የግል አሰሪና ሰራተኛ (ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ) እና በሰራተኛ የሚነሳ ማንኛውም የስራ ክርክር የሚፈታው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 4
No summary available.
ሚያዝያ 24 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካቾች፡-
ይህ የሰበር ጉዲይ ላቀርብ የቻለው የአሁን አመልካቾች በስር ፍርድ ቤቶች የቀረበው ክስ እልባት ማግኘት የሚገባው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቀጥር 377/1996 መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 632/2004 የሚደነግግ በመሆኑ ጉዲዩ ልዩ ችልት የተቋቋመለት ስለሆነ በመደበኛው ፍትሐ ብሓር ችልት አይታይም በማለት መዝጋቱ ነው። የክርክሩ መነሻ የአመልካቾች ልጅ ኩየት የቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ሄዲ አሰሪዎቿ ተገቢውን ጥንቃቄ ለድህንነትዋ ተገቢው እንክብካቤ ሳይደረግላት መቅረቱ በካርቦን ጭስ መርዝ ታፍና በሞት ተለይታለች። አመልካቾች በልጃቸው ሞት ምክንያት ኩየት ሆና በገንዘብ ትረዲቸው ስለነበር የተቋረጠባቸው ጥቅም ለማግኘት በኃላፉነት ወደ ኩየት አገር ለላካት በተጠሪ ላይ በፋ/የመ/ደ/ፍ/በት አራዲ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሓር ችልት ከውል ውጭ ኃላፉነት ክስ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም ክሱ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሚታይ ስለሆነ ለስራ ክርክር ችልት የሚቀርብ ነው በማለት እንዱዘጋ ትእዛዝ ሰጥቷል። ይህን ትዕዛዝ በመቃወም አመልካቾች ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አይደለም። ይህ ጉዲይ ከውል ውጭ ኃላፉነት በተደነገገው በፍ/ብ/ህ/ቁ.2035፤2090፤2091 ነው መታየት ያለበት ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዱታረም በማለት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ በመመርመር ስህተት የለውም በማለት በትእዛዝ ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትእዛዝ ላይ የሰጡት ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ነው። አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባ ነው ተብል በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል። የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን በዚህ መሰረትም ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፤ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
አመልካቾች ጉዲዩ መታየት ያለበት ከውል ውጭ ኃላፉነት ነው። በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3(1)(2)(መ) በቤት ሰራተኛነት በትርፍ ላልተመሰረተ የአግልግልት ቅጥር የማይሸፍን መሆኑ ህጉ በግልፅ ይደነግጋል። በተመሳሳይ ጉዲይም የፋዳራል ሰበር ችልት በሰ/መ/ ከውል ውጭ ኃላፉነት እንደሚታይ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። በልላ በኩል በመ/ቁ.
419560 ፋዳራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችልት 2ኛ ፍ/ብሓር ችልት ክስ አቅረበን በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 መሰረት አይሸፈንም በሚል መዝገቡ ተዘግቶብናል።
በይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.130500 ጉድለት የለበትም በማለት ዘግቶታል።
የስር ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የህግ ክርክሮች ሳያዩትና ሳይመለከቱ ሳይመረምሩ መዝገብ በመዝጋት የሰጡት ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ጥሰት ነው ስለዚህ የሥር ፍርድ ቤቶች ትእዛዝ በመሻር ጉዲዩ በመመሪያ ወደ ታች ፍርድ ቤት ተመልሶ ከውል ውጭ ኃላፉነት ታይቶ እንዱወሰን አመልክተዋል።
በተጠሪ በኩል ደግሞ ግንኙነቱ የስራ ውል ነው። በስራ ላይ እንዲለች በደረሰባት ጉዲት መሞቷን የተገለፀ ስለሆነ አዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 4፤20 ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3፤110 መሰረት የሚስተናገድ ነው። የአመልካቾች ልጅ ከተጠሪ ጋር የሥራ ውል ስምምነት በማድረግ በውጭ ሀገር ለስራ ለሶስተኛ ሰው አገልግልት እንድትሰጥ በህጋዊ መንገድ የሄደች በመሆኑ አመልካቾችም በስራ እንዲለች በደረሰባት ጉዲት መሞቷን የገለፁ ስለሆነ በመካከላችን የሚኖረው ክርክር አፈታት አዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 4 በግልፅ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ይታያል በማለት በግልፅ ተመልክቷል። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 632/2001 እና በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መታየት አለበት ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሉፀና ይገባል ሲል ተከራክረዋል።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 /2/መ/ መሰረት ለትርፍ በሚካሄድ ስራ ላይ ያልተመሰረተ የግል አገልግልት ቅጥር ላይ ህጉ ተፈፃሚነት እንደላለው በግልፅ የተደነገገ ነው።
በልላ በኩል ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 3/2/ መሰረት ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 /2/መ/ ቢኖርም ለትርፍ በሚካሄድ ስራ ላይ ላልተመሰረተ የግል አገልግልት ስራ ላይ ለመቀጠር ወደ ውጭ አገር በሚሄድ ኢትዮጵያዊ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ሲል ተደንግጓል።
ስለዚህ የቤት ሰራተኛ ወደ ውጭ የተላከ ከሆነ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ተፈፃሚነት ያለው በመሆኑ በዚህ ረገድ በአመልካቾች የቀረበው ተቀባይነት የለውም። በአዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 4 መሰረት የግል ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ እና በሰራተኛ የሚነሳ ማንኛውም የስራ ክርክር የሚፈታው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ እንደሚታይ ተመልክቷል። አዱስ በወጣው የኢትዮጵያ የውጭ አገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 አንቀጽ 71 በሰራተኛ መሰረት እና በአሰሪው ወይም በኤጀንሲው መካከል ካለው የስራ ግንኙነት በመነጨ ማንኛውም የመብትና የጥቅም ክርክር ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት በተቋቋመ የስራ ክርክር ችልት ይታያል በማለት ተደንግጎ ይገኛል።
በአጠቃላይ የአመልካቾች ጉዲይ በውል የስራ ግንኙነት የተመሰረተ በልጃቸው የደረሰው ጉዲት መስተናገድ ያለበት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሆኑን በዝርዝር ከላይ እንደተመለከተው ነው።
ስለሆነም በአመልካቾች የሚቀርበው ጉዲዩ መታየት ያለበት ከውል ውጭ ኃላፉነት ነው የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም። በልላ በኩል አመልካቾች በመጀመሪያ ጉዲያቸው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት አቅርበው ፍርድ ቤቱም በእንደዚህ አይነት የስራ ግንኙነት በአዋጅ ቁጥር 337/1996 አንቀጽ 2 እና 3 መሰረት ሉሸፈን የማይችል እና የክርክር መንፈስም ፍርድ ቤቱ የማየት ሥረ ነገር ስልጣን የለውም በማለት የተዘጋ መሆኑን ከመ/ቁ.41956 ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ከተሰጠው ትእዛዝ መገንዘብ ይቻላል። ይህ የሚያመለከተው ደግሞ አመልካቾች ጉዲያቸውን በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱሰጣቸውና መብታቸውን ለማሰጠበቅ በተለያየ ጊዜ ከመጠየቅ ያልተቆጠቡና ጥረት ያደረጉ መሆናቸውን ነው።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ትእዛዝ በህጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈፀመበት ነው የምንልበት ምክንያት አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መ/ቁ.147425 የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ትእዛዝ እና የፋ/መ/ደ/ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.111396 ታህሳስ 11 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካቾች ክሱን ማቅረብ የሚገባቸው ለስራ ክርክር ችልት ነው በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.