እኩል እንከፊፈል በሚል በፍ/ቤት የፀደቀን የቦታና ቤት ስምምነት እኩል ለማካፈል የከተማ አስተዲደሩ የፕላን ስታንዲርድን አያሟላም በተባለ ጊዜ የባልና ሚስትን የጋራ ሀብት በሀራጅ ተሸጦ ይካፈለ ብል መወሰን የግራ ቀኙን በቤቱ የመጠቀም ፍላጎት /ነጻነት የሚገደብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ 277/1/,325,392 የአማ/ክልል የቤተሰብ ህግ አዋጅ 79/95 አንቀጽ 73,74 101-103
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ታንጎት ሰጠ ተጠሪ፡- አቶ ፈንታው ትኩ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረዉ በአ/ብ/ክ/መ/ በሰሜን ወል ወልዱያ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካችና ተጠሪ ባልና ሚስት የነበሩና ጋብቻቸው በፍቺ በመፍረሱ የዚሁ ውጤት በሆነዉ የጋራ ንብረትን አስመልክቶ በተደረገው ክርክር፤- አመልካች አከራካሪው ቤትና መሬት የግላ እንጂ የጋራ ንብረት አይደለም በማለታቸው ምክንያት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ካዬ በኋላ ንብረቱን አስመልክቶ ተጣርቶ ይወሰን ዘንድ ወደ ወረዲ ፍርድ ቤት በመመለሱ ምክንያት ጉዲዩን በተመለሰለት መሰረት በተጠቃሾቹ ንብረት ላይ በማከራከር ንብረቱ በአንደኛዉ ተጋቢ ስም መመዝገቡ ብቻውን በክልለ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 74(1) መሰረት የግል አያደርገውም፣ በመሆኑም ቤቱ የጋራ ንብረት ሲሆን የእርሻ መሬቱ የአመልካች የግል ንብረት መሆኑን በማረጋገጥ ወስኗል። ቤቱን አስመልክቶ አመቺ በሆነ መንገድ ይካፈለ በማለት ወስኗል። በዚሁ መሰረት ለማስፈጸም በተያዘው ቀን የግራቀኙ ቤቱን አስመልክቶ በእርቅ ለሁለት ተካፍለን ለመኖር ተስማምተናል በማለት ወደ ፍርድ ቤቱ ቀርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህ/ቁ. 277(1) መሰረት ተቀባይነት አግኝቷል። በመቀጠልም ተጠሪ የይግባኝ ጊዜ ካለፈ በኋላ ቅሬታቸዉን ለከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ጥያቄያቸዉ ተቀባይነት በማጣቱ በፍ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁ 325 መሰረት መዝገቡ በመዘጋቱ በቀጣይነት ጉዲዩን ያየው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ቅሬታውን ባለመቀበል በትእዛዝ ሰርዞታል። በወረዲው ፍርድ ቤት የጸደቀው ስምምነትን አስመልክተው በአፈጻጸም መ/ ላይ ማዘጋጃ ቤቱ የአንደኛው ድርሻ ከ100 ካ.ሜ ያነሰ በመሆኑ ለአፈጻጸም አስቸጋሪ ነው በማለቱ ቤቱ በመነሻ ዋጋ እንዱሸጥ ትእዛዝ በመሰጠቱ አመልካች አፈጻጸሙን አስመልክቶ በእርቅ ስምምነት መሰረት ባለመፈጸሙ ክፍፍለ በእርቁ መሰረት ሉፈጸም ሲገባ ቤቱ እንዱሸጥ መባለ ዋናዉን ፍርድም ሆነ እርቁን የሚጻረር ነው በማለት ወደ ክልለ ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት አመልክተዉ ጉዲዩን ያየው ችልትም በእርቁ ስምምነት መሰረት በአይነት መካፈል የማይቻል መሆኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት በሰጠው መረጃ መሰረት መሆኑ በመረጋገጡ የተሰጠ ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስኗል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው። በመሆኑም አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ቅሬታቸውን ሲገልጹ፡- ከተጠሪ ጋር አከራካሪውን ቤት መጋቢት 13 ቀን 2000 ዓ/ም ባደረግነው የእርቅ ስምምነት ክፍፍል አድርገን በፍርድ ቤት መጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ/ም ጸድቋል። ቤቱን ስጠቀምበት ቆይቼ ተጠሪ በቤቱ ካርታ ሉያሰራ ጠይቆ ቦታህ 100 ካ.ሜ በታች በመሆኑ ሉሰራልህ አይችልም ስለተባለ ፍርድ ቤቱ እኔን ጠርቶ ቦታቻው ተሸጦ እንድትካፈለ ተባለ ፣በውላችን መሰረት ካርታ ማሰራት ሲገባው፤ ቦታው ተሸጦ እንድንካፈል መወሰኑ የሚጎዲኝ ነው፤ ከ100 ካ.ሜ በታች ቦታ ካርታ ይሰራላቸው ነበር፤ ተጠሪ በራሳቸው ቦታ ካርታ ያላሰሩት በቸልተኝነታቸዉ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቀዋል።
በዚህም መሰረት ችልቱም የግራ ቀኙ በስምምነት ጨርሰው ፍርድ ቤቱም ይህንኑ መጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ/ም ተቀብል በስምምነታቸው መሰረት መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ በተጠሪ አመልካችነት በ26/4/2005 ዓ/ም በዋለው ችልት በሀራጅ እንዱሸጥ መወሰኑን በጭብጥነት በመያዝ የግራ ቀኙን በጽሁፍ መልስና የመልስ መልስ በማቀባበል አከራክሯል።
ተጠሪ በሰበር መልሳቸው የሚለት ፡- አመልካች እኩል አላካፍልህም በማለቷ 100 ካ.ሜ ደግሞ መውጫ መግቢያ ሉኖረዉ አይችልም በሚል ተሸጦ እንድንካፈል መወሰኑ ባግባቡ ነዉ፣ ስምምነታችን እኩል ለመካፈል እንጂ ለአንደ ያነሰ የሚል አይደለም፣ ባጠቃላይ ቤትና ቦታዉ 250 ካ.ሜ ነው፣ አመልካች ቦታዉን ተካፍለን የየራሳችንን ካርታ እንዲንይዝ የተጠሪ ድርሻ 100 ካ.ሜ ብቻ ነዉ በማለታቸው ነው። ፍርድ ቤቱ በስምምነታችን መሰረት መዝገቡን ዘጋው ማለት፣ ቤትና ቦታው ክፍፍል ተጠቃል ተፈጽሟል ማለት አይደለም፣ በስምምነቱ መሰረት ተካፍል ካርታ በእጃችን አልገባም፤ መሀንዱስ በቦታው ተገኝቶ መካፈል እንደማይመች ገልጿል።
በመሆኑም የስር ውሳኔ ሉጸናልኝ ይገባል በማለት ጠይቋል። አመልካች በበኩላቸው በስምምነት ባለቀ ጉዲይ ድጋሚ ይሸጥ መባለ ስህተት ነው፣ አመልካች 100 ካ.ሜ. ነው አላልኩም፣ የተጠሪ ድርሻ 76.88 ካ.ሜ ብቻ ነዉ። ተጠሪ ስምምነቱን በማፍረሱ 5000 መቀጮ ያለበት በመሆኑ ይህን ለመንግስት እንዱከፍል ይወሰን፣በመሆኑም የስር ዉሳኔ ሉሻር ይገባል ሲለ ተራክረዋል።
ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተጠቀሰዉ ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የህግ ድንጋጌ አንጻር መርምረናል።
እንግዱህ ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር አጠቃላይ የክርክሩን ይዘት እንዲየነዉ የግራቀኙ ጋብቻ በፍቺ በመፍረሱ ምክንያት ይህን ተከትል በተጀመረዉ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ በዋናው ክርክር አከራካሪዉ ቤት የተጋቢዎቹ የጋራ ንብረት ነዉ፣ የእርሻ መሬቱ የአመልካች የግል ሀብት ነው ተብል ከተወሰነ በኋላ በአፈጸጸም በተጀመረዉ ክርክር ቤትና ቦታዉን እኩል ለመካፈል ተስማምተው ስምምነቱን መጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ/ም በፍርድ ቤት ካጸደቁ በኋላ በተግባር ለመከፊፈል አመቺ ያለመሆኑ በመረጋገጡ ታህሳስ 6 ቀን 2005 ዓ/ም ቤቱ በሀራጅ ተሸጦ ባልና ሚስቱ እንዱካፈለት ተወስኗል።
በመሰረቱ ባልና ሚስቱ በጋብቻ ጸንተዉ ባለበት ጊዜ ባፈሩት ንብረት ላይ የጋራ ባለሀብቶች እንደሚሆኑ በክልለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 73 እና 74 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘት የምንረዲው ጉዲይ ነው።በተያዘዉ ጉዲይ አከራካሪዉን ቤትና ይዞታ አስመልክቶ የጋራ ሀብት ነዉ ተብል ተወስኖ ያለቀ ሲሆን እያከራከረ ያለዉ አፈጻጸምን አስመልክቶ በእርቅ ለመካፈል የግራ ቀኙ ከተስማሙ በኋላ በማዘጋጃ ቤቱ በአይነት መካፈል አለመቻለን በተገለጸዉ መሰረት ፍርድ ቤት በሀራጅ ተሸጦ ሉካፈለ ይገባል በማለት የሰጠው ትዕዛዝ ነዉ። አከራካሪዉ ንብረት ላይ ተከራካሪዎቹ የጋራ ባለሀብት ነው ተብል ከተወሰነ ክፍፍለ መደረግ ያለበትም በዋናው ውሳኔ፤ስለባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል በሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስለ አፈፃጸም የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው። በዚህ አግባብ አፈጻጸሙን ከመምራት በተጨማሪ የግራ ቀኙ ያደረጉትና በፍርድ ቤት ያጸደቀ የእርቅ ስምምነት መኖሩ ከተረጋገጠም እርቁ እንደ ፍርድ የሚቆጠርና ሉፈፀም የሚገባው ሲሆን አፈጻጸሙ የሚመራውም በሕጉ አግባብ ነው። በመሆኑም ግራ ቀኙ ሉካፈለትም የሚገባዉ በተስማሙት መንገድ ነዉ። በስምምነቱ መሰረት ሉፈፀም ካልተቻለ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ባለው መሰረት ማስፈፀም እንዱሚችል ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 392 ድንጋጌ ይዘት መረዲት የምንችለው ጉዲይ ነው። ይህ ድንጋጌ ደግሞ በቤተሰብ ህጉ በተቀመጠው መፍትሄ መሰረት አፈጻጸሙን ለመምራት የሚያስችል።
ከግራ ቀኙ ክርክር እንደተገነዘብነዉ ተጠሪና አመልካች በጋራ ሀብታቸዉ ክፍፍል መጠን ላይ በፍርድ ቤት የጸደቀ ስምምነት መኖሩ ሳይክደ በዚህ ሰምምነት መሰረት ንብረቱ በአይነት ሉካፈል የሚችል በመሆኑ ላይ ግን ስምምነት ላይ ያለመድረሳቸዉን ነዉ። ይህ ከሆነ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ክፍፍለ አመቺ በሆነ መንገድ እንዱያልቅ ሉያደርግ (ሉያስፈጽም )የሚችል መሆኑን ከፍ.ብ.ሥ.ሥ/ህ ቁ 392 እና ከክልለ ቤተሰብ ህጉ ከአንቀጽ 101፣102 እና 103 ስር ክፍፍል እንዳት ሉፈጸም እንደሚችል ሰፍሯል። እንግዱህ እያከራከረ ያለዉ የአንደኛዉ ወገን ድርሻ በማነሱ ምክንያት ካርታ ሉወጣለት አልተቻለም የሚል በመሆኑ ክፍፍለ አጠቃላይ የንብረት መጠን ማእከል በማድረግ በእኩልነት መርህ የሚከናወን መሆኑ ተጠቃሹ ህግ ግዳታ የጣለ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ቤቱንና ይዞታዉን በመለየት የእርሻ መሬቱ የአመልካች የግል ንብረት ነዉ ሲለ የወሰኑት በዚህ ችልትም አከራካሪ ባለመሆኑ የሚነካ አይደለም። የቤቱን ክፍፍል አፈጻጸም አስመልክቶ ቤቱ የጋራ በመሆኑና ክፍፍለ ላይ ስምምነት ባለመኖሩ በሀራጅ ተሸጦ ይካፈለ የተባለዉ የክልለን የቤተሰብ ህጉን መርህ ሉከተል ስለሚገባዉ ከአንቀጽ 101-103 በተጠቀሰዉ መሰረት ኣጠቃላይ ይዞታዉ 250 ካ.ሜ ለመሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ ባልና ሚስቱ በፍርድ ቤት በፀደቀው ስምምነት መሰረት ይካፈለ፣በዚህ መሰረት ክፍፍለ የማይቻል ከሆነ አንደ ላንደ በስምምነቱ ድርሻ መጠን(Proportion) ከፍል እንዱያስቀር፣ይህ የማይሆን ከሆነ ደግሞ ቤቱ በገበያ ዋጋ ተሸጦ በስምምነቱ ድርሻ መጠን(Proportion) መሰረት የሽያጭ ገንዘብ እንዱካፈለ ማድረግ ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቤቱ ማካፈል አልተቻለም፣ ስለተባለ ብቻ ህጉ ያስቀመጠዉን ቅደም ተከተል ባለማገናዘብ በሀራጅ ተሸጦ ይካፈለ መባለ የግራ ቀኙን በቤቱ የመጠቀም ፍላጉት (ነጻነት) ስለሚገድብ ተቀባይነት ሉሰጠው የማይገባ በመሆኑ ያለቅድመ ሁኔታ በሀራጅ እንዱሸጥ የተሰጠዉን ትእዛዝ ክፍል ሉታረም የሚገባዉ ነዉ ብለናል።
ባጠቃላይ የክልለ ፍርድ ቤቶች ለአፈጻጸም የቀረበዉን አከራካሪዉን ቤትና ይዞታ በመቁ.04585 በእርቁ መሰረት ሉፈጸም ባለመቻለ አከራካሪዉ ንብረት አመቺ በሆነ መንገድ ሉካፈል ሲገባ በሀራጅ ይሸጥ ተብል መወሰኑ የቤተሰብ ህጉን የክፍፍል እኩልነት መርህ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በአ/ብ/ክ/መ/ የወልድያ ወረዲ ፍርድ ቤት በአፈጻጸም መ. መጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ,የሰሜን ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ በ26/04/2005 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰብ ሰሚ ችልት በመ. ሰኔ 24ቀን2006 የሰጠው ወሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ዉሳኔ ተሻሽሎል።
አከራክሪውን ቤትና ይዞታ የግራቀኙ የጋራ ሀብት በመሆኑ ክፍፍለን አስመልክቶ በክልለ የቤተሰብ ህግ ከአንቀጽ 101 እስከ 103 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች መሰረት 250 ካ.ሜ ለመሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ ባልና ሚስቱ በፍርድ ቤት በፀደቀው ስምምነት መሰረት ይካፈለ፣በዚህ መሰረት ክፍፍለ የማይቻል ከሆነ አንደ ላንደ በስምምነቱ ድርሻ መጠን(Proportion) ከፍል እንዱያስቀር፣ይህ የማይሆን ከሆነ ደግሞ ቤቱ በሒራጅ ተሸጦ በስምምነቱ ድርሻ መጠን (Proportion)፣ ስምምነት አለመኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ በእኩልነት መርህ መሰረት የሽያጭ ገንዘብ እንዱካፈለ ብለናል። በዚህ ውሳኔ መሰረት የወልዱያ ወረዲ ፍርድ ቤት አፈጻጸሙን እንዱያስቀጥል በፍ.ብ.ሥ.ሥ..ህ.ቁ 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
የግራ ቀኙ የወጪ ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
መስከረም 12 ቀን 2007 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።
No topics extracted.