የዝውውር ውሳኔን ተከትል ሰራተኛው ለአምስት የሰራ ቀናት የሰራ ቦታ ላይ አልተገኘም በማለት የማሰናበት እርምጃ ተገቢነት ለማጣራት ፤ ከነባራዊ ሁኔታ እንዱሁም ሰራተኛው የሰራ ቦታ ላይ መገኘት ከሚችልበት ሁኔታ አንፃር እንዱሁም ከቀረበው ማስረጃ አንፃር በመመዘን የሚወሰን ስለመሆኑ አዱስ ፊና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ሆቴልች ንግድ አ.ማ እና አቶ ሉቁ ብርሃነ
No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- አዱስ ፊና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ሆቴልች ንግድ አ.ማ.
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ተጠሪው በባህርዲር ወረዲ ፍርድ ቤት በ27/11/2007 ዓ.ም. አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ አመልካች ተጠሪን ይሰሩበት ከነበረው የባህርዲር ቅርንጫፍ ከ13/08/2007 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ጅማ ቅርንጫፍ ያዛወራቸው መሆኑን፣ የዝውውር ደብዲቤው በ07/08/2007 ዓ.ም. የተጻፈ ሆኖ ለተጠሪው የደረሰው በ09/08/2007 ዓ.ም. መሆኑን፣ ተጠሪው ወደ ተዛወሩበት ቦታ ሳይሄደ በባህርዲር ቅርንጫፍ ሲሰሩበት የነበረው የስራ መደብ ሳይሰረዝ ወደ ጅማ ቅርንጫፍ እንዱዛወሩ የተደረገው አለአግባብ መሆኑን ገልጸው ዝውውሩን በመቃወም ለምዕራብ አማራ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በ16/08/2007 ዓ.ም. ክስ አቅርበው መጥሪያውን በ17/08/2007 ዓ.ም. ለአመልካች ማድረሳቸውን፣ተጠሪው ከ13/08/2007 ዓ.ም.
ጀምሮ እስከ 17/08/2007 ዓ.ም. ድረስ በመደዲው ለአምስት ቀናት በተዛወሩበት ጅማ ቅርንጫፍ በስራ ላይ አልተገኙም በሚል የስራ ውላቸውን ስለማቋረጡ አመልካች 19/08/2007 ዓ.ም.
በተጻፈ ደብዲቤ ለተጠሪው ያሳወቀ መሆኑን፣አመልካቹ በቦርድ ለቀረበበት ክስ ተጠሪውን ያሰናበታቸው በመሆኑ ከስራ የተሰናበተን ሰራተኛ ጉዲይ ቦርደ የማየት ስልጣን የለውም የሚል መቃወሚያ ማቅረቡን፣ቦርደም የአመልካቹን የስንብት እርምጃ በ20/08/2007 ዓ.ም. በተሰጠ ትዕዛዝ ካገደው በኃላ ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለኝ በማለት በ04/09/2007 ዓ.ም. ብይን መስጠቱን፣አመልካቹ በዕግድ ትዕዛዙ መሰረት ተጠሪውን እስከ 29/09/2007 ዓ.ም. ድረስ ሲያሰራው ቆይቶ በቃል ትዕዛዝ ያሰናበተው መሆኑን፣በልላ በኩል የቦርደን ብይን በመቃወም አመልካች ለአማራ ብሓራዊ ክላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ ሳቢያ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ቦርደ ከስራ የተሰናበተን ሰራተኛ ጉዲይ የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለውም በሚል ብይኑን በመዝገብ በ03/11/2007 ዓ.ም. የሻረው መሆኑን፣ ተጠሪው ለወረዲው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡትም ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች በዝርዝር ገልጸው ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደስራቸው እንዱመለሱ በመጠየቅ መሆኑን፣በፍርድ ቤት በቀረበበት ክስ አመልካቹ በፍሬ ጉዲዩ ረገድ በሰጠው መልስ የአዱስ አደረጃጀት እና ደመወዝ ስኬል ጥናት በማድረግ ከ01/11/2006 ዓ.ም. ጀምሮ አዱስ ምደባ እንዲካሄደ፣ ተጠሪውም እንዱዛወሩ የተደረገው በዚሁ መሰረት እንደሆነ፣ ከስራ እንዱሰናበቱ የተደረገው ደግሞ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት በተዛወሩበት ቦታ በስራ ላይ ባለመገኘታቸው እንደሆነ እና በተዛወርኩበት ቦታ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት በስራ ላይ ያልተገኘሁት ዝውውሩን በመቃወም አቤቱታ እና ክስ በማቅረቤ ነው በሚል በሰራተኛው የሚቀርበው ምክንያት ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ስላለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሰጠው አስገዲጀ የሕግ ትርጉም መሰረት የስንብት እርምጃው የተወሰደው በአግባቡ እንደሆነ ገልጾ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ የተከራከረ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
የወረዲው ፍርድ ቤትም ክሱን እና የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኃላ የስራ መደቡ ባልተሰረዘበት ሁኔታ አመልካች ለ30 ዓመታት ያገለገለትን ሰራተኛ ወደ ላላ ቦታ ማዛወሩ ተገቢ አለመሆኑን፣ዝውውሩ ተገቢ ነው ቢባል እንኳ ተጠሪው በነበሩበት ባህርዲር ቅርንጫፍ ርክክብ የጨረሱት በ12/08/2007 ዓ.ም. ስለመሆኑ በተጠሪው ምስክሮች መረጋገጡን፣ ይህም ጉዞው ከሚፈጀው ጊዜ አንጻር ተጠሪው በ13/08/2007 ዓ.ም. በጅማ ቅርንጫፍ በስራ ላይ ሉገኙ የሚችለበት ሁኔታ እንዲልነበረ የሚያመለክት መሆኑን፣ የቦርደ የዕግድ ጊዜ ካበቃ በኃላም ተጠሪው ወደ ተዛወሩበት ቦታ እንዱሄደ አመልካች ዕድል ያልሰጣቸው መሆኑን ገልጾ ስንብቱ ሕገወጥ ነው በማለት አመልካች የአራት ወር ደመወዝ ከፍል ተጠሪ ወደ ስራ እንዱመልሳቸው በመዝገብ በ18/06/2008 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበው የባህርዲር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የቀረበላቸውን ይግባኝ እና አቤቱታ እንደቅደም ተከተላቸው በመዝገብ 3 በ05/07/2008 ዓ.ም. እና በመዝገብ በ07/07/2008 ዓ.ም. በትዕዛዝ ዘግተው በማሰናበታቸው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ተጠሪው ለአምስት ተከታታይ ቀናት ከስራ በመቅረታቸው ተሰናብተዋል በማለት የቀረበው የፊርማ መቆጣጠሪያ ሰነድ በስር ፍርድ ቤቶች ሳይታይ የመታለፈን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
የስራ መደቡ ባልተሰረዘበት ሁኔታ አመልካች ለ30 ዓመታት ያገለገለትን ሰራተኛ ወደ ላላ ቦታ ማዛወሩ ተገቢ አይደለም በማለት የወረዲው ፍርድ ቤት የደረሰበት መደምደሚያ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ ተጠሪው ወደስራ ሉመለሱ ይገባል በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም?
አመልካች የአራት ወራት ውዝፍ ደመወዝ ለተጠሪው እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ ጉዲዩን መርምረናል።
የመጀመሪያው ነጥብ በተመለከተ በመሰረቱ ተጠሪው ለወረዲው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት ዝውውሩን ሳይሆን የስራ ስንብት እርምጃውን በመቃወም ነው። ዝውውሩ እና ስንብቱ ተያያዥነት ያላቸው መሆኑን ከክርክሩ መገንዘብ የተቻለ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የዝውውሩን አግባብነት እንደ አንድ የክርክር ጭብጥ አድርጎ ውሳኔ ማሳረፈ ተገቢውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት ያደረገ አይደለም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለስራው አስፈላጊ መሆኑ ሲታመን አንድ ሰራተኛ ከአንድ የስራ መደብ ተመሳሳይ ደረጃ ወዲለው ላላ የስራ መደብ ወይም ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ላላ ቅርንጫፍ የማዛወር መብት በመሰረቱ የአሰሪው ነው። የሰራተኛው የአገልግልት ዘመን መጠን እና የስራ መደቡ አለመሰረዝ በራሱ ሰራተኛውን ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ላላ ቅርንጫፍ አዛውሮ ከማሰራት የሚከለክል አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የወረዲው ፍርድ ቤት የደረሰበት መደምደሚያ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የወረዲው ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ለማለት ከቻለባቸው ዓበይት ምክንያቶች አንደ ተጠሪው ርክክብ የጨረሱት በ12/08/2007 ዓ.ም. እንደሆነ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ጉዞው ከሚፈጀው ጊዜ አንጻር ሰራተኛው በ13/08/2007 ዓ.ም. በተዛወሩበት ጅማ ቅርንጫፍ ለመገኘት የሚችለበት ሁኔታ አልነበረም የሚል ነው። በግራ ቀኙ በኩል ከተሰሙት ምስክሮች መካከል የተጠሪው 1ኛ ምስክር ተጠሪው ርክክብ የጨረሱት በ12/08/2007 ዓ.ም. እንደሆነ በመግለጽ የመሰከሩ ሲሆን የተጠሪው የቅርብ አለቃ መሆናቸውን የገለጹት የአመልካቹ 2ኛ ምስክር በበኩላቸው ተጠሪው ርክክብ ያጠናቀቁት በ09/08/2007 ዓ.ም. እንደሆነ ገልጸው መመስከራቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ከዚህ ምስክርነት መካከል የወረዲው ፍርድ ቤት ተገቢ አድርጎ የተቀበለው በተጠሪው 1ኛ ምስክር የተሰጠውን ምስክርነት ነው።
አመልካች በሰበር አቤቱታው ላይ ርክክቡ የተፈጸመው በ09/08/2007 ዓ.ም. መሆኑን አስረድተን እያለ ተቀባይነት ያጣው አለአግባብ ነው ከማለት በቀር ተጠሪው ርክክቡን የፈጸሙት በ12/08/2007 ዓ.ም. ስለመሆኑ በተጠሪው ምስክር የተሰጠው ምስክርነት ተቀባይነት የሚያጣበት ሕጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ ያቀረበው ክርክር የለም። ርክክቡ የተፈጸመበትን ሰነድ በማስረጃነት አቅርቦ የነበረ ስለመሆኑም የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።
አመልካች በሰበር አቤቱታው ላይ ከስንብቱ ጋር የተያያዙትን ሰነድች ፍርድ ቤት በማስረጃነት አቅርበን ነበር ከማለት በቀር ካቀረቧቸው ሰነድች መካከል የርክክቡን ቀን የሚያመለክት ሰነድ ስለመኖሩ አልገለጸም። በሰበር አጣሪ ችልት አቅርቦ ከመዝገቡ ካያያዛቸው ሰነድች መካከልም ይህ ሰነድ የለም። ተጠሪው ከስራ የተሰናበቱት ከ13/08/2007 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 17/08/2007 ዓ.ም.
ድረስ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት በስራ ላይ አልተገኙም በሚል ሲሆን ርክክቡን ያጠናቀቁት በ12/08/2007 ዓ.ም. ከሆነ ደግሞ ከባህርዲር ወደ ጅማ የሚደረግ ጉዞ የሚፈጀው ጊዜ የሚታወቅ በመሆኑ ተጠሪው በ12/08/2007 ዓ.ም. በስራ ላይ አልተገኙም ሉባለ የሚችለበት አግባብ አይኖርም። ተጠሪው ርክክቡን ባህርዲር ላይ በ12/08/2008 ዓ.ም. አጠናቀው በ13/08/2007 ጅማ ቅርንጫፍ በስራ ላይ ለመገኘት የሚያስችላቸው ሁኔታ የነበረ ስለመሆኑም በአመልካቹ በኩል የቀረበ ክርክር የለም። በመሆኑም ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብል ተጠሪው ወደስራ እንዱመለሱ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም። ይሁን እንጂ አመልካች የወሰደው የዝውውር እርምጃ ተቀባይነት የሚያጣበት ሕጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ እና ተጠሪውም ወደ ስራ መመለስ የሚገባቸው በጅማ ቅርንጫፍ በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪው ወደ ስራ የሚመለሱበትን ቅርንጫፍ ሳይለይ በደፈናው ወደስራ ሉመለሱ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ውሳኔው በዚህ አግባብ ብቻ ሉታረም የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
ሶስተኛውን ነጥብ በተመለከተ ወደ ስራው እንዱመለስ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስራ ክርከር ችልት የተወሰነለት ሰራተኛ ከስድስት ወራት የማይበልጥ ውዝፍ ደመወዝ እንዱከፈለው ፍርድ ቤቱ የሚወስን ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43 (5) የተመለከተ በመሆኑ ለተጠሪው የአራት ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዱከፈል መወሰኑ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል ጉዲዩ በይግባኝ ታይቶ የሰራተኛው ወደስራ የመመለስ ውሳኔ ከፀና ከአንድ ዓመት ያልበለጠ ውዝፍ ደመወዝ ፍርድ ቤቱ ለሰራተኛው የሚወስን ስለመሆኑ በዚሁ ድንጋጌ ተመልክቷል። በመሆኑም ጉዲዩ በዚህ ችልት ከቆየበት ጊዜ አንጻር ለተጠሪው በተጨማሪ የሁለት ወራት ደመወዝ ሉወሰን የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በባህርዲር ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ18/06/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ በባህርዲር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት እንደቅደም ተከተላቸው በመዝገብ 3 በ05/07/2008 ዓ.ም. እና በመዝገብ በ07/07/2008 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የስራ ስንብት እርምጃው ሕገወጥ በመሆኑ ተጠሪው የአራት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደስራ ሉመለሱ ይገባል በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በስር ፍርድ ቤቶች ከተወሰነው በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43 (5) በተመለከተው መሰረት አመልካች የሁለት ወር ውዝፍ ደመወዝ ለተጠሪው ሉከፍል ይገባል በማለት ወስነናል።
ወደስራ የሚመለሱበት ቅርንጫፍ ሳይለይ ተጠሪው ወደስራቸው ሉመለሱ ይገባል በሚል በደፈናው የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
ተጠሪው ወደ ስራ ሉመለሱ እና ውዝፍ ደመወዝም ሉከፈላቸው በተዛወሩበት ጅማ ቅርንጫፍ ነው በማለት ወስነናል።
በባህርዲር ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ09/07/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.