No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል ቀነአ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካቾች፡- የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት -ወኪል ነ/ፈጅ ይግረም ነጋሽ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ካሳሁን በዛብህ -ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይን የሚመለከትና ጡረታ ለመውጣት ከመጠየቅ ጋር የተያያዘ ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የስር ከሳሽ የነበሩት የአሁን ተጠሪ በአማራ ክልል ደቡብ ወል ዞን ደሴ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ፍሬ ነገርም በአጭሩ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ለ31 ዓመታት ሳገለግል ቆይቼ እድሜዬ 55 ሲሞላ ጡረታ ለመውጣት ማህበራዊ ዋስትና ብጠይቅም ማህበራዊ ዋስትና ለአመልካች ድርጅት የግል ማህደሬን እንዱልክ በደብዲቤ ብጠይቅም አመልካች ድርጅት ለመላክ ፍቃደኛ አይደለምና የግል ማህደሬን እንዱልክ ይታዘዝልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው የአሁን አመልካች በበኩለ ተጠሪ በስራ አጋጣሚ በእጁ የገባ የአመልካች ንብረት ሳያስረክብ የግል ማህደሩን ለመላክ አልችልም ስለሆነም የተጠሪ ክስ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ ጉዲዩን በመመርመር ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ንብረት አልተረከብኩም አላለም አስረክቤያለሁ ቢለም ያቀረቡት ማስረጃ ካለመኖሩም በተጨማሪ ያቀረባቸው ምስክሮች ተጠሪ ሉያስረክቡ ሲሄደ ቢሯቸው ክፍት ሆኖ ስላገኙት ተመለሱ ከማለት ውጪ ንብረት ስለማስረከባቸው አላስረደም ብል ተጠሪ የአመልካችን ድርጅት ንብረት ሳያስረክቡ የግል ማህደሬ ለማህበራዊ ዋስትና ይላክልኝ ዘንድ ይታዘዝልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታቸውን ለደቡብ ወል ዞን ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ቅሬታው መ/ሰጪን መልስ እንዱያቀርብ በማድረግ አከራክረዋል ። ቀጥልም ተጠሪ ከአመልካች የተረከበውን ንብረት እንዱያስረክብ የስር ፍ/ቤት መወሰኑ ተገቢ ቢሆንም ንብረት ባለማስረከቡ ብቻ ግን ለጡረታው አፈጻጸም ከማህበራዊ ዋስትና እንዱላክ የታዘዘውን የግል ማህደር አለመላክ የመንግስት ሰራተኛ ጡረታ አዋጅ ቁጥር. 345/95 አንቀጽ 47/2/ን የሚቃረን ነው በማለት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር አመልካች የተጠሪን የግል ማህደር ለማህበራዊ ዋስትና ይላክ በማለት ወሰነ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁኑ አመልካች ለአማራ ክልል፤ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታውን ቢያቀርብም የዞኑ ከ/ፍ/ቤትን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱያርም ጉዲዩ የቀረበለት የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ የሚጣራ መሰረታዊ የህግ ጭብጥ የለውም በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 /1/ን በመጥቀስ ሰርዞታል ።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህን በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም እንዱታረም ሲሆን አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ተጠሪ የአመልካችን ንብረት ሳያስረክብ አመልካች የተጠሪን የግል ማህደር የማስረከብ ግዳታ ከመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ. 345/95 አንጻር ተጠሪ ባለበት ለመመርመር ቅሬታው ተጠሪን ያስቀርባል ብል ግራ ቀኙ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸውን አድርገዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተመለከተውን የሚመስል ሲሆን እኛም በበኩላችን አቤቱታው ለዚህ ሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር ብቻ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
በመሰረቱ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ በስራው አጋጣሚ በእጃቸው የገባውን የአመልካች ማንኛውም ንብረት የማስረከብ ግዳታ አለባቸው ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ተቀጥረው ሲሰሩ በስራ አጋጣሚ የገባ የአመልካች ንብረት እንዲለ የተረጋገጠ ሲሆን ተጠሪ አስረክቤያለሁ ሲለ አመልካች አላስረከቡም ብለዋል።
ዋናው ጉዲይ ንብረት ማስረከብ ያለማስረከብ ጉዲይ ለተጠሪ ጡረታ መውጫ ፍርማሉቲ ከማህበራዊ ዋስትና የተጠየቀን የግል ማህደር አመልካች አልሰጥም ማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው ላታይ የሚገባው ጉዲይ ነው አመልካች በህ/ስምምነታችን አንቀጽ 9/7/ መሰረት ሰራተኛ ያለበትን ንብረት ሳያስረክብ ከማህበራዊ ዋስትና የታዘዘው የተጠሪን የግል ማህደር መላክ ይከለክላል ሲል ተጠሪ በበኩላቸው የህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 9/7/ የሚከለክለው መሸኛና የስራ ልምድ ነው እንጂ በማህበራዊ ዋስትና የተጠየቀን የግል ማህደር አይደለም ብለዋል በመሆኑም ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሰው የህብረት ስምምነት በተዋዋዮች መሀከል ህግ በመሆኑ ለማየት የሚቻል ቢሆንም ባለመቅረቡ አልታየም።የህብረት ስምምነት አመልካች ክርክር የሚደግፍ ቢሆንም የህብረት ስምምነት በህግ ለሰራተኞች የሚሰጠው መብት የበለጠ የሚጠቅሞ ሆኖ ካልተገኘ ተግባራዊ ላሆን እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 134/2/ ተፈጻሚ እንደማይሆን ይደነግጋል።
ላላው ግን የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ. 345/95ን ስንመለከት በአንቀጽ 47/2 ላይ ማንኛውንም አሰሪ /ግለሰብ/ ቀርቦ አስተያየትና መረጃ ወይም የጽሁፍ ማስረጃ እንዱሰጥ በማህበራዊ ዋስትና /በባለስልጣኑ/ ሲታዘዝ የመስጠት ግዳታ አለበት ይልና በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 44 ላይ እንደተመለከተው የጡረታ አበል የማግኘት መብት የዕዲ መያዣ ላደረግ ወይም በውርስ ወይም በማናቸውም መንገድ ሉተላለፍ አይችልም ብል በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 55/2/ ላይም ይህንን አዋጅ የሚቃረኑ ህጎችና ማሟያዎች ይህንን አዋጅ በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም ይላል።
ይህንን ህግ መነሻ ስናደርግ ተጠሪ እንዲቀረቡት ዝርዝር የህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 9/7/ ሰራተኛው ንብረት ባላስረከበ ጊዜ አሰሪ ለመያዝ የሚችለው የስራ ልምድና መሸኛ ካልሆነ በስተቀር በማህበራዊ ዋስትና የሚታዘዘውን ማንኛውንም ለጡረታ መውጫ የሚያስፈልግ ማስረጃ የመስጠት ግዳታ በመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 ላይ የተጣለበት ስለሆነ ይህንን ላለመስጠት መስማማት የማይችልና የጡረታ መብትን የማግኘት መብት በእዲ መያዣ ላደረግ እንደማይገባ ከመደንገጉም በተጨማሪ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 55/2 ላይም ይህንን ድንጋጌ የሚቃረን ህ/ስምምነት ተፈጻሚ እንደማይሆን የደነገገ በመሆኑ ተጠሪ የአመልካችን ንብረት ያልመለሰ ስለሆነ ሳይመልስ የተጠሪን የግል ማህደር ለማህበራዊ ዋስትና ሉልክ አይገባም በማለት የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ዉሳኔ በመሻር የስር ከ/ፍ/ቤት አመልካች የተጠሪን ማህደር ለማህበራዊ ዋስትና እንዱልክ መወሰኑንና የክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይህን ውሳኔ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ጥሰት አለበት የሚያሰኝ ጉድለት ያላገኘን በመሆኑ ውሳኔው የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በደቡብ ወል ዞን ከ/ፍ/ቤት በመ// ታህሳስ 10 2008 ዓ.ም የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ 03-13048 በቀን ሚያዚያ6 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
ይህ ውሳኔ አመልካች በተጠሪ ላይ አለኝ የሚለት ንብረት ካለ ከመጠየቅ አያግዲቸውም
በየደረጃ ለሚገኙ ፍ/ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ ይተላለፍ
በዚህ ፍ/ቤት ተሰጥቶ የነበረው የአፈጻጸም እግድ ተነስቷል ይጻፍ
ግራ ቀኙ የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ
No topics extracted.