No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ክፍለጽዮን ማሞ ሰናይት አድነዉ አመልካች...........ሲዉ ኢንፍራስትራክቸር ተጠሪዎች........... 1. አቶ መሳይ ወ/ገብርኤል 2. አቶ አለላ አበጋዘእ 3. አቶ በፍርድ ጥላሁን 4. አቶ ዘሪሁን ከድር መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መነሻ ያደረገ የሥራ ስንብትን የሚመለከት ክርክር ነዉ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡--በሥር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች የሥር ከሳሾች፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የሥር ከሳሾች በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከሳሾች በተከሳሽ ድርጅት በዲም ትራክ ኦፕሬተር ተቀጥረን ሥራችንን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እያለ እኛ ደንብ በመጣስ የድርጅቱ ተሽከርካሪ ታንከር ነዲጅ እንዲይሰረቅ የሚያደርገዉን የተሻለ የነዲጅ መያዣ ታንከር መቆጣጠሪያ መሳሪያ /የደህንነት መጠበቂያ/ ላይ ሆን ብለን ያደረሰን ጉዲት ሳይኖር ጉዲት አድርሳችኋል በማለት የሥራ ዉላችንን በሕገ ወጥ መንገድ በማቋረጥ ስላሰናበተን ተከሳሽ ተገቢዉን ክፍያዎች እንዱከፍለን፣ የሥራ ልምድ እንዱሰጠን እንዱወሰንልን በማለት ከሷል። የሥር ተከሳሽ አሻሽል ባቀረበዉ መልስ 1ኛ ከሳሽ በ9/08/2007 ዓ.ም፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ከሳሾች በ10/08/2007 ዓ.ም እያንዲንዲቸዉ ለሥራ በተረከቡት ተሽከርካሪ ላይ የነዲጅ ስርቆትን ለመከላከል በታንከሩ ላይ የተሰራዉን መሳሪያ ላይ ጉዲት ማድረሳቸዉ በድርጅቱ የቴክኒክ ክፍል ተጣርቶ የተረጋገጠ ሲሆን ከሳሾች ጉዲቱ የደረሰዉ በልላ ሰዉ መሆኑን ባለማረጋገጣቸዉ፣ በድርጅቱ ንብረት ላይ ጉዲት በማድረሳቸዉ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/ /ሸ፣ ቀ/ እና በድርጅቱ ዉስጠ ደንብ መሰረት ከሥራ የተሰናበቱ በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ ከሳሾች የጠየቁትን ክፍያዎች ለመክፈል ኃላፉነት የለብንም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ የሰነድ ማስረጃም በመመዘን፣ በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ የከሳሾችን የሥራ ዉል ያቋረጠዉ ከሕግ ዉጭ በመሆኑ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ በማለት ለከሳሾች በሕጉ አግባብ ክፍያዎችን እንዱከፍላቸዉ ወስኗል።
የሥር ተከሳሽ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የሰበር አቤቱታ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ቅሬታዉ ተቀባይነት ሳይገኝ ዉድቅ ተደርጎ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔን በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ24/07/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ አቅርቧል። የአቤቱታዉም ይዘት፡-- የሥር ፍ/ቤት አመልካች መልሱን እንዱያሻሽል በፈቀደለት መሰረት በ22/12/2007 ዓ.ም የተጻፈዉን መልስ ያቀረበ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ግን መልሱን ከመሻሻለ በፉት የተያያዘዉን የሰነድ ማስረጃ ከተሻሻለዉ የመከላከያ መልስ ማስረጃ ጋር እያነጻጸረ የሰነድ ማስረጃዎቹ እምነት የማይጣልባቸዉ ናቸዉ በማለት የአመልካችን ክርክር ዉድቅ ማድረጉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 /1/ ያላገናዘብ ዉሳኔ ነዉ። የአሁን ተጠሪዎች በመመሳጠር ለነዲጅ ስርቆት እንዱያመቻቸዉ የድርጅቱን አራት መኪኖች የነዲጅ ታንከር በተከታታይ ቀናት በ9/8/2007 ዓ.ም እና በ10/8/2007 ዓ.ም ሰብረዉት እና ቀደዉት ጉዲት ማድረሳቸዉን በሰነድ ማስረጃ እና በሰዉ ምስክሮች አረጋግጠዉ እያለ የሥር ፍ/ቤት እነዚህን የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ አስፈላጊም ከሆነ ገለልተኛ ባለሙያዎችን በተጨማሪ ማስረጃነት አስቀርቦ ምርመራ ማድረግ እየቻለ ማስረጃዉን በማለፍ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ መብት ማለፊቸዉ በመሆኑ እንዱሻርልን። ስለዚህ የአሁን አመልካች ተጠሪዎች በድርጅቱ መኪኖች የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት እና ጥፊት በማድረሳቸዉ ስንብቱ ሕጋዊ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/ /ሸ፣ ቀ/ መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልን፣ ክፍያንም በተመለከተ ቅሬታዉን በማቅረብ አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ይህን ጉዲይ በማየት ፣ተጠሪዎች ጥፊት ለመፈጻማቸዉ አልተረጋገጠም ተብል በሥር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ በሚል የመወሰኑን አግባብነት ከሰበር መ.ቁ.112733 አንጻር፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት የአሁን ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ በታዘዘዉ መሰረት ግንቦት 12 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት፡--የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች መኪኖች የነዲጅ መያዣ ክፍል ላይ ጉዲት ያላደረስን ሲሆን የአሁን አመልካች ያለጥፊታችን የሥራ ዉላችንን ማቋረጡ ያለአግባብ በመሆኑ የቀረበዉ ቅሬታዉ ዉድቅ እንዱደረግልን እና የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካችም የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን፣ ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። ጉዲዩን እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች የተጠሪዎችን የሥራ ዉል በማቋረጥ ከሥራ ያሰናበታቸዉ ተጠሪዎች ከድርጅቱ መኪኖች ታንከር ላይ ነዲጅ እንዲይሰረቅ የሚከላከለዉን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ላይ ጉዲት በማድረሳቸዉ በአመልካች ንብረት ላይ ሆን ብለዉ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ባደረሱት ጉዲት ምክንያት እንደሆነ ከሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ መገንዘብ ይቻላል። የአሁን ተጠሪዎች የተለያዩ ምክንያቶችን በመዘርዘር በመኪኖቹ የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት አለማድረሳቸዉን እና ስንብቱ ሕገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበዉን መልስ ለማሻሻል ጥያቄ አቅርበዉ ሲፈቀድለት፣ በተሻሻለዉ መልስ የአሁን ተጠሪዎች በመኪኖቹ የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት አደረሱ በማለት መጀመሪያ ባቀረበዉ ክስ ላይ የጠቀሰዉን ቀን እና መጀመሪያ የተጻፈዉን የስራ የስንብት ደብዲቤ በመቀየር ላላ የስራ የስንብት ደብዲቤ አያይዞ ያቀረበ መሆኑን በሥር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነዉ።
በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 /1፣ 3/ እንደሚደነግገዉ የክሱ ወይም የመከላከያ መልሱ ማሻሻል አስቀድመዉ የቀረበዉን ሁኔታ የሚያብራራ ወይም የቀረበዉን ክርክር በተሻሻለ ዓይነት ገልጾ የሚያስረዲ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት የሚረዲ መሆኑን ፍ/ቤቱ ከገመተ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት የቀረበዉን ክስ ወይም መልስ እንዱሻሻል እንደሚፈቅድ ያመለክታል። በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች መልስ ለማሻሻል አቤቱታ አቅርቦ የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሱን አሻሽል እንዱያቀርብ የፈቀደለት ሲሆን፣ አመልካችም በ22/12/2007 ዓ.ም የተጻፈ የተሻሻለ መልስ ያቀረበ መሆኑን ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ መገንዘብ ይቻላል። ነገር ግን የአሁን አመልካች ባቀረበዉ መልስ አስቀድመዉ የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች መኪኖች የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት አድርሰዋል በማለት ተጠሪዎችን ከሥራ ያሰናበተባቸዉን የስንበት ደብደቤ ሙለ በሙለ በመቀየር ላላ የስንብት ደብዲቤ /ላላ አዱስ ማስረጃ ፈጥሮ/ እንዲቀረበ ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ መረዲት ተችሎል። በዚህ መሰረት የአሁን አመልካች አስቀድመዉ ለተጠሪዎች የሰጣቸዉን የስንብት ደብዲቤ በመቀየር፣ ተጠሪዎች በመኪኖቹ የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት አድርሷል ያለዉን ቀን በመቀየር ያቀረበ መሆኑን ያመለክታል። የአሁን ተጠሪዎች ክሳቸዉን ሲመሰርቱ የአሁን አመልካች የጻፈላቸዉን የስንብት ደብዲቤ እና በስንብት ደብዲቤዉ ላይ በድርጅቱ ንብረት ላይ ጉዲት አድርሳችኋል የተባለዉን ቀን እና ሁኔታ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነዉ። የአሁን አመልካች አሻሽል ባቀረበዉ መልስ ይህን ሁለ ቀይሮ መልሱን አሻሽል አቀረበ ማለት ተጠሪዎችን ከሥራ ከማሰናበቱ በፉት በትክክል አጣርቶ እርምጃ መዉሰድ ሲገባዉ አሁን ክርክር ከተጀመረ በኋላ አስቀድመዉ ተጠሪዎችን ካሰናበታቸዉ ደብዲቤ ላላ ደብዲቤ መጻፈ ከላይ የተመለከተዉን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.91 /1፣ 3/ አላማ እና መንፈስ የሚያሟላ ሁኖ አይታይም። አመልካች ራሱ በጻፈዉ የስንብት ደብዲቤ መሰረት በማድረግ የአመልካችን እርምጃ በመቃወም ተጠሪዎች ክስ ከመሰረቱ በኋላ አመልካች ላላ የስንብት ደብዲቤ በማዘጋጀት መልሱን አሻሽል ማቅረቡ በቀድሞ መልስ የቀረበዉን ሁኔታ የሚያብራራ ወይም የቀረበዉን ክርክር በተሻሻለ ዓይነት ገልጾ የሚያስረዲ ወይም ትክክለኛ ፍትሕን ለመስጠት የሚረዲ ሳይሆን አዱስ ክርክር እንደማቅረብ የሚገመት ነዉ። እንዱያዉም ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክርክር ተገቢ መከላከያ መልስ ማቅረብ ሳይሆን ላላ የማይገናኝ አዱስ ክርክር እንደማቅረብ የሚቆጠር ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም።
ይህ በእንዱህ እንዲለ የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር ይህን ጉዲይ ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። የሥር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች መኪኖች የነዲጅ ታንከር ላይ ጉዲት ማድረስ ወይም አለማድረሳቸዉ በተመለከተ የግራ ቀኙን የሰዉ ምስክሮችን በመስማት የሰነድ ማስረጃ በመመዘን ዉሳኔ የሰጠ መሆኑን ማየት ይቻላል። በዚህ መሰረት የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ተጠሪዎች በድርጅቱ መኪኖች የነዲጅ ታንክር ላይ ጉዲት አድርሷል በማለት ከሥራ ያሰናብታቸዉ እንጂ የቀረበዉ የሰነድ ማስረጃ እና የሰዉ ምስክሮች እምነት የሚጣልባቸዉ እንዲልሆኑ በማረጋገጥ፣ የሥራ ስንበቱ ሕገ ወጥ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ ማስረጃን በመመዘን ዉሳኔ መስጠቱን ችልቱ ተገንዝቧል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ተጠሪዎችን በሕጉ አግባብ በጥፊታቸዉ የሥራ ዉላቸዉን በማቋረጥ ያሰናበታቸዉ እና ስንብቱ ህጋዊ መሆኑን የማስረዲት ሸክሙን ያልተወጣ መሆኑን ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ማየት ይቻላል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር መሰረት ተጠሪዎች በድርጅቱ መኪኖች የነዲጅ ታንከር መቆጣጠሪያ መሳሪያ ላይ ጉዲት ማድረሳቸዉን ባላረጋገጠበት የተጠሪዎች የሥራ ስንብት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/ /ሸ፣ ቀ/ መሰረት ሕጋዊ ነዉ በማለት ያቀረበዉ ክርክር የድንጋጌዉን መንፈስና ይዘት ያላገናዘበ ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም።
የአሁን የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል ሲባል በተያዘዉ ጭብጥ ጉዲዩን በሰበር መ.ቁ.112733 ላይ ከተሰጠዉ ዉሳኔ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። በሰበር መ.ቁ.112733 ላይ አመልካች ሲዉ ኢንፍራስትራክቸር ሲሆን፣ ተጠሪ አቶ ጴጥሮስ ስዩም በመሆን፣ ችልቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በ4/6/2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን ተጠሪ ከአመልካች መኪና ነዲጅ እንዲይሰረቅ ለመከላከል የሚያገለግለዉን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ላይ ጉዲት ማድረሱ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች የሥራ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነዉ በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ በመሻር የአሁን አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተዉ በሕጋዊ መንገድ ነዉ፣ የሥራ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ በማለት ወስኗል። በሰበር መ.ቁ.112733 እና አሁን በተያዘዉ መዝገብ ላይ ያለዉ ክርክር ሲታይ በዚህ መዝገብ የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች መኪኖች ነዲጅ እንዲይሰረቅ የሚያገለግለዉን መሳሪያ ላይ ጉዲት ማድረሳቸዉ በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ በሰበር መዝገብ ውሳኔ ካገኘው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይ ጭብጥ ነዉ ለማለት ስለማይቻል በዚህ ጉዲይ ላይ አስገዲጅነት ያለዉ የሕግ ትርጉም አይደለም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪዎችን ከድርጅቱ መኪኖች ታንከር ነዲጅ እንዲይሰረቅ ለመቆጣጠር የሚያገለግለዉን መሳሪያ ላይ ጉዲት ማድረሳቸዉ በማስረጃ ባልተረጋገጠበት የሥራ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ በማለት አመልካች ለተጠሪዎች በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ክፍያዎች እንዱከፍላቸዉ የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት ስለማይቻል የሚከተለዉ ተወስኗል።
የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.07323 በ15/04/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.19019 በ13/05/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.66951 በ20/7/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ሚያዝያ 5 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም እግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል።
ይጻፍ።
No topics extracted.