የዝውውር ውሳኔን ተከትል ሰራተኛው ለአምስት የሰራ ቀናት የሰራ ቦታ ላይ አልተገኘም በማለት የማሰናበት እርምጃ ተገቢነት ለማጣራት ፤ ከነባራዊ ሁኔታ እንዱሁም ሰራተኛው የሰራ ቦታ ላይ መገኘት ከሚችልበት ሁኔታ አንፃር እንዱሁም ከቀረበው ማስረጃ አንፃር በመመዘን የሚወሰን ስለመሆኑ አዱስ ፊና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ሆቴልች ንግድ አ.ማ እና አቶ ሉቁ ብርሃነ
No summary available.
ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሰሁን አመልካች፡- ወ/ሮ ወይንሸት በቀለ ከጠበቃ ወይንሽት ከበደ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ኦልምፒያኮስ ሄላኒክ አትላቲክስ ማህበር /ግሪክ ክለብ / የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። አመልካች ባቀረቡት ክስ፤በተጠሪ ድርጅት ከጥር 16/1990 ዓ.ም ጀምሮ እየሰሩ እንደሚገኙ ይሰሩት ከነበረው ተጨማሪ ስራ ደርበው እንዱሰሩ በተደረገ ጊዜ የደመወዝ ማሻሻያ እንዱደረግላቸው ጠይቀው በዚሁ መሰረት ከነሐሴ 1 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዛቸው ተሻሽል ያገኙት ከነበረው በተጨማሪ በየወሩ ከሚገኘው አጠቃላይ የመጠጥና የምግብ ሽያጭ ገቢ ላይ 3% /ሶስት በመቶ/ የደመወዝ አካል ሆኖ እንዱከፈል ወስኗል። በዚሁ ውሳኔ መሰረት ከነሐሴ 11 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 2006 ዓ.ም ለ11 ዓመታት እየተከፈላቸው ሲሆን ምክንያቱ ባልተወቀ ከ3% /ሶስት በመቶ/ ቀንሶ 1% /አንድ በመቶ/ ብቻ እንዱከፈል በውሳኔ ያሳወቃቸው ስለሆነ ከነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ህዲር 2007 ዓ.ም በጠቅላላ 95,445.95 /ዘጠና አምስት ሺ አራት መቶ አርባ አምስት ከዘጠና አምስት ሳንቲም እንዱሁም ከታህሳስ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዛቸውን 2% ኮሚሽን ክፍያውን አካቶ እንዱከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በከተከሳሽነት ቀርበው አመልካች የመጠጥና ምግብ ሰራተኞችን የሚቆጣጠሩ ኃላፉ ስለሆኑ የስራ መሪ ናቸው ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት መቃወሚያ አቅርበዋል። በፍሬ ነገር ላይም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 53 መሰረት ኮሚሽን ደመወዝ አይደለም ስለሆነም ተጠሪ ከመጠጥና ከምግብ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ 3% /ሶስት በመቶ/ በፍቃደኝነት ቢወስንም እንደ አስፈላጊነቱ ደግሞ 1% /አንድ በመቶ/ እንዱከፈላቸው መወሰኑ እንደ ጥፊት ተቆጥሮ ኮሚሽን እንደ ደመወዝ ይቆጠርልኝ በማለት የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት መልሳቸውን አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም መቃወሚያውን በብይን ወድቅ በማድረግ አመልካች የኮሚሽን ክፍያን እንደ ደመወዝ በመቁጠር ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር እንዱቀርብ ተደርጎ ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል። የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ከደመወዛቸው በተጨማሪ 3% /ሶስት በመቶ/ ከጠቅላላው የምግብና የመጠጥ ሽያጭ እንደሚከፈላቸው በውላቸው የተቀመጠውን ተጠሪው ይህንን ገንዘብ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ምላሽ ማግኘት ያለበት ነጥብ ሆኖ አግኝቶታል።
ከተጠሪው ነሐሴ 11 ቀን 1995 ዓ.ም ለአመልካች የተፃፈ ደብዲቤ ይዘት መመልከቱ ተገቢ ነው።
ስለ ደመወዝ ማሻሻያ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ስለ ስራዎት ሁኔታ የክለቡ ኮሚቴ አባላት ተወያይተን ውሳኔ ሰጥተናል። ታታሪ ሰራተኛ መሆንዎ እና በሙለ ፍላጎት ስራዎትን የሚያከብሩ መሆኑን በመገንዘብ ከመስከረም 1995 ጀምሮ የክለቡ ተቆጣጣሪ እና ዋና ገንዘብ ያዥ መሆኖትን እና እንዱሁም ከአጠቃላይ የምግብና የመጠጥ ሽያጭ ላይ ኮሚሽን የደመወዝዎ አካል ሆኖ እንዱከፈልት ወስነናል የሚል ነው። አመልካች የጠየቁት የደመወዝ ጭማሪ ነው። ተጠሪም ጥያቄቸው መሰረት በማድረግ ከምግብና የመጠጥ ሽያጭ 3% /ሶስት በመቶ/ ከሚሽን የደመወዝ አካል እንደሆነ በሚገልፅ ነው የፃፈላቸው። አመልካችም ያቀረቡት የደመወዝ ጭማሪ ምላሽ በማገነኘቱ ተስማምተው ለ11 አመታት በዚሁ ስምምነት እየተከፈላቸው እንደነበረና መጠኑም በግራ ቀኙ ያልተካደ ፍሬ ጉዲዮች ናቸው።
ከጅምሩ የአመልካች ጥያቄ የደመወዝ ጭማሪ እንጂ ኮሚሽን እንዱከፈላቸው ያልነበረ መሆኑን የደብዲቤው ይዘትና መንፈስ ያሳያል። ከምግብና መጠጥ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ 3% /ሶስት በመቶ/ የደመወዛቸው አካል መሆኑ በግልፅ ተመልክቷል። ተጠሪ ኮሚሽን ስለሆነ በፍቃድኝነት ያደረኩትን በፈለጉሁት ጊዜ ሁኔታዎች እየታየ የሚሰጥ እንጂ እንደ ደመወዝ በመቁጠር ሉጠየቅ አይገባም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም። ምክንያቱ ለአመልካች የተደረገው ጭማሪ በተጠሪ ተነሳሽነት ሳይሆን አመልካች ባቀረቡት የደመወዝ ማሻሻያ ጥያቄ መሆኑ ከላይ በተገለፀው መሰረት የተረጋገጠ ነው። በግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ተስማምተውበት ለ11 ዓመታት የደመወዝ አካል አድርገው ተግባራዊ ያደረጉትን ኮሚሽን ነው የደመወዝ አካል አይደለም በማለት በተጠሪ የሚቀርበው ክርክር ተቀበይነት የለውም።
በአጠቃላይ ተጠሪ በግልፅ የደመወዝ አካል አድርጎ ለአመልካች ከምግብና ከመጠጥ ሽያጭ ገቢ 3% /ሶስት በመቶ/ እየከፈላቸው የነበረው ኮሚሽን ስለሆነ ወደ 1% /አንድ በመቶ/ መቀነሱ ከስምምነታቸው ውጪ ሆኖ እያለ፤የስር ፍርድ ቤቶች የሚከፈለው መደበኛ ደመወዝ አለ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 53/2/መ/ ኮሚሽን እንደ ደመወዝ አይቆጠርም፤ደመወዝ የሚያስብል መደምደሚያ ላይ አያደርስም ሲል መወሰኑ በበቂ የህግ ምክንያት ያልተደገፈ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 17578 ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 156579 ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ከተጠሪ ድርጅት ከምግብና ከመጠጥ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ 3% /ሶስት በመቶ/ ኮሚሽን በስምምነታቸው መሰረት የአመልካች ደመወዝ አካል በመሆኑ ተጠሪ ብቻውን ሉቀንስ አይገባም። ስለሆነም ተጠሪ ከነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም ብር 23,907.19፤ ከመስከረም 2007 ዓ.ም 25,762.38፤ከጥቅምት 2007 ዓ.ም ብር 25,612.60፤ከህዲር 2007 ዓ.ም ብር 20,165.73 በጠቅላላ 95,445.95 /ዘጠን አራት ሺ አራት መቶ አርባ አምስት ከ0.95/100 /እንዱከፈላቸው እንዱሁም ከታህሳስ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ወደፉት የተቀነሰውን 2% /ሁለት በመቶ/ ኮሚሽን ክፍያውን ከደመወዛቸው አካቶ ለአመልካች እንዱከፍል ወስነናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.