለውጥ የባንክ ሑሳብ እንዲይከፍትና እንዲያንቀሳቅስ ተደርጎ ከሆነ አመልካች በንግድ ህጉ መሰረት ¾ የነበረውን ካፒታል የተጠቀመ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ የከሰረ መሆኑ ባይረጋገጥም በፍተሐ ብሓር ህግ ቁጥር 1793 (ለ) መሰረት አመልካች ከአቅሙ በላይ በሆነ የመንግስት አካላት ንብረቱን እንዲያንቀሳቅስ በሰጡት ዕግድና ጊዜያዊ ክልከላ ምክንያት ለጊዜው ይግባኙን ለማሳየት የዲኝነት የሚከፍለው ገንዘብ የላለ መሆኑ ከተረጋገጠ ንብረቱን መሸጥ መለወጥ ሲፈቀድለት በቅድሚያ የዲኝነት ክፍያውን የሚከፍል ሆኖ ለጊዜው ይግባኙ በነፃ እንዱከፈትለት ከመጠየቅ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 467 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እና የህገ መንግስቱ አንቀጽ 37(1) ድንጋጌ ይዘት፡- አመልካች አለኝ የሚለውን ንብረት እንዲላንቀሳቅስ ታግድብኛል ከሚለው ክርክር ጋር በማገናዘብ ለመረዲት ችለናል። ከዚህ አንፃር ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ከነበረው ካፒታል ¾ኛ መጠቀሙ ስላልተረጋገጠ በነፃ ዲኝነት ሉከፈትለት አይገባም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካች ለጊዜው ይግባኙን ለማሳየት የሚከፍለው የዲኝነት ገንዘብ ለመክፈል የማያስችለው በተለያዩ ንብረቶች ላይ የተለያዩ የመንግስት አካላት የሰጡት ዕግድ ያለመሆኑን የገለፀውን ፍሬ ነገር ይግባኝ ሰሚው ችልት ዕውነትነት ያለው መሆኑን በጭብጥነት በመያዝ ያላጣራው መሆኑን ተገንዝበናል። ከዚህ አንፃር ይግባኝ ሰሚው ችልት፡ሀ) የድርጅቱ ሰራተኞች ገዥዎች የፍርድ ባለመብት በመሆናቸው በፍርድ ቤት የታገደ የአመልካች ገንዘብና የሚንቀሳቀስንና የማይንቀሳቀስ ንብረት፣ ለ) አክስዮን ማህበሩ የባንክ ሑሳብ እንዲያንቀሳቅስና እንዲይከፍት ከብሓራዊ ባንክ ለላልች ባንኮች የተሰጠ መመሪያና ዕግድ ያለ መሆኑን፣ ሐ) ድርጅቱ በሑሳብና በልላ መንገድ የያዛቸውና ያለማቸው መሬቶች ላይ ማናቸውንም እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ለላልች አካላት የተሰጠ መመሪያና ዕግድ ያለ መሆኑንና መ) ድርጅቱ በስሙ ያለትን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲይሸጥ፣ እንዲይለውጥ፣ እንዲያከራይ፣ በዕዲ እንዲያሲዝ ከሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንስ የተላለፈ መመሪያና የተሰጠ ዕግድ ያለ ስለመሆኑ አመልካች ማስረጃውን እንዱያቀርብ በማድርግና ተጠሪም የአመልካችን ማስረጃ የሚያስተባቡለ ማስረጃዎች እንዱያቀርቡ በማድረግ አመልካች በፍተሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 1793 (ለ) በንብረቶች ላይ ባስተላለፈው ዕግድና ጊዛዊ ክልከላ መሰረት ይግባኙን በማሳየት መክፈል የሚገባውን የዲኝነት ገንዘብ ለጊዜው መክፈል የማይችልበት ሁኔታ አለ ወይስ የለም የሚለው ጭብጥ ላይ ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት በዚህ ፍርድ የተገለፁትን ነጥቦች በማጣራት የይግባኝ መዝገቡ በነፃ ሉከፈት ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.