በሃራጅ ጨረታ ያሸነፈ አንድ አካል ያሸነፈውን ንብረት በስሙ ካዘወረና ካስተላለፈ በኋላ የሃራጅ ሽያጩ ሙለ በሙለ ከተፈፀመለት በኋላ፣ ንብረቱ በሃራጅ ከተሸጠበት ዋጋ ላይ እንዱቀነስለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢነት የላለው ስለመሆኑ፡የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.429፣441 እና 447 XXV
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 17 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጤታ አመልካችዎች፡- 1. ወ/ሮ አልማዝ አርዕያ - ተወካይ ለማ ሀይላ ቀረቡ 2. አቶ ፍቀሩ አርዕያ ቀረቡ 3. አቶ ደረሰ አርዕያ ቀረቡ 4. ወ/ሮ አለምነሽ መኮነን ተወካይ ሁለተኛ ተጠሪ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አሸናፉ አልታየ ጠበቃ እዩኤል ጀረኔ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካችዎች የሶድ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአፈፃፀም መዝገብ ሐምል 5 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የደቡብ ብሓርብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ ታህሳስ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ በሀራጅ የተሰጠበት ዋጋ ተቀንሶ እንዱከፈል የተሰጠ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ተገቢነት የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ እነ አልማዝ አርዕያ የአፈፃፀም ከሳሾች፣ አንተነህ አሰፊና ፍቀሩ አርዕያ የአፈፃፀም ተከሳሾች ሆነው በሚከራከሩበት የአፈፃፀም መዝገብ የውርስ ንብረት የሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሀራጅ እንዱሸጥ በአፈፃፀም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ተጠሪ በሀራጅ ጨረታው አሸናፉ በመሆን ንብረቱን በብር 1‚573‚000 /አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ብር/ ለመግዛት ተስማምቶ፣ የጨረታው አሸናፉ ሆኖ፣ የንብረቱን ሰባ ፏርሰንት በቼክ ገቢ በማድረግ፣ ገዝቷል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በሀራጅ የገዛው ቤት ስመ ንብረት፣ በጨረታ አሸናፉው በተጠሪ ስም እንዱዛወር፣ ሰባ ፏርሰንቱ የቤቱ ዋጋ ክፍያ እንዱፈፀምና፣ ታግድ ያለው የቤቱ ሰላሣ ፏርሰንት ዋጋ የማዛወር ሑደቱ ሲለቀቅና በያዘው ቦታ ላይ መንግስት ከውራሾች ወይም ግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የሚፈልገውን ዕዲ ከፍለው ሲጨርሱ ወይም ሽያጭ የተፈፀመበትን ንብረት ነፃ ሲያደርጉ ክፍያው እንዱፈፀም በማለት የካቲት 15 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላ አመልካችዎች ግንቦት 27 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የጨረታ አሸናፉው በጨረታ የገዛዉን ንብረት በስሙ አዛውሮ የጨረሰ በመሆኑ ቀሪውን ሰላሳ ፏርሰንት እንዱከፍል ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት አመልክተዋል የስር ፍርድ ቤት የጨረታው አሸናፉ /ተጠሪ/ የአመልካችዎችን ቀሪ ክፍያ ይዞ እንዱቀርብ ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠሪ ሰኔ 1ዐ ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በአራት አቅጣጫ አዋሳኝ ምልክቶቹ ተገልፀው በጨረታ አሸንፋ የገዛሁት ቤት በ134ዐ ካሬ ሜትር ስፊት ያለው መሆኑን ሰነድቹ ያሳያለ። ነገር ግን ስም ለማዛወር ቦታው ሲለካ 113ዐ ካሬ ሜትር ብቻ ሆኖ ሰለተገኘ የ21ዐ ካሬ ሜትር ቦታ ዋጋ ይቀነስልኝ በማለት ጥያቄ አቅርቧል። አመልካችዎች ይኽ የአመልካች ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም ካልሆነ የሀራጅ ሽያጩ ፈርሶ ንብረታችንን ያስረክቡን፣ ገንዘቡን እንመልስ በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የ21ዐ ካሬ ሜትር ቦታ ዋጋ /ሁለት መቶ አርባ ስድስት ሺ አምስት መቶ አሰራ አምስት ብር/ ተቀንሶለት ላላውን ገንዘብ ይክፈል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካችዎች ይህንን የአፈፃፀም ትዕዛዝ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ አፅንቷል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበዋል። የሰበር ችልቱ የአመልካችዎችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም።
አመልካችዎች ጥር 7 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ተጠሪ የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገው የሀራጅ ሽያጭ ከዘጠኝ ሰዎች ጋር ተወዲድረው አሸናፉ ሆነዋል።
የካቲት 15 ቀን 2005 ዓ.ም የገቡት ስመ ሀብት እንዱዛወርላቸው እና ሰባ ፏርሰንት ክፍያ እንዱከፈለን ትዕዛዝ ተጥቷል። ተጠሪ የሀራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ ያቀረቡት አቤቱታ የለም። ከዚያ በኋላ ዋጋ እንዱቀነስላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የሕግ ስርዓቱን ያልተከተለ ሆኖ እያለ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንን ጥያቄ ተቀብለው የሰጡት ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በሀራጅ የገዛሁት ቦታና ንብረት ስም ሲዛወር ተለክቶ የተገኘው ቦታ ልዩነት ያለበት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ሉዝ ዋጋ አስልተው ከቤቱ ዋጋ መቀነሳቸው መሰረታዊ የሕግ ሰህተት የለበትም በማለት የካቲት 19 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ መልሶ ሰጥተዋል። አመልካች መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅረበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥ በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በሀራጅ ጨረታ ንብረቱን ከገዛበት ዋጋ ተቀንሶ ሉዝ ዋጋ ሑሳብ 21ዐ ካሬ ሜትር ቦታ ለአመልካችዎች እንዱከፍል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገው የሀራጅ ሽያጭ ተወዲዲሪ ሆኖ ቀርቦ በብር 1‚573‚000 /አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሰባ ሶስት ሺ ብር/ የሀራጅ ሽያጭ አሸናፉ ሆኗል። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሀራጅ ሽያጩን ዋጋ ተጠሪ በቼክ እንዲስያዘ ገልፆ፣ ሰባ ፏርሰንቱ ለአመልካችዎች እንዱከፈል፣ ሰላሳ ፏርሰንቱ ስመ ሀብቱ እስኪዛወር እንዱቆይ የካቲት 15 ቀን 2005 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አመልካችዎች ግንቦት 27 ቀን 2005 ዓ.ም አፈፃፀሙን ለያዘው የስር ፍርድ ቤት፣ የንብረቱ ስመ ሀብት ወደ ተጠሪ የተዛወረና ተጠሪ ንብረቱን የተረከበ በመሆኑ ቀሪ ሰላሳ ፏርሰንት የንብረቱን ዋጋ እንዱከፈል ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት ነው።
በመሰረቱ የስር ፍርድ ቤት የሀራጅ ሽያጭ አሸናፉ የሆነው ተጠሪ የጨረታው አሸናፉ ከሆነበት፣ ከየካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ባለት አስራ አምስት ቀናት፣ የገዛውን ንብረትሙለ ዋጋ በፍትሐብሕር ስነ-ስርዓት ሕግ ቁጥር 441 መሰረት ሙለ በሙለ ገቢ እንዱያደርግ ማድረግ ሲገባው፣ ሰባ ፏርሰንቱን የንብረቱን ዋጋ ብቻ ተጠሪ በቼክ እንዱከፍል አድርጎ ሰላሳ ፏርሰንቱ የንብረቱ ዋጋ በተጠሪ እጅ እንዱቆይ ማድረጉ፣ ተጠሪ ንብረቱን የገዛው ፍርድ ቤት ባወጣው ሀራጅ ማስታወቂያ ፍርድ ቤት በመደበው ሀራጅ ባይ በኩል ከፍርድ ቤቱ ሆኖ እያለ፣ በሀራጅ ሽያጩ ውስጥ ምንም አስተዋፅኦ የላላቸውንና ፍርድ ቤት የሸጠውን የቤት ዋጋ በሕግ አግባብ ተቀብል ሉከፍላቸው ከሚገባቸው አመልካችዎች፣ ከተጠሪ ጋር አላስፈላጊ ክርክር ውስጥ እንዱገቡና በዚህም መጉላላትና ኪሳራ እንዱደርስባቸው የሚያደርግ ስርዓት የስር ፍርድ ቤት የተከተለ መሆኑን ያሳያል።
የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በሀራጅ የገዛውን ንብረት ሙለ ዋጋ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 441 በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ሙለ በሙለ ገቢ እንዱያደርግ አድርጎ ቢሆን ኖሮ፣ የቤቱ ስመ ሀብት ለተጠሪ መዛወሩን እንዲረጋገጠ፣ ተጠሪን ሣይጠራ፣ ቀሪው የቤቱ ዋጋ ለአመልካቾች እንዱከፈል ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር። ፍርድ ቤቱ ይህንን አስገዲጅ ስርዓት ባለመከተለ ተጠሪ በሀራጅ የገዛውን ቤት ሙለ ዋጋ የመከፈል ግዳታውን የሚቀንስለት ወይም የሚሻሻልለት፣ አይሆንም። ከዚህ በተጨማሪ የሀራጅ ሽያጩ የተከናወነው የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም ነው። ተጠሪ የገዛሁት ንብረት የይዞታ መጠን በሰነድ ከተገለፀው 134ዐ ካሬ ሜትር ሣይሆን 113ዐ ካሬ ሜትር ሆኖ ተገኝቷል በማለት አቤቱታ ያቀረበው፣ የቤቱ ስመ ሀብት በስሙ ካዛወረና ንብረቱን ከተረከበ እንደዚሁም አመልካችዎች ቀሪው የቤቱ ዋጋ ይከፈለን ብለው ግንቦት 27 ቀን 2005 ጥያቄ አቅርበው፣ ፍርድ ቤቱም ተጠሪ ቀሪውን የቤቱን ዋጋ ገቢ እንዱያደርግ ግንቦት 3ዐ ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም መሆኑን መዝገቡ ያሳያል።
ተጠሪ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም ላቀረበው ጥያቄ እድል የሰጠው የስር ፍርድ ቤት የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 441 አስገዲጅ ድንጋጌ በጥብቅ ባለመከተለና በድንጋጌው መሰረት አፈፃፀሙን ባለመምራቱ ነው። እንደዚሁም ተጠሪ በሰነድ የሚታየው በሀራጅ የተሸጠለት ቤት የይዞታ መጠንና ቦታው፣ ሲለካ የተገኘው የይዞታ መጠን ልዩነት አመልካችዎች በፈፀሙት የተንኮል ድርጊት የደረሰ ስለመሆኑ የገለፀውም ሆነ ያስረዲው ነገር የለም።
ተጠሪ አዋሳኝ ምልክቶቹ በፍ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 228 ንዐስ አንቀፅ 2 ተለይተው በሀራጅ ማስታወቂያ ተገልፆ፣ ካርታውና ኘላኑ ላይ የቦታው ስፊት 1340 ካሬ ሜትር መሆኑ ተገልፆ፣ ፍርድ ቤቱ በሀራጅ የሸጠለት ንብረት ይዞታ፣ ስም በማዛወር ልኬት ሲፈፀም 113ዐ ካሬ ሜትር ብቻ መሆኑን እንደተረዲ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 447 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት የሀራጅ ሽያጩ እንዱሰረዝ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ማመልከቻ የለም። ይህ ከሆነ፣ ተጠሪ ንብረቱን በስሙ ካዛወረና፣ ከተላለፈ በኋላ የሀራጅ ሽያጩ ሙለ በሙለ ከተፈፀመለት በኋላ፣ ንብረቱ በሀራጅ ከተሸጠበት ዋጋ ላይ እንዱቀነስለት ያቀረበው ጥያቄ የስነ ስርዓት ሕጉን ያልተከተለና ሕጋዊ ዕውቀትና ውጤት ሉሰጠው የማይገባው ነው።በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የ21ዐ ካሬ ሜትር ቦታ ዋጋ በሉዝ ሑሳብ /ሁለት መቶ አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ አስራ አምስት ብር/ ተቀንሶለት፣ ቀሪውን ገንዘብ ይክፈል በማለት የሰጡት ውሳኔ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 441፣ አንቀፅ 447 እና አንቀፅ 429 ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የሶድ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምል 5 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ታህሳስ 1 ቀን 2ዐዐ6 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪ ለአመልካችዎች ሉከፍል የሚገባው በሀራጅ ጨረታ ቤቱን አሸንፍ የገዛበትን ብር 1‚573‚000 /አንድ ሚሉዮን አምስት መቶ ሰባ ሶሰት ሺ ብር/ ሰላሳ ፏርሰንት ሙለ በሙለ ነው በማለት ወስነናል።
ተጠሪ ይህንን ገንዘብ ሙለ በሙለ አጠቃልል ለመከፈል ፈቃደኛ ካልሆነ የስር ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 429 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ አፈፃፀሙ እንዱቀጥል ማድረግ ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።