አንድ የፖለቲካ ድርጅት የላላ የፖለቲካ ድርጅት አባል የሆኑ ሰዎችን አባልነታቸው ህጋዊ በሆነ መልኩ ሳይቋረጥ ወይም ቀሪ ሳይሆን እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የሁለት የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆን የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 532/199 አንቀፅ 46፣102/4//ለ/፣አዋጅ ቁጥር 632/2002 አንቀፅ 7
No summary available.
ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- መድህን ኪሮስ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ አመልካች፡- አንድነት ለፍትህና ለዱሞክራሲ ፓርቲ ወኪል መልካሙ ሙጬየ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ሰማያዊ ፓርቲ ወኪል ወረታው ዋሴ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ነው። በምርጫ ክልለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አመልካች አቤቱታ አቅራቢ ተጠሪ መልስ ሰጭ በመሆን ተከራክረዋል። ጉዲዩ በግንቦት ወር 2007 ዓ/ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የተጠሪ በምርጫ ክልለ እጩ አድርጎ ያስመዘገባቸውን ሰዎች በመቃወም የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ነው።
አመልካች በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል ባቀረበው አቤቱታ ተጠሪ ደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል እጩ አድርጎ ያቀፈረባቸው አቶ ግርማ ቢተው፣ አቶ መለስ ዘለቀ፣ ወ/ሮ የርጋደ ታደገ እና አቶ ይሁኔ ጥላሁን የአመልካች ድርጅት አባላት እንጂ የተጠሪ አባላት አይደለም። ተጠሪ ፓርቲውን እንዱወክለ በእጩነት አቅርቦ በቅጽ 003 ያስመዘገባቸው ግለሰቦች በእጩነት እስከ ተመዘገቡበት ጊዜ ድረስ የአመልካች አባልና አመራር ሆነው ተልዕኮ ሲያስፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው ግለሰቦቹ ተጠሪን (ሰማያዊን ፓርቲን) በመወከል እጩ ሆነው ሉወዲደሩ አይገባቸውም በማለት በጽሐፍ አቤቱታ አቅርቧል። የደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ ከላይ ስማቸው የተገለፁት ግለሰቦች የላላ የፖለቲካ ፓርቲ (አመልካች) አባል በመሆናቸው ተጠሪን በመወከል እጩ ተወዲዲሪ ሆነው መቅረብ አይችለም በማለት የካቲት 10 ቀን 2007 ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለብሓራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ አቅርቧል። የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተጠሪ ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታና ደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ ከመረመረ በኃላ የመርዓዊና ገርጨጭ ምርጫ ክልል ቢሮ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ የሚያስለውጥ ምክንያት የለም በማለት የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ የደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ የቀረቡትን ክርክር ከሰማ በኃላ ከመዝገብ ጋር በማጣመር በመዝገብ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት ይግባኝ ባይ (ተጠሪ) እጩ ተወዲደሪ ሆነው ሉመዘገቡልኝ ይገባል የሚላቸው ግለሰቦች የፓርቲ አባል በነበሩበት አንድነት ለፍትህና ዱሞክራሲ ፓርቲ (አመልካች) መተዲደሪያ ደንብ መሰረት አቤቱታ አቅርበው የተሰናበቱ ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም። እንደዚሁም የይግባኝ ባይ (ተጠሪ) አባል ለመሆን መጠበቅ የሚገባቸውን ጊዜ ያህል ጠብቀው በመተዲደርያ ደንቡ መሰረት አባል ስለመሆናቸው ያቀረበው ማስረጃ የለም።
ስለሆነም መርዓዊና ገርጨጭ ምርጫ ክልል ቢሮ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት የለም በማለት የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በእጩ ተወዲዲሪነት ያቀረባቸው ሰዎች የላላ ፖለቲካ ድርጅት አባል ለፍትህና ዱሞክራሲ ፓርቲ (አመልካች) የነበሩ ቢሆንም በማናቸውም ጊዜ አባልነት መብታቸውን በመተው የላላ ፖለቲካ ድርጅት አባል የመሆን መብት አላቸው። ስለዚህ ተቃውሞ የቀረበባቸው ሰዎች ለፍትህና ዱሞክራሲ ፓርቲ (አመልካች) አባላት የነበሩ ቢሆንም የሰማያዊ ፓርቲ አባልና እጩ ተወዲዲሪ የመሆን መብት አላቸው። ተቃውሞ የቀረበባቸውን ሰዎች በአባልነት የተቀበላቸውና ዕጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ሰማያዊ ፓርቲ ግለሰቦቹ በፓርቲው መተዲደሪያ ደንብ የተደነገገውን ስድስት ሳምንት የመጠበቂያ ጊዜ ሳይቆዩ የፓርቲው ሙለ አባልና እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ማቅረብ እንደሚችል በመተዲደሪያ ደንቡ የተደነገገ በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የመርዓዊናገርጨጭ ምርጫ ክልል ቢሮ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ግለሰቦቹ በእጩነት አይመዘገቡም በማለት የሰጡትን ውሳኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ሽሮ ግለሰቦቹ ተጠሪን ወክለው በምርጫ ለመወዲደር ይመዝገቡ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች መጋቢት 25 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ግለሰቦች የአመልካች አመራርና አባላት የነበሩ ናቸው። ተጠሪ ግለሰቦቹ የአመልካች አባልነታቸውን የተውት መሆኑን ለአመልካችና ለሕዝብ አሳውቀው የለቀቁ መሆኑን ሳያረጋግጥ የላላ የፖለቲካ ድርጅት እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ አቅርቧል። ተጠሪ እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ሰዎች በአመለካች ያላቸውን አባልነት መብት በፈቃዲቸው የተውት ስለመሆኑ በጽሁፍ አላሳወቁም። አንድ ፓርቲ አባል በአባልነትና በአመራርነት ሲሳተፍ ለነበረበት ፖለቲካ ድርጅት ሳያሳውቅ የላላ ፖለቲካ ድርጅት አባል ነኝ ብል እንዲሻው በልላ ፖርቲ አባልነት መመዝብና የላላ ፓርቲ እጩ ሆኖ መቅረብ አይችልም። በመሆኑም የአመልካችን አባላት ተጠሪ በተወዲዲሪነት ለማቅረብ ህጉ እንደሚፈቅድለት በመግለጽ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በድምጽ ብልጫ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ደርሶት ሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የመምረጥና የመመረጥ መብት ሕገ መንግስታዊ ዕውቅና የተሰጠው መብት ነው።
ማንኛውም ሰው የፖለቲካ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስፈልገውን መሰፈርት እስካሟላ ድረስ በፍላጎቱ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት አባል ለመሆን ይችላል። በመሆኑም አመልካች የላላ ፖለቲካ አባል የነበረን ሰው ከነበረበት የፖለቲካ ድርጅት በአግባቡ ሳይሰናበት የላላ ፖለቲካ ድርጅት አባል ለመሆንና እጩ ተወዲዲሪ ሆኖ ለመቅረብ አይችልም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህገ መንግስቱን ድንጋጌ የሚቃረን ነው። ተጠሪ እጩ ተወዲዲሪ ያደረጋቸው ሰዎች የተጠሪ መተዲደሪያ ደንብ ያሰቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነዋል። ሰዎቹ ከዚህ በፉት የላላ የፖለቲካ ድርጅት አባል የነበሩ መሆናቸው የተጠሪ አባላት ከመሆን አይገድባቸውም። እንደዚሁም የአመልካች ክርክር ተጠሪ እጩ ተወዲዲሪ ያደረጋቸው ሰዎች የፖለቲካ ድርጅት አባልነታቸውን በማናቸውም ጊዜ የመተው መብት ያላቸው መሆኑንና የፖለቲካ ፓርቲው ይህንን መብት በመተዲደሪያ ደንቡ መገደብ እንደላለበት በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ የተደነገገውን ግልጽ ድንጋጌ የሚጥስ ነው።
ሰዎች ከነበራችሁበት የፖለቲካ ድርጅት በአግባቡ አልተሰናበታችሁም በሚል ህጋዊነት የላለው ምክንያት በማይፈልጉት የፖለቲካ ድርጅት በአባልነት እንዱቆዩ ሉደረጉ አይገባም።
ስለዚህ የአመልካች ክርክር ውድቅ ተደርጎ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠውን ውሳኔ እንዱያፀናልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ መስጠት አያስፈልገኝም ብሎል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ለዚህ ሰበር ችልት አመልካችና ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለጸው ሲሆን እኛም የክልለ ጠቅላይ ፍርፍ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩን በሰበር አይቶ የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩን በሰበር የማየት ሥልጣን አለው ቢባል ተጠሪ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊናገርጨጭ ምርጫ ክልል እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ሰዎች በእጩ ተወዲዲሪነት ሉመዘገቡ ይገባል በማለት የሰጠው የህግ ትርጉምና ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ ለመወሰን ከምርጫ ሂደት የሚቀርቡ አቤቱታዎች ስለሚስተናገደበት ሥርዓትና ጉዲዩን በዲኝነት አይተው ውሳኔ የመስጠት የዲኝነት ሥልጣን ስላላቸው የክልልና የፋዳራል ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 532/1999 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘትና የድንጋጌቹን አቀራረጽና መሰረታዊ ባህሪ መመልከት ያስፈልጋል። በምርጫ ሂደት ስለሚነሱ አቤቱታዎች ክርክሮች አቀራረብና አወሳሰን መሰረታዊ መርሆችን የሚደነግገው የአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 92 ንዐስ አንቀጽ 6 እና ንዐስ አንቀጽ 10 የክልል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በይግባኝ አይተው የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጡባቸውን ጉዲዮች ገልጿል።
የአዋጁ አንቀጽ 93 ንዐስ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 95 ንዐስ አንቀጽ 3 እና ንዐስ አንቀጽ 5 የወረዲው ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥባቸውን ጉዲዮች በግልጽ ይደነግጋል። በእጩ ምዝገባ ሂደት አከራካሪ ጉዲይ ሲያጋጥም በመጀመሪያ ለምርጫ ክልለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታ ላቀርብ እንደሚገባውና የምርጫ ክልለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሃያ አራት ሰዓት ውሳኔ እንደሚሰጥ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 94 ከንዐስ አንቀጽ 1 እስከ ንዐስ አንቀጽ 4 ያለት ድንጋጌዎች ያሳያለ። የምርጫ ክልለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ ወይም የምርጫ ክልለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ በሰጠው ውሳኔ ያልተስማማ ወገን በሰባ ሁለት ሰዓት ውስጥ ለክልለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ሉያቀርብ እንደሚችልና ይግባኙም ለክልለ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ታይቶ ውሳኔ ሰለሚሰጥበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር. 532/1999 አንቀጽ 94 ከንዐስ አንቀጽ 5 እስከ ንዐስ አንቀጽ 10 ባለት ድንጋጌዎች ተደንግጓል።
የክልለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በይግባኝ አይቶ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባለት አርባ ስምንት ሰዓታት ማቅረብ እንደሚችልና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆን በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 94 ንዐስ አንቀጽ 11 ይደነግጋል። ከላይ የገለጽናቸው የአዋጅ ቁጥር 532/1999 ድንጋጌዎች ሕግ አውጭው የክልለ ፍርድ ቤቶች በይግባኝ አይተው የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጡባቸውን ክልላዊ ባሕሪ ያላቸውን ጉዲዩች በግልፅ በመደንገግ ለክልል ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ የይግባኝ የዲኝነት ሥልጣን የሚሰጡ ናቸው። አዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 92 ንዐስ አንቀጽ 6 በላልች ጉዲዮች የሚቀርቡ የምርጫ አቤቱታዎች ሰምቶ የመወሰን የዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች መሆኑን ይደነግጋል። ከላይ የገለጽነው የህጉ ድንጋጌዎች አቀራረጽ የክልል ፍርድ ቤቶች በይግባኝ አይተው የመጨረሻ ውሳኔ እንዱሰጡባቸው በአዋጁ በግልጽ ያልተደነገጉ ቀሪ የዲኝነት ስልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ነው የሚለውን መርህ የሚያራምድ ነው።
ይህም ለክልለ ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 532/1999 በግልጽ ተለይቶ የተሰጣቸው የዲኝነት ሥልጣን ክልላዊ ባህሪ ያላቸውና በክልል ፍርድ ቤቶች በይግባኝ ታይተው የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጡባቸው ሙለ በሙለ በክልለ የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚወድቁ መሆናቸውን ያሳያል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ሥልጣን እንዲለው በኢ/ፋ/ዱ/ሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ለ) ተደንግጓል። በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 93 ንዐስ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 95 ንዐስ አንቀጽ 3 እና ንዐስ አንቀጽ 5 መሰረት የወረዲው ፍርድ ቤት በይግባኝ አይቶ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥባቸውን ጉዲዩችና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአንቀጽ 94 ንዐስ አንቀጽ 11 መሰረት ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ወገን የሰበር አቤቱታውን በመጀመሪያ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ማቅረብ እንዲለበት ከሕግ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ለ) እና የተሻሻለው የክልለ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሐ/ ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ አንፃር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ጉዲዩን በሰበር የማየት ስልጣን አለኝ በማለት ጉዲዩን አይቶ መወሰኑ ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በሁለተኛነት የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ለአመልካችና ለተጠሪ ክርክር መነሻ የሆኑትንና በየደረጃው ባለ የምርጫ አቤቱታና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባለው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና በህገ መንግስቱ ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ የተሰጠው የመምረጥ፣ የመመረጥና የመደራጀት መብት መሰረታዊ ይዘት፣ መብቶቹ ተግባራዊ ለማድረግ የወጡ ዝርዝር ህጎች መሰረታዊ ግብ፣ እነዚህን መብቶች ተግባራዊ በሚደረጉበት ጊዜ ግለሰቦችም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ሉያሟሎቸው የሚገቡ ዝቅተኛ መስፈርቶች ወይም ቅድመ ሁኔታዎችና ግለሰቦች ወይም የፖለቲካ ድርጅቶቹ ሉያሟሎቸው የሚገቡ ዝቅተኛ መስፈርቶች ወይም ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላታቸው የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊና ገርጨጭ ምርጫ ክልል እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ሰዎች፣ ከዚህ በፉት አመልካች አባልና አመራር የነበሩ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ በምርጫ ክልልቹ እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ሰዎች እስከቀርብ ጊዜ ድረስ የአመልካችን የፖለቲካ ተልዕኮ ሲያስፈጽሙ የነበሩ መሆኑን ተጠሪ ማስተባብያ ያላቀረበበት ዕውነታ መሆኑን ተረድተናል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ሰዎች የተጠሪ እጩ ሆነው ከመቅረባቸው በፉት አባልና አመራር ሆነው ለኖሩበት የፖለቲካ ድርጅት ማለትም አመልካች የድርጅቱ አባል ሆነው የማይቀጥለና አባልነታቸውን በፈቃዲቸው የተው ስለመሆናቸው በጽሁፍ ያሳወቁ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ያላቀረቡ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማናቸውም አይነት ልዩነት ሳይደረግበት በቀጥታ እና በነፃነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በህዝብ ጉዲይ አስተዲደር የመሳተፍ፣ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላው በህግ መሰረት የመምረጥ፣ በማናቸውም የመንግስት ደረጃ በየጊዜው የመምረጥና የመመረጥ መብት ያለው መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 38 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ ማናቸውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት ያለው መሆኑ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 31 ተደንግጓል። እንደዚሁም የፖለቲካ ድርጅቶች በሰራተኞች ፣ በንግድ፣ በአሰሪዎችና በሙያ ማህበራት ለመሳተፍ ድርጅቱ የሚጠይቀውን ጠቅላላና ልዩ የአባልነት መስፈርት የሚያሟላ ማናቸውም ሰው በፍላጎቱ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ መሆን ያለበት መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 38 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። እነዚህ በህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች የዜጎች የመምረጥ የመመረጥና የፖለቲካ ድርጅት የመመስረትና የፖለቲካ ድርጅት አባል የመሆን መብትን ጨምሮ ላልች የመደራጀት መብቶች ዕውቅናና ጥበቃ የሚሰጡ የህገ መንግስት ድንጋጌዎች ናቸው።
ከላይ የተገለጹት ህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መብቶቹን በጥቅል አገላለጽ የሚደነግጉ በመሆናቸው ማናቸውም ዜጋ የመምረጥ፣ የመመረጥና የመደራጀት መብት ዝርዝር ይዘትና መብቶቹ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ስርዓቶች አካትተው የሚይዙ አይደለም። ከህገ መንግስቱ መብቶቹን በመርህና በጥቅለ ከመደንገግ አልፍ የመብቶቹን ዝርዝር ይዘትና መብቶቹ ተፈፃሚ የሚሆኑበትን ስርዓት በዝርዝር እንዱደነግግ አይጠበቅበትም። ይህም በመሆኑ ዜጎች በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን የመምረጥ፣ የመመረጥና የመደራጀት መብት የሚዘረዝሩ፣ መብቶቹ ተፈፃሚ የሚሆኑበትን ስርዓትና መብቶቹን ተግባራዊ በሚደረጉበት ጊዜ ግለሰቦችም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ሉያሟላቸው የሚገቡ ዝቅተኛ መስፈርቶች ወይም ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር የሚያስቀምጡ ላልች ህጎች ማለትም አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ የተለያዩ የህግ ማዕቀፍች ወጥተው ስራ ላይ ውለዋል።
ከላይ የተገለጹትን የዜጎች መሰረታዊ የመምረጥ የመመረጥና የመደራጀት መብት ተግባራዊ ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ ወጥተው ስራ ላይ ከዋለት የህግ ማዕቀፍች የተሻሻለው የኢትዮጵያ ምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 የመጀመሪያው ተጠቃሽ ነው። ህግ አውጭው አዋጁን በማወጅ ለማሳካት ከሚያስባቸው ግቦች መካከል፣ የተለያየ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሳተፈበትና ዓላማቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመራጩ ህዝብ የሚገልጹበት መራጩ ህዝብም በመረጃ ላይ በመመስረት ፈቃደን በነፃት በመግለጽ ወኪልቹን የሚመርጥበትን የምርጫ ስርዓት መዘርጋት፣ በምርጫው ተሳታፉ የሚሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ የግል እጩዎች ለፍታሀዊ ሰላማዊ ነጻና ዱሞክራሳዊ የምርጫ ስርዓት መስፈን ገንቢ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበትን ግልጽ አሰራር መዘርጋትና ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ነጻ ገለልተኛና ፍታሀዊ ምርጫ በማካሄድ በህዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግስት እንዱቋቋም ማድረግ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 532/1999 መግቢያ አራተኛውና አምስተኛው ፓራግራፍና ከአዋጁ አንቀጽ 3 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
ከላይ የተገለጹትን ህገ መንግስት መሰረታዊ መብቶች ተፈፃሚ ለማድረግ የወጣው ላላው የህግ ማዕቀፍ የፖለቲካ ፓሪቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ነው። በዚህ አዋጅ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ድርጅት ማለት ከህብረተሰቡ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎችን በማሰባሰብ የራሱን የፖለቲካ እምነትና ዓላማ የሚያንጸባርቅ ፕሮግራም በማውጣት በሀገር አቀፍ ወይም በክልል የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፍ በዳሞክራሳዊ ስርዓት የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ በአዋጁ መሰረት የተቋቋመና የተመዘገበ ልዩ ባህሪና ተልዕኮ ያለው ማህበራዊ ተቋም እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶታል። ህግ አውጭው አዋጅ ቁጥር 573/2000 ያወጀው በህገ መንግስቱ መሰረት ዜጎች የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው በሰላማዊና ህጋዊ የፖለቲካ እንቅሳቄሴ በመሳተፍ የሚይዙበትን ሁኔታ በህግ ለመደንገግ፣ ዜጎች የፖለቲካ ፓርቲ ሲመሰርቱና በአባልነት ሲንቀሳቀሱ ስለሚኖራቸው መብትና ግዳታ እንዱሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሉከተሎቸው ስለሚገቡ መርሆች ለመደንገግና የፖለቲካ ፓርቲዎች በመዋሃድ ወይም ግንባር በመፍጠር ወይም በመቀናጀት ሉንቀሳቀሱ የሚችለበትን ሁኔታ ግልጽ ለማድረግ እንደሆነ በመግቢያው በግልጽ አስቀምጧል።
በህገ መንግስቱ አንቀጽ 38 ንዐስ አንቀጽ 1 አንድ ዜጋ በማናቸውም የመንግስት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄደው ምርጫ በተመራጭነት ለመቅረብና በህገ መንግስቱ የተረጋገጠለትን የመመረጥ መብት ለመጠቀም ሉያሟላቸው የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በዋናነት በአዋጅ ቁጥር 532/1999 ከአንቀጽ 44 እስከ አንቀጽ 57 ተደንግጓል። በተለይም የአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 45 እና አንቀጽ 46 እጩዎች በህግ የተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት ወይም በግላቸው ተወዲዲሪ ሆነው ለመቅረብ የሚችለበትን ህጋዊ ሁኔታ በዝርዝር ያስቀምጣለ።
የአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 የፖለቲካ ድርጅት በመወከል ወይም በግላቸው ተወዲዲሪ ለእጩነት የሚቀርቡ ሰዎች ሁለም በጋራ ሉያሟላቸው የሚገቡና ለእጩነት የሚያበቁ መመዘኛዎች የሚደነግጉ ናቸው። አዋጁ ቁጥር 532/1999 የአንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 3 በግል እጩ ሆኖ የሚቀርብ ተወዲዲሪ በልዩ ሁኔታ ሉያሟላው ስለሚገባው ተጨማሪ መስፈርት፣ ማለትም በግል እጩ ሆኖ ለመቅረብ በምርጫ ክልለ ኗሪ የሆኑ ከአስራ ስምንት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውና የመምረጥ መብታቸውን ያልተከለከለ ከአንድ ሺ የማያንሱ ሰዎች የድጋፍ ፊርማ የግል ተወዲዲሪው የማቅረብ ግዳታ ያለበት መሆኑን ይደነግጋል።
የፖለቲካ ድርጅት ወክለው የሚቀርቡ እጩዎች ከግል ተወዲዲሪዎች በተለየ ሁኔታ የሚያሟላቸው ተጨማሪ መስፈርቶች አለ የሚባል ከሆነ መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው?
በተለይም የላላ የፖለቲካ ድርጅት አባላት የነበሩ ሰዎችን በእጩ ተወዲዲሪነት ያቀረበ የፖለቲካ ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 46 መሰረት የላላ የፖለቲካ ድርጅት አባላት የነበሩ ሰዎች እጩ አድርጎ ሲያቀርብ ሉያረጋግጣቸውና በማስረጃ አስደግፍ ሉያቀርባቸው የሚገቡት ተጨማሪ ፍሬ ጉዲዮች ወይም መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
የፖለቲካ ድርጅት ወክለው የሚቀርቡ እጩዎች ተጨማሪ መስፈርቶቹን ባያሟለ ህጋዊ ውጤቱ ምንድን ነው? የሚለት ናቸው።
ከላይ የተገለጹትን ጥያቄዎች ለመመለስ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 ከአንቀጽ 44 እስከ አንቀጽ 57 የተደነገጉትንና ላልች የአዋጁን ድንጋጌዎች መመልከት ብቻውን በቂ አይደለም። በአንፃሩ በመጀመሪያ ደረጃ የእነዚህን ድንጋጌዎች ይዘት ህግ አውጭው አዋጅ ቁጥር 532/1999 ካወጀበት መሰረታዊ ምክንያትና በአዋጁ ሉያሳካቸው ከሚፈልጋቸው ግቦች ጋር በጣምራ መመርመርና ለድንጋጌዎቹ ትርጉም መስጠት ይጠይቃል። በሁለተኛ ደረጃ የአዋጅ ቁጥር 532/1999 ድንጋጌዎች፣ ህግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 573/2000 ለፖለቲካ ፓርቲ ከሰጠው ትርጓሜ፣ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ካወጀበት መሰረታዊ ግብና ዓላማ ከአዋጁ ድንጋጌዎች ይዘት ጋር ማገናዘብና ህግ አውጭው እነዚህን የህግ ማዕቀፍች በማሟላት ሉያሳካው ከፈለገው መሰረታዊና አገራዊ ግብ አንፃር ጉዲዩን መመርመርና የህግ ትርጉም መስጠት ያስፈልጋል።
ከዚህ አንፃር ስናየው አዋጁ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 1 እስከ ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች መሰረት የፖለቲካ ድርጅቶች እጩ ተወዲዲሪ አድርገው የሚያቀርቧቸው ሰዎች፣ አዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ከተደነገጉት መመዘኛዎች በተጨማሪ፣ የፖለቲካ ድርጅቱን ወክለው በእጩነት ለመቅረብ በልዩ ሁኔታ ሉያሟለ የሚገባቸው ተጨማሪ መስፈርቶች ያለ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። የፖለቲካ ድርጅቱን ወክለው በእጩነት የሚቀርቡ ሰዎች በልዩ ሁኔታ የሚያሟለት መስፈርት እጩ ተወዲዲሪዎቹ በህግ አግባብ የተመዘገቡና በእጩነት ያቀረባቸው የፖለቲካ ፖርቲ አባላት መሆን ያለባቸው መሆኑን ከአዋጁ ቁጥር 573/2000 መግቢያ፣ አዋጅ 573/2000 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 6 ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
የፖለቲካ ድርጅቶች ወክለው የሚቀርቡ እጩዎች በግላቸው እጩ ሆነው በተወዲዲሪነት እንዱሚቀርቡ ዜጎች የሚወዲደሩበት የምርጫ ክልል ኗሪዎች የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው እንዱያቀርቡ በህጉ የማይጠየቁት በእጩነት የወከላቸው የፖለቲካ ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 6 የሚጠይቀውን የመስራች አባላት ድጋፍና ድምጽ በማሟላት የተመዘገበ መሆኑን ህግ አውጭው ከግንዛቤ በማስገባቱ ነው። ህግ አውጭው ፖለቲካ ድርጅቶቹን ወክለው የሚቀርቡ ተወዲዲሪዎች የመራጭ ድጋፍ የማሰባሰብ ግዳታ እንዲይኖርባቸው ያደረገው የፖለቲካ ድርጁቱን በመወከል በእጩነት የሚቀርቡት ሰዎች ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟለ የፓርቲው ትክክለኛ አባላት ይሆናለ በሚል ዕምነት እንደሆነ፣ የአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 45 እና አንቀጽ 46 ድንጋጌዎችና የአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 6 ድንጋጌዎች በጣምራ በማየት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ አንጻር የፖለቲካ ድርጅቶች ወክለው የሚቀርቡ እጩዎች ሁለንም ህጋዊ ሁኔታዎች አሟልተው በእጩነት የሚወክለት የፖለቲካ ድርጅት አባላት መሆን አለባቸው።
የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያየ አመለካከት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍልች የሚወክለ፣ የራሳቸው የሆነ የፖለቲካ ፕሮግራምና ዓላማ ያላቸው፣ የፖለቲካ ዓላማቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለማሳካትና በምርጫ የመራጩን ህዝብ ዓመኔታ፣ ድጋፍና ድምጽ አግኝተው፣ የመንግስት ስልጣን ለመያዝ የሚወዲደሩ ለየት ያለ ባህሪና ተልዕኮ ያላቸው ማህበራዊ ተቋማት መሆናቸው በሁለቱም አዋጅዎች በግልጽ ተደንግጓል። ይህም በመሆኑ አንድ ሰው በአንድ ጊዜ የአንድ የፖለቲካ ፕሮግራምና ዓላማ ያለው ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅት አባል የመሆን መብት ይኖረዋል። ከዚህ አሰራር በሚቃረን ሁኔታ አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ የሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል የመሆን መብት እንደላለው ከአዋጅ ቁጥር 573/2000 መግቢያ፣ ከአዋጁ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2፣ አንቀጽ 13፣ አንቀጽ 14ና አንቀጽ 15 ድንጋጌዎች ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል።
በአዋጁ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባል የነበረ ሰው አባል ሆኖ የተደራጀበትን የፖለቲካ ድርጅት አባልነት መብት የሚያጣው በሁለት መሰረታዊ ሁኔታዎች መሆኑን በአዋጁ ቁጥር 573/2000 በምዕራፍ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት መብትና ግዳታ በሚል ርዕስ ከአንቀጽ 28 እስከ አንቀጽ 31 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመመልከት ለመረዲት ይቻላል። የመጀመሪያው በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 30 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲው በመተዲደሪያ ደንቡ መሰረት ከአባልነት እንዱወገድ ሲወሰንበት መሆኑ ተደንግጓል። ፓርቲው አባለ ከፖለቲካ ድርጅት አባልነቱ እንዱወገድ የተወሰነበት ከፓርቲው መተዲደሪያ ደንብ ውጭ ነው ብል የሚያስብ ከሆነ ከፖለቲካ ድርጅት አባልነት እንዱወገድ የተሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማቅረብ መብት ያለው መሆኑ አንቀጽ 30 ንዐስ አንቀጽ 2 በግልጽ ተደንግጓል።
ሁለተኛው የፓለቲካ ፓርቲ አባል የሆነ ሰው የፓርቲው አባል መሆኑ ቀሪ የሚሆንበት መንገድ አባለ በአዋጁ አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 3 የተሰጠውን የፓለቲካ ፓርቲ አባልነት የመተው መብቱን ተጠቅሞ የፓለቲካ ድርጅት አባልነቱን ሲተወው መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት ለመረዲት ይቻላል።እዚህ ላይ መታየት ያለበት አንድ ሰው የፓለቲካ ፓርቲ አባልነቱን በፈቃደ ትቷል የሚባልበት ህጋዊ መስፈርት ምንድን ነው የሚለው ነጥብ ነው። አንድ ሰው የፓለቲካ ፓርቲ አባልነቱን በፈቃደ ትቷል የሚባለው በማያሻማ ሁኔታ የፓርቲ አባልነቱን በፈቃደ የተወው መሆኑን ለፓርቲው ሲያሳውቅ እንደሆነና አንድ ሰው የፓርቲ አባልነቱን በማያሻማ ሁኔታ ገልፆ ትቷል ለማለት አባል የሆነበት የፓለቲካ ድርጅት፣ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 12 መሰረት አቅርቦ ባስመዘገበውና በጸደቀው የፓለቲካ ድርጅት መተዲደሪያ ደንብ መሰረት አባልነቱን በፈቃደ የተወው መሆኑን ሲያሳውቅ እንደሆነ የአዋጁን አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 3 ፣አንቀጽ 15 ንዐስ አንቀጽ 1(ለ) እና አንቀጽ 12 ድንጋጌዎች ጋር በጣምራ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል።
ይህም የአንድ የፓለቲካ ፓርቲ አባል የሆነ ሰው የፓለቲካ ድርጅቱ የአባልነት መብት በፈቃደ የተወው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በአባልነት ለሚሳተፍበት የፓለቲካ ድርጅት መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ሳይገልፅና ሳያሳውቅ፣ በአባልነት ስሳተፍበት የነበርኩትን የፓለቲካ ፓርቲ አባልነት በፈቃዳ ትቼ የላላ ፓለቲካ ድርጅትአባል ሆኛለሁ ስለዚህ ለሁለተኛ ጊዜ የተደራጀሁበትን የፓለቲካ ድርጅት ፓርቲ ወክየ በእጩነት ለመመዝገብና ለመወዲደር እችላለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር ከላይ የገለጽናቸውን የፓለቲካ ድርጅት የአባልነት መብት ሉቋረጥ ስለሚችልባቸው ሁለት መሰረታዊ ሁኔታዎችና የአዋጅ ቁጥር 573/2000 ድንጋጌዎች መስፈርት የማያሟላና የህግ መሰረት የላለው ክርክር ነው።
ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊና ገርጨጭ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለአማራ ክልል ምክር ቤት እጩ ተወዲዲሪ አድርጎ ያቀረባቸው ግለሰቦች፣ አንድነት ለፍትህና ለዳሞክራሲ በመባል የሚታወቀው የፓለቲካ ድርጅት(አመልካች)አባል መሆናቸው ተረጋግጧል። ተጠሪ ግለሰቦቹን በእጩነት አቅርቦ ለማስመዝገብ ጥያቄ ሲያቀርብ ሰዎች አባል ከሆኑበት የፓለቲካ ድርጅት(አመልካች)በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 30 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በዱስፒሉን ጥፊት ከአባልነት የተወገደ ወይም አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 12 መሰረት አመልካች ለብሓራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቦ ባስመዘገበውና ባጽደቀው የፓለቲካ ድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብ የተቀመጠውን ግልጽ መስፈርት በማሟላት የአመልካች አባልነቻቸውን የተውት መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።ይህም ማለት ተጠሪ እጩ አድርጏ ያቀረባቸው ግለሰቦች በአባልነት ለተደራጁበት አመልካች አባልነታቸውን በፈቃዲቸው የተውት ስለመሆኑ በጽሐፍ ያሳወቁ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 46 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት አያይዞ በማቅረብ የማስረዲት ግዳታ አለበት።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ በእጩነት ያቀረብኳቸው ሰዎች የአመልካች አባል ሆነው መቀጠል እንደማይፈልጉ በጽሐፍ በአመልካች መተዲደሪያ ደንብ መሰረት አሳውቀዋል የሚል መከራከሪያ አላቀረበም። ተጠሪ የሚከራከረው በእጩነት ያቀበረብኳቸው የአመልካች አባል ሆነው መቀጠል እንደማይፈልጉ በጽሐፍ በአመልካች መተዲዲሪያ ደንብ መሰረት ባያሳውቁም ግለሰቦቹን የተጠሪ አባልና እጩ ከመሆን የሚከለክላቸው ህግ የለም በማለት ተከራክሯል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አብላጫው ድምፅ ይህንን የተጠሪን ክርክር በመቀበል ማናቸውም ሰው አባል ሆኖ በተደራጀበት የፓለቲካ ድርጅት መተዲዲሪያ ደንብ መሰረት የድርጅት አባልነት መብቱን የተወው መሆኑን በጽሐፍ ሳያሳውቅ የላላ የፓለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ ከተመዘገበና የላላ የፓለቲካ ድርጅት እጩ ሆኖ ከቀረበ በፉት ተደራጅቶ ሲሳተፍበት የነበረውን የፓለቲካ ድርጅት የአባልነት መብቱን እንደተወው ይቆጠራል፣ በዚህ መንገድ ለምንም ቅድመ ሁኔታ ቀድሞ አባል የሆነበት የፓለቲካ ድርጅት አባልነት በመተው ለላላ ፓለቲካ ድርጅት አባልና እጩ ተወዲዲሪ መሆን ይችላል በማለት የህግ ትርጉም ውሣኔ ሰጥቷል።
ሆናም ይህ ትርጉም ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 መሰረት የአንድ ሰው ተደራጅቶበት በነበረው የፓለቲካ ፓርቲ አባልነት መብት ቀሪ የሚሆነው በአዋጁ አንቀጽ 30 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በዱስፒሉን ጥፊት በአባልነት ሲወገድ ወይም አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 12 መሰረት በተመዘገበው የድርጅቱ መተዲዲሪያ ደንብ መሰረት የአባልነት መብቱን የተወው መሆኑን ግልፅ አድርጎ በጽሐፍ ሲያሳውቅ ብቻ መሆኑን ያገናዘበ አይደለም። አንድ ሰው በአባልነት የሚሳተፍበት የፓለቲካ ፓርቲ መተዲዲሪያ ደንብ በሚደነግገው መሰረት የአባልነት መብቱን በፈቃደ የተወው መሆኑን ግልፅ አድርጎ በጸሐፍ ሳያሳውቅ የላላ ፓለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ ተመዝግቦ መገኘቱ በመጀመሪያ ተደራጅቶበት የነበረውን ፓለቲካ ፓርቲ አባልነት ትቶታል ከሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። በአንፃሩ ፓርቲው አባለ ከህግና ከሥርዓት ውጭ ከአንደኛው የፓለቲካ ድርጅት ጋር የነበረውን የአባልነት ትስስር በሕግ አግባብ ሳያቋርጥ በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የላላ ድርጅት አባል መሆኑ በልላ አነጋገር በአንድ ጊዜ የሁለት የፓለቲካ ድርጅቶች አባል በመሆን ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚያሳይና ህጋዊ ውጤት ሉሰጠው የማይገባ አድራጏት ሆኖ አግኝተዋል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አብላጫው ድምፅ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 4 የሰጠው ትርጉምም የህጉን ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም የአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 4 ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ” የፓለቲካ ድርጅቶች መተዲዲሪያ ደንብ የዚህን ምዕራፍ ድንጋጌዎች የሚቃረን መሆን የለበትም” የሚል ይዘት ያለው ነው። ይህ ድንጋጌ የፓለቲካ ፓርቲዎች አባላቶችቻቸው በራሳቸው ፈቃድና ፍላጏት አባልነት መብታቸውን የተውት ስለመሆኑ ለፓርቲው የሚያሳውቁትን ሥርዓት በመተዲደሪያ ደንባቸውን እንዲያካትቱ የሚከለክል ድንጋጌ አይደለም። ይህም በመሆኑ ተጠሪ በእጩነት ያቀረባቸው ሰዎች አባል ሆነው የተደራጁበት የፓለቲካ ፓርቲ(አመልካች) በመተዲደሪያ ደንብ የድርጅቱ አባል ሆኖ መቀጠል የማይፈልግ አባል አባልነቱን የተወው መሆኑን ለድርጅቱ በጽሐፍ የማሣወቅ ግዳታ እንዲለበት ያስቀመጠውን ድንጋጌ ህጋዊነት የላለው ገደብ የማድረግ ይዘት የለውም።
እንደዚሁም ይህ የደንቡ ድንጋጌ አዋጅን የማስፈፀም ኃላፉነት በህግ ሥልጣን በተሰጠው ብሓራዊ የምርጫ ቦርድ ተመርምሮ በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 3 ለድርጅቱ አባላት የተሰጠውን መብት የማያጣብብ መሆኑ ተረጋግጦ በአዋጁ አንቀጽ 12 መሰረት የተመዘገበና የጸደቀ ነው።
በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አብላጫው ድምፅ አመልካች በመተዲደሪያ ደንቡ ያስቀመጠው አባልነት መቀጠል የማይፈልግ የድርጅቱ አባል ይህንኑ በጽሐፍ የማሳወቅ ግዳታ ያለበት መሆኑን በመተዲደሪያ ደንቡ ያስቀመጠው መስፈርት በአዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀጽ 31 ንዐስ አንቀጽ 4 የሚጥስ ነው በማለት የሰጠው የህግ ትርጉም ከላይ የገለፅናቸውንና ሕግ አውጩው በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 54 ንዐስ አንቀጽ 2 የደነገገውን መስፈርት ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር ከተገለፁት የህግ ትንተናዎች በተጨማሪ የህዝብ ለዓላዊ ስልጣን በምርጫ ተወዲድሮ ለማሸነፍና ለመረከብ በህጋዊ መንገድ በተቋቋመ የፓለቲካ ፓርቲ አባል የሆነ ሰው፣ አባል ሆኖ ለኖረበት ፓርቲ ሳያሳውቅ የላላ ፓለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ የመመዝገብና በእጩነት የመቅረብ መብት አለው፣ የላላ የፓለቲካ ድርጅት አባል የነበረን ሰው በአባልነት የሚመዘግብና በእጩነት የሚያቀርበው የፓለቲካ ድርጅት አባል ለመሆን የተቀበለውና እጩ ያደረገው ሰው አባል ሆኖበት ከነበረው የፓለቲካ ድርጅት ጋር የነበረውን የፓለቲካ ትስስር ለመተው ያለውን ፍላጏት በግልፅ ያሳወቀ መሆኑን ሳያረጋግጥ አባል አድርጏ መመዝገብና በእጩ ተወዲዲሪነት ማቅረብ ይችላል በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አብላጫው ድምፅ የሰጠው ትርጉምና ውሣኔ ሕግ አውጭው በሁለት አዋጆች የተለያየ አመለካከት ያላቸው የፓለቲካ ድርጅቶች የሚሳተፈበትና ዓላማቸውን በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለመራጩ ሕዝብ የሚገልጹበት መራጩ ህዝብም በመረጃ ላይ በመመስረት ፈቃደን በነፃነት በመግለፅ ወኪልቹን የሚመርጥበት ሥርዓት ለመዘርጋት ያሰበውን ዓላማና ላልች ከላይ የገለፅናቸውን መሰረታዊ ግቦች የሚያሳካ አይደለም።
በተቃራኒው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አብላጫው ድምፅ የተከተለው አተረጓጏም በምርጫ ወቅት የአንደኛው የፓለቲካ ድርጅት አባላት አባል ለሆኑበት የፓለቲካ ድርጅት አባልነታቸውን የተውት መሆኑን ሳያሳውቁ፣ የፓለቲካ ድርጅታቸውን የሚከደበትና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዘልለው በመሄድ የላላ የፓለቲካ ድርጅት አባልና እጩ ሆነው የሚቀርቡበትን አሰራር የሚያበረታታ ነው። ይህ አሰራር ህጋዊ እውቅና ከተሰጠው በፓለቲካ ድርጅቶችና በአባላቶቻቸው መካከል መተማመን እንዲይኖር የሚደረግ፣ የፓለቲካ ድርጅቶች የአባልነት መብታቸውን በፈቃዲቸው የተውትንና በአባልነት ለመቀጠል ቁርጠኛ የሆኑትን ለመለየት የሚያስችለው ማስረጃ ኖሮት የምርጫ ዝግጅት እንዲያደርግ እንቅፊት የሚፈጥር፣ በፓለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት አንደኛው የፓለቲካ ፓርቲ አባላትና እጩ የፓለቲካ ድርጅቱ ሳይሰማና ሳያውቅ ላላው የፓለቲካ ድርጅት በማስከዲት ወይም በመቀበል በሰዓታትና በቀናት ልዩነት የራሱ አባልና እጩ አድርጏ እንዱያቀርብ ሰፉ እድል የሚፈጥርና በፓለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚኖረው ግንኙነት በጥራጣሬና በሽኩቻ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የሚያደርግ ነው። ይህም ሕግ አውጭው በህገ መንግስቱ መሰረት ዜጏች የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው በሰላማዊና ህጋዊ የፓለቲካ እንቅስቃሴ በመሳተፍ የመንግስት ስልጣን የሚይዙበትን ሁኔታ ለማረጋገጥና በፓለቲካ ድርጅቶች መካከል እንዱኖር የሚፈልገውን ሰላማዊና ፍትሐዊ ህጋዊ የፓለቲካ ውድድር በእጅጉ የሚጎዲና በአዋጅ ቁጥር 632/2002 አንቀጽ 7 የተደነገገው የምርጫ ሕግ ማክበር ግዳታ የሚሰጥና በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀጽ 102 ንዐስ አንቀጽ 4(ለ) ማንኛውም የፓለቲካ ድርጅት በምርጫ ከሚወዲዲሩ ላልች የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር መልካም ግንኙነት እንዱፈጥር የተጠቀመውን የሥነ ምግባር ግዳታ ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው።
በምርጫ ወቅትና ከተመረጡ በኋላ የፓለቲካ ድርጅቶች አባላት የሚፈጽሙትን የክዲት ተግባር ለመቆጣጠርና ለማስቀረት የዲበረ ዱሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው እንደ እስራኤል ያለ ላልች አገሮች በሕገ መንግስታቸውና በላልች የሕግ ማዕቀፍች ከልካይ የሆኑና ይህንን ተግባር በሚፈፅሙ ላይ ተጠያቂነት የሚያስከትለ የህግ ድንጋጌዎችን በመደንገግ ተግባራዊ አድርገዋል። እኛም አገር የምርጫና የፓለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ አዋጆች የአንድ የፓለቲካ ድርጅት አባል የነበሩ ሰዎች አባል ሆነው ለተደራጁበት የፓለቲካ ድርጅት አባልነታቸውን መቀጠል የማይፈልጉ ስለመሆኑ ሳያሳውቁና አባል ከሆኑበት የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር የነበራቸውን ትስስር በህግ አግባብ ለማቋረጥ ያላቸውን ሀሳብ ሳይገልፁና በምርጫ ወቅት ዘለው የላላ ፓለቲካ ድርጅት አባልና እጩ ሆነው የሚቀርቡበትን ሁኔታ በሚፈቅድና በሚያበረታታ መንገድ ታልመው የታወጁ አለመሆናቸውን ከላይ በዝርዝር የገለፅናቸው የህግ ማዕቀፍቹን ድንጋጌዎች ይዘቶችና መሰረታዊ ዓላማዎች በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች ተጠሪ የላላ ፓለቲካ ድርጅት(አመልካች) አባልነታቸውን በህግ አግባብ እንዱቋረጥ በጽሐፍ ያላሳወቁ የላላ ፓለቲካ ድርጅት አባል የሆኑ ሰዎች ተወዲዲሪ አድርጏ እንዱያቀርብ አዋጅ ቁጥር 532/199 አንቀጽ 46 እና አንቀጽ 102 ንዐስ አንቀጽ 4(ለ) የማይፈቅድለትና አድራጏቱም በአዋጅ ቁጥር 662/2002 አንቀጽ 7 ተደነገገውን ሕግ ማክበር ግዳታ የሚሰጥ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ተጠሪ ያቀረባቸው እጩ ተወዲዲሪዎች እንዱመዘገቡ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ እጩ አድርጏ ያቀረባቸው ግለሰቦች በህግና አባል በሆኑበት የፓለቲካ ድርጅት መተዲዲሪያ ደንብ የተጣለባቸውን አባልነታቸውን የተውት መሆኑን በጽሐፍ የማሳወቅ ዝቅተኛ መስፈርት ያላሟለ በመሆኑ ወይም በአባልነት ተደራጅተውበት የነበረው የፓለቲካ ድርጅት በዱስፒሉን ጥፊት ከባልነታቸው እንዱሰረዙ የሰጠው ውሣኔ የላለ በመሆኑ አሁንም ቢሆን የላላ ፓለቲካ ድርጅት አባላት ናቸው። ከዚህ አንፃር አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የሁለት የፓለቲካ ድርጅት አባል ለመሆን የማይችል በመሆኑ ተጠሪ ግለሰቦቹ በድርጅቱ መተዲዲሪያ ደንብ የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው ስላገኘኋቸው በአባልነት ተቀብያቸዋለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር የሕግ መሰረት ያለው አይደለም፣ ከላይ በዝርዘር በተቀመጡት ምክንያቶች የአማራ ክልል ሰበር ችልት ተጠሪ በእጩነት ያቀረባቸው የላላ ፓለቲካ ድርጅት (አመልካች)አባላት የተጠሪ እጩ ሆነው እንዱመዘገቡ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሕገ መንግሰቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ታይቶ ተሽሯል።
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ተጠሪ በደጋ ዲሞት ምርጫ ክልል እጩ አድርጎ ያቀበባቸው አቶ ግርማ ቢተው፣ አቶ መለሰ ዘለቀ፣ ወ/ሮ ይርገደ ታደገ እና አቶ ይሁኔ ጥላሁን የአመልካች ድርጅት አባላት በመሆናቸው የተጠሪ እጩ ተወዲዲሪዎች ሆነው ሉመዘገቡ አይገባም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 9 ቀን 2007 የተሰጠው የእግድ ትዕዘዝ ተነስቷል።ይፃፍ።
በዚህ ክርክር ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.