የአሰሪውን ትእዛዝ አልፈፀመም ተብል የስራ ስንብት ያደረገ አሰሪ ትእዛዙ ያለመፈጸሙን የማስረዲት ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13
No summary available.
ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች- የደብረዘይት ሄልሜክስ ቄራ ድርጅት- ተወካይ ፀጋ መርጋ ቀረቡ ተጠሪዎች- 1.አየለ ዱባባ 2. ግርማ ፍቃደ ጠበቃ አቦነሽ በላቸው ቀረቡ 3. መኮንን ሳህለ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች በአድአ ወረዲ ፍ/ቤት በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ፍሬ ነገርም ባጭሩ በድርጅቱ ውስጥ በቆዲ መግፈፍ እርድ ሥራ መደብ ተቀጥረው ሲሰሩ ቆይተው ተከሳሽ ድርጅት በቀን 14/06/2007 እና በ16/06/2007 በተጻፈ ደብዲቤ የስራ ዉለን አቋርጦ ያላግባብ ከስራ ያሰናበታቸው በመሆኑ እና በደብዲቤ የተገለፁት ምክንያቶች የስራ አስኪያጅ ትዕዛዝን አለመቀበል፤ ስራን በመሰልቸት ማጓተት፤ በቀን 8 ሰዓት አለመስራት፤ እንዱሁም ከስጋ መጫን ጋር የተያያዘ ሲሆን አንቀበልም ያልንዉ የስራ አስኪያጅ ትዕዛዝ ባለመኖሩ፤ ስራን ያላጓተትን በመሆኑ፤ እንደ ህጉ ሙለ የስራ ሰዓት አንሰራም ያላልን በመሆኑ እና የተቀጠርንበት የስጋ መግፈፍ ቢሆንም በተጨማሪ ስንታዘዝ ለስጋ መጫን የተቀጠሩትን አግዘን ስንጭን የነበረ በመሆኑ የተጠቀሱት ምክንያቶች በሙለ ሆነ ተብለው ከስራ ለማሰናበት በተከሳሽ ድርጅት የተፈጠሩ በመሆኑ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ተብል ልዩ ልዩ ክፍያ ይከፈለን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሹ ለክሱ በሰጠው መልስ በቆዲ መግፈፍ ሥራ ላይ የተሰማሩ ቢሆንም እነሱ ስራ በልላቸው ጊዜ ተከሳሽ ላላ ስራ ማሰራት እንደሚችል በህጉ የተፈቀደ በመሆኑ፤ ሰራተኛው ምን አይነት ስራ ቢሰራ ትርፍ ያስገኛል የሚለውን ከግምት በማስገባት ሰራተኛውን ከተቀጠረበት ስራ ዉጪ ማሰራቱ ከስራ ስምሪት ስልጣን የመነጨ መብት በመሆኑ፤ ከሳሾች ታዘው ስራ አንሰራም ስላለ ስጋ በጊዜ ሳይጫን ቀርቶ በምን አገባኝነት የተከሳሽ ንብረት እንዱጠፊ ስላደረጉ ተከሳሽ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት ያለማስጠንቀቂያ አሰናብቷል። ነገር ግን ከሳሾች በ17/06/2007 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ወደ ስራ ለመመለስ ጠይቀዉ ተከሳሽ ወደ ስራ የመለሳቸው ቢሆንም በገዛ ፈቃዲቸው ስራውን ትተው ክሱን ያቀረቡ በመሆኑ መሰናበታቸው ህጋዊ ነው ይባል፤ ከዓመት ዕረፍት በቀር ላልች ክፍያዎችም ሉከፈሎቸው አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተው የወረዲ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሽ ያቀረበው መከራከሪያ በራሱ ምስክሮች ጭምር አለመረጋገጡን በመጥቀስ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ብል ተከሳሽ በአዋጁ መሰረት ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ለከሳሾች እንዱከፍል ወስኗል። ይግባኙ የቀረበለት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔዉን በማሻሻል በአንቀፅ 38 መሰረት ክፍያ ለዘገየበት የተወሰነውን ቅጣት በመሻር ላላው የውሳኔ ክፍል እንዱፀና ወስኗል። አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጓል።
የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ህዲር 2/2008 ዓ.ም ያቀረቡት ማመልከቻ ተመርምሮ ለተጠሪዎች የተሰጠው ስራ ቀድሞ ሲሰሩት ከነበረው ስራ ጋር ተያያዥነት (ተመሳሳይነት) ያለው መሆን አለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች ተጣርቶ የመወሰን አለመወሰኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ተጠሪዎችም ቀርበው ታህሳስ 14/2007 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የተቀጠሩበት የቆዲ ገፊፉነት ስራ ከጭነት የስራ መደብ የተለየ መሆኑን እና ለሸክም ስራውም አልታዘዙም የተባለው ከእውነት የራቀ መሆኑን በመጥቀስ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም ተብል እንዱፀና ጠይቀዋል። አመልካቹ ክርክሩን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከላይ ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የሰበር አቤቱታ በቀረበበት ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በጭብጥነት ይዘን ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪዎችን ከስራ ለማሰናበት ምክንያት ያደረገው የስራ ሰዓትን ተከትል በትጋት አለመስራትንና ከስራ መደባቸው ዉጭ የጭነት ስራ እንዱሰሩ ሲታዘዙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ አክብረው አለመስራታቸውን ሲሆን ተጠሪዎች የተጠቀሱት ምክንያቶች ሆነ ተብል ለስንብት የተዘጋጁ ናቸው በማለት በመካድ ተከራክረዋል። በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀጽ (2) እና (7) እንደተመለከተው ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ዉለ እና በስራ ደንቡ መሰረት በአሰሪው የሚሰጠውን ትዕዛዝ የመፈፀም እንዱሁም የአዋጁን ድንጋጌዎች፤
የህብረት ስምምነትን፤ የስራ ደንብንና በህግ መሰረት የሚተላለፈ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን የማክበር ግዳታ አለበት። አመልካች በዚህ የህጉ አግባብ ስራውን በመምራት ለስራው ውጤታማነትና ቅልጥፍና የሚረደ የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ሰራተኞችን ለስራ የማሰማራት ተግባር እንዱያከናውን የተፈቀደለት ቢሆንም ለስንብቱ የተጠቀሱት ምክንያቶች መኖራቸውን፤የሰጠው ትዕዛዝም አለመከበሩን የማስረዲት ግዳታ ይኖርበታል። በተያዘው ጉዲይ የተካደውን ፍሬ ነገር በማስረጃ ለማጣራትና ማስረጃንም ለመመዘን ስልጣኑ የተሰጠው የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃዎች ሰምቶ ተጠሪዎች ለስንብቱ የተጠቀሱትን ምክንያቶች አለመፈፀማቸውን አረጋግጫለሁ በማለት የስንብቱን ህገ ወጥነት ወስኗል።
ተጠሪዎች የስራ ግዳታቸውን አለመወጣታቸዉን በማንሳት አመልካች ያቀረበውን ክርክር በፍሬ ነገር ረገድ ስላላስረዲ የስራ ውለን ማቋረጡ ህገወጥ ነው ተብል መወሰኑ የአሰሪና ሰራተኛ የአዋጁን ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ያገናዘበ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘንውም።
ስለሆነም በውሳኔው የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስላላገኘን ተከታዩን ውስነናል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ23/10/2ዐዐ7ዓ.ም. ተሻሽል የተሰጠው ፍርድ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ በ04/02/2008 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የተጀመረው አፈፃፀም ታግድ እንዱቆይ በዚህ ፍርድ ቤት ህዲር 6/2008 ዓ.ም በዋለ ችልት የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.