አሰሪ የተጠየቀን የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ አጠቃላይ ተቃውሞ አቀርቦበት እያለ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ሰላቱን በተመለከተ አልተቃወመም በሚል በመተርጎም በሰራተኛው የተጠየቀን የስንብት ክፍያ ዲኝነት ሙለ በሙለ በመወሰን የሚሰጥ ዲኝነት ተገቢ ስላለመሆኑ ፤ፍ/ቤቱ በሕጉ አግባብ አስልቶ መጠኑን ሉወሰን የሚገባ ሰለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 40 (1 እና 2) 119694 ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና አቶ አለማየሁ ሁለቃ 27/11/ 2008ዓ.ም 22 7. ለጡረታ አፈፃፀም ተብል የመንግሰት ሰራተኛን የግል ማህደር በኤጀንሲው እንዱላክ ተጠይቆ፤ሰራተኛው ኢትዩጵያ እህል ንግድ ድርጅት 23/1/ 2009 ዓ.ም 28 III ንብረት አልመለሰም በማለት ማህደር አልክም ማለት ህጋዊ ሰላለመሆኑ ፤ የጡረታ አበል የማግኘት መብት የዕዲ መያዣ ላደረግ ወይም በውርስ ወይም በማናቸውም መንገድ ሉተላለፍ የማይችል ሰለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 345 /97 አንቀፅ 47 (2) ፣ 44 እና 55 (2) እና አቶ ካሳሁን በዛብህ 8. አሰሪ ሰራተኞችን ከማሰናበቱ በፉት በትክክል አጣርቶ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ፤ክርክር ከተጀመረ በኃላ ከስንብት ደብዲቤ ላላ ደብዲቤ መፃፈ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ዓላማ እና መንፈስ የማያሟላ ሰለመሆኑ ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 (1) (3) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 (1) (ሸ) ( ቀ) 125778 ሲው ኢንፍራስትራክቸር እና እነ አቶ መሳይ ወ/ገብርኤል ( አራት ሰዎች) 23/1/ 2009 ዓ.ም 32 9. አንድን ሰራተኛ የሥራ መሪ ነው ልባልበት ስለሚቻልበት አግባብ፡የሥራ መሪን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ ተግባራዊ ሉሆኑ ስለሚገባቸው ህጎች፡የስራ መሪ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ቀሪ ስለሚደረጉበት የይርጋ ፍራውን ኮ/ህንፃ ተቋራጭ እና እነ አቶ ካህሳይ ገ/እግዚአብሄር (ሁለት ሰዎች) 21/2 /2009 ዓ.ም 37 IV አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2(!)፣ 3(2(ሐ) የፍ/ሕ/ቁ.1677(1)፣1845፣2512፣2593 10. ተዋዋይ ወገኖች በስራ ውል ስምምነታቸው በግልፅ ኮሚሽንን የደሞዝ አካል አድርገው እስከተዋዋለ ድረስ ቅራኔ በተነሳ ሰዓት ኮሚሽንን እንደ ደመወዝ አይደለም በማለት መውሰድ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/1996 አንቀፅ 53(2(መ) 117070 ወ/ሮ ወይንሸት በቀለ እና ኦልምፒያኮስ ሄኔኒክ አትላቲክስ ማህበር (ግሪክ ክለብ) 22/2/ 2009 ዓ.ም 46 የፍትሐ ብሓር ሥነ- ሥርዓት 49 11. ቼክን በተመለከተ በአጭር ስነ ስርዓት /Summary proceding/ ዲኝነት ታይቶ እንዱወሰን ክስ በቀረበበት ወቅት ተከሳሽ መከላከያውን እንዱያቀርብ ጥያቄ አቅርቦ ተፈቅድለት መልስ እንዱያቀርብ ተደርጎ መልስና በሕግ አግባብ ምስክር ቆጥሮ እያለ ምስክሮች ሳይሰሙ ይኼው ታልፍ የቼክ ባሕርይን ብቻ መሰረት ተደርጎ ዲኝነት የሚሰጥበት አግባብ ትክክል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 285/1/ 286 እና 291 የን/ሕ/ቁ. አንቀጽ 717 V ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በተለይ በእያንዲንደ ጉዲይ እንዱታይ የሚጠይቀውን ዲኝነት መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224(2) እና አቶ ሐረጳ ቤኛ
No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- አቶ ነገሰ ግዛው -ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ሑርጳ ቤኛ - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች አቶ ነገሰ ግዛው ጥር 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጡት ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የቀረበ ነው። ቅሬታውም በዋናው መዝገብ በቀን 9-4-2006 ዓ.ም በዋለው ችልት በተሰጠው ውሳኔ አዋሳኙ ተጠቅሶ 1 ቀርጥ የመሬት ይዞታ እንደሆነ በግልጽ ተጠቅሶ የቀረበ ሲሆን ሁለት ተኩል ቀርጥ መሬት እንድፈጽም መታዘዙ ተገቢ ባለመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. የአሁን ተጠሪ ሂርጳ ቤኛ የአፈጻጸም ክስ አቅርቦ ፍ/ቤቱ የቀበላው መስተዲድር የአፈጻጸም ተከሳሽ አቶ ነገሰ ግዛው ከመሬቱ ላይ ባህር ዛፍቹን ለማንሳት ፍቃደኛ ስላልሆነ ከባህርዛፍቹ ጋር ለአፈጻጸም ከሳሽ አስረክበናል። ባህርዛፍቹ 1 ዓመት የሞላቸው ሆኖ በሁለት ቀርጥ ተኩል መሬት ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል። የአፈጻጸም ተከሳሽ ለአ/ከሳሽ የተወሰነለት መሬት አንድ ጥማድ ብቻ በመሆኑ ላላውን መፈጸም አይገባኝም ሲል የአ/ከሳሽ ደግሞ ክስ ያቀረብኩትና የተወሰነልኝ የመሬት አዋሳኝ ይሄው የተፈጸመልኝ መሬት በመሆኑ ባግባቡ የተፈጸመ ነው በማለት የተከራከሩትን መዝግቦ የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ የተሰጠው ውሳኔ የመሬቱን አዋሳኝና ስፊቱ በክሱ ውስጥ የተቀመጠው ነው በማለት ስለተወሰነ ለአፈጻጸም ከሳሽ የተፈጸመለት መሬት የተወሰነለትን ነው በማለት ወስደን ውሳኔው ፍጻሜ ስላገኘ መዝገቡን ዘግተነዋል ሲል አዟል። የአፈጻጸም/ ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ. ነሐሴ 22/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ የስር ፍርድ ቤት በዋናው ውሳኔ በመ. ታህሳስ 9/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ የመሬቱ አዋሳኝ በምስራቅ አቶ ጣፊ ሀይለ እና አበራ ሃይለ በምዕራብ እና በሰሜን በአፈጻጸም ተከሳሽ እና በደቡብ የመኪና መንገድ ሲሆን አንድ ቀርጥ መሬት ነው። ቀበላው በውሳኔ ውስጥ የተጠቀሰውን አዋሳኝ መሬት 2 ቀርጥ ተኩል ያስፈጸመ መሆኑን በሪፖርቱ ጠቅሷል። የመሬቱ አዋሳኝ በውሳኔ በተጠቀሰው አዋሳኝ ውስጥ ያለው መሬት ሁለ በመሆኑ ይግባኝ ባይ ቅሬታ ካለው በይግባኝ ማስተካከል ነበረበት እንጂ እንደውሳኔው በመፈጸሙ ቅር የሚያሰኝ አይደለም ሲል የወረዲ ፍ/ቤትን ትዕዛዝ አጽንቷል። አ/ተከሳሽ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ቁ. 187309 ጥር 14/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ የቀረበው አቤቱታ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ አቤቱታ አያስቀርብም ሲል ውድቅ አድርጎታል።
የአሁን አመልካች ይህን ትዕዛዝ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡ ተመርምሮ አመልካች በዋናው ፍርድ ለተጠሪ እንዱያስረክቡ የተወሰነባቸው አንድ ቀርጥ መሬት መሆኑን የስር ፍ/ቤት በውሳኔው ላይ ገልጾ አመልካች ለተጠሪ ያስረከቡት ግን ሁለት ቀርጥ ተኩል መሆኑን የቀረበው ሪፖርት የሚያሳይ ሆኖ እያለ ከፍርደ ውጪ አንድ ቀርጥ ተኩል መሬት በተጨማሪ ማስረከብ የለብኝም ሲል አመልካች ያቀረበውን ቅሬታ የስር ፍ/ቤት ሳይቀበለው የመቅረቱን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም. በተጻፈ መልስ የወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች መብቱ ያልሆነውን እና በአዋሳኝ የማንገናኝ ይዞታየን ይዞ ባህር ዛፍ መትከለ ተረጋግጦ ባህርዛፈን አንስቶ ይዞታዬን እንዱለቅልኝ በውሳኔው መሰረት የተፈፀመ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ይሁንልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ሰኔ 18/2007 ዓ.ም. በተፃፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል። በዚሁ መሰረት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው ፡ በዋናው መዝገብ የተሰጠው ውሳኔ አንድ ቀርጥ መሬት አዋሳኙ ተጠቅሶ የአሁን አመልካች ለተጠሪ እንዱለቅለት የተወሰነ ስለመሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም። ውሳኔ የተሰጠበት መሬት ስፊቱ አንድ ቀርጥ መሬት ሆኖ እያለ ሁለት ቀርጥ ተኩል መሬት ለአሁን ተጠሪ መፈጸሙን በተመለከተ የሥር ፍ/ቤት በዋናው መዝገብ ውሳኔ ሲሰጥ አዋሳኙ ተጠቅሶ የተወሰነ በመሆኑና አሁንም ለተጠሪ (የአፈጻጸም ከሳሽ) የተፈጸመው በዚሁ አዋሳኙ በተጠቀሰው ክልል ውስጥ የሚገኘው መሬት በመሆኑ አፈጻጸሙ ተገቢ ነው በማለት ወስኗል።
ለዚህ ውሳኔያቸው ድምዲሜ ምክንያት ያደረጉት የዋናው መዝገብ ውሳኔ የመሬት አዋሳኝን መሰረት በማድረግ ብቻ እንደሆነ ከተደረገው ክርክር መረዲት የሚቻል ነው።
ይሁንና በዋናው መዝገብ አንድ ቀርጥ የመሬት ይዞታ ውሳኔ ተሰጥቶበት ከእጥፍ በላይ ሁለት ቀርጥ ተኩል መፈጸሙ የመሬቱ አዋሳኝ በአንድ በኩል በደቡብ አቅጣጫ የአፈጻጸም ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) የሚያዋስነው ሆኖ እያለና በዚሁ አቅጣጫ ወደ አመልካች የመሬት ይዞታ ሉታለፍ የሚችልበት ሁኔታ ሉኖር ስለሚችል የስር ፍ/ቤት በሚከተለት 1. ክርክር ስላስነሳው የእርሻ መሬት አዋሳኝ እና መጠን ጉዲይ ተጠሪዋ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ በፍ/ብ/ህ/ቁ.
224(2) መሰረት የሰጡት መግለጫ ይዘት ምን እንደሆነ 2. በአመልካቹ መልስ ላይ የተሰጡት ትችት ምን እንደ ሆነ፡ 3. ክርክር ስላስነሳው የእርሻ መሬት አዋሳኝ እና መጠን ጉዲይ በስረ ነገሩ ፍርድ ላይ የተገለጸው የውሳኔ ክፍል የተሟላ ይዘት ምን እንደሆነ 4. ተጠሪዋ ክስ ያቀረቡበት እና የስረነገሩ ፍርድ ያረፈበት የእርሻ መሬት ይታወቅ የነበረው በቀርጥ በምን ያክል መጠን እንደ ሆነ፡ ከተጠቀሱት ነጥቦች በመነሳት በስረነገሩ ፍርድ ላይ በተገለጸው መጠን እና በአፈጻጸም ጊዜ በተለካው መጠን መካከል ልዩነት ሉከሰት የቻለበት አጠቃላይ ምክንያት ምን እንደሆነ ተጣርቶና ተለይቶ ከታወቀ በኃላ መፈጸም ነበረበት። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በዋናው መዝገብ ውሳኔ የተሰጠበት መሬት አንድ ቀርጥ ሆኖ እያለ ሁለት ቀርጥ ተኩል የሆነበት ምክንያት ሳይጣራ አዋሳኙን ብቻ መሰረት በማድረግ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ እና ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ፣ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ. ቁ. 00164 ነሐሴ 22/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ የሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. ቁ. 21780 የካቲት 6/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት በዋናው መዝገብ ቁ. 21302 የተሰጠው ውሳኔ አንድ ቀርጥ መሬት አዋሳኙ ተጠቅሶ ለአሁን ተጠሪ አመልካች እንዱለቅለት ተወስኖ እያለ የተፈጸመው መሬት ሁለት ቀርጥ ተኩል የሆነበት ምክንያት ከላይ በፍርደ ክፍል ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ተራ ቁጥር አራት የተጠቀሱትን እና ተያያዥ ነጥቦችን ከስረ ነገሩ ፍርድ ይዘት እና ጉዲዩ ከሚመለከተው አካል ጭምር በማጣራት ውሳኔውን እንዱያስፈጽም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰናል።
የውሳኔው ቅጂ በዚህ ውሳኔ መሰረት እንዱከወን ለሜታ ሮቢ ወረዲ ፍ/ቤት እንዱያውቁት ደግሞ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እና ለምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ይላክ።
በዚህ መዝገብ ወጪና ኪሳራ ተቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.