ተከሳሽ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ አምኖ ነገር ግን ሕግ ወይም ላላ ፍሬ ነገር በመጥቀስ የቀረበብኝ ክስ ዋጋ የለዉም ብል የሚከራከር ከሆነ ሙግቱን የሚጀምረው ተከሳሽ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 258/1/
No summary available.
ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ዲዊት በለጠ የጠጠር አምራች ድርጅት -ጠበቃ እሸቱ አሰፊ -ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አብደራዛቅ ሙሳ ኡስማን -አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የአሁን ተጠሪ ህግ ከደነገገው ውጭ አመልካች የስራ ውላን አቋርጧል፤
ስለሆነም ለህገውጥ ስንበት በህጉ የተፈቀደው ልዩ ልዩ ክፍያዎች ይከፈለኝ በማለት የክፍያ አይነቶችን ዘርዝሮ ዲኝነት ሲጠይቅ፤ የአሁን አመልካች በበኩለ ተጠሪ ከነሀሴ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመደዲ ከስራ የቀረ በመሆኑ የስራ ውለ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/ለ/ ስር በተመለከተው መሰረት እንዱቋረጥ ተደርጓል። ስለዚህ ስንብቱ ህጋዊ ስለሆነ ክፍያ ልንጠየቅ አይገባም። የ25 ቀን የዓመት እረፍት እንከፍላለን በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ምስክሮቹን ለማቅረብ በተያዘው ቀጠሮ ቀን ያላቀረበ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 199/1/ መብቱ የታለፈ መሆኑን በመግለፅ፤ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ ስለላለ ስንብቱ ህገወጥ ነው በማለት ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በማስላት በድምሩ ብር 23,000 ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት ስላለገኘ በትእዛዝ ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ:- ማስረጃ የማሰማት መብት የታለፈው በግልፅ የተካደ ፍሬ ነገር በማስረጃ ሳይነጥር አምነዋል ተብል ውሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተብል እንዱሻርልን ወጪና ኪሳራ እንዱተካልን የሚል አቤቱታ አቅርበዋል።
የአመልካች የሰበር አብቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርበዋል ።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካች ጥያቄ የማስረዲት መብት በማለፍ በማስረጃ ሳይረጋገጥ ውሳኔ መሰጠቱ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ደግሞ አመልካች አዱስ ነገር በማቀረቡ ክሱ የሚከፍተው ተከሳሽ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተከሳሽ የማሰረዲት ኃለፉነቱ ነው ማለቱ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት የአሁኑ አመልካች ምስክሮቹ እንዱያቀርብ በተያዘው ቀጠሮ አለመቅረቡን ነው።
ክስን መክፈትና ሙግትን የመጀመር መብት የከሳሽ ነው። ነገር ግን ተከሳሹ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ አምኖ ነገር ግን ሕግ ወይም ላላ ፍሬ ነገር በመጥቀስ የቀረበብኝ ክስ ዋጋ የለውም ብል የሚከራከር ከሆነ ሙግቱን የሚጀምረው ተከሳሹ እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 258/1/ ስር ተመልክቷል። ከሳሽ በማስረጃ አቀራረብ ረገድ ጀማሪ የሚሆነው ሁል ጊዜ እንዲልሆነ የስነ ስርዓት ህጉ በግልፅ ይደነግጋል።
ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ በተጠሪ የቀረበው ክስ የስራ ስንብቱ ህገወጥ ነው የሚል ሲሆን አመልካች ደግሞ ከስራ ያሰናበተው መሆኑን በማመን ነገር ግን በተከታታይ የስራ ቀናት በመቅረቱ ስንብቱ ህገወጥ ልባል አይችልም የሚል ነው። እዚህ ላይ አመልካች ተጠሪን ከስራ ማሰናበቱን ከተቀበለ ፤ ለሰንብቱ ምክንያት የሆነው የተጠሪ ጥፊት መሆኑን የማሰረዲት ሸከሙ የስር ተከሳሽ የአሁኑ አመልካች ነው። ተጠሪ በተከታታይ የስራ ቀናት መቅረቱን ማረጋገጥ ያለበት አመልካች እንጂ ተጠሪ እንዱያስረዲ አይጠበቅም። አመልካች ምስክሮቹን እንዱያቀርብ በተያዘው ቀጠሮ ባለማቅረቡ የታለፈበት መሆኑ ከስር መዝገብ ተመልክቷል።
ተጠሪ ከህግ ውጭ ከስራ ስላሰናበተኝ ተገቢውን ክፍያ ይከፈለኝ የሚል ክስ ያቀረበው አመልካች ያሰናበተው መሆኑን አምኖ የተሰናበተው በተጠሪ ጥፊት መሆኑን ገልፆ ስለተከራከረ መጀመሪያ ማስረዲት ያለበት አመልካች ነው። ነገር ግን በአመልካች ጉድለት ምክንያት ምስክሮቹን በማቅረብ ማስረዲት አልቻለም። በማስረጃ ያልተደገፈ የፍሬ ነገር ክርክር ረቺ ላሆን አይችልም። ስለዚህ ከላይ በተዘረዘሩ ምክንያቶች አመልካች ማስረጃ ሳይሰሙ መወሰኑ አግባብ አይደለም ሲል ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በዚሁ መሰረትም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.54094 ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ /ፍ/ቤት በመ/ቁ. 10627 ሰኔ 4 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/በ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በፋ/መ/ደ/ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 57878 የተጀመረው አፈፃፀም ታግድ እንዱቆይ በዚህ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነሰቷል። ለሚመለከተው አካል ይፃፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.