በመመሪያ ቁጥር 4/2004 መሰረት በልዩ ሁኔታ በንግድ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ሉሟለ ስለሚገባቸው እነ አቶ ዱንሳፊ ያዕቆብ/ሦስት ሰዎች/ እና ወ/ሮ አየለች በቀለ ሒምላ 14 ቀን 2007 ዓ.ም 373 77. የህብረት ሥራ ማህበራት በመሰረታዊነት ለትርፍ ተብል የሚቋቋሙ ሳይሆን የአባላቱን ፍላጕት በአነስተኛ ወጪ ለሟሟላት የሚቋቋሙ በመሆኑ ለትርፍ ስራ የሚሰሩ የንግድ ስራዎች የሚያስፈልጋቸውን የንግድ ፊቃድ እንዱያወጡ የሚገደድበት አግባብ የላለ ሥለመሆኑ የኃብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 ማሻሻያው አዋጅ ቁ. 402/96 አንቀጽ 6
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/103717 ሐምል 03 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- የወንጂ ስኳር ፊብሪካ ሰራተኞች ሸማቾች ህብረት ስራ ኃ.የተ.የግል ማህበር ተወካይ ጥላሁን ንዋይ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- የአዲማ ወረዲ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የቀረበ የለም።
መዝገቡ ተመርመሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉደዩ በአዋጅ ቁጥር 147/1991 መሰረት የተቋቋመ ሸማቾች ህብረት ስራ ኃ.የተ.የግል ማህበር በአዋጅ የንግድ ፊቃድ የሚያስፈልገው መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። ክርክር የጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁን ተጠሪ እና በአቶ ዘላለም ታዬ በወ/ሮ በድሪያ ሁሴን እና በአቶ ዮናስ አስፊው ላይ በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የክስ ይዘትም አመልካች ቁጥራቸው 205 በሚሆኑ አባላት በአዋጅ እና 402/96 ድንጋጌዎች አግባብ የተቁቋመ ሆኖ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ የማህበሩን እባላትና የአካባቢው ህብረተሰብ እያገለገለ መቆየቱን በወንጅ አካባቢ ወፍጮ ቤትና ዲቦ ቤት ከፍቶ አገልግልት በመስጠት ላይ እያለ የተጠሪ ሰራተኞች የሆኑትና የስር ከ2ኛ እስከ 4ኛ የተጠቀሱት እነ አቶ ዘላለም ታዩ አመልካች እየሰራ ያለውን ሰራ ንግድ ፍቃድ እንደሚያስፈልገው አመልካች እንደማያስፈልገው አመልካች እየነገራቸው ግንቦት 09 ቀን 2005 ዓ.ም ወፍጮ ቤትንና ዲቦ ቤቱን ያለአግባብ ያሸጉት መሆኑን በዚህ አድራጕት ምክንያትም አመልካች ሲያገኝ የነበረውን ገቢ ያሳጡና ለሰራተኞቹም ያለ ምንም ገቢ ደመወዝ እንዱከፍል ያደረጉ መሆኑን በዚህ ምክንያት የታጣ ገቢ መጠንና አመልካች ላይ የደረሰውን ወጪ አይነቱንና መጠኑን በመጥቀስ ተጠሪ በሕገወጥ መንገድ ያሸገውን የወፍጮ ቤትና የዲቦ ቤት እንዱከፍት የተቋረጠ ገቢና ያለአግባብ ወጪ የሆነ ገንዘብ በድምሩ ብር 34.982.28 ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍል ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቁ የሚያሳይ ነው ። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 147/91 የተቋቋመ ቢሆንም ከዚህ አዋጅ በኃላ የወጣው አዋጅ ቁጥር 686.2002 ማንኛውም የንግድ ስራ የንግድ ፍቃድ የሚያስፈልገው መሆኑ መደንገጉን በመቀነስ ከህግ የአወጣጥ ጊዜ ቅደም ተከተል አንፃር ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሆኑን አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት የመቆጣጠር ስራ ደግሞ የተጠሪ መሆኑ እና ተጠሪ በሰራተኞቹ አማካኝነት ኃላፉነቱን ሲወጣ ላከናወነው የማሸግ ስራ ለታጣ ጊዜ የሚጠየቅበት የህግ አግባብ የላለ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የሥር 2ኛ 3ኛ፣ እና 4ኛ ተከሳሾች የተጠሪ ስራተኞች በመሆናቸው በግላቸው የሚከሰሱበት አግባብ የለም በማለት ከክሱ ውጪ ከአደረጋቸው በኃላ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለውን ክርክር መርምሮ ከሕግ አወጣጥ የጊዜ ቅደም ተከተል አንፃር በኃላ የወጣው አዋጅ ቁጥር 686/2002 ሆኖ ይህ አዋጅ በአንቀጽ 31/2/ እና 42 ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ ማንኛውም የንግድ ስራ የሚሰራው በንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚደነግግ መሆኑን እንደሚያስገነዝብና ይህ አዋጅ የአዋጅ ቁጥር 147/91 በአዋጅ ቁጥር 402/96 እንደተሻሻለው አዱስ አዋጅ በመሆኑ የበላይ ተፈፃሚነት አለው በማለት አመልካች ያለ ንግድ ፍቃድ የወፍጮ ቤትና የዲቦ ቤትን ስራ ሉሰራ አይችልም የንግድ ስራን የመቆጣጠር ኃላፉነት ደግሞ የተጠሪ በመሆኑና ተጠሪ ይህንኑ በሕጉ የተሰጠውን ኃላፉነት ሉወጣ ለታጣ ገቢ ኃላፉ የሚሆንበት አግባብ የለም በማለት የአመልካችን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጏታል በዚህ ውሳኔ የአሁን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ተብል አቤቱታው ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በጉዲዩ ልዩ ህግ የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/91 በአወጅ ቁጥር 402/96 እንደተሻሻለ ሆኖ እያለ የበታች ፍ/ቤቶች አግባብነት የላለውን አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት በማድረግ አመልካች ለሚያከናውናቸው የወፍጮ ቤትና የዲቦ ቤት ስራዎች የንግድ ፍቃድ ያስፈልገዋል። በማለት መወሰናቸው ያለአግባብ ነው የሚል ሲሆነ አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱያከራክር አድርጓል።
በክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታም መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጓጌዎች አንፃር ጉዲዩ እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ለጉዲዩ ያዘገት ያለው ህግ የትኛው ነው? የሚለው ነጥብ ሆኖ አግኝቶታል።
ለክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቸለው አመልካች በአዋጅ ቁጥር 147/91 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 402/96 የተቋቋመ መሆኑንና የወፍጮ ቤትና የዲቦ ቤት ክፍቶ ሲሰራ መገኘቱ ግራ ቀኙን ያላከራከሩ ጉዲዩች መሆናቸውን ግራ ቀኙ እያከራከረ ያለው የሕግ ነጥብ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 686/2002 በተደነገገው አግባብ የንግድ ፊቃድ የሚያስፈልገው መሆን ያለመሆን የሚመለከት ነጥብ ስለመሆን ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 686/2002 በአዋጅ ቁጥር 147/91 እና አዋጅ ቁጥር 402/96 በኃላ የወጣ አዱስ አዋጅ መሆኑና ይህ አዋጅ በማንኛውም የንግድ ስራ የንግድ ፊቃድ የሚያስፈልገው መሆኑን መደንገጉን መሰረት በማድረግ አዱስ አዋጅ ለጉዲዩ የበላይ ተፈፃማነት አለው በማለት ወስነዋል። በመሆኑም ይህ የበታች ፍርድ ቤቶች ይህን አተረጓጕምና አተገባበር የተጠቃሽ ሕጏችን ሙለ ይዘትና መንፈስ የተከተለ መሆን ያለመሆን እንደሚከተለው አይተናል።
በመሰረቱ የህብረት ስራ ማህበት የፋዳራል ደረጃ አዋጅ ቁጥር 147/1991 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 402/1996 እንዱሁም በደንብ ቁጥር 106/1996 መሰረት የተደራጀ ሲሆን።
ክልልቹም የየራሳቸውን አዋጆች ቀርፀው እነዚህ ማህበራት የሚገዙበትን ስርዓት ዘግተዋል።
ፋዳራልም ሆነ በክልል የተቋቋመበት የንብረት ሥራ ማህበራት በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዲዩች ላይ በመሳተፊ ለአባባልቻቸውና ለጠቅላላው ሕብረተሰብ የራሳቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። እነዚህን አካላት ያደራጀ ህጏች ይዞታቸውና መንፈሳቸው ሲታይም ማህበራቱ የራሳቸውን የቻለ አደረጃጀትና ልዩ ባህሪያት ያላቸው መሆኑን ያስገነዝባለ።
የህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991አንቀጽ 2/2/ ሲታይ የህብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች በፍቃደኝነት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታታ የሚያቋቁሙትና ዱሞክራሲያዊ በህግ መንገድ የሚያስተዲድሩት ማህበር ነው። በሚል ትርጉም ያስቀመጠ ሲሆን የድንጋጌ ይዘቱና መንፈስ ሲታይ በሕብረት ስራ ማህበራት ለማህበራዊነት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፍ ሲባል የሚደራጅ መሆኑን ያሳያል። አዋጅ ቁጥር 147/91 እና በዚሁ አዋጅ ማሻሻያ የሆነው አዋጅ ቁጥር 402/97 ድንጋጌዎች ሲታይ የንብረት ሥራ ማህበራት ከበጏ አድራጏት ድርጅቶችም ሆነ ከንግድ ማህበራት የሚለዩበት ባህሪያት ያሎቸው መሆኑን ያሳያለ።
በህጏቹ ከተቀመጡት መለያ ባህሪያት አንደ ማህበራት የሚቋቋሙበት ዓላማ ሲሆን የህብረት ሥራ ማህበራት የሚቋቁሙበት ዓላማ የአባላትን ተመሳሳይ ፍላጏት በአነስተኛ ወጪ ለማሟላት እንጅ በአባላት ትርፍ ለማስገኘት ተብል የማይቋቋም መሆኑን ያሳያል። አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 4 በተለይ ሲታይም የህብረት ስራ ማህበራት የሚቋቋሙበትን ዓላማዎች የዘረዘረ ሲሆን በዝርዝሩ ውስጥ ለአባላት ትርፍ ለማስገኘት የሚያስችል ሥራ እንደሚሳተፍ አይገልጽም።
የተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 35 ድንጋጌ አንድ ማህበር ለአባላት ወይም በዚህ አዋጅ መሰረት ለተቋቋመ ላላ ማህበር ካልሆነ በቀር ብድር መስጠት እንደሚችል የደነገገው ሲሆን ይህም ማህበር በትርፍ ተብል የሚቋቋሙና መሰረታዊ ግባቸው የአባላቱን ፍላጏት በአነስተኛ ወጪ ማሟላት ነው የሚለውን ድምዲሜ የሚያጠናክር ነው። የህብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀት ሲታይ የህብረት ሥራ ማህበር አባል ለመሆን አንድ ሰው 14 ዓመት የሞላው የማህበሩን ዕጣ ለመግዛትና የመመዝገቢያ ክፍያ ለመክፈል የሚችልና የማህበሩ ደንብና የተለያዩ አዋጆችን ለማክበር ፍቃደኛ ላሆን እንደሚገባ ሕጉ የሚያሳይ ሲሆን የማህበራት ስያሜም አዋጅ በአንቀጽ 8 ማንኛውም ማህበር መመሪያ ስም ሲኖረው እንደሚገባ ስሙ በመጨረሻ ኃላፉነቱ ስያሜም አዋጅ በአንቀጽ 8 ማንኛውም ማህበር መጠሪያ ስም ሉኖረው እንደሚገባ ስሙ በመጨረሻ ኃላፉነት የተወሰነ የኃብረት ሥራ ማህበር የሚለ ቃላት መያዝ እንደሚገባ አንድ ማህበር በተመዘገበበት ስምና ምልክት ላላ ማህበር ሉጠቀምበት እንደማይችል ሕጉ አስቀምጧል። ላላው ስለ ህብረት ስራ ማህበር በሕጉ የተቀመጠው ጉዲይ ማህበራቱ ያላቸው ልዩ መብቶች ናቸው። አዋጅ ቁጥር 147/1991 እና የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ የሆነው አዋጅ ቁጥር 402/96 ድንጋጌወች ሲታዩ ለህብረት ሥራ ማህበራት ልዩ መብቶች እንዲሎቸው ያሳያለ። በሕጏቹ ከተመለከቱት ልዩ መብቶች የማህበራት ዕዲ በቀዲሚነት እንዱከፈል የተቀመጠው ደንብ የህብረት ሥራ ማህበራት የአለበትን ዕጣ ወይም ጥቅም የማቻቻል የኃብረት ሥራ ማህበራት በመንግስት የሚሰጧቸው ልዩ ልዩ ድጋፍችንና የንግድ ፍቃድን የሚመለከቱ ጉዲዮችን የሚሸፈኑ መሆኑን አዋጆቹ ያሳያለ።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ ተግባራት ያለው የንግድ ፍቃድን የሚመለከተው ልዩ መብት ሲሆን አዋጅ ቁጥር 402/96 አንቀጽ 6 ስር ማህበራት ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ የንግድ ፍቃድ ሳያስፈልጋቸው በማንኛውም የንግድ ሥራ ላይ መሰማራት ይችላለ በሚል ተቀምጧል።
በዚህ ረገድ የተቀመጠው ድንጋጌ ግልጽ ነው። ሆኖም የንግድ ፈቃደ ልዩ መብት ንግድን ያለንግድ ፊቃድ ለማከናወን የሚፈቅድ በመሆኑና ማህበራቱ ከሚሰሩት ስራ ውጭ ባለ የንግድ ሥራዎችም ተፈፃሚ ላሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 686/2002 እና 813/2006 ሉገዙ ያሰቡትን የንግድ ውድድርን ትርጉም ሉያሳጣው ይችላል የሚል ክርክር ላቀርብበት የሚችል መሆኑ እሙን ነው።
ወደ አዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረታዊ አላማ ስንመጣ የንግድ ዘርፍ የሀገሪትን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚደግፍበትን ሁኔታ የማጠናክር የንግድ ምዝገባና የንግድ ስራ ፊቃድ አሰጣጥ ሥርዓትን በአግባቡ በሚደራጁት የንግደን ዘርፍ ጏጂና ተገቢ ያለሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከለ በንግድ ዘርፍ መንግስት ሉኖረው የሚገባውን መረጃ ሰበአግባቡ ለመያዝ የሚያስችለውን ሁኔታ ማመቻቸት እና ለንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሆኔታዎችን መፍጠር ስለመሆናቸው በአዋጅ አንቀጽ 3 ስር በግልጽ ተቀምጧል። የአዋጅ ተፈፃሚነትን በተመለከቱም የንግድ ፈቃድን የሚመለከቱ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች በዚህ አዋጅ አንቀጽ 30 ንዕስ ለአንቀጽ /1/ ከተመለከቱት የንግድ ስራዎች በስተቀር በልላ ማናቸውም የንግድ ሥራ በተሰማራ ሰው ላየ ተፈፃሚ ይሆናለ ሲል የደነገገው ሲህን በአዋጅ አንቀጽ 30/1/ ስር የተመለከቱት የንግድ ስራዎች ደግሞ በማዕድን ፍለጋና ልማት የውሃ ነክ ስራወች ግንባታ አገልግልትን ሳየጨምር በልዩ ለዩ ውሃ ነክ ሥራዎች በባንክ መድን እና ማይክሮ ፊይናንስ ንግድ ሥራወች በአየር ማመልከቻና አገልግዘለት ስራ ሬዱዮ አክቲብ ቁሶዎችንና ጨረር አመንጪ መሳሪያወችን በሚመለከቱ የንግድ ስራዎች በቴላኮሚኒኬሽን አገልግልት የኤላክትሪክ ማመንጨት ማስተላለፍ አከፊፈል ወይም መሸጥ ንግድ ሥራ በቀርና ተኩል መስሪያወች ጥገና እድሳትና ፈንጅ ሽያጭ ሥራ በባህርና የሃገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት ንግድ ሥራ የመልቲ ሞዲል ትራንስፖርት ንግድ ሥራ የዕቃ ማከማቻ ቤት ንግድ ሥራ እና በትምባሆና የትምባያ ውጤቶች ንግድ ሥራ መሆናቸውን የዘረዘረ ሲሆን አግባብ ላቸው ላልች መስሪያ ቤቶች ከሚሰጡ ፊቃድች በስተቀር ላልች የንግድ ስራ ፊቃድች የሚሰጡት እንደአግባቡ በሚኒስተሩ ወይም በቢሮው ወይም በኢትዮጵያ ኢንበስትመንት ኤጀንሲ ስለመሆኑም ይህው ድንጋጌ ያሳያል።
የአዋጅ አንቀጽ 31/1/ ማንኛውም ሰው የፀና የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖረው የንግድ ሰራ መሥራት እንደሚይችል በኃይል ቃል የደነገገ ሲሆን የአዋጅ አንቀጽ 42 ድንጋጌም ተገቢው የንግድ ሥራ ፊቃድ ሳይኖረው በልላ አይነት ፊቃድ ይህ አዋጅ ፈፃሚ የሚሆንበት የንግድ ሥራ ሲካሄድ የነበረ ማገኛውም ሰው ይህንኑ ሥራ ለማካሄድ ይህ አዋጅ ከመጣበት ቀን ጀመሮ በ12 ወራት ውስጥ አግባብ ያለውን ቅጽ ሞልቶ ማመልከቻ በማቅረብ ተገቢውን የንግድ ሥራ ፊቃድ ማውጣት እንዲለበት በአስገዲጅነት ደንግጓል።
እነዚህን የአዋጅ ቁጥር 686/2002 ድንጋጌዎች ስንመለከት በሕጉ ንግድ ፊቃድ የሚያስፈለጋቸው ተግባራት ተለይተው የተቀመጡ በመሆኑ በህጉ ተዘርዝረው የተቀመጡ ውጩ ያለት የንግድ ስራዎች ፊቃድ የሚያስፈለጋቸው መሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው በማለት መደምደሚያ ይቻላል።
ይሁን እንጂ የድንጋጌወቹን ተፈፃሚነት በአወጅ ቁጥር 147/91 እና በአዋጅ ቁጥር 402/96 መሰረታዊ አላማና ከማህበራት ልዩ ባህር አንፃር ማየቱ ተገቢነት ይኖረዋል። በመሆኑም ማህበራት በመሰረታዊነት ለትርፍ ተብል የሚቋቋሙ ሳይሆን የአባላቱን ፍላጕት በአነስተኛ ወጪ ለሟሟላት የሚቋቋሙ በመሆኑለትርፍ ስራ የሚሰሩ የንግድ ስራዎች የሚያስፈልጋቸውን የንግድ ፍቃድ እንዱያወጡ የሚጋደድበት አግባብ የለም። አዋጅ ቁጠር 402/96 አንቀጽ 6 ድንጋጌም በዚህ ረገድ ግልጽ የሆነ ይዘት ያለው በመሆኑ ማህበራት የንግድ ፍቃድ አያስፈልጋቸውም በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 31/1/ እ 42 ድንጋጌዎች ስር ማንኛውመ የንግድ ስራ የንግድ ፍቃድ እንደሚያስፈልገው የተቀመጠው ድንጋጌ ከማህበራቱ መሰረታዊ አላማና ባህርይ አዋጅ ቁጥር 686/2002 ሉያሳካው ካሰበው ግብ አንፃር ታይቶ ተግባራዊ ላሆን የሚገባው እንጂ አዋጅ የወጣበትን ጊዜ ብቻ መሰረት በማድረግ ለማንኛውም የንግድ ስራ ተፈፃሚነት እንዱኖረው ላደረግ የሚገባው ሆኖ አልተገኘም። ከዚህ አንፃር ጉዲዩን ስንመለከተው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 147/91 እና በማሻሻያው የሚገዛ ነው። ከተባለ ደግሞ የተጠሪ አድራጕት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2027/2028 እና 2035 መሰረት ሕገ ወጥ በመሆኑ በአመልካች ላይ ለደረሰው የጉዲት ካሳ ኃላፉነት ይኖርበታል። የጉዲት ካሳ መጠኑ ግን በስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ያልታየ በመሆኑ በዚህ ችልት እልባት የሰጠው ሆኖ አልተገኘም። በአነዚህ ሁለ ምክንያቶች ተከታዮን ወስነናል።
በአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 01 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 22 ቀን 2006 ዓ.ም በክለለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የሆነው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በአወጅ ቁጥር 147/91 እና በማሻሻው በተቋቋመና የሚገባ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት የንግድ ፊቃድ እንዱወጣ አይገደድም ብለናል። በመሆኑም የተጠሪ እርምጃ ሕግ ነው ብለናል። ተጠሪ እሽጉን ሉያሳይ ይገባል በአመልካች ላይ የደረሰውን የጉዲት ካሳ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2027/2028 እና 2035 የመክፈል። ሀላፉነት አለበት ብለናል። የጉዲት ካሳ መጠኑን በተመለከተ ግን የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ሉወሰን ይገባል በማለት በዚህ ነጥብ ብቻ ጉዲዩን በስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343/1/ መሰረት መልስን ልከንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.