አሰሪ የተጠየቀን የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ አጠቃላይ ተቃውሞ አቀርቦበት እያለ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ሰላቱን በተመለከተ አልተቃወመም በሚል በመተርጎም በሰራተኛው የተጠየቀን የስንብት ክፍያ ዲኝነት ሙለ በሙለ በመወሰን የሚሰጥ ዲኝነት ተገቢ ስላለመሆኑ ፤ፍ/ቤቱ በሕጉ አግባብ አስልቶ መጠኑን ሉወሰን የሚገባ ሰለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 40 (1 እና 2) 119694 ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና አቶ አለማየሁ ሁለቃ 27/11/ 2008ዓ.ም 22 7. ለጡረታ አፈፃፀም ተብል የመንግሰት ሰራተኛን የግል ማህደር በኤጀንሲው እንዱላክ ተጠይቆ፤ሰራተኛው ኢትዩጵያ እህል ንግድ ድርጅት 23/1/ 2009 ዓ.ም 28 III ንብረት አልመለሰም በማለት ማህደር አልክም ማለት ህጋዊ ሰላለመሆኑ ፤ የጡረታ አበል የማግኘት መብት የዕዲ መያዣ ላደረግ ወይም በውርስ ወይም በማናቸውም መንገድ ሉተላለፍ የማይችል ሰለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 345 /97 አንቀፅ 47 (2) ፣ 44 እና 55 (2) እና አቶ ካሳሁን በዛብህ 8. አሰሪ ሰራተኞችን ከማሰናበቱ በፉት በትክክል አጣርቶ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ፤ክርክር ከተጀመረ በኃላ ከስንብት ደብዲቤ ላላ ደብዲቤ መፃፈ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ዓላማ እና መንፈስ የማያሟላ ሰለመሆኑ ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 (1) (3) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 (1) (ሸ) ( ቀ) 125778 ሲው ኢንፍራስትራክቸር እና እነ አቶ መሳይ ወ/ገብርኤል ( አራት ሰዎች) 23/1/ 2009 ዓ.ም 32 9. አንድን ሰራተኛ የሥራ መሪ ነው ልባልበት ስለሚቻልበት አግባብ፡የሥራ መሪን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ ተግባራዊ ሉሆኑ ስለሚገባቸው ህጎች፡የስራ መሪ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ቀሪ ስለሚደረጉበት የይርጋ ፍራውን ኮ/ህንፃ ተቋራጭ እና እነ አቶ ካህሳይ ገ/እግዚአብሄር (ሁለት ሰዎች) 21/2 /2009 ዓ.ም 37 IV አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2(!)፣ 3(2(ሐ) የፍ/ሕ/ቁ.1677(1)፣1845፣2512፣2593 10. ተዋዋይ ወገኖች በስራ ውል ስምምነታቸው በግልፅ ኮሚሽንን የደሞዝ አካል አድርገው እስከተዋዋለ ድረስ ቅራኔ በተነሳ ሰዓት ኮሚሽንን እንደ ደመወዝ አይደለም በማለት መውሰድ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/1996 አንቀፅ 53(2(መ) 117070 ወ/ሮ ወይንሸት በቀለ እና ኦልምፒያኮስ ሄኔኒክ አትላቲክስ ማህበር (ግሪክ ክለብ) 22/2/ 2009 ዓ.ም 46 የፍትሐ ብሓር ሥነ- ሥርዓት 49 11. ቼክን በተመለከተ በአጭር ስነ ስርዓት /Summary proceding/ ዲኝነት ታይቶ እንዱወሰን ክስ በቀረበበት ወቅት ተከሳሽ መከላከያውን እንዱያቀርብ ጥያቄ አቅርቦ ተፈቅድለት መልስ እንዱያቀርብ ተደርጎ መልስና በሕግ አግባብ ምስክር ቆጥሮ እያለ ምስክሮች ሳይሰሙ ይኼው ታልፍ የቼክ ባሕርይን ብቻ መሰረት ተደርጎ ዲኝነት የሚሰጥበት አግባብ ትክክል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 285/1/ 286 እና 291 የን/ሕ/ቁ. አንቀጽ 717 V ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በተለይ በእያንዲንደ ጉዲይ እንዱታይ የሚጠይቀውን ዲኝነት መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224(2) እና አቶ ሐረጳ ቤኛ
No summary available.
ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ኤልያስ ተፈራ - ጠበቃ ዲንኤል ፀጋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አንዋር ሁሴን - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ የሰበር ጉዲይ የተጀመረው በተጠሪ ከሣሽነት አመልካች ለተጠሪ ፈርመው የሰጡትን ቼክ ተጠሪ ቼኩን እንዱከፍላቸው ባንክ ሲያቀርቡ ቼኩ ሳይከፈል በመመለሱ ምክንያት ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ከነ ሕጋዊ ወለደ እና ላልች ተያያዥ ወጪዎች ጋር በአመልካች እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ተጠሪ በተፊጠነ ስነ ስርዓት በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
አመልካች በመቃወሚያነት በቼኩ የተመለከተው ገንዘብ ለተጠሪ የተሰጠው ከተጠሪ ጋር በነበራቸው የኪራይ ውል ግንኙነት የተነሳ በሕገ ወጥ መንገድ ተጠሪ ጫና ፈጥረው ቼኩን የወሰደ በመሆኑ ቼኩ እንዲይከፈል አመልካች ያሳገደ መሆኑን ገልፀውና ይህንኑ ግንኙነት ለማስረዲት እንደሚችለ ገልጸው በን/ሕ/ቁጥር 717 መሰረት ለመቃወም የሚያስችል የመከላከያ ማስረጃ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው የቀረበውን ክስ ለመከላከል እንዱፈቀድላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የአመልካችን የማስፈቀጃ ጥያቄ መርምሮ አመልካች የሚያቀርቡትን የመከላከያ ማስረጃ መስማት አስፈላጊ ሆኖ ማግኙቱን ገልጾ የአመልካችን የመከላከያ መልስ እንዱቀርብ የፈቀደ ሲሆን በዚህም መሰረት አመልካች መከላከያ መልሳቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል። በመልሳቸውም የተጠሪ እናት የሆኑት ወ/ሮ ከድጃ ሰዑድ ከመንግስት የተከራዩትን ቤት ለአመልካች ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ አከራይተው አመልካች የንግድ ስራ ሲሰሩበት የቆየ መሆኑን፣ በኋላም በመንግስት መመሪያ መሰረት ነጋዳዎች የንግድ ፈቃዲቸውን ለማሳደስ ዲግም ምዝገባ እንዱያደርጉ በሚደረግበት ጊዜ የሚሰሩበት የንግድ ቤት ከላላ ሰው የተከራዩት ከሆነና አከራዩ በበኩለ ቤቱን ከመንግስት የተከራየው እንደሆነ ከመንግስት ጋር ያደረገውን የኪራይ ውል እንዱያቀርቡ በተጠየቁት መሰረት ተጠሪ ከመንግስት ጋር ያደረገውን የኪራይ ውል እንዱያቀርቡ በተጠየቁት መስረት አመልካች ተጠሪን ከመንግስት ጋር ያደረጉትን የኪራይ ውል እንዱሰጡና ዲግም ምዝገባውን እንዱያካሂደ በሚጠይቅበት ወቅት ተጠሪ የእናታቸው ወኪል ሆነው ቤቱን ለአመልካች አከራይተው የነበሩ በመሆኑ ተጠሪ በማያውቁት መንገድ አመልካች ቤቱን በስማቸው ለማዛወር የሚያደርጉት ጥረት ነው በሚል ምክንያት የኪራይ ውለን አመልካች እንዱሰጣቸው ከፈለጉ አመልካች ቼክ ፈርመው ለተጠሪ እንዱሰጡ፣ያለዚያ የኪራይ ውለን እንደማይሰጧቸውና ቤቱንም ታስረክባለህ ወይም ለቀህ ትወጣለህ በማለታቸው ምክንያት አመልካች ቼኩን ፈርመው ለተጠሪ የሰጡ መሆኑን በመዘርዘር ተጠሪ በሕገ ወጥ መልኩ የራሳቸው ባልሆነ የመንግስት ቤት የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ላላ ከቤት ኪራይ ውል ውጪ ምንም ግንኙነት ከአመልካች ጋር ሳይኖራቸው አጋጣሚውን በመጠቀምና ጫና በማሳደር በአመልካች የተፈረመ ቼክ ነው በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆንላቸው ተከራክረዋል። ይህንኑ ለማስረዲትም አለኝ ያሎቸውን የሰው ምስክሮች ቆጥረዋል። የስር ፍርድ ቤትም በአመልካች የተቆጠሩት የሰው ምስክሮች ለጉዲዩ አግባብነት የላቸውም በሚል ምክንያት አልፍ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካችን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ ብር 500,000.00( አምስት መቶ ሺህ ብር) ቼኩ ለክፍያ ከቀረበበት ከመጋቢት 18 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ከመቶ ሕጋዊ ወለድ(9%)፣ ከመቶ 1/3ኛ እንዱከፍለና ተጠሪ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር ማቅረብ መብታቸውን በመጠበቅ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተስርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ነው። የአመልከች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን የመከላከያ ማስፈቀጃ ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ ሕጋዊ ባልሆኑ ምክንያቶችና የን/ሕ/ቁጥር 717 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ አስገዲጅነት ካላው የሰበሩ ውሳኔ ጋር ባግባቡ ሳያገናዝብ በአመልካች የተቆጠሩትን የሰው ምስክሮችን ሳይሰማ ምንም ግንኙነት ሳይኖር ለተጠሪ አከራካሪው ገንዘብ እንዱከፈል በማለት የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ ባለመሆኑ ተሸሮ የአመልካች ማስረጃዎች ተሰምተው በጉዲዩ ላይ ተገቢው ዲኝነት እንዱሰጥ የሥር ፍርድ ቤት ይታዘዝ ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የበታች ፍርድ ቤቶች ለን/ሕ/ቁጥር 717 አፈጻጸም የሰጡትን ትርጓሜ አግባብነት ለማየት ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ለዚህ ችልት ያስቀርባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ አንፃርና በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 284 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በአጭር ሁኔታ በሚወሰኑ ክርክሮች ላይ ስለሚፈፀም ሥነ ሥርዓት በሕጉ የተመለከቱ ሥርዓቶችን መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው መርምሮታል።
በመሰረቱ በአጭር ሥነ ሥርዓት ዲኝነት ታይቶ እንዱወሰን ክስ የሚቀርብበት ጊዜ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 285/1/ እንደተመለከተው ከሕጉ ጋር በተያያዘው ሰንጠረዥ ቁጥር 2 መሰረት ተከሣሽ የሆነው ሰው መጥሪያ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በአሥር ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ክሱን ለመከላከል እንዱፈቀድለት ፍ/ቤቱን ፈቃድ እንዱጠይቅ መደረግ እንዲለበት ተደንግጓል። አመልካች ቼኩ ለተጠሪ የተሰጠበት ምክንያት በኪራይ ውል ግንኙነት መሆኑንና ይኼው የኪራይ ውል በመንግስት በወጣው መመሪያ የተነሳ በአመልካችና በተጠሪ ያለመግባባት ፈጥሮ በዚሁ ምክንያት ቼኩን ባልተገባ መንገድና ሁኔታ ለተጠሪ ፈርመው የሰጡ መሆኑን በመጥቀስ ለመከላከል እንዱፈቀድላቸው በቃለ መሐላ የጠየቁ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ ተችሎል። ይህንኑ የአመልካችን ምክንያት በመቀበልም የስር ፍርድ ቤት አመልካች የመከላከያ መልስ እንዱያቀርቡ ፈቅድላቸው አመልካች ሙለ የሆነ መከላከያ መልስና አለኝ የሚሎቸውን የሰው ምስክሮችን ቆጥረው የማስረጃ ዝርዝር መግልጫ ያቀረቡ መሆኑን የሰበር አጣሪ ችልት የያዘው የስር ፍርድ ዋና መዝገብ በግልጽ ያሳያል።
የተጠሪ ዋና ክርክር በቼኩ ላይ ሐተታ ወይም ገደብ የለበትም የሚል ነው። አመልካች ደግሞ ለቼኩ መሰጠት መሰረቱ አመልካች ከተጠሪ እናት ጋር ያላቸው የመንግስት ቤት ላይ የተደረገ የኪራይ ውል የሚል ነው። በአመልካችና በተጠሪ እናት መካከል የኪራይ ውል መኖሩ አልተካደም። ከአመልካች ጋር የተጠሪ እናት ያደረጉትን የኪራይ ግንኙነትን የሚያስተዲድሩት ደግሞ ወኪላቸው የሆኑት የአሁኑ ተጠሪ መሆኑን አመልካች ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። እንዱሁም በአመልካች በመከላከያ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ላይም ይህ ግንኙነት መኖሩ ተገልጿል። ይህንኑ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶም የስር ፍርድ ቤት አመልካች መከላከያ መልሳቸውን እንዱያቀርቡ አድርጓል። ምንም እንኳን ቼክ እንደ ገንዘብ ለተለያዩ ሰዎች በቀላለ ሉተላለፍ የሚችል ባሕርይ ያለው የገንዘብ ሰነድ በመሆኑ ቼክ አከፊፈል ላይ ማንኛውም መቃወሚያ ላቀርብበት እንደማይችል በንግድ ሕጉ የተደነገገ በመሆኑ ሕጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ጉዲዮች ካልሆነ በስተቀር የቼክ ክፍያ በማናቸውም ምክንያት ሉቆምና ሉታገድ የማይችል መሆኑ አከራካሪ ያለመሆኑን የን/ሕ/ቁጥር 717 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በምንመለከትበት የምንረዲው ጉዲይ ነው። ነገር ግን በባለጉዲዮቹ መካከል ግልጽ የሆኑ ሁኔታዎች ወይም ግንኙነቶች በተፈጠሩ ጊዜ ብቻ ይህን መቃወሚያ ለማድረግ እንደሚቻል በን/ሕ/ቁ. 717/1/ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ይህን መሰረት በማድረግ ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ የተቀበለው ሲሆን በኋላ ግን በአመልካች የተቆጠሩትን የሰው ምስክሮች ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው ናቸው በማለት ሳይሰማ አልፍ የቼክ ክርክር በመሆኑ ብቻ የቼክን ባህርይ መሰረት በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል።፡ ሆኖም በዚህ የፈቃድ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ አመልካች መከላከያ መልስ እንዱያቀርብ ተደርጎ መልስና በሕግ አግባብ ምስክር ቆጥረው እያለ ምስክሮች ሳይሰሙ ይኼው ታልፍ የቼክ ባሕርይ ብቻ መሰረት ተደርጎ ዲኝነት የሚሰጥበት አግባብ የላለ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 286፣ 291 እና 717 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ በአንድ ላይ በማንበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። አመልካች ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበው ምክንያት ፈቃድ የሚያሰጥ መሆኑ እስከታመነ ድረስ የቼክ ባህርይ መሰረት ተደርጎ ምስክሮችን የማሰማት መብታቸው ሉታለፍ የሚችልበት ምክንያት መኖሩን ከክርክሩ ሂደት ማግኘት አልተቻለም።
ከፈቃድ በኋላ ያለው የፍሬ ነገር ክርክር ማስረጃ ተሰምቶ ሉነጥር የሚገባውና ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን የማስረጃ ምዘና መርህ በመከተል የሚታይ ይሆናል እንጂ የተከሳሽን የመከላከል መብት ወደ ኃላ በመመለስ መብቱን ለማጥበብ የሚያስችል አይሆንም። ከዚህ አኳያ አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበረውን የኪራይ ውል ግንኙነት መሰረት በማድረግ ለመከላከል እንዱፈቀድ ፍ/ቤቱን ጠይቆ ተቀባይነት ያገኘው ጉዲይ ማስረጃ ሳይሰማ ውድቅ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ስለሆነም በጉዲዩ የስር ፍ/ቤቱ በአጭር ሥነ ሥርዓት እንዱታይ የሚቀርቡ ክሶች አመራር ሥርዓትን ሳይሆን የቼክ ባሕርይን መሰረት በማድረግ ውሣኔ መደምደሚያ ላይ መድረሱ አግባብ ሆኖ አላገኘንም። ምክንያቱም አመልካች ለመከላከል እንዱፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በፍ/ቤቱ አግኝቶ የተጠየቀውን ገንዘብ ላለመክፈል በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑ የሚታወቀው ፍ/ቤቱ ከአጭር ሥነ ሥርዓት ወደ መደበኛ የክርክር ሥነ ሥርዓት ውስጥ በመግባት ግራ ቀኙን በአግባቡ በማስረጃ ካከራከረ በኋላ ነው። በእነዚህ ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 09 2006 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን በመ/ ቀጥል ግራ ቀኙን በመደበኛ የክርክር ሥርዓት አከራክሮና ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውንውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343(1) መሰረት መልሰናል።ይጻፍ።
መዝገቡን ዘግተናል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.