ለአፈፃፀም መነሻ የሆነን ፍርድ ይግባኝ በመጠየቅ ሳያሽሩ ወይም ሳያሻሽለ በዋናው ጉዲይ ሉነሱ የሚገባቸውን የክርክር ነጥቦች በአፈፃፀም በተያዘው መዝገብ የክርክር መሰረት ማድረግ ተገቢ ወ/ሮ በድሪያ መሐመድ እና አቶ አደም ዐመር
No summary available.
ሐምል 13 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቁጠታ አመልካች፡- ወ/ሮ በድሪያ መሐመድ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አደም ዐመር ቀረቡ መዝገቡን መርመረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት መቋረጡን ተከትል የተነሳው የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ አመልካች አመልካች ደግሞ ተጠሪ በመሆን ነው። ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ ከ1980 እስከ 2001 ዓ.ም እንደባልና ሚስት አብረው በሚኖርበት ጊዜ የአመልካች አባት አሮጌ አፈር ቤት ሉሾ በማድረግ እና ደረጃው 12 በረንዲ ቆርቆሮ በመቀየር ተጠሪ ማሳደሳቸው እንዱሁም ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤት እንዱሰሩ አብረው ሲኖሩ የተለያዩ የቤት መገልገያ ዕቃዎች ማፍራታቸውን መሰረት በማድረግ ንብረቱ የሚቻል ከሆነ በዓይነት እንዱከፈለ የማይቻል ከሆነ በሀራጅ ተሽጦ እኩል እንዱካፈለ ተጠሪ በዲኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ይዘት ያለው ክስ አቅርቧል።
የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት የመከላከያ መልስ በወላጅ አባታቸው ቤት የተደረገ እድሳትም ሆነ የተቀየረ በረንዲ እንደላለ የተሰሩ ሁለት ሰርቪስ ቤቶች መኖራቸው አምነው ተጠሪ ተክተው አፍርሰው መውሰድ እንደሚችለ ዛፍች የአመልካች አባት የተከለዋቸው እንደሆነ፣ አመልካች በተጠሪ ከሚከራየው ቤት ድርሻቸው እንዱያካፍላቸው ጠይቋል።
የሥር ፍርድ ቤትም በተጠሪ በኩል የቀረበ ምስክሮች ያዲመጠ ሲሆን አመልካች ግን ማስረጃ አለማቅረባቸውን በውሳኔው ገልጾ በፍሬ ጉዲዩም ሁለት ሰርቪስ ቤቶች ግራ ቀኙ በጋራ እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ የተሰሩ የጋራ ንብረት መሆናቸው እንደታመነ መዝግቦ፤ በአመልካች በኩል በቀረበው ክርክር ተጠሪ የተሰራውን ሰርቪስ ቤት አፍርሰው ይውሰደ የሚለውን ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 40/3/ እንደተመለከተው መሬት የመንግስትና የህዝብ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንዲልተቀበለው የአመልካች አባት አሮጌ ቤት በጋራ ማደሳቸው ከ30-40 የሚሆኑ ዛፍች በጋራ መትከላቸው መረጋገጡን እንደሁም የጋራ የተባለትን የቤት ዕቃዎች በመለየት ሁለት ሰርቪስ ቤቶች አንድ የደጅ ሽንትቤት ቧንቧ እና በግምት ከ30-40 ዛፍች የጋራ ንብረት ስለሆነ በዓይነት መክፈል የሚቻል ከሆነ በዓይነት ይህ ካልተቻለ ዎጋ በማይቻል ይህ ካልተቻለ በስምምነት በመሸጥ ይህ ካልተቻለ በሐራጅ በመሸጥ ሽያጩ እኩል እንዱከፈለ ቀደም የነበረው ሳልንና መኝታ ቤት በ12 ቆርቆሮ በረዲ የተሰራበት እና በኦብጀዲድ እና በሽራ ኮርኒስ የተሰራበት ገንዘብ በባለሙያ ተገምቶ የግምቱ ግማሽ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ ላልች የቤት ዕቃዎችም እንዱከፈለ ወስኗል።
የሥር ፍርድ ቤት በከ.መ.ቁ.28071 በ24/07/2004 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ማብራሪያ የሚፈልግ በመሆኑ በፍርድ አፈፃፀም መመሪያ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ በ30/08/2005 ዓ.ም መብራሪያ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በሰጠው መብራሪያም ባህርዛፍን የተተከለበት ቦታ መምራ እኩል እንዱካፈለ በአጠቃላይ ውሳኔ ያረፈባቸው ሰርቪስ ቤቶች ቧንቧ እና ባህርዛፍች ከእነ ይዞታቸው ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ አዟል። አመልካች ይህንን ትዕዛዝ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥነው ጉዲዩ የሰበር ይመርመር በመባለ በግራ ቀኙም የጽሐፍ ክርክር አደርጓአል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ዋና ፍሬ ነገር ለክርክሩ መነሻ የሆነውን በአባታቸው የመሬት ይዞታ የተሰሩትን ሰርቢስ ቤቶችን እና ተተከለ የተባለ ዛፍች ተጠሪ አፍርሰው ወይም ግምት ወስደው ከሚሰናበቱ በቀር አኩል የሚካፈለበት ምክንያት አይኖሩም በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች ለአፈፃም መነሻ የሆነውን ፍርድ የግባኝ ጠይቀው ሳያሸሩ በአፈፃፀም ጊዜ የክፍፍል ሥርዓቱ መቃወም እንደማይችለ ሰርቪስ ቤቱም በደመወዛቸው እንዱሰሩት የሥር ፍርድ ቤት ከነይዘታው እኩል እንዱከፍለ የሰጠው ትዕዛዝ የሚነቀፍ ነጥብ የለም የሚል መልስ አቅርበዋል። አመልካች ባቀረቡት የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራራሯል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝ ፍርደን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ ይዘት ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል። እንደመረመርነውም በሥር የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደገለፀው ግራ ቀኙ እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ እንደነበር ከአብራካቸው ሓዋን አዲም የተባለችው ልጅ እንደተወለደች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ሰርቪስ ቤቶች የደጅ ሽንት ቤት ቧንቧ እና ግምቱ ከ30-40 የሆኑ ዛፍች የጋራ ንብረት እንደሆኑ፤ የክፍፍል ሥርዓቱም ከተቻለ በዓይነት፤ ካልተቻለ ዋጋ በማቻቻል ካልተቻለ በስምምነት በመሸጥ ይህ ካልተቻለ በሀራጅ በመሸጥ እኩል እንዱከፍለ በኮ.መ.ቁ. 28071 በ24/07/2004 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቲል። ይህ ውሳኔ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወይም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የተሻረ የተሻሻለ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበ ክርክር የለም። የፍርድ አፈፃፀም የሚመራው ፍርድ ቤት እንደ ፍርደ የማያስፈፀም ግዳታ አለበት። ተጠሪ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ባስቀመጡት አግባብ የአፈፃፀም ክስ አቅርበዋል። ፍርድ ቤትም መጀመሪያ በሰጠው ፈርድ መሰረት እንዱፈፀም በ3ዐ/ዐ8/2ዐዐ5 ዓ.ም በሰጠው የመብራሪያ ትዕዛዝ ግልጽ አደርጓአል።
የአሁኑ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አልነበረም የሚል ቅሬታ ከነበራቸው በሕጉ የተዘረጋው የይግባኝ ሥርዓት ተጠቅመው መብታቸው ሉያስከብሩ ይገባ ነበር ለአፈፃፀም መነሻ የሆነውን ፍርድ ይግባኝ በመጠየቅ ሳይሻሩ ወይም ሳያሻሽለ በዋናው ጉዲይ ሲነሱ የሚገባቸው የክርክር ነጥቦች በአፈፃፀም በተያዘው መዝገብ የክርክር መሰረት ለማድረግ የሚያስችላቸው ሕጋዊ ምክንያት የለም። በእርግጥ አመልካች በአፈፃፀም የተያዘው ጉዲይ በአፈፃፀም ጊዜ እንደ ፍርደ ለመፈፀም የሚያስችለ ሕጋዊ ምክንያቶች መኖራቸው ካሳዩ ሥርዓቱን ጠብቀው አቤቱታ የማቀርብ መብት አላቸው። ከዚህ ውጭ ግን በዋናው ጉዲይ ሰርቪስ ቤቶች፣ የደጅ ሽንት ቤት እና ባህር ዛፍች እኩል እንዱካፈለ ግልጽ ውሳኔ በተሰጠበት ሁኔታ በአፈፃፀም ወቅት ሰርቪስ ቤቶቹ የተሰሩት በአባቴ ይዞታ ነው በማለት ብቻ የአፈፃፀም ሂደቱን ለማቆም የሚያስችል የሕግ መሰረት የላቸውም። የሥር ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙ ከመረመረ በኃላ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 392/1/ እና /2/ መሰረት እንደ ፍርድ እንዱፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች በመ/ በ24/07/2004 ዓ.ም የተሰጠው ፍርድ መሰረት በማድረግ የተከፈተው አፈፃፀም እንደ ፍርደ እንዱፈፀም ትዕዛዝ መሰጠታቸው ሕጉን ተግባራዊ አድርጓል ከሚባል በቀር የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
1/ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.28071 በ30/08/2005 ዓ.ም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ1/4/2006 ዓ.ም የሰጡት ትዕዛዝ ጽንቷል።
2/ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች እና ተጠሪ የሚከራክረው የሰርቪስ ቤቶች የደጅ ሽንት ቤት እና ባህር ዛፍ እንደ ፍርደ እንዱፈጽሙ የሰጠው ትዕዛዝ ፍርደን መሰረት ያደረገ ነው በማለት ወስነናል። አመልካች በፍርድ አፈፃፀም ጊዜ እንደ ፍርደ እንዲስፈጽም የሚገድብ ሕጋዊ ምክንያት ካለ ሥርዓቱን ጠብቀው አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው በዚህ ፍርድ አልተገደቡም /አልተነካም/።
3/ የሰበር ችልት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙን የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
1/ ከዚህ ችልት ታህሳስ 15 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የተሰጠው ዕግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
2/ መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.