በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በግልጽ በተቀመጡ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር አንዱት ሰፍሰጡር ሴት ከወሉድ በኋላ አራት ወራት ውስጥ ከስራ ያለመባረር መብት ያላት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 25፣27፣29/3/ እና 87/5//6/
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 121063 የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻዉ አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- መ/ርት ሙለነሽ መለሰ ወኪል ገ/አምላክ አበጋዝ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዋሉያ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በአ/ብ/ክ/መንግስት ጎንደር ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ፍሬ ነገርም ባጭሩ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በመምህርነት የስራ መደብ ላይ ከ2004 ዓ/ም እስከ 2007 ተቀጥረው ስራቸውን ሲሰሩ እንደነበር፣ በስራቸው ላይ እያለ ነፍሰጡር የነበሩ ቢሆንም የቅድመ ወሉድ ፈቃድ ሳይወስደ በመውለዲቸው በህጉ የተጠበቀላቸውን የድህረ ወሉድ ፈቃድ በመጠቀም ላይ እያለ ያልተጠቀሙበትን የቅድመ ወሉድ ጊዜ በድህረ ወሉድ በመጠቀም ወደ ስራቸው ሲመለሱ ተጠሪ አመልካች ከስራ ተሰናብተሻል ያላቸው መሆኑንና ይህም ከህጉ ይዘትና መንፈስ ውጭ መሆኑን ጠቅሰው የተጠሪ እርምጃ ህገ ወጥ ነው ተብል የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም ቀርቦ በሰጠው መልስ አመልካች በራሳቸው ጊዜ ያልተጠቀሙበትን የቅድመ ወሉድ ፈቃድ ለድህረ ወሉድ መጠቀማቸው ህጋዊ ያለመሆኑና ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖር ከስራ ገበታቸው በመቅረታቸው መሰናበታቸው ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች የቅድመ ወሉድ ፈቃድ ሳይጠቀሙ በድህረ ወሉድ ጊዜ መጠቀማቸውና ከስራ መቅረታቸው ህጋዊ አይደለም በማለት ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት በዚህ ረገድ የተጠየቁትን የአመልካች ክፍያዎችን ውድቅ አድርጎ ከህዲር 01 ቀን እስከ ህዲር 12 ቀን 2007 ዓ/ም ድረስ ያለውን ውዝፍ ደመወዝ ብቻ ይከፈላት ሲል ወስኗል።
አመልካችም በውሳኔው ቅር በመሰኘት ቅሬታውን ለሰሜን ጎንደር መስተዲደር ዞን ፍ/ቤትና ቀጥልም ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም በሁለቱም ተቀባይነት አላገኘም።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ከፍ ሲል በተገለጸው መልኩ የተሰጡትን ውሳኔዎች በመቃወም ለማስቀየር ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በቅድመ ወሉድ ጊዜ ያልተጠቀመችበት የአንድ ወር የእረፍት ጊዜ በድህረ ወሉድ ጊዜ ከሚሰጠው ሁለት ወር የእረፍት ጊዜ ጋር መጠቀም አትችልም በማለት የሰጡት ውሳኔ የህጉን መንፈስና ይዘት ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ አንድ ሴት ከወለደች በኋላ ከአራት ወራት በፉት ከስራ መሰናበት የለባትም ተብል በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 87/4/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ እንዱሁም በላልች የመንግስት ሰራተኞች ህግጋት የተመለከተውን የመብት ጥበቃና የህግ አተረጓጎም ያልተከተለ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታውም ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት የህግ ትርጉም ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል መዝገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪም ቀርበው መልስ ሉሰጡ ስላልቻለ መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ተይዞ ከነበረው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
በመሰረቱ የአሰሪና ሰራተኛ ህጉ በአንድ በኩል ሰራኛው ያለአግባብ ከስራ እንዲይፈናቀል ጥበቃ የሚያደርግ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ የኢንደስትሪ ሰላምን በመፍጠር የምርትና ምርታማነት እድገቱ እንዱጨምር ዋስትና ሲጪም እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ይሄንኑ መሰረታዊ ሐሳብ መነሻ ባደረገ መልኩ ብልም የኢንደስትሪ ሰላሙን ከመጠበቅ አኳያ አንድ ሰራተኛ በአዋጅ ቁ/ 377/96 አንቀጽ 27 ንዐስ አንቀጽ 1 ከፉደል ‛ሀ“ እስከ ‛በ“ ባለት ስር የተዘረዘሩትን ጥፊት ፈጽሞ ከተገኘ አሰሪው ያለቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የስራ ውለን ማቋረጥ እንደሚችል መደንገጉን ከህጉ አጠቃላይ ድንጋጌዎች ከአንቀጽ 87/6/ ድንጋጌ የምንረዲው ጉዲይ ነው።
እንዱሁም ህጉ ለተለዩ የሰራተኛ ክፍልች የተለዬ ጥበቃ የሚያደርግባቸው ምክንያቶች መኖራቸውን ህጉ ያሳያል። ህጉ በአዋጅ አንቀጽ 14፣ ከአንቀጽ 87 እስከ 88 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች በተለየ መልኩ ድንጋጌዎችን ከአስቀመጠላቸው ሰራተኞች መካከል ሴት ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ድንጋጌዎች በአንድ በኩል ሁለንም ሴት ሰራተኞችን፣ በልላ በኩል ደግሞ በተለየ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴት ሰራኞችን የሚመለከቱ ናቸው። እርግዝናና ወሉድ ደግሞ ሴቶችን በተለያየ ሁኔታ ውስጥ እንዱገኙ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በመሆናቸው በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ህጉ ልዩ ጥበቃ ያደርግላቸዋል። ወሉድን በተመለከተ ህጉ ለሴቶች የሚያደርገው ልዩ ጥበቃ የቅድመ ወሉድና የድህረ ወሉድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር የማግኘት መብትና እንዱሁም በልላ ጊዜም ሀኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር እረፍት የማግኘት መብት ስለመሆናቸው የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 88 ድንጋጌዎች ያሳያለ። እንዱሁም አሰሪው ሰራተኛዋ ነፍሰ ጡር ከሆነችበትና ከወለደችበት ቀን ጀምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከስራ እንዱያሰናብታት ህጉ ጥበቃ የሚያደርግ መሆኑን ከአዋጅ አንቀጽ 87/5/ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የቅድመ ወሉድ ፈቃድ ባልወሰደበት ሁኔታ የወለደ ሲሆን በአዋጅ አንቀጽ 88/3/ የተጠበቀላቸውን የስልሳ ቀን የድህረ ወሉድ ፈቃድ ከክፍያ ጋር አግኝተው በቅድመ ወሉድ ጊዜ ሉጠቀሙ ይችለ የነበረውን የሰላሳ ቀን የወሉድ ፈቃድ በህጉ የተጠበቀላቸው የድህረ ወሉድ ጊዜ ሲያልቅ አንድ ላይ በመጠቀም ላይ እያለ ተጠሪ በህጉ የተጠበቀላቸው የድህረ ወሉድ ጊዜ በማለቁ አመልካች ስራ ላይ አልተገኘም በሚል የስራ ውልን ያቋረጠባቸው መሆኑን ክርክሩ ያሳያል። ከላይ እንደተገለጸው አንዱት ሴት በእርግዝና ምክንያት በህጉ የተጠበቀላት የቅድመ ወሉድና የድህረ ወሉድ ፈቃድ ጊዜ የሚታወቅ መሆኑን ህጉ ቢያስቀምጥም በቅድመ ወሉድ ጊዜ በህጉ የተጠበቀላትን የፈቃድ ጊዜ ሳትጠቀም ብትወልድ በቅድመ ወሉድ ጊዜ ይሰጥ የነበረው ፈቃድ ያልተጠቀመች ሴት ሰራተኛ ይህንኑ ጊዜ በድህረ ወሉድ ጊዜ መጠቀም የምትችል መሆኑን ያለመሆኑን ግን ህጉ በግልጽ አያስቀምጥም። ይሁን እንጂ ህጉ ከወሉድ በኋላ አንድ ሴት ሰራተኛ አራት ወር ሳይሞላት ከስራ ልትሰናበት እንደማትችል በአዋጅ አንቀጽ 87/5/ ስር የተመለከተው ድንጋጌ በህጉ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል መሆኑን ተቀባይነት ያላቸው የህግ አተረጓጎም ደንቦች ያስገነዝባለ።
አንድ ልዩ ህግ አግባብነት ባለው ድንጋጌ ውስጥ ግልጽ የሆነ መፍትሓ ካላስቀመጠ ይኸው ድንጋጌ ባለበት ክፍልና ምእራፍ ስር ያለትን ድንጋጌዎች አስተሳስሮ በማየት ተገቢውን ትርጉም መስጠት የህግ ትርጉም ደንቦች የሚፈቅደት ጉዲይ ነው። ከዚህ አንፃር ጉዲዩን ስንመለከተው አመልካች በአዋጅ አንቀጽ 25፣ 27 እና 29/3/ ድንጋጌዎች አግባብ ካልሆነ በስተቀር ከወሉድ በኋላ አራት ወራት ውስጥ ከስራ ያለመባረር መብት ያላቸው መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 87 /5/ እና /6/ የሚያስቀምጥ በመሆኑና ተጠሪ ደግሞ ለስንብቱ ህጋዊ ምክንያት ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክር በአዋጅ አንቀጽ 27 /1/ለ// ድንጋጌ ስር የተመለከተውንና ህግ አውጪው ከወሉድ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ ተቀባይነት ያለውን ድንጋጌ በመጥቀስ በመሆኑና የአመልካች ከስራ መባረር ከዱሲፕሉን ወይም ከቅነሳ ስርዓት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ባላስረዲበት ክርክሩ የህግ መሰረት የላለው ነው። የስር ፍርድ ቤቶች በህጉ ያለውን ክፍተት በማየት ተገቢውን የህግ አተረጓጎም በመከተል ለጉዲዩ በአዋጅ አንቀጽ 87/5/ የተመለከተውን ጥበቃ ተግባራዊ ማድረግ ሲገባቸው ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት የላለውን የአዋጅን አንቀጽ 88 /4/ ድንጋጌን መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባው የህግ ትርጉም አተገባበር ሆኖ አልተገኘም። ቀጥል መታየት ያለበት ውጤቱ ነው። የስራ ውል የተቋረጠበት አግባብ ከሕግ ውጭ ነው ከተባለ ውጤቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 42 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የሚወሰን ይሆናል። አመልካች በስር ፍርድ ቤት የጠየቁት የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ነው። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 35/1/ለ/ መሰረት የሁለት ወር ደመወዝ፣ ክፍያ ለዘገየበት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 38 መሰረት የሁለት ወር ደመወዝ፣ በአዋጅ አንቀጽ 43/4/ሀ/ ደግሞ ካሳ በህጉ በተቀመጡት ስላቶች መሰረት አመልካች ሉከፍሎቸው ይገባል ብለናል። በልላ በኩል አመልካች የዓመት እረፍት የጠየቁ በመሆኑና ተጠሪ ደግሞ አመልካች የወሰደ ስለመሆኑ ገልጾ የሚከራከር በመሆኑ አመልካች የአመት እረፍት ያልተጠቀሙ መሆን ያለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተጣርቶ እንዱወሰን ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። ላላው አመልካች የጠየቁት የዲኝነት ጥያቄ ያልተከፈላቸው ደመወዝ ነው። ሆኖም ይህ ክፍያ ከድህረ ወሉድ ፍቃድ መጠናቀቅ በኃላ ለነበረው ጊዜ ስራ ስላልሰሩ በአዋጅ አንቀጽ 377/96 አንቀጽ 54 መሰረት እንዱከፈላቸው ማድረግ ሕጋዊ ሆኖ አልተገኘም።
በመሆኑም በዚህ ረገድ የተጠየቀው ክፍያ ህጋዊ ሆኖ አልተገኘም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
በጎንደር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/1 በ16/06/2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/8 በ30/06/2007 ዓ.ም በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በ18/02/2008 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው ከሕግ ውጪ ነው ብለናል። በመሆኑም ተጠሪ ለአመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 35/1/ለ/ መሰረት የሁለት ወር ደመወዝ፣ ክፍያ ለዘገየበት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 38 መሰረት የሁለት ወር ደመወዝ፣ በአዋጁ አንቀጽ 43/4/ሀ/ ደግሞ ካሳ እና በአንቀጽ 39 እና 40 መሰረት ደግሞ የአገልግልት ክፍያ በህጉ በተቀመጡት ስላቶች መሰረት ሉከፈሎቸው ይገባል ብለናል። የአመት እረፍትን በተመለከተ ግን አመልካች የወሰደ መሆን ያለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተጣርቶ እንዱወሰን ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ስለተገኘ በዚህ ረገድ የጎንደር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አጣርቶ እንዱወሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይፃፍ።
ከድህረ ወሉድ ፈቃድ በኃላ ላለው ጊዜ አመልካች የሚከፈላቸው ደመወዝ የለም ብለናል።
የሰበር ክርክር ወጪና ኪሳራን ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።