አንድ በፍርድ ቤት የተወከለን ሰው በችልት ተገቢ ያልሆነ ስነ ምግባር አሳይቷል በማለት ፍ/ቤት የውክልና ስልጣንን መሻር የማይቻል ስለመሆኑ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 41 አቶ አደን የሱፍታረ እና አቶአህመድ አብደላሂ ተረቢ
No summary available.
. መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ አደን ዩሱፍ ታኒ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አህመድ አብደላሂ ተረቢ - ጠበቃ ሽፈራው በላይ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በቀረበበት የድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የተጠሪው አባት መሆኑ በተረጋገጠው ይዞታ ላይ ለገነቡት ቤት የቤቱን የዋጋ ግምት ብር 346,292 (ሶስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት) ወስደው ቤቱን ከነይዞታው ከሳሽ ለነበሩት የአሁኑ ተጠሪ ለቀው እንዱያስረክቡ በድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር M/13/06 በ06/05/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በሶማላ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ ቁጥር 05-33/06 በ03/08/2006 ዓ.ም እና በመዝገብ ቁጥር 05-1-91/06 በ14/09/2006 ዓ.ም. የፀናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አመልካች የተጠሪ አባት ይዞታ በሆነው ቦታ ላይ አላግባብ ቤት መስራታቸውን የሚገልጽ ሆኖ ይህንኑ ይዞታና ቤት ለቀው እንዱያሰረክቡ ዲኝነት የተጠየቀበት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይዘቱ ከላይ የተገለፀውን ውሳኔ የሰጠው የአመልካቹን መልስ የመስጠት መብት አልፍ የተጠሪውን ምስክሮች በመስማት እና ቀጥልም ክሱን ከሰማ እና አመልካቹ በይዞታው ላይ የገነቡት ቤት በባለሙያዎች ተገምቶ እንዱቀርብ ካደረገ በኃላ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ተጠሪው ባድ መሬት በብር 100,000 ገምተው ክስ ማቅረባቸውን፣የአመልካች ተወካይ ከክርክሩ እንዱሰናበቱ ተደርጎ አመልካች መልስ ለማቅረብ በቂ ጊዜ ሳይሰጣቸው መልስ አላቀረቡም በሚል መልስ የመስጠት መብታቸው የመታለፈን፣በኋላም ቀርበው የቃል ክርክር አድርገዋል ተብል ማስረጃ የማቅረብ ዕድል ሳይሰጣቸው የተጠሪ ምስክሮች ብቻ ተሰምተው አመልካች ከ35 ዓመት በላይ ሰርተው የሚኖሩበትን ቤት ለተጠሪው እንዱለቁ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመወሰኑን እና ውሳኔው በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች የመፅናቱን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እልባት ማግኘት የሚገባው ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቹን መልስ የመስጠት መብት አልፍ የተጠሪውን ክርክር እና ማስረጃ ብቻ መሰረት አድርጎ ውሳኔ መስጠቱ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከዚሁ ነጥብ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው የድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይዘው እንዱቀርቡ በተሰጣቸው የ19/03/2006 ዓ.ም. ቀጠሮ አልቀረቡም በሚል በ30/03/2006 ዓ.ም. በተጻፈ መጥሪያ መልሳቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ለ02/04/2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑን፣በዚህ ቀነ ቀጠሮ የአመልካቿ ልጅ እና ተወካይ የጽሁፍ መልሳቸውን ይዘው የቀረቡ መሆኑን፣ይሁን እንጂ መልሱ ስህተት አለበት በሚል አስተካክለው እንዱያቀርቡ በተነገራቸው መሰረት ለመፈጸም ተወካይዋ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እና ችልቱንም ስለሰደቡ በአመልካች የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ተሰርዟል በሚል አመልካች ራሳቸው መልሳቸውን ይዘው እንዱቀርቡ ለ04/04/2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑን፣የአመልካቹ የጽሁፍ መልስ የመስጠት መብት የታለፈውም አመልካች በዚህ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርቡ በመቅረታቸው መሆኑን፣ከዚህ በኃላ ፍርድ ቤቱ በ05/04/2006 ዓ.ም. ክርክር ያስነሳውን ቤት እና ይዞታ በአካል ሄድ የተመለከተ መሆኑን፣በ07/04/2006 ዓ.ም. የተጠሪውን ምስክሮች የሰማ መሆኑን እና በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 ድንጋጌ መሰረት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል የተባለውም ከላይ የተመለከተው ሂደት ሁለ ከተከናወነ በኃላ በመጨረሻ ላይ በ15/04/2006 ዓ.ም. መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
በመሰረቱ ተገቢው የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው እስከሆነ ድረስ የዋናው ባለጉዲይ ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት፣አያት ስለዋናው ባለጉዲይ ሆነው በወኪልነት ለመከራከር፣ ለመሟጋትና ነገሩን ለመከታተል የሚችለ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 58 (ሀ) ስር የተመለከተ ሲሆን የአመልካች ልጅም በዚሁ ስርዓት መሰረት ከአባታቸው በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን መሰረት በ02/04/2006 ዓ.ም. ቀነ ቀጠሮ የጽሁፍ መልስ ይዘው ቀርበው እንደነበረ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ ገልጿል።መልሱ ስህተት አለበት ከመባለ በቀር ስህተቱ ምን እንደሆነ እና ስርዓቱን ጠብቆ የተሰጠ የመልስ ይሻሻል ትዕዛዝ ስለመኖሩ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።የአመልካች ልጅ ከክርክሩ እንድትሰናበት የተደረገው አባቷን ወክላ ለመከራከር የሚያስችል ተገቢ የውክልና ስልጣን ስላልነበራት ነው በማለት ተጠሪው በሰበር መልሳቸው ያቀረቡት ክርክር የመዘገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ አይደለም።ከላይ እንደተገለጸው ፍርድ ቤቱ ከክርክሩ ያሰናበታትም ለችልቱ ያልተገባ ሥነ ምግባር አሳይታለች በሚል እንጂ ይዛው የቀረበችው የውክልና ስልጣን ማስረጃ ጉድለት አለበት በማለት አይደለም።
በመሰረቱ የአመልካቹ ተወካይ ለችልቱ ተገቢ ያልሆነ ስነ ምግባር አሳይተዋል የሚባል ከሆነ የችልቱን ክብር ለማስጠበቅ ፍርድ ቤቱ በሕግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይችል የነበረ ከመሆኑ ውጪ አመልካች ለልጃቸው የሰጡትን የውክልና ስልጣን ለመሰረዝ ወይም ለመሻር የሚያስችል ስልጣን የለውም።በልላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተገቢ ምክንያቶች ሲያጋጥሙት ምክንያቱን በማስፈር ዋናው ባለጉዲይ እራሱ እንዱቀርብ ትዕዛዝ መስጠት የሚችል ስለመሆኑ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተ ቢሆንም በተያዘው ጉዲይ አመልካች ራሳቸው መልሳቸውን አዘጋጅተው እንዱቀርቡ የተሰጣቸው የሁለት ቀናት ጊዜ ብቻ ነው።ይህ ጊዜ ደግሞ ከተለያዩ ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ በቂ ነው ልባል የሚችል አይደለም።በመሆኑም የአመልካች ወኪል ያቀረቡት የጽሁፍ መልስ ተቀባይነት ያጣበት በቂ እና ሕጋዊ ምክንያት መኖሩ ባልተገለጸበት እና ስርዓቱን ጠብቆ የተሰጠ የመልስ ይሻሻል ትዕዛዝ በላለበት ሁኔታ፣ እንዱሁም አመልካች እራሳቸው መልሳቸውን አዘጋጅተው ማቅረብ እንዱችለ በቂ የሆነ ጊዜ እንዱሰጣቸው ባልተደረገበት ሁኔታ የአመልካቹ የጽሁፍ መልስ የመስጠት እና ማስረጃ የማሰማት መብት ታልፍ የተጠሪውን ክርክር እና ማስረጃ ብቻ መሰረት አድርጎ አመልካቹን ለክሱ ኃላፉ የሚያደርግ ውሳኔ መሰጠቱ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር M/13/06 በ06/05/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በሶማላ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ ቁጥር 05-33/06 በ03/08/2006 ዓ.ም እና በመዝገብ ቁጥር 05-1-91/06 በ14/09/2006 ዓ.ም. የፀናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካቹ ለደረሳቸው ክስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 334 (1) ድንጋጌ መሰረት ተገቢ ነው የሚለትን የጽሁፍ መልስ እንዱያቀርቡ ካደረገ በኃላ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት አድርጎ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ ጭምር መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ለድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱመለስ ወስነናል።
የውሳኔው ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለድል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣እንዱያውቀው ደግሞ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይላክ።
በሶማላ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 05-1-91/06 የተሰጠው ፍርድ አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ04/13/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.