ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቦታ በሉዝ ለገዛ ሰው ቦታውን ለግንባታ ምቹ አድርጎ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑና በወቅቱ ካላስረከበ ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ የሁለት አመት የችሮታ ጊዜ ለገዥው ሉሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 14/3/ ፣ 37/6/ለ/ ፣ 38/8/ ደንብ ቁጥር 48/2004 አንቀፅ 11/1/ ፣ አንቀፅ 12/2/ XXVI
No summary available.
ሚያዝያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ሁሴን ሰይድ ቀረቡ ተጠሪ፡- የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ጽ/ቤት አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጳግሜ 5 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና፣ የሰበር ችልቱ በመዝገብ ታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱተረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በሉዝ የተገዛ ቦታ ክፍያ አፈፃፀምን የሚመለከት ነው። በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ነው። ከሳሽ ባቀረበው ክስ፣ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር ጥቅምት 8 ቀን 1998 ዓ.ም በተዋዋለው የሉዝ ውል መሰረት በቀድሞው ቀበላ 16/17/18 ክልል ስፊቱ 425 ካሬ ሜትር ቦታ በሉዝ በመግዛት ቦታውን ተረክቧል። የቦታው ጠቅላላ ዋጋ .80 /አሪት መቶ ሰላሳ ሺህ ሶስት መቶ አሰራ ሁለት ብር ከሰማንያ ሳንቲም/ ነው። ከዚህ ውስጥ ተከሳሽ 20% ከፍሎል። ተከሳሽ የሁለት አመት የቸሮታ ጊዜ ተሰጠቶት ቀሪውን የሉዝ ዋጋ ከ2002 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም በየአመቱ ከፍል ለመጨረስ ግዳታ ገብቷል። ተከሳሽ በሉዝ ውለ መሰረት የ2001 ዓ.ም የሉዝ ክፍያ ወለድና ቅጣት የ2003 ዓ.ም የሉዝ ክፍያ ወለድና ቅጣትና የ2003 ዓ.ም የ275 ቀናት የሉዝ ክፍያ ወለድና ቅጣት በድምሩ ብር 153‚820.29 /አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት ሺ ስምንት ሃያ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሣንቲም/ አልከፈለም። ከሳሾች ተከሳሽ ገንዘቡን እንዱከፍል ቢጠየቅ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ገንዘቡን ከባንክ ወለድ ጋር እንዱከፍል ዉሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ጉዲዩ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ታይቶ የተወሰነ ስለሆነ በፍርድ ቤት መታየት የለበትም በማለት የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ አቅርቦ ፍ/ቤቱ በብይን ውድቅ አድርጎታል። ተከሳሽ /አመልካች/ ለክሱ ባቀረበው የመከላከያ መልስ ከሳሽ በሉዝ የሸጠልኝን ቦታ በመናፈሻ ክልል ውስጥ ሆኖ በመገኘቱ ቦታው እንዱቀየር ተወስኖ ቦታውን በመቀየር አንድ አመት ከአምስት ወራት ወስድበታል ከሳሽ ከአንድ አመት ከአምስት ወራት በኋላ ቀይሮ የሰጠኝ ቦታ ባለሶስት መዓዘን ከመሆኑም በላይ የስልክና የመብራት ፖል /ምሰሶ/ የነበረበት በመሆኑ መሰሶው እንዱነሳ ጥያቄ አቅርቤ ከሳሽም ምሰሶው እንዱነሳ ሲፃፃፍ ቆይቶ፣ የምሰሶውን ማስነሻ ወጭ ተከሳሽ ክፍያ ቦታውን ግንባታ ለመጀመር በሚያመች ሁኔታ የተረከብኩት፣ ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። ከሳሽ በሉዝ ውለ መሰረት ቦታውን ለግንባታ ምቹ አድርጎ ማስረከብ ስላልቻለ፣ ቦታውን ካስረከበበት ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የሁለት ዓመት የችሮታ ጊዜ፣ የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ የሉዝ ውለን በማሻሻልና በሉዝ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር አንቀፅ 14/3/ አንቀፅ 36 /7/ የተደነገገ በመሆኑ፣ ይኽም የአዱስ አበባ አስተዲደር ባወጣው የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት መሰረት አቅርቤ ያስወሰንኩ በመሆኑ የከሳሽን ክስ ውድቅ በማድረግ ያሰናብተኝ በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ከሳሽና ተከሳሽ ግንቦት 6 ቀን በ1999 ዓ.ም ያደረጉት የሉዝ ውል መሰረት ተከሳሽ እስከ 2001 ዓ.ም የችሮታ ጊዜ ተሰጥቶታል።
የመመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 37/6/ የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ ስለማራዝምበት ሁኔታ የሚደነግግ ሲሆን፣ የቸሮታ ጊዜ የሚራዘም ስለመሆኑ አይደነግግም ተከሳሽ የአስተዲደሩ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ወስኖልኛል ቢልም ውሳኔ አስገዲጅነት የለውም። ስለዚህ ተከሳሽ ክስ የቀረበበትን የሉዝ ኪራይ ከቅጣትና ከወለድ ጋር ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ አቅርቧል።
የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች ለከተማው ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ተደርጎበታል።
አመልካች የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ተጠሪ ቦታውን ነፃ አድርጎ ያስረከበኝ ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። ተጠሪ ቦታውን ለግንባታ ምቹ አድርጎ የማስረከብ ግዳታዉን ሣይወጣ አመልካች የሉዝ ክፍያ እንዱከፍል የመጠየቅ መብት የለውም። ጉዲዩ በደንብ ቁጥር 48/2004 መሰረት ታይቶ፣ ተጠሪ የሉዝ ውለን በማደስ፣ የቸሮታ ጊዜ፣ የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ እንደሰጠኝ አስተዲደራዊ ውሳኔ ተሰጥቶበታል። ከዚህ በተጨማሪ መመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 14 /3/ እና አንቀፅ 37 /6/ መሰረት ተጠሪ መፈፀም ሲገባው የሉዝ ክፍያ እንዱከፍል በማለት ያቀረበው ክስ የሕግ መሰረት የለውም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ባቀረበው መልስ አመልካች የሉዝ ውለ ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ይታሰብልኝ በማለት የሚከራከረው ከግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው መመሪያ ቁጥር 11/2004 ወደ ኋላ ሄድ እንዱሰራለት በመጠየቅ ነው።
ሆኖም ለአመልካች ጉዲይ ተፈፃሚነት ያላቸው በወቅቱ ስራ ላይ የነበሩት መመሪያዎች እንጅ መመሪያ ቁጥር 11/2004 ስላልሆነ የአመልካች ክርክር የሕግ መሰረት የለውም። በደንብ ቁጥር 48/2004 መሰረት ታይቶ የተሰጠ የቅሬታ ሰሚ ውሳኔ አስገዲጅነት ያለው አይደለም።
ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀናልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሚያዝያ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ መመሪያ ቁጥር 11/2004 የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ያለው በመሆኑ የተጠሪ ክርክር ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን፣ መርመረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን፣ በአመልካችና ተጠሪ ክርክር የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ካላቸው የአዱስ አበባ አስተዲደር የሕግ ማዕቀፍች ጋር በማገናዘብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካችና ተጠሪ የሉዝ ውል የተዋዋለት ተጠሪ ለስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ በገለፀው ጊዜ፣ ማለትም ጥቅምት 8 ቀን 1998 ዓ.ም ቢሆንም፣ ተጠሪ በሉዝ ውለ መሰረት ለተጠሪ የሸጠው ቦታ የመናፈሻ ክልል ውስጥ ሆኖ በመገኘቱ፣ ቦታ መቀየሩን፣ ቦታውንም ለመቀየር አንድ አመት ከአምስት ወራት የወሰደ መሆኑን አመልካች ያቀረበውን ክርክር ተጠሪ ክድ አልተከራከረም። ከዚህ በተጨማሪ ለአመልካች ተቀይሮ የተሰጠው ቦታ ላይ የመብራትና የስልክ ምሰሶዎች የነበሩ መሆኑንና አመልካች በፍትሐብሓት ሕግ ቁጥር 1862 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ጉዲቱን ለመቀነስ የስልክ እና የመብራት መሰሶ ከቦታው ለማንሳት የሚያስፈልገውን ወጭ በራሳቸው ሸፍነው የስልክና የመብራት ምሰሶዎቹ ተነስተው ቦታው ለግንባታ ዝግጁ ሆኖ የተሰጣቸው ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሉዝ ለአመልካች የሸጠውን ቦታ ነፃ አድርጎና ለግንባታ ዝግጁ አድርጎ የማስረከብ ኃላፉነት ተጠሪ ያለበት መሆኑ፣ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጭብጥ ሆኖ አላገኘነውም። ይህም ተጠሪ በሉዝ ውል የተመለከተውን ቦታውን ነፃ በማድረግ በተከራዩ /አመልካች/ የማስረከብ ግዳታውን የተወጣው ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም መሆኑን ያሳያል።
ተጠሪ እስከ ሚያዝያ 23 ቀን 2003 ዓ.ም በሉዝ ውለ የተመለከተውን መሰረታዊ ግዳታ አለመወጣቱ፣ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የከተማ መሬት ሉዝ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 14 ንዐስ አንቀፅ 3 በጨረታ የተሰጡ ቦታዎች በመስሪያ ቤቱ ችግር ምክንያት በውለ መሰረት ማስረከብ ካልተቻለ ውለ እንደገና ይታደሳል፣ የችግር ጊዜና የግንባታ መጀመሪያ ጊዜ፣ የሉዝ ማጠናቀቂያ ጊዜ እንደገና እንደ አዱስ የሚወስን መሆኑን ይደነግጋል። እንደዚሁም የመመሪያ ቁጥር 37 አንቀፅ 6/መ/ መሰረት ቦታውን ለማስረከብ ካልተቻለ፣ ተጨማሪ የግንባታ መጀመሪያ ጊዜ ላሰጥ እንደሚችል የሚደነግግ ሲሆን በአንቀፅ 38 ንዐስ አንቀፅ 3 ተጨማሪ የማጠናቀቂያ ጊዜ ሉፈቀድ እንደሚችል ይደነግጋል።
የስር ፍርድ ቤት የመመሪያውን ቁጥር አንቀፅ 37 ብቻ በማየት፣ መመሪያው የቸሮታ ጊዜ የማራዘም ድንጋጌ የለውም በማለት ውሳኔ የሰጠ መሆኑን ከውሳኔው ግልባጭ ለማየት ይቻላል። ተጠሪ በበኩለ በዚህ ሰበር የሚከራከረው መመሪያው ወጥቶ ስራ ላይ የዋለው ግንቦት 16 ቀን 2004 ዓ.ም ስለሆነ ለዚህ ጉዲይ ተፈፃሚነት የለውም በማለት ነው። ሆኖም ይህ የተጠሪ ክርክር በመመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 83/ሀ/ ይህ መመሪያ ከመወጣቱ በፉት በአስተዲደሩ ቦርድ ወይም በመሬት አስተደደር ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን የተፈረሙ ውልች ወይም የተከናወኑ ስራዎች ህጋዊነታቸው ተጠብቆ በዚህ መመሪያ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል በማለት በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ፣ የተጠሪ ክርክር፣ ይህን የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና ህጋዊ መሰረት የላለው ክርክር በመሆኑ አልተቀበለነውም። ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው የህግ ምከንያቶች የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ውለን በማደስ፣ ከሁለት አመት የሉዝ ክፍያ የቸሮታ ጊዜ፣ የሉዝ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜና የግንባታ መጀመሪያና የግንባታ ማጠናቀቂያ የጊዜ የሚያሳይ ላላ ውል ሳያቀርብ፣ አመልካች የሉዝ ክፍያ እንዱከፍል ያቀረበው ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባው አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን ክፍያ፣ እንዱከፍል በማለት የሰጠው ውሳኔና ይግባኝ ሰሚው ችልትና የሰበር ችልቱ ይህንን ውሳኔ በትዕዛዝ ማፅናታቸው አመልካች በመመሪያ ቁጥር 11/2004 የተረጋገጠላቸውን መብት የሚያጣብብና መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመሬት ሉዝ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 11/2004 በአንቀፅ 14/3/፣ በአንቀፅ 37 ንዐስ አንቀፅ 6/ለ/ እና በአንቀፅ 38 ንዐስ አንቀፅ 8 የሚጥስ ከመሆኑ በተጨማሪ የከተማው ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር 48/2004 መሰረት በክፍለ ከተማው የህዝብ አቤቱታና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የካቲት 8 ቀን 2005 የሰጠው ውሳኔ አስገዲጅነት የላለው ነው በማለት የሰጠው የህግ ትርጉም ስህተት ሉታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። ምክንያቱም ይህ አተረጓጎም፣ በደንብ ቁጥር 48/2004 አንቀፅ 11/1/ እና አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 ቅሬታና አቤቱታ ሰሚ የስራ ሂደቱ የቀረበለትን ጉዲይ በማጣራት የእርምት እርምጃ እንዱወስድ ውሳኔ እንደሚሰጥ፣ የተደነገገውን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ይህ የስር ፍርድ ቤት ትርጉም በደንብ ቁጥር 23 ድንጋጌዎች ያላገናዘበና በአጠቃላይ የከተማው አስተዲደር ደንብ ቁጥር 48/2004 የወጣለትን መሰረታዊ ዓላማና ደንቡን በማውጣት ሉያሳካው የሚፈልገውን ግብ የማያገናዘብ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያትና የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የከተማው የሰበር ችልት የአመልካች የሉዝ ክፍያ እንዱከፍል የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች የከተማው አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 11/2004 አንቀፅ 14 ንዐስ አንቀፅ 3 መሰረት ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የሁለት አመት የሉዝ መክፈያ የቸሮታ ጊዜ፣ የማግኘት መብት ያለው በመሆኑ፣ ተጠሪ የጠየቀውን የ2002 ዓ.ም የ2003 ዓ.ም እና የ2004 ዓ.ም የሉዝ ክፍያ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።