No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንዲሻዉ አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች.............ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. -የቀረበ የለም ተጠሪ...................አቶ አለማየሁ ሁለቃ -ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የሥራ ስንብትን የሚመለከት ክስን መነሻ ያደረገ ነዉ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡--በሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች /የሥር ተከሳሽ/፣ የአሁን ተጠሪ /የሥር ከሳሽ/ ሆኖ ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የሥር ከሳሽ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በተከሳሽ ኩባንያ በኢንፍርሜሽን ቴክኖልጂ ሥራ አስኪያጅነት ተቀጥሬ እንዱሁም የኢንፍርሜሽን ሲስተም ፕሮጀክት ማናጀርነት በአጠቃላይ ብር 11,327.00 እየተከፈለኝ እየሰራሁ እያለ ምንም ዓይነት የሥራ ብቃት ማነስ ሳይኖርብኝ እና ከሥራ ገበታዬም የቀረሁበት ቀን ሳይኖር ተከሳሽ መጋቢት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ከሕግ ዉጭ ከሥራ ስላሰናበተኝ ወደ ሥራ እንዱመልሰኝ፣ ይህ ካልሆነ በአጠቃላይ ብር 219,439.56 እንዱከፍለኝ በማለት ከሷል። የሥር ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ከሳሽ ከሥራዉ ሉባረር የቻለዉ በሥራዉ ላይ ባሳየዉ በብቃትና በጥራት ለመስራት ያለመቻል የብቃት ማነስ በመሆኑ ከሥራ የተሰናበተዉ በሕጉ አግባብ ስለሆነ ያቀረበዉ ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም፣ ፍ/ቤቱ የሥራ ዉለ የተቋረጠዉ ከሕግ ዉጭ ነዉ የሚል ከሆነ የተከሳሽ ኃላፉነት የ3 ወር ደመወዝ ብቻ ነዉ፣ ወደ ሥራ መመለስ የለበትም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ የቀረበዉ የሰነድ ማስረጃዎች በማየት በመመዘን በሰጠዉ ዉሳኔ ተከሳሽ ከሳሽን ከሥራዉ ያሰናበተዉ የሥራ ጥራት እና አቅም ማነስ እንዱሁም አለቃን ሳያሳዉቁ በሥራ ገበታ ላይ አለመገኘትን ሲሆን ይህን በማስረጃ ያስረዲዉ ነገር ስለላለ ተከሳሽ ከሳሽን ያለ በቂ ምክንያት ከሥራዉ ያሰናበተዉ በመሆኑ፣ ከሳሽ ወደ ሥራ ሉመለስ አይገባም በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም፣ ተከሳሽ በአጠቃላይ ብር 106,431.89 ዉሳኔዉ ከተሰጠ ቀን ጀምሮ ከ9% ወለድ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍለዉ በማለት ወስኗል። የሥር ተከሳሽ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፣ የሥር ከሳሽም የመስቀለኛ ይግባኝ ያቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ፍ/ቤት የሥራ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ መባለን አግባብ እንደሆነ በማረጋገጥ፣ ክፍያዎችን በተመለከተ የስንብት ክፍያ ብር 35,146.23፣ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ብር 21,400.66፣ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 /4/ /ሀ/ መሰረት ብር 59,862 ብር ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ከ9% ወለድ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍለዉ በማለት በማሻሻል ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ህዲር 3 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ ስድስት ገጽ አቤቱታ የአሁን ተጠሪ የሥራ ብቃትና ችልታ የመመዘን ስልጣን የኩባንያዉ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በዚህ አግባብ የብቃት ማነስ ያለባቸዉ መሆኑ ከተገመገመ በኋላ ለሥራ አመራር ቦርድ ቀርቦም ከተጣራ በኋላ ከሥራ የተሰናበት በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ተጠሪን እንደሰራተኛ በመቁጠር በአዋጅ ቁጥር 377/96 /አዋጅ ቁጥር 494/98 እንደተሻሻለ/ አንቀጽ 39 /1/ /መ/ መሰረት የስንብት ክፍያ እንዱከፈለዉ መወሰናቸዉ የሕግ ስህተት ነዉ። የስንብት ከፍያዉ ይከፈል ቢባል እንኳን ብር 15,796.92 ብቻ ሆኖ ሳለ ብር 35,146.23 ብር እንዱከፈለዉ መወሰኑ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። የአሁን አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተዉ በአግባቡ ሆኖ ሳለ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 /4/ /ሀ/ መሰረት ብር 59,862.00 እንዱከፈለዉ መወሰኑ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። የአሁን ተጠሪ የተሰናበተዉ በችልታ ማነስ ምክንያት በመሆኑ የፕሮቪደንት ፈንድ ብር 21,400 የተወሰነዉ የሕግ መሰረት የለዉም። የሥር ፍ/ቤት የሥራ ዉል የተቋረጠዉ ከሕግ ዉጭ ነዉ የሚል አቋም የሚይዝ ከሆነም የአመልካች ኃላፉነት የሶስት ወር ደመወዝ ብቻ የማያልፍ ሆኖ እያለ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት በማድረግ የወሰኑት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምልኝ በቂ ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ይህን ጉዲይ በማየት ፣ተጠሪ በሥራ መሪነቱ ከ3 ወር በላይ ደመወዝ በላይ ሉከፈለዉ አይገባም በማለት አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘዉ መሰረት ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት፡--የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ተጠሪ ከሕግ ዉጭ ከሥራ ያሳናበተዉ መሆኑን በማረጋገጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 እና በድርጅቱ የሰዉ ሃይል አስተዲደር፣ ግዢና ልጂስቲክ ፖሉሲ እና ፕሮሲጀር ማኑዋል መሰረት ዉሳኔዎችን የሰጡ በመሆኑ ዉሳኔዎቹ እንዱጸኑልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች መልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል በማቋረጥ ከሥራ ያሰናበተዉ ተጠሪዉ በሥራዉ የብቃት ወይም የችልታ ማነስ በማሳየቱ እና ከ19/3/2013--23/3/2013 እ.ኤ.አ. ያለ ፈቃድ ከሥራ ገበታዉ በመቅረቱ በሚል ምክንያት እንደሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች ያመለክታል። የአሁን ተጠሪ በበኩለ ባቀረበዉ ክስ ምንም ዓይነት የሥራ ብቃት ማነስ እንደላለበት እና ከሥራዉም ያለፈቃድ ቀርቶ እንደማያዉቅ በመግለጽ ተከራክሯል። ከዚህ አንጻር የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪን ከሥራዉ ያሰናበተበት ምክንያቶች መኖራቸዉን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ የማስረዲት ሸክም አለበት። በዚህ አግባብ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረባቸዉ የሰዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል የአሁን ተጠሪ በሥሩ ለነበረችዉ አንድ ሰራተኛ በሰጠዉ ዝቅተኛ የሥራ ግምገማ ዉጤት ምክንያት በአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በሰራተኛዉ መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ከመግለጽ ዉጭ ተጠሪ በሥራዉ ላይ የብቃት ማነስ ሁኔታ ያሳየ መሆኑን ያላረጋገጡ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ያመለክታል። በተጠሪ በኩል የቀረቡት የሰዉ ምስክሮች በሰጡት የምስክርነት ቃል ተጠሪ ላለፈት ሁለት አመታት በተደረገ የሥራ ግምገማ ከአጥጋቢ በላይ የሥራ አፈጻጸም እንደነበረዉ፣ በሥራዉ ዕዉቀት እና ችልታ እንዲለዉ ማረጋገጣቸዉ ማስረዲታቸዉ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ያሳያል። በሶስተኛ ዓመት የሥራ ግምገማ ወቅት ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር በተፈጠረዉ አለመግባባት ምክንያት ዋና ሥራ አስኪያጁ ዝቅተኛ የስራ አፈጻጸም ዉጤት የሰጡት መሆኑን መስክሯል። በልላ በኩል የአሁን አመልካች ተጠሪን ከሥራዉ ያሰናበተበት ምክንያት የአሁን ተጠሪ ያለ ፈቃድ ከ19/3/2013-- 23/3/2013 እ.ኤ.አ. ከሥራ ገበታቸዉ ቀርተዋል የሚል ሲሆን አመልካች ይህን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲላቀረበ ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ማየት ይቻላል። የአሁን ተጠሪ ግን ያለ ፈቃድ ከሥራዉ እንዲልቀረ የህክምና ሰርትፍኬት እንዱሁም ለቅርብ አለቃዉ በማሳወቅ ሆስፒታል ሄድ እንዱታከም ከአመልካች ኩባንያ ወደ ሆስፒታል መላኪያ ቅጽ እንደተሰጠዉ ባቀረበዉ ማስረጃ ያረጋገጠ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ያሳያል። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች ፍሬ ነገርን በማስረጃ አጣርቶ ለመወሰን በተሰጣቸዉ ሥልጣን መሰረት ይህን ጉዲይ በማጣራት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመዘን በሰጡት ዉሳኔ የአሁን አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ያቋረጠዉ ያለበቂ ምክንያት ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ እና ከኩባንያዉ ማንዋል ዉጭ መሆኑን በማረጋገጥ የሥራ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ከማለት ዉጭ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት የለም።
በመሆኑም የአሁን አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል በማቋረጥ ከሥራዉ የተሰናበተበት ሁኔታ ከሕግ ዉጭ በመሆኑ ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ የዚህን ዉጤት በሕጉ አግባብ ማየቱ አስፈላጊ ነዉ። ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 /2/ መሰረት መገንዘብ እንደሚቻለዉ ሕገ ወጥ የስራ ስንብት ዉጤት ሰራተኛዉን ወደ ሥራ መመለስ ወይም ተገቢ ክፍያዎች ተከፍልት እንዱሰናበት ማድረግ እንደሆነ ነዉ። በዚህ መሰረት የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ የአሁን ተጠሪ ወደ ሥራ መመለስ የለበትም በማለት የወሰኑትን በተመለከተ የአሁን ተጠሪ በየደረጃዉ ላለት ፍ/ቤቶች ቅሬታዉን በማቅረብ ያስለወጠዉ ነገር ስለላለ ይህን ነጥብ ማየቱ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም መታየት ያለበት የአሁን አመልካች ተጠሪን ከሕግ ዉጭ ከሥራ በማሰናበቱ ለተጠሪዉ ሉከፍለዉ የሚገባዉ ክፍያዎች ምን እንደሆኑ ነዉ። የአሁን ተጠሪ የሥራ መሪ ቢሆንም የአመልካች የሰዉ ሃይል አስተዲደር፣ ግዢና ልጂስቲክ ፖሉሲ እና ፕሮሲጀር ማንዋል በሚደነግገዉ አግባብ ተጠሪዉ የስራ ዉል የተቋረጠ እንደሆነ ከፍትሐብሕር ሕግ ከተደነገገዉ ይልቅ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ተጠቃሚ እንደሚሆን ያስገነዝባል። ስለሆነም ለተጠሪ ሉከፈል የሚገቡት ክፍያዎች መታየት ያለባቸዉ ይህን ማንዋል እና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን ባማከለ መልኩ መሆን እንዲለበት የሚያከራክር አይደለም። የአሁን አመልካች በድርጅቱ ማንዋል መሰረት የሰራተኛዉን መብት ከፍትሐብሕር ሕጉ እና ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በተሻለ ሁኔታ ተጠቃሚ የሚያደርገዉ እስከሆነ ድረስ ተፈጻሚ መሆን ያለበት ይህ ማንዋል እንደሆነ ግልጽ ነዉ። በዚህ አግባብ የአሁን አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተወሰኑትን ክፍያዎች ማየቱ ተገቢ ነዉ።
በዚህ መሰረት መጀመሪያ መታየት ያለበት የስራ ስንብት ክፍያ ሲሆን የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር በኩባንያዉ ማንዋል ክፍል 1-ሀ ተራ ቁጥር 13.4 መሰረት የአሁን ተጠሪ የስንብት ክፍያ ተጠቃሚ እንደሆነ ሳይክድ ፣ ተጠሪዉ ለአምስት አመት በኩባንያዉ ዉስጥ ስላላገለገለ የስንብት ክፍያ አይገባዉም የሚል ነዉ። ነገር ግን የአሁን ተጠሪ ከሥራዉ የተሰናበተዉ በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በአመልካች አነሳሽነት ከሕግ ዉጭ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 /አዋጅ ቁጥር 494/98 እንደተሻሻለ/ አንቀጽ 39 /1/ /ሸ/ ተፈጻሚነት የለዉም።
በመሆኑም የአሁን አመልካች ተጠሪዉን ከሥራ ያሰናበተዉ ከሕግ ዉጭ በመሆኑ የኩባንያዉ ማንዋል በሚያመለክተዉ አግባብ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የስንብት ክፍያ ለተጠሪ ሉከፈል ይገባል። በዚህ መሰረት የሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ለተጠሪ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አግባብ የሥራ ስንብት ክፍያ ሉከፍለዉ ይገባል በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት አይቻልም። ነገር ግን የአሁን አመልካች የሥራ ስንብት ክፍያ ስንት ብር ለተጠሪዉ መከፈል አለበት የሚለዉ ስላቱ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ ብር 35,146.23 የጠየቀ ሲሆን፣ የአሁን አመልካች በበኩለ ባቀረበዉ ክርክር በአጠቃላይ የሥራ ስንብት ክፍያ መክፈል የለብንም የሚል ነዉ። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ተጠሪዉ የጠየቀዉን ገንዘብ በሙለ እንዱከፍለዉ ወስኗል። የአሁን አመልካች ይህን በመቃወም ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበዉ ይግባኝ ለተጠሪ የሥራ ስንብት ከፍያ መክፈል የለብንም ፣ መክፈል ካለብን ደግሞ ተጠሪዉ የጠየቀዉን ገንዘብ በሙለ ሳይሆን ብር 15,796.92 ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ በተመለከተ በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች የሥራ ስንብት ክፍያ መክፈል የለብንም ከማለት ዉጭ ስላቱን በተመለከተ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበዉ ተቃዉሞ ባለመኖሩ በዚህ ፍ/ቤት ደረጃ ማቅረብ አይችልም በማለት ወስኗል። ነገር ግን የአሁን አመልካች ለተጠሪዉ ሉከፍለዉ የሚገባዉ የሥራ ስንብት ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 40 አግባብ መሆን አለበት እንጂ የአሁን ተጠሪ ዲኝነት ስለጠየቀ ብቻ እሱ የጠየቀዉ ገንዘብ በሙለ ሉወሰንለት ይገባል ማለት አይደለም። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ለተጠሪዉ የሥራ ስንብት ክፍያ መክፈል የለብንም በማለት አጠቃላዩን እየተቃወመ በመሆኑ ስላቱን በተመለከተ ያቀረበዉ መቃወሚያ የለም ለማለት አይቻልም። ስለዚህ የአሁን አመልካች ለተጠሪዉ መክፈል ያለበት የሥራ ስንብት ክፍያ በሕጉ አግባብ ተሰልቶ ሉከፈለዉ ይገባል እንጂ ተጠሪ የጠየቀዉ ገንዘብ በመለ ሉወሰንለት የሚገባበት አግባብ የለም። የአሁን ተጠሪ ደመወዝ በወር ብር 9,977 /ዘጠኝ ሺህ ዘጠን መቶ ሰባ ሰባት/ እና ተጠሪዉ በአመልካች ኩባንያ ሁለት አመት ከዘጠኝ ወር ያገለገለ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 40 /1፣ 2/ መሰረት ሲሰላ የአሁን አመልካች ለተጠሪዉ መክፈል ያለበት የሥራ ስንብት ክፍያ ብር 15,796.91 /አስራ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንትም/ ነው። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ገንዘብ መወሰን ሲገባቸዉ ተጠሪዉ የጠየቀዉን ገንዘብ በሙለ አመልካች እንዱከፍል መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል። ስለዚህ የአሁን አመልካች የሥራ ስንብት ክፍያ ብር 15,796.91 /አስራ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንትም/ ለተጠሪ መክፈል አለበት ብለናል።
በልላ በኩል የካሳ ክፍያን በተመለከተ የአመልካች ኩባንያ ማንዋል ክፍል 1-ሀ በተራ ቁጥር 13.4 መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 /4/ /ሀ/ መሰረት የካሳ ክፍያ ሉከፈለዉ እንደሚገባ ስለሚደነግግ፣ የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2574 /2/ መሰረት የሶስት ወር ደመወዝ ብቻ ነዉ መከፈል ያለበት በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም። ስለዚህ በዚህ ረገድ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ ሕግ ድንጋጌ አግባብ የካሳ ክፍያዉን በማስላት የአሁን አመልካች ብር 59,862 /አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሁለት/ ዉሳኔዉ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠዉ ዉሳኔ በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት አይቻልም።
ላላዉ መታየት ያለበት ፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካች ኩባንያ ደንብ ተራ ቁጥር 1.4.3.2 መሰረት በማስላት የአሁን አመልካች ብር 21,400.66 /ሀያ አንድ ሺህ አራት መቶ ብር ከስልሳ ስድስት ሳንቲም/ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት የሰጡት ዉሳኔዎች በሕጉ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት አይቻልም። ስለዚህ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሥራ ስንብት ክፍያ የገንዘብ ስላትን በተመለከተ ብቻ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.147858 በ09/02/2008 ዓ.ም የተሰጠዉ ዉሳኔ የሥራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የአሁን አመልካች የሥራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ ብር 15,796.91 /አስራ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንትም ብቻ ለተጠሪ ሉከፍለዉ ይገባል ብለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላልች ክፍያዎችን በተመለከተ የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ህዲር 23 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠዉ የአፈጻጸም እግድ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
ግራቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.