የጥብቅና አገልግልት የሚሰጥ ጠበቃ በደንበኛው የአገልግልት ክፍያ ሲፈጸምለት ለተፈጸመው ክፍያ ደረሰኝ አለመስጠት የዱሲፕን ግድፈት ስለመሆኑ አዋጅ 199/92 አንቀፅ 30/2/ ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 8/1/
No summary available.
መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ ሞገስ ናደው እንዲይላለ ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፍትህ ሚኒስተር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከጥብቅና የዱሲፕሉን ጋር የተያያዘ ሲሆን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤ 78/06 ግንቦት 22 ቀን 2006 ዓ.ም አመልካች ለአንድ ዓመት ከጥብቅና ሙያ እንዱታገደ በማለት ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በሚኒስትሩ ጸድቆ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የክርክሩ መነሻ ወ/ሮ አስቴር ወ/ሚካኤል ለዱሲፕሉን ጉባኤው ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ያቀረቡት አቤቱታ ነው።የግለሰቧ አቤቱታ ይዘትም የአሁኑ አመልካች ከግለሰቧ ጋር በገቡት የጥብቅና አገልግልት ውል መሰረት ጉዲዩን በመደበኛው የክርክር ሂደት ክስ ማቅረብ ሲገባቸው በተፊጠነ ስርነ ስርዓት ክስ አቅርበው ግለሰቧን ለተጨማሪ ወጭና ጉዲት መዲረጋቸውን፣ የአሁኑ አመልካች ከግለሰቧ ለቅድሚያ ክፍያ ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ) ተቀብለው ደረሰኝ የከለከሎቸው፣ውለ ከተቋረጠ በኋላም ገንዘባቸውን አልመልስም ያሎቸው መሆኑን መዘርዘራቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም በመጀመሪያ ከግለሰቧ ጋር በሚገባ ተመካክረውና ግለሰቧ አለኝ በአሎቸው ማስረጃዎች መሰረት ክሱን በተፊጠነ ስነ ስርዓት መሰረት አቅርበው ለክሱ መነሻ የሆነው ቼክ ለመያዣነት የተሰጠ መሆኑ ሲገለጽላቸው የክስ ማሻሻል ጥያቄ ክሱ ከመሰማቱ በፉት ማቅረባቸውን፣የቅድሚያ ክፍያው ብር 20,000.00 ሳይሆን ብር 10,000.00 መሆኑንና ጉዲዩ በጅምር ላይ እንዲለ ውክልናው የተሻረ በመሆኑ ሉጠየቁ የማይችለ መሆኑን ዘርዝረው ተከራክራል። በዚህ መልክ የግራ ቀኙ ክርክር የቀረበለት ጉባኤውም አመልካች የግለሰቧን ክስ በመደበኛ ክስ ማቅረብ ሲገባቸው በተፊጠነ ሥነ-ሥርዓት ክስ ማቅረባቸው ተገቢነት የላለው መሆኑን፣ የቅድመ ክፍያውን በተመለከተ አመልካች በከፉል ክደው ቆይተው ምስክሮች ሉሰሙ ሲለ ማመናቸው የግለሰቧን ምስክሮች ጊዜ ከማባከኑም በላይ በጉባኤው ስራ ላይም ከፍተኛ ጫና የፈጠረና ከአንድ ጠበቃ የማይጠበቅ ተግባር መሆኑን እንዱሁም አመልካች በክርክሩ ሂደት ግለሰቧን ከጉባኤው አዲራሽ ውጪ ምንም ልታደርጊኝ አትችይም አስር ሺህ ብር ከፍዬ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ስራ እገባለሁ በማለት የዛቻ አነጋገር መናገራቸው ከጠበቃ የማይጠበቅ ተግባር ሁኖ መገኘቱን ዘርዝሮ አመልካች ክሱን ያቀረቡበት አግባብ በአዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 30(2)፣ለጥብቅና አገልግልት ለተቀበለት ገንዘብ ደረሰኝ አለመስጠታቸው ደግሞ በደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 8(1) ከጉባኤው አዲራሽ ውጪ በግለሰቧ ላይ ለተናገሩት ንግግር ደግሞ በደንብ ቁጥር 52/92 አንቀጽ ቁጥር 24(3(ለ)) ((2)) መሰረት ለአንድ ዓመት ከጥብቅና ስራቸው እንዱታገደ በማለት የውሳኔ ሃሳብ አቅርቦ ይኼው የውሳኔ ሃሳብ በሚኒስትሩ ጸድቋል። የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የክስ አመሰራረቱ ግለሰቧ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሁነው በሰጡት ማስረጃ መሰረት ሙያውን ተመርኩዘው ያቀረቡት ሁኖ እያለ እና በኋላም ቼኩ በመያዣነት የተሰጠ መሆኑ ሲገለጽላቸው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት የክስ ማሻሻል ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው ተቀባይነት ያጡ መሆኑን፣ለጥብቅና አገልግልት ክፍያም ደረሰኝ ያልተሰጠው ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ ከግለሰቧ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት መሆኑንና አመልካች ግለሰቧ ላይ ከጉባኤው አዲራሽ ውጪ ዛቻ ፈጽመዋል የተባለው የአንድ ወገን የቃል አቤቱታ ተሰምቶና በማስረጃ ሳይጣራ መሆኑን ዘረዝረው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻርላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።እንደመረመረውም አመልካች የዱሲፒሉን ጥፊት ፈፅመዋል ተብል ለአንድ ዓመት ከጥብቅና ስራ እንዱታገደ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ መሰረት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ሉያዝ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።፡ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የታቻለው የጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤ አመልካች የስነ ምግባር ጥፊት ፈፅሟል ከሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰበት የመጀመሪያው ምክንያት አመልካች የአቤቱታ አቅራቢዋን ግለሰብ ክስ ለፍርድ ቤት ሲያቀርቡ በተፊጠነ ስነ ስርዓት መሰረት ሉያቀርቡ አይገባም ነበር በሚል ነው።አመልካች ይህንኑ የጉባኤውን የውሳኔ ሀሳብ ተገቢነት የለውም የሚለት ክሱ ሉመሰረት የቻለው ግለሰቧ ለጠበቃው በሰጧቸው ማስረጃዎች አግባብ ነው፣ክሱ ከቀረበ በኋላ ግለሰቧ ለአመልካች በአሳወቁት ማስረጃ መሰረትም የክስ ላሻሻል ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ በጊዜው አቅርበው የነበሩ መሆኑን በመጥቀስ ነው። የጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤ፣በጠበቃ ላይ ያቀረበውን የዱስፒሉን ክስ ሉወስን የሚገባው በጠበቃው ላይ የቀረበውን የዱስፒሉን ክስና ማስረጃ እንደዚሁም በጠበቃው በኩል የቀረበውን መልስና ማስረጃ በመመርመር እንደሆነ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች የጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1ዐ9/1992 አንቀፅ 24(3) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነው።
በተያዘው ጉዲይ የዱሲፕሉን ጉባኤው ከአንድ ጠበቃ በክስ አቀራረብ ሂደት የሚጠበቁ ሙያዊ ግዳታዎች ምን እንደሆኑ ከዘረዘረ በኃላ አመልካች የዱሲፕሉን ጥፊት ፈፅመዋል ያለው ጉዲዩ በጅምር ላይ ከማለት ያለፈ በመልሳቸው ላይ በቀጥታ የካደት ነጥብ የለም በማለት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ለጠበቆች የዱሲፕሉን ጉባኤ የካቲት 07 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት የመልስ ማመልከቻ ክሱ መቅረብ የሚገባውን ስርዓት ከግለሰቧ ጋር ተማምነው በስርዓቱ መሰረት ማቅረባቸውን በተራ ቁጥር አንድ ስር፣እንዱሁም ግለሰቧ ክሱ ከቀረበ በኋላ በዋስትና በተያዘው ቼክ ምክንያት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ሀራጅ መውጣቱን እና እዲ መክፍል መጀመራቸውን ለአሁኑ አመልካች ሲያሳውቋቸው በጉዲዩ ላይ ሰፉ ውይይት አድርገው ክሳቸው ተሻሽል እንዱቀርብ ግለሰቧ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ተስማምተው ክስ ከመሰማቱ በፉት አስቀድመው ለፍርድ ቤቱ የክስ ማሻሻያ አቤቱታ ለማቅረብ እንዱፈቀድላቸው ሕጉ በሚፈቅደው አግባብ ጥያቄውን ማቅረባቸውን በመልሳቸው ተራ ቁጥር ሶስት ስር የዘረዘሩ መሆኑን ከመልስ ማመልከቻቸው ይዘት ተመልክተናል። ይህንኑ ክርክራቸውን በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምል 05 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት የይግባኝ ማመልከቻም ያቀረቡት መሆኑን ከማመልከቻው ይዘት ተመልክተናል። ይህ የአመልካች ክርክር ይዘት በግልጽ የሚያሳየው ደግሞ አመልካች ከመነሻውም ክሱን ያቀረቡት አግባብ የሙያው ስነ ምግባር በሚፈቅደው ስርዓት መሆኑን እንጂ ከደንቡ ውጪ መሆኑን አምነዋል የሚያሳየኝ አለመሆኑን ነው። በመሆኑም አመልካች ከስር ጀምሮ ባቀረቡት ክርክር ክሱን ያቀረቡበትን ስርዓት ግለሰቧ ጋር በግልጽ ተማምነውና በእጃቸው ላይ ባለት ማስረጃዎች ስለመሆኑ ገልጸው እያለ አልካደም በማለት በዱሲፒሉን ጉባኤው አመልካች አልካደም ተብል የተመዘገበው ተገቢውን የክርክር አመራር የተከተለ ሁኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም የዱስፒሉን ጉባኤው በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀፅ 24 ንዐስ አንቀፅ 3 በጠበቃው ላይ የሚቀርበውን ክስና ማስረጃ ብቻ ሣይሆን በጠበቃው የሚሰጠውን መልስና የመከላከያ ማስረጃ በመመርመር ውሣኔ የመስጠት ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የተደነገገውን ድንጋጌ የጣሰ ነው። እንግዱህ አንድ ጠበቃ የደንበኛውን ጉዲይ የሚያቀርብበት ሕጋዊ አግባብ ምንድነው? የሚለውን ስንመለከትም ሙያው የሚፈቅደውን የስነ ምግባር ደንብ ተከትል መሆን እንደአለበት የሚታወቅ ነው።
በመሰረቱ በማንኛውም ጠበቃ ሕግን ለማስከበርና ፍትህን ለማስገኘት የፍትህ አስተዲደሩን የሚገባ ኃላፉነት ያለበት መሆኑንና ጠበቃው ልዩ ደንበኛውን ለላልች የሕግ ባለሙያዎች ተከራካሪ ወገኖች ለፍርድ ቤት፤ለሙያውና ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ያለበትን የሙያ ኃላፉነት በቅንነት፤
በታማኝነትና በእውነተኝነት የመወጣት ሙያዊ ግዳታ ያለበት መሆኑ በደንብ ቁጥር 57/1992 አንቀጽ 3 በግልፅ ተደንግጓል።ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም ጠበቃ የደንበኛውን ጉዲይ በትጋት የመከታተል አፊጣኝና ፍትሀዊ ውሳኔ ለማግኘት ሉወሰድ የሚገባውን እርምጃ ሁለ በጥንቃቄና በወቅቱ የመፈፀም ሙያዊ ግዳታ ያለበት መሆኑ በደንብ አንቀጽ 8 ንዐስ አንቀጽ 2(ለ) ስር በግልጽ ተደንግጓል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ከደንበኛቸው ጋር ተነጋግረው ክሱን በተፊጠነ ስነ ስርዓት ማቅረባቸውን ገልጸውና በኋላም ግለሰቧ እዲውን መክፈል መጀመራቸውን ለአመልካች ሲገልፁ ክሱን ለማሻሻል ጥረት ያደረጉ መሆኑን አመልካች ጠቅሰው የተከራከሩ ሲሆን አመልካች ክሱን ያቀረቡት ለሙያውና ለግለሰቧ ያላቸውን የሙያ ኃላፉነት በአጓደለ መልኩ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም። አመልካች ለሙያውና ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ያለባቸውን የሙያ ኃላፉነት በአጓደለ መልኩ ክሱን አቅርበዋል ልባል የሚችልው በተገቢው መንገድ ከደንበኛቸው የቀረበላቸውን ሕጋዊ ማስረጃ መሰረት በአላደረገ መልኩ ክስ አቅርበው ስለመሆኑ በሚገባ ከተረጋገጠ ነበር። አመልካች ደንበኛቸውን በቅድሚያ የሰጡትን ማስረጃ መሰረት አድርገው ክስ ማቅረባቸውና በኋላም ግለሰቧ እዲውን መክፈል መጀመራቸውን ሲገልፁላቸው ክሱን ለማሻሻል ተገቢውን ጥረት ማድረጋቸው በደንብ ቁጥር 57/1992 አንቀጽ 3 እና 8 ድንጋጌዎች መሰረት ሙያዊ ኃላፉነቱን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የዱስፒሉን ጉባኤ ክስ አቀራረቡ በተፊጠነ ስነ ስርዓት ማቅረብህ ያላግባብ መሆኑን አመልካች አምነዋል ያለበት ድምዲሜ የአመልካችን የመልስ ይዘት ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ አመልካቹ ከደንበኛቸው የተቀበሎቸው ማስረጃዎች፣ከግለሰቧ ጋር ቅድሚያ ስለ ክስ አቀራረብ ስርዓት የተስማሙ መሆን ያለመሆኑንና በኋላም ግለሰቧ ለአመልካች የገለጹት እዲ መክፍል መጀመራቸው ጉዲይ መኖር ያለመኖሩንና ይህንኑ ተከትል አመልካች የክስ ማሻሻል ጥያቄ ማቅረባቸው ከሙያው ስነ ምግባር፤ ቅንነትና እውነትነት አንፃር ሲታይ ተቀባይነት ያልነበረው መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ ሳያረጋገጥ የአመልካች የክስ አቀራረቡ ብቻውን የዱስፒሉን ጥፊት ነው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ህጋዊ መሰረት የላለው ሁኖ አግኝተናል።በመሆኑም አመልካች ለክስ አቀራረቡ የዱሲፕሉን ጥፊት ፈጽመዋል የተባለት ያላግባብ ነው ብለናል።
ላላው የዱስፕሉን ጉባኤው አመልካች የዱሲፕሉን ጥፊት ፈጽመዋል ያለው ለጥብቅና አግልግልት ለተቀበለት ገንዘብ ደረሰኝ ለደንበኛቸው ያለመስጠታቸው ተረጋግጧል በሚል ነው።
አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ማስተባበያ ክርክርና ማስረጃ ያለመኖሩን በዱሲፕሉን ጉባኤው የግለሰቧ ምስክሮች የምስክርነት ቃል ለመስጠት ከቀረቡ በኋላ አመልካች አስመዘገቡ ተብል ከተመዘገበው ቃል ይዘት ተረድተናል። በመሆኑም አመልካች ደረሰኝ ያለመስጠታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ በደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 8(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የጣሱ በመሆኑ ለዚህ አድራጎታቸው በዱሲፕሉን ተጠያቂ መደረጋቸው በአግባቡ ሁኖ አግኝተናል። ላላው አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ነጥብ የዱስፕሉን ጉባኤው አመልካች ግለሰቧን ከዱሲፕሉን ጉባኤው አዲራሽ ውጪ ዛቻ ፈጽሞባቸዋል በማለት ያስተላለፈው ውሳኔ የአንድ ወገን አቤቱታን መነሻ ያደረገና በልላ ማስረጃ ያልተደገፈ ነው በሚል ነው። እኛም ጉዲዩን እንዲየነው ድርጊቱ መፈጸሙን የዱሲፕሉን ጉባኤው ያረጋገጠው ሲሆን ጉባኤው ለአመልካች በጉባኤው ፉት ተግሳጽ የሰጠ መሆኑን ከገለፀ በኃላ እንደገና በውሳኔው እለት ደግሞ ለዚህ አድራጎት የዱሲፕሉን ጥፊት ነው ከስራ ለማገድም ምክንያት አድርጎታል።ይህ ደግሞ አመልካች ለአንድ ጥፊት ሁለት አይነት ቅጣት የተወሰነባቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው።የዱሲፕሉን ጉባኤው ይኼው የአመልካች አድራጎት በደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 57 ድንጋጌን የጣሰ መሆኑን በውሳኔ ላይ የገለፀ ቢሆንም ይኼው ተጠቃሽ ድንጋጌ ግን አመልካቹን ለሁለት ጊዜ ሉያጠይቅ የሚችልበትን አግባብ ስለመኖሩ ያስፈረው ምክንያት የለም። አንድ ጠበቃ ለፈፀመው የዱሲፕሉን ግድፈት ተገቢ ነው የተባለውን የዱሲፕሉን ቅጣት ከአገኘ በኋላ በተመሳሳይ የዱሲፕሉን ጥፊት ድጋሚ እንዱቀጣ ለማድረግ የሚያስችል የህግ መሰረት የላለውና ከጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ መሰረታዊ ዓላማም ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። ሲጠቃለልም የዱሲፕሉን ጉባኤው አመልካችን ለክስ አመሰራረቱና አመልካች ግለሰቧን ከዱሲፕሉን ጉባኤው አዲራሽ ውጪ ዛቻ ፈጽሞባቸዋል በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕግ መሰረት የላለው ሁኖ አመልካች ደረሰኝ ያለመስጠታቸውን በማረጋገጥ የሰጠው ውሳኔ ግን ተገቢ ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት አመልካች ሉቀጡ የሚገባው ደረሰኝ ባለመስጠታቸው ምክንያት በደንብ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 30(2) ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 8(1) እና በአዋጅ ቁጥር 199/92 አንቀጽ 24(3(ለ)) ድንጋጌ አግባብ አመልካች ከጥብቅና ስራ ሉታገደ የሚገባው ለስድስት ወር ብቻ ላሆን የሚገባ ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመ በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፍትህ ሚኒስቴር የጠበቆች የዱስፒሉን ጉባኤ በመ/ቁጥር 78/06 ግንቦት 22 ቀን 2006 ዓ/ም የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ በሚኒስትሩ ሰኔ 06 ቀን 2006 ዓ/ም የፀደቀውና በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።፡
የጠበቆች የዱስፕሉን ጉባኤና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የክስ አቀራረብ እና የዛቻ ተግባር የሥነ ምግባር ጥፊት ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ ህጋዊ አይደለም በማለት ሽረናል።
አመልካች ከደንበኛቸው ለተቀበለት ገንዘብ ደረሰኝ ያለመስጠታቸው ግን በአዋጅ ቁጥር 199/1992 አንቀጽ 30(2) ድንጋጌን የጣሰ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 24(3)(ለ))) መሰረት ከጥብቅና ስራ ለስድስት ወር ሉያሳግዲቸው የሚገባ ነው በማለት ወስነናል።ይህ ጊዜ አመልካች ከዚህ በፉት የታገደበትን ጊዜ መነሻ አድርጎ ሉቆጥር ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዱፈጸም ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ግልባጩ ይላክ ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.