የአፈፃፀም ችልቶች ስለፍርድ አፈፃፀም የተዘረጉትን ሥርዓቶች በመከተል እንደ ፍርደ ከመፈፀም በቀር የአንድ ፍርድ ይዘትን በመመልከት የፍርደን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፊት ረገድ ፍርድን የመተርጎም ሥልጣን የላላቸው ሥለመሆኑ፡የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 372፣378
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 14 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ አብድሽ አዱሽ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰብለ ዘውዳ -የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአፈጻጸም ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀረመው የአሁኗ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በሐረሪ ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ06/08/2002 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ የአፈጻጸም ክስ መሰረት ያደረገውም በሐረር ከተማ ከፍተኛ 2 ቀበላ 17 ክልል ውስጥ የሚገኘው፣ በ1280 ካ/ሜትር ስፊት ባለው ቦታ የሰፈረና ቁጥሩ 668 የሆነ፣ በካርታ ቁጥር 1035 የሚታወቀው የመኖሪያ ቤት ሲሆን ይህን ቤት በተመለከተ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት መሆኑን፣ለሁለት መከፈል የሚችል መሆኑን በተገቢው ባለሙያ አረጋግጦ ለተጠሪ በእጣ ምድብ "B" በ640 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ሶስት ክፍል ቤት፣ለአሁኑ አመልካች ደግሞ በምድብ "A" 640 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን አምስት ክፍል ቤት እንዱወስደ መወሰኑን ነው። በዚህ አግባብ እንዱፈፀምላቸው አፈፃጸሙን ለስር ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱን ግራ ቀኙን እንዱከራከሩ ከአደረገ በኋላ ፍርድ ቤቱ ላላ ባለሙያ መድቦ ቤቱ በአይነት ሉከፈል የሚችል መሆን ያለመሆኑንና ግምቱ ምን ያህል እንደሆነ አጣርቶ እንዱቀርብ አድርጓል። የስር ፍርድ ቤት የአፈፃጸም ችልት የመደበው ባለሙያም ቤቱ በአይነት ሉከፈል የማይችል መሆኑንና ቀድሞ የቀረበው የአይነት ክፍፍል የባለሙያ ሐሳብ ቤቱን ሙለ በሙለ ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑን፣ ግምቱም በፍሬ ነገሩ ጊዜ የተገመተው ብር 520,683.18 ሳይሆን ብር 365,080.60 መሆኑን ዘርዝሮ ሪፖርቱን ለፍርድ ቤቱ የላከለት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ በፍሬ ነገሩ ጊዜ የተሰጠው የባለሙያ አስተያየት ስህተት መሆኑ በአፈፃጸም ጊዜ ከሚመለከተው አካል በተመደበ ባለሙያ አስተያየት መረጋገጡን፣ በአፈጻጸም ጊዜ የተመደበው ባለሙያ ቤቱ በአይነት ቢከፈል ቤቱ እንደሚጎዲና ግምቱም ብር 365,080.60 መሆኑን ማረጋገጡን፣ይህ ከተረጋገጠ ደግሞ በዋና ፍርድ ቤት ጊዜ የተሰጠውን ውሳኔ በአፈጻጸም ጊዜ አመቺ በሆነ መንገድ ማስፈፀም እንደሚቻል በሕጉ የተፈቀደ መሆኑን፣ይዞታውን እኩል ማካፈል የሚቻል ቢሆንም ቤቱን ግን ጉዲት ሳይደርስበት በእኩል ማካፈል የማይቻል መሆኑን ጠቅሶና በአማራጭነትም ክፍፍለ በቀድሞው ክፍፍል ጊዜ አብዛኛው ቤት ያለበት ይዞታ ለአሁኑ አመልካች ደርሶ የነበረ መሆኑን፣አመልካች ከአስራ አምስት አመታት በላይ በቤቱ እየኖሩ ያለ መሆኑን፣በቀዲሚነት የግዥ መብት ስርዓትም ሁለት ሰዎች በእኩል ደረጃ የሚገኙ ሲሆን በይዞታ ላይ ላለው ሰው የቀዲሚነት መብት ያለው መሆኑ በሕጉ መመልከቱን መሰረት በማድረግ ቤቱ ያለበትን የይዞታ ክፍል የአሁኑ አመልካች እንዱወስደ፣ ቤቱ የላለበትን የይዞታ ክፍል ደግሞ ተጠሪ እንዱወስደ፣ በአፈጸጸም ጊዜ ተገምቶ በቀረበው ብር 365,080.64 ግማሹን ብር 182,540.32 አመልካች ለተጠሪ ሉከፍላቸው ይገባል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ችልቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት አፈጻጸሙን የመራው ከዋናው ፍርድ ውጪ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን የአፈጻጸሙን ውሳኔ በመሻር አፈጻጻሙ በዋናው ጉዲይ ላይ በመ/ በ01/07/2002 ዓ/ም በተሰጠው አግባብ ሉመራ ይገባል በማለት ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አፈፃጸሙን የመራው ቤቱ በአይነት ቢከፈል ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጪ የሚሆን ስለመሆኑና በዋናው ክርክር ጊዜ የቀረበው የባለሙያ አስተያየት ስህተት መሆኑን በማረጋገጥ እንዱሁም አመልካችም ከውጪ አገር መጥተው በቤቱ ላይ ለረዥም አመታት የኖሩበት መሆኑን በመገንዘብ አግባብነት ካላቸው ሕጎችና አስገዲጅነት ካለው የሰበር ውሳኔ አንጻር ሁኖ እያለ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አፈፃጸሙ በዋናው ፍርድ መሰረት መመራት አለበት ብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በነበረው የዋናው ክርክር የአሁኗ ተጠሪ ከሳሽ፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ሁነው መከራከራቸውን፣ የግራ ቀኙን ክርክር የሰማውና ተገቢውን ማጣራት ያደረደገው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ተገቢ ነው ያለውን ፍርድ መስጠቱን፣ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ ክርክር የተነሳበት ቤት ለአመልካች ቤቱን የሸጡትና የተጠሪ ወላጅ አባት (ኮልኔል ዘውዳ ወ/ማርያም) ሚስት የነበሩት ወ/ሮ እታፈራሁ ፈጠነ እና ተጠሪ (የሥር ከሳሽ) ያልተከፊፈለ የጋራ ሀብት መሆኑን ከዚህ ቀደም በመ/ቁ/00923 ታህሳስ 01 ቀን 2000 ዓ/ም ውሳኔ የተሰጠበት ጉዲይ ከመሆኑም ላላ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የሚያምኑት ጉዲይ መሆኑን፣ በዚሁ መሰረት ቤቱንና ቦታውን ለሁለት ማካፈል የሚቻል መሆኑንና አለመሆኑን፤ የሚካፈል ከሆነ የሚደርሳቸውን መጠን ገምቶ እንዱገልጽ የከተማው ማዘጋጃ ቤት በታዘዘው መሰረት በሰጠው ምላሽ ቦታውን ምድብ " A" ምድብ "B" አድርጎ በማካፈል ምድብ " A" 5 ክፍልች ያለበት ቤት ሆኖ ስፊቱም 640 ካሬ ሜትር መሆኑንና ግምቱም ብር 115,983.96 እንደሆነ፣ ምድብ " B " ደግሞ ስፊቱ 640 ካሬ ሜትር ሆኖ 3 ክፍልች ያለበት ቤት ሆኖ ግምቱም ብር 96,820 መሆኑን የገለጸ ስለሆነና ተከሳሽም ክርክር የተነሳበትን ቤት አጠቃልለው ይዘው የሚገኙ በመሆኑ ከሁለቱ ምድቦች መርጠው እንዱወስደ ዕድል ቢሰጣቸውም ለመውሰድ ፈቃደኛ ካለመሆናቸውም ላላ ዕጣ ተጥል የደረሳቸውን እንዱወስደ ቢደረግም ዕጣ ማንሳት እንደማይፈልጉ በመግለፃቸው ከሳሽ ዕጣ እንዱያነሱ ተደርጎ ምድብ "B" የደረሳቸው ስለሆነ የሁለቱን ምድቦች ድምር ግምት 212,803.96 ለሁለት ሲካፈል ብር 106,401 ስለሚሆን ተከሳሽ ልዩነቱን ብር 9,581 ለከሳሽ ከፍለው በምድብ "A" ያለውን ቤት እና ቦታ እንዱወስደ ሲል መወሰኑን፣ 166 ወራት የቤት ኪራይ በተመለከተም ተከሳሽ ቤቱን የገዙት ከከሳሽ የጋራ ባለሀብት ከሆኑት ከወ/ሮ እታፈራሁ ፈጠነ ሚያዚያ 30 ቀን 1987 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል ሆኖ እስካሁን ድረስ ቤቱን ይዘው የሚገኙ ሲሆን ከሳሽም ከቤቱ ድርሻ ያላቸው መሆኑን በፍርድ ቤት እስከሚወሰን ድረስ ሉያውቁ የሚችለበት ሁኔታ አልነበረም፣ ከሳሽ በቤቱ ላይ ግማሽ ባለመብት መሆናቸውን በፍርድ ከታወቀ በኋላም ከቤቱ የሽያጭ ገንዘብ ግማሹ ብር 65,000 ለከሳሽ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን ክርክሩ ስለሚያሳይና ቤቱን በቅን ልቦና ይዘው ቆይተዋል ለማለት ስለሚቻል ሉከፈለ አይገባም ሲል የወሰነ መሆኑን፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገን በማከራከር የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ የሚነቀፍ አይደለም በሚል ያፀናው መሆኑን፣ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካችም በሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔና በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የሰበር አቤቱታቸውን፣ተጠሪዋ ደግሞ የሰበር መስቀለኛ አቤቱታ ለዚህ ችልት በመ/ አቅርበው ይህ ችልትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን በ25/01/2005 ዓ/ም በዋለው ችልት መርምሮ የሐረሪ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 01280 በቀን 01/07/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/62252 በቀን 12/07/2003 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348 (1) መሰረት በማሻሻል የአሁኑ አመልካች የአሁኗን ተጠሪን የውርስ ድርሻ ይዘው ለተጠቀሙበት ጊዜ ኪራዩን ሉከፍለ አይገባም፣ እንዱሁም ለተጠሪዋ ምድብ "B" ውስጥ ያለውን የቤት ግምት በምድብ "A" ውስጥ ካለው የቤት ግምት ጋር ለማመጣጠን የልዩነት ገንዘብ ሉከፍለ አይገባም፣የአሁኗ ተጠሪ የአሁኑ አመልካች ላከናወኑት ተጨማሪ የአራት ክፍልች ግንባታ የወጣውን ወጪ በድርሻቸው መጠን ለመክፈል አይገደደም በማለት ወስኖ ከዚህ በፉት በስር ፍርድ ቤት ተጀምሮ በነበረው የአፈጻጸም መ/ቁ/ 0547 ክርክር ታግድ እንዱቆይ የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቶ በዚህ ችልት ውሳኔ መሰረት አፈጻጸሙ እንዱቀጥል በማለት ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በሕግ አግባብ ታይቶ የተሰጠ ፍርድ እንደ ፍርደ መፈጸም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያሳያለ። በእነዚህ ድንጋጌዎች በተዘረጋው ስርአት አግባብ በመመራት ካልሆነ በስተቀር በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ ሕጋዊ ባልሆነ እና ውሳኔውን ውጤት አልባ በሚያድርግ መልኩ ውድቅ ሉደረደግ የሚችልበት አግባብ አይኖርም።ድንጋጌዎች በግልጽ የሚያስገነዝቡት አቢይ ነጥብ የፍርድ አፈጻጸም ስርአት ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር ወይም ውጤት የሚለውጥበት ስርአት መሆኑን ነው። በልላ አገላለጽ የድንጋጌዎች አቀራረጽ ይዘትና መንፈስ በጥንቃቄ ሲታይም የፍርድ አፈጻጸም ስለፍርድ አፈጻጸም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የአፈጻጸም ስርአቱ ህጉን መሰረት ማድረግ ያለበትና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉን መሰረታዊ ዓላማ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአነስተኛ ወጪ ጊዜና ጉልበት በተፊጠነና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዱፈፀም በሚያስችል አግባብ ሕግ አውጪ ያስቀመጣቸው መሆኑን የምንረዲው ጉዲይ ነው።ውሳኔው የማይፈፀመበት ሕጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩም በፍርድ ቤቱ ታይቶ ተገቢው እልባት የሚሰጥበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 392 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው።ይህ ድንጋጌ አፈጻጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት አምፃፀሙን ምቹ ሁኔታዎች ሁለ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ በተቻለ መጠን ፍርደ ተግባራዊ የሚሆንበትን መንገድ ሉከተል የሚገባ መሆኑን ያሳያል።ስለሆነም አንድን ፍርድ እንደፍርደ ይዘትና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ መፈጸም የግድ የሚል ሲሆን ይህ ደግሞ የፍርድ አፈጻጻምን በተመለከተ በስነ ስርዓት ሕጉ የተዘረጉት ስርዓቶች በአግባቡ በማየትና ተፈፃሚ በማድረግ የሚከናወን መሆኑን የድንጋጌዎቹ ይዘት የሚያሳይን ጉዲይ ነው።በህግ አግባብ የተሰጠን ፍርድ በማስፈፀም ረገድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና 372 መሰረት ሥልጣን ያላቸው የአፈፃፀም ችልቶች ስለ ፍርድ አፈፃፀም የተዘረጉትን ሥርዓቶች በመከተል እንደ ፍርደ ከመፈፀም በቀር የአንድ ፍርድ ይዘትን በመመልከት የፍርደን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፊት ረገድ ፍርድን የመተርጎም ሥልጣን የላላቸው መሆኑ ይታወቃል።
የአፈጻጸም ክስ መቅረብ ያለበትም እንደ ፍርደ እንዱፈፀም ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ለአፈፃጸም ማመልከቻቸው መሰረት ያደረጉትና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት አያያዘው ያቀረቡት አከራካሪው ቤትና ቦታ ላይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን የክፍፍል ውሳኔ እና በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ25/01/2005 ዓ/ም ተሻሸል የፀናውን ውሳኔ ነው። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ምድብ "B" የደረሳቸው መሆኑ ተረጋግጦ ከምድብ "A" ቦታ ጋር ያለው ድምር ግምት ብር 212,803.96 ሁኖ ይህ ገንዘብ ለሁለት ሲካፈል ብር 106,401.00 ስለሚሆን የአሁኑ አመልካች ልዩነቱን ብር 9,581.00 ለተጠሪ ከፍለው በምድብ "A" ያለውን ቤት እና ቦታ አመልካች ሉወስደ እንደሚገባ ተወስኗል። ይህ የሚያሳየው በዋናው ክርክር ጊዜ ተገቢው መጣራት ተደርጎ በክፍፍለ ስርዓትና ቅደም ተከተል ላይም ግራ ቀኙ ስምምነት ሉያደርጉ ባለመቻለ የስር ፍርድ ቤት ተገቢ ነው ባለው መንገድ የቤቱና ይዞታው ግምት፣ግራ ቀኙ በንብረቱ ላይ ያላቸው ድርሻ እና ክፍፍለ በእጣ ሲከናወነንም ግራ ቀኙ የደረሳቸው ቤትና ይዞታው አቅጣጫ ጭምር ተለይቶ መወሰኑን ነው። በመሆኑም ቤቱና ይዞታው በዋናው ክርክር ጊዜ ምን ያህል ግምት እንዲለውና በምን አግባብ ክፍፍል እንደሚደረግ የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ታይቶና ተገቢው መጣራት ተደርጎ ከተወሰነ በኃላ በዋናው ክርክር ጊዜ ያለቀ የፍሬ ነገር ክርክር እንደገና በአፈጻጸም ተነስቶ በዋናው ክርክር ጊዜ የቀረበው ማስረጃ ሐሰተኛ/ተገቢነት/ የላለው ነው ተብል የሚቀርበው ክርክርም ሆነ አፈጸጸም ችልቱ በዚህ ረገድ የሚቀርበውን ክርክር ተቀብል ላላ ማጣራት በማድረግ የቀደመውን ማስረጃ ሐሰተኛ ነው በማለት የሚቀርበውን የባለሙያ አስተያየት የሚቀበልበት የአፈጻጸም ክርክር አመራር ስርዓት የለም። በዋናው ክርክር ጊዜ ስለ ቤቱና ቦታ ክፍፍል የቀረበው የባለሙያ አስተያየት በንብረቱ የአይነት ክፍፍል የሚያመጣውን ጉዲት ያለማገናዘቡ በዋናው ክርክር ጊዜ ይታይ ይችል የነበረ እንጂ በዋናው ክርክር ጊዜ ተቀባይነት ከአገኘ በኋላ በአፈፃጸም ክርክር የሚታይ አይሆንም።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሁኑን አመልካች በቤቱ ላይ ረዥም አመታት መኖራቸውን መሰረት አድርጎ የቀደምትነት መብት እንዲላቸው በማድረግ መወሰኑም ተገቢውን የክርክር ደረጃ ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። በእርግጥ ሕጉን መሰረት አድርጎ የተሰጠ የንብረት ክፍፍል ውሳኔ በአፈፃጸም ጊዜ የንብረቱ ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ትርጉም እንዲያጣ ተደርጎ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 392(1) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አግባብ አመቺ በሆነ ሁኔታ ተመርቶ መፈፀም ያለበት መሆኑ እሙን ነው። ይህ ግን ተከራካሪ ወገኖች ሕጉ በዘረጋው ስርዓት ክርክር አቅርበውና ፍርድ ቤቶቹም በሕግ አግባብ አጣርተው የወሰኑትን የዋና ክርክር ውሳኔ በሚሽር መልኩ ሉከናወን የማይገባ መሆኑን ስለአፈጻጸም ስርዓት ከሚደንግጉት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘብ ጉዲይ ነው።
በአጠቃላይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዋናው ውሳኔ ውጪ እና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 392 ድንጋጌ መሰረታዊ አላማ ጋር ባልተገናዘበ መልኩ የሰጠውን ውሳኔ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመሻር አፈጻጸሙ በዋናው ክርክር ጊዜ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ሉፈጸም ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጌዎች ይዘትና መንፈስ ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት ስላለገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አፈጻጻሙ በዋናው ጉዲይ ላይ በመ/ በ01/07/2002 ዓ/ም በተሰጠው አግባብ ሉመራ ይገባል በማለት መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።ይጻፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.