አንድን ሰራተኛ በስራ ላይ አልተገኘም ማለት የሚቻለው ጎል ኢትዩጵያ II ውለ ፀንቶ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ብቻ ስለመሆኑ፡አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27 (1) (ለ) እና አቶ ዱዱሞ አጋቶ
No summary available.
ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች- ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች- ጎል ኢትዮጵያ ነ/ፈ ሙስሐረድ ደሳለኝ ቀረቡ ተጠሪ- አቶ ዱዱሞ ኦጋቶ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው።
የአቤቱታው ይዘት በአመልካች ድርጅት ውስጥ በመዛኝ የስራ መደብ ተቀጥሬ እያገለገልኩ እያለ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ለ) ከተደነገገው ውጭ የስራ ውለን ያቌረጠ በመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 43(2) መሰረት ወደ ስራዬ እንዱመልሰኝ ወይም ጥቅማ ጥቅም ተከፍልኝ እንዱያሰናብተኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ለቅርብ አለቃቸው ሆነ ለላላ ለሚመለከተው አካል ሳያሳውቁ ለቀሩባቸው ሰባት ቀናት በቂና ህጋዊ ምክንያት ባለማቅረባቸው ከስራ መባረራቸው በአዋጁ አንቀጽ 27(1) መሰረት ህጋዊ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ማስረጃውን መርምሮ ከሳሽ በአያቱ ሞት ምክንያት ሃዘን ላይ እንደነበር የሚያስረዲ ማስረጃ በማቅረቡ በሃዘን ምክንያት በአዋጁ አንቀፅ 81(1)(ለ) መሰረት የሚሰጠው ፈቃድ እና የሳምንት የእረፍት ፈቃድ ተካቶ ሲሰላ ከስራ ያለምክንያት ቀርቷል ልባል የሚችለው ለሁለት የስራ ቀናት ብቻ በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው፤
ስለሆነም ድርጅቱ ሰራተኛውን ወደ ስራው እንዱመልስ ወደ ስራው መመለስ ካልፈለገም ክፍያ እንዱፈፅም ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ቅሬታቸውን ለጋምቤላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ጳጉሜ 2/2007 ዓ.ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ ተጠሪ 5 (አምስት) ቀናት በመደዲው ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱ በተረጋገጠበት ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብል መወሰኑ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ዓላማ እና ይዘት በአግባቡ ያገናዘበ መሆኑን ለማጣራት ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ተጠሪ መጥሪያውን ተረክበው መልስ በሚሰጥበት ቀን ስላልቀረቡ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
ከላይ ባጭሩ ለመግለፅ የሞከርነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን ቅሬታ በቀረበበት ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ቢኖር መርምረናል። እንደመረመርነው አመልካች በሰበር ቅሬታቸው ተጠሪ ለድርጅቱ ሳያሳውቁ ከየካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ መቅረታቸውንና፤ በዚህም መነሻ ድርጅቱ ከየካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከተጠሪ ጋር የነበረው የቅጥር ውል መቌረጡን የሚገልፅ ደብዲቤ መፃፈን በመካድ አልተከራከሩም። የስንብት ደብዲቤውም ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። ነገር ግን ተጠሪ ከስራ ከቀሩ በአስራ ሁለተኛው ቀን ማለትም መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ መመለሳቸውን እና ባቀረቡት የሀዘን ማስረጃ የሚሰጠው ሶስት የረፍት ቀናት እንዱሁም የበዓል እና እሁድ ቅዲሜ የረፍት ቀናት ቢቀነሱ በአዋጁ አንቀፅ 27(1)(ለ) ከተመለከተው ጊዜ በላይ ያለምክንያት ከስራ መቅረታቸውን ስለሚያሳይ ስንብቱ ህጋዊ ነው እንዱባል ተከራክረዋል።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27(1)(ለ) እንደተደነገገው በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረት አሰሪው የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቌረጥ ያስችለዋል። ከድንጋጌው መረዲት እንደሚቻለው ሰራተኛው ከስራ የቀረበት ቀን የሚቆጠረው እና የቀረበትም ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑ የሚመዘነው የስራ ዉለ ፀንቶ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ነው። ከዚህ በቀር የስራ ውለ ከተቌረጠ በኋላ ላለ ቀናት ሰራተኛው በስራው እንዱገኝ ስለማይጠበቅ የቀረበትን ጊዜ መቁጠር እና የቀረበትን ምክንያት በቂነት መመዘን አያስፈልግም።
በመሆኑም በተያዘው ጉዲይ አመልካች ሰራተኛው ለድርጅቱ ሳያሳውቅ ከየካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ መቅረቱንና፤ በዚህ ምክንያት ድርጅቱ ከየካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከተጠሪ ጋር የነበረው የቅጥር ውል መቌረጡን የሚገልፅ ደብዲቤ መፃፈን ሳይክደ ሰራተኛው መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ መመለሱን መሰረት በማድረግ ከየካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲታሰብ በመደዲው ለአምስት የስራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከስራ መቅረቱን ያሳያል ስለሆነም ስንብቱ ህጋዊ ልባል ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1)(ለ) የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ መሰረት ያላደረገ፤ ድንጋጌውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያበቁ ሁኔታዎችን ያላሟላ ክርክር በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም። የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት በሕጉ ከተደነገገው ውጭ እንዱሰናበት ተደርጓል ስለሆነም ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት ወደ ስራው እንዱመለስ ወይም ለዚህ ዓይነት ሕገ-ወጥ ስንብት ሉከፈል የሚገባው ክፍያ እንዱከፈል ያሳለፈት ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላላገኘነው በአብላጫ ድምፅ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመ//07 በቀን 8/10/2ዐዐ7 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የጋምቤላ ከፍ/ፍ/ቤት በ14/11/2007 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በፍ/ሰ/መ//07 በ26/12/2007 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት መስከረም 12/2008 ዓ.ም አፈፃፀሙ እንዱታገድ ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።