የጥብቅና ሙያ አገልግልት ክፍያ ለመወሰን በልምድ የዲበረውና በአጠቃላይ ተቀባይነት ያገኘው የአከፊፈል መርህ ጉዲዩ የወሰደው ጊዜ፣ የሚጠይቀው ድካም፣ የጉዲዩ ውስብስብነት የክርክርን ግምት ታሳቢ በማድረግ ስለመሆኑ፣ የጥብቅና ሙያ አገልግልት ክፍያ ያለምንም ገደብ ስምምነት የሚደረግበት አለመሆኑን ከስነ ህግ እና የፍርድቤቶች አሰራር የዲበረ ስለመሆኑ፣ የአብክመ የጥብቅና ስራ ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ የጠበቆች ስነ-መግባር ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 75/1994 አንቀፅ 50፣51፣52 የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 462
No summary available.
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ነገረ ፈጅ - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡- እነ አቶ ግርማ ሞገስ 8 ሰዎች - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩ ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የጥብቅና ሙያ አገልግልት ክፍያ አወሳሰን ሥርዓት የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በአብክመ ደቡብ ወል ዞን ደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በክርክር ሂደቱ ተጠሪዎች ከሳሾች አመልካች ተከሳሽ በመሆን የተሳተፈ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም አመልካች ተጠሪዎች ለጥብቅና ሙያ አገልግልት የከፈለት 40,000 እንዱከፍል ተወስኗል። ጉዲዩ በአፈፃፀም የተመለከተው ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በዋናው ፍርድ በመ/ቁ 0180/8 በነበረው ክርክር የተደረገው ወጪ በደረሰኝ እንዱተካላቸው መወሰኑን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል።
የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከጠበቃቸው በተናጠል ባደረጉት ውል እያንዲንዲቸው 5,000 ብር ለመክፈል መስማማታቸው ያሳያል። የወረዲ ፍርድ ቤትም በቀረበው ሰነድ መሰረት አመልካች በድምር 40,000 እንዱከፈል ወስኗል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ ለአፈፃፀም ክስ መነሻ በሆነው መዝገብ ላይ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ በቀረበው ደረሰኝ እንዱከፍል መወሰኑን በመግለጽ፤ምንም እንኳ የተጠሪዎች የክርክር ጭብጥ አንድና ተመሳሳይ ነው ቢባልም አንኳ የተሰጠው መብትና በተጣለው መብት ተጠቃሚዎች ቁጥር ሲታይ 8 ተከራካሪዎች ናቸው። የፈጀው ጊዜም ሲታይ ከጥር 20/2005 ዓ.ም ጀምሮ ጉዲዩ በይግባኝ እስከሚታይበት ጊዜ 1 ዓመት ከ 6 ወር ዕድሜ አስቆጥሯል።
ተጠሪዎች የጠበቃ አበል በማለት የተዋዋለት 40,000 በዝቷል ለማለት የሚቻል አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አጽንቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ በመባለ ግራቀኙ የጽሐፍ ክርክር አድርጓል። የአመልካች ቅሬታ መሰረታዊ ይዘት የተጠሪዎች ክስ በህብረት የቀረበ ስለሆነና ለእያዲንዲቸው የተደረገ ክርክር የላለ ስለሆነ የጠበቃ አበልን በተናጠል 5000 ማድረጋቸው፤ፍ/ቤቱም እንዱከፍል መወሰኑ ተገቢነት የለውም የሚል ነው። ተጠሪዎች በበኩላቸው የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን በማጣራት የወሰነው በመሆኑ ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክሯል። የመልስ መልስ ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ግራቀኙ በዚህ ችልት ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች በማዛመድ እንዱሁም ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም ግራቀኙ እያከራከረ ያለው ጉዲይ ለጥብቅና ሙያ አገልግልት ተከፈለ የተባለው የገንዘብ መጠን ነው። አመልካች ክፍያው የተጋነነ ነው ክሱ በሕብረት የቀረበ ከመሆኑ አንፃር 40,000 እንዱከፍል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት የተከራከረ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው ክርክሩ ረጅም ጊዜ የወሰደ ከመሆኑ አንፃር የተከፈለው ገንዘብ የተጋነነ የሚባል አይደለም በማለት መልስ አቅርበዋል።
በመሰረቱ የወጪና ኪሳራ አከፊፈል ሥርዓት በፍርድ ቤቶች የመወሰን ሥልጣን የተመሰረተ ስለመሆኑ ከፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 462 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነው።
ተጠሪዎች በጠበቃ ተወክለው የተከራከሩ ስለመሆኑ የተካደ ጉዲይ አይደለም። ክሱ የቀረበውም በአንድ ድርጅት በተመሳሳይ የሕግ ጭብጥ በአንድ ጊዜ ስለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል። የአብክመ የጥብቅና ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ ምዝገባ የጠበቆች ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 75/1994 ዓ.ም የአገልግልት ክፍያ በግራ ቀኙ ስምምነት እንደሚፈጸም፤መጠኑ ያልተወሰነ የአገልግልት ክፍያ ከሆነ በመቶኛ ስላት እንደሚውል፤በባልና ሚስት ክርክር ፍቺ ቀለብ በተመለከተ፤በወንጀል ጉዲዮች በሚሰጠው ውሳኔ እና ቅጣት ያልተወሰነ የአገልግልት ክፍያ እንደማይደረግ ከአዋጅ አንቀጽ 50፣51 እና 52 ጥምር ንባብ መገንዘብ ይቻላል። የጥብቅና ሙያ አገልግልት ተገቢ የድካም ዋጋ የሚሰጠው መሆን እንዲለበት የታመነ ቢሆንም ከሚገባው በላይ የናረ መሆን የለበትም። የጥብቅና ሙያ አገልግልት ለመወሰን በልምድ ከዲበረው እና በአጠቃላይ ተቀባይነት ያገኘው የአከፊፈል መርህ ጉዲዩ የወሰደው ጊዜ፣የሚጠይቀው ድካም፣የጉዲዩ ውስብስብነት፤የክርክሩ ግምት ታሳቢ የሚደረጉ ናቸው።
የጥብቅና ሙያ አገልግልት ክፍያ ሥራውን ያለውን ውጣ ውረድ ድካምና ያስከተለው ወጭ ታሳቢ መደረግ አለበት። የጥብቅና ሙያ አገልግልት ክፍያ ያለምንም ገደብ ስምምነት የሚደረግበት አለመሆኑን ከሥነ ሕግ እና የፍ/ቤቶች አሰራር የዲበረ ልምድ ነው። በመሆኑም የአገልግልት ዋጋ ክፍያ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ላሆን ይገባል። ከላይ እንደተመለከተው ተገቢ የሆነውን የአገልግልት ዋጋ ለመወሰን የተደረገው ጥረት (ድካም)፣የወሰደው ጊዜ እና የጉዲዩ ውስብስብነት ታሳቢ ማድረጉ ሚዛናዊ የሆነ ክፍያ ለመወሰን እንደ መስፈርት የሚወሰድ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ግራቀኙ ያከራከረው ነጥብ የሥራ ክርክር ሲሆን ተጠሪዎች በአንድ ዘንግ ቁመው የሕብረት ክስ ማቅረባቸው አልተካደም። ጉዲዩ የያዙት ጠበቃ የሚያስፈልጋቸው ጊዜ፤የሚነሳው የሕግና ፍሬ ነገር ክርክር ተመሳሳይነት ያለው ከመሆኑ አንፃር ብዙ ጥረት ይጠይቃል ተብል አይገመትም። ከሥር ፍርድ ቤት መዝገብ እንደተመለከትነው ጠበቃው በችልት የቆሙባቸው ጊዜያት የተወሰኑ ስለመሆናቸው ተመልክተናል። እንዱህ ከሆነ ተጠሪዎች በተናጠል 5,000 በድምር 40,000 መክፈላቸው ጠበቃው በክርክሩ ያጠፈት ጊዜ፣ጉዲዩ ከወሰደው ጊዜ ግምቱ የክርክሩ ባሕሪ እና ይዘት አንፃር የተጋነነ ነው። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች ያደረጉት የጥብቅና አገልግልት ውል ከጉዲዩ ክብደት እና ውስብስብነት፤ግምቱ የወሰደው ጊዜ አንፃር መዝነው ትክክለኛ ወይም ተቀራራቢ ዋጋ መወሰን ሲገባቸው በተጠሪዎች የቀረበው ውል እንዲለ ወስደው አመልካች 40,000 ብር እንዱከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም አመልካች መክፈል ያለበት የጥብቅና አገልግልት ዋጋ ከተሰጠው አገልግልት መጠን አንፃር በዲኝነት የተወሰነው ብር 145,360 አሥር ፏርሰንት (10%) አሥራ አራት ሺ አምስት መቶ ሰላሳ ስድስት ነው ብለናል። በእዚህ ሁለ ምክንያት የሥር ፍርድ ቤቶች የፈጸሙት ስህተት በማረም ተከታዩን ወስነናል።
የደሴ ወረዲ ፍ/ቤቶች በመ/ቁ. 36/018018 ግንቦት 01/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 17030 በ9/11/2006 የሰጠው ፍርድ የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/6 በ27/01/2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሎል።
አመልካች ለተጠሪዎች መክፈል የሚገባው በዲኝነት የተወሰነው ብር 145,360 10% ብር 14,536 ነው በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
በዚህ ፍ/ቤት የተሰጠው ዕግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት ተመለስ።
No topics extracted.