በሞተ ሰው ሥም የተመዘገበን የአክስዮን ድርሻ ላይ ሟቹ እንደተገኘ ተቆጥሮ የሚተላለፍ ውሳኔ አግባብነት የላለው ሥለመሆኑ እና ተፈፃሚነት ያለው በንግድ ህጉ የተቀመጠው የሦስት ወር ጊዜ ሳይሆን በፍ/ሕ/ቁ 1845 የተመለከተው የአስር ዓመት ይርጋ ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.416 የፍ/ሕ/ቁ.1845 XXIV
No summary available.
ሐምል 3 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ለልሰገድ ምጆ- ጠበቃ ደሳለኝ ድረስ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 13 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ብይንና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 18 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ ይርጋ የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ የሚወለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ያቀረበው ክስ ነው። ከሳሽ እናቱን ወ/ሮ አማራች ኦዲ በቀድሞው ወረዲ 5 ቀበላ ዐ6 በአዱሱ አጠራር አዱስ ከተማ 10/11/12/ የመደብ ቁጥሩ 1 የሆነ የቅቤ ንግድ ችርቻሮ የሚነግድበት መደብ ነበራቸው በአካባቢው ያለ ነጋዳዎች ተደራጅተው አክሲዮን ማህበር 1990 ዓ.ም ሲመሰርቱ እና የአንደኛ ተከሳሽ መሥራች አባል ሆነው አንድ የአክሲዮን ድርሻ ነበራቸው። እናቴ ወ/ሮ አማረች ኦዲ ታህሳስ 27 ቀን 1997 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ሆኖም እናቴ ታህሳስ 27 ቀን 1997 ዓ.ም መሞቷ እያታወቀ አንደኛ ተከሳሽ መጋቢት 24 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የአክሲዮን ማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ በህይወት እንደለች በማስመሰል ስሜን በአባላት ሥም ዝርዝር ላይ በመፃፍና ሀሰተኛ ቃለ ጉባኤ በማዘጋጀት በአክሲዮን ማህበሩ የነበረትን አንድ የክሲዮን ድርሻ ለሁለተኛ ተከሳሽ እንደሸጠች አድርጏ የአክሲዮን ባለቤትናቱን ለሁለተኛ ተከሳሽ አዛውሯል። ይህንን በሀሰት የተከናወነ ተግባር የተፈፀመ መሆኑን ያወቅሁት በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ሀሰተኛ ቃለ ጉባኤ ተሽሮ የአክሲዮን ድርሻው የወ/ሮ አማረች ኦዲ ወራሽ በሆንኩት በከሳሽ ስም እንድመዘገብ ውሣኔ ይሰጥልኝ የሚል ይዘት ያለው ክስ አቅርቧል።
ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ አቅርበዋል። ተጠሪዎች በከሳሽ እናት ስም የነበረው የክሲዮን ድርሻ ለሀለተኛ ተከሳሽ /ሁለተኛ ተጠሪ/ የተወሰነው መጋቢት 24 ቀን 1998 ዓ.ም ነው። የአንደኛ ተከሳሽ ባለ አኪስዮኖች ጉባኤ ቃለ ጉባኤ የካቲት 9 ቀን 1999 ዓ/ም በሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ቀርበው ተመዝግቧል። ከሳሽ ቀለ ጉበኤው እንዱሻር መጠየቅ የሚችለው መጋቢት 24 ቀን 1994 ዓ/ም ጀምሮ ወይም ቃለ ጉባኤው በተመዘገበበት የካቲት 9 ቀን 1999 ዓ/ም ጀምሮ ባለት ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ነው ከሳሽ ጥያቄ ያቀረቡት ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ/ም በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል።
የሥር ፍርድ ቤት ተከሳሾች ያቀረቡት መቃወሚያ የንግድ ህግ ቁጥር 4/6(2) መሰረት ያደረገ ነው በማለት የከሳሽ ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን ሰጥቷል። አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሀምላ 22 ቀን 2006 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት የቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የሰጡት ብይን ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ክስ ያቀረበው፣ አንደኛ ተጠሪ ተህሳስ 27 ቀን 1997 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችውን ወላጅ እናቴ፣ በህይወት ያለች በማስመሰልና መጋቢት 24 ቀን 1998 በተደረገው የባለአክስዬኖች ጉባኤ ስሜን በመመዝገብ ሀሰተኛ የሆነ ቃለ ጉባኤ በማዘጋጀት የእናቴን ድርሻ ለሁለተኛ ተጠሪ እንዱተላለፍ በመወሰን የአክሲዮን ድርሻዎን ለሁለተኛ ተጠሪ አስተላልፎል። አንደኛ ተጠሪ ይህንን ተግባር የፈፀመ መሆኑን ያወቅሁት በጥቅምት ወር 2005 ዓ/ም በማለት ነው። ይህም የአመልካች ጥያቄ አንድ ሰው የሲቪል መብትና ግዳታ የሚኖረው ከተወለደበት ቀን አንስቶ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ መሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1 የተደነገገ ሆኖ እያለ አንደኛ ተጠሪ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለያች በኃላ እናቴን በባለአክሲዬኖች ጉባኤ ላይ እንደተገኘች አድርጎ በሀሰት በመመዝገብ የአክሲዬን ድርሻ ዝውውር ፈፅሟል የሚል ይዘት ያለው ነው።
አንድ ሰው የሲቪል መብትና ግዳታ የሚኖረው በህይወት ባለበት ጊዜ መሆኑ ሟች ከዚህ ዓለም በሞት ከተለያየ በኃላ በሟች መሞት የማይቋረጡ መብቶችና ግዳታዎች ለወረሾቹ የሚተላለፍ መሆኑ በፍተብሓር ህግ ቁጥር 1 እና በፍትሐብሕር ህግ ቀጥር 826 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። ማናቸውም አክስዬን ማህበር፤ በመመሥረቻ ፅሐፍም ሆነ በመተዲደሪያ ደንቡ ወይም በባለአክሲዬኖች ጉባኤው በህይወት የላለ የአክስዮን ባለ ድርሻ በህይወት አንዲለ ተደርጎ በባለአክሲዮን ጉባኤ ላይ ስሙ እንዱመዘገብና በለ አክሲዮኑ ከሞተ በኃላ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ በሰጠው ውሳኔ በህይወት እንዲለ ተቆጥሮ እንዱፈፀምበት ለመደንገግ መብትና ሥልጣን የለውም። ይህም የሚያሳየው አመልካች የሚያቀርበው ጥያቄ በሟች ምትክ የሟችን ወራሽ መጥረትና በባለአክሲዮኖች ጉባኤ እንዱሳተፍ ማድረግ ሲገባው የአክሲዮን ማህበሩ መሥራች የሆነችው ወላጅ እናቴ በሞት የተለያች መሆኑን እያወቀ በሞት ከተለየች ከአንድ ዓመት በኃላ በግል አክሲዮኖች ጉባኤ ላይ እንደተገኘች አድርጎ ስሟን በመመዝገብና የሀሰት ቀለ ጉባኤ በማዘጋጀት የፈፀመው የአክሲዮን ድርሻ ዝውውር ፈራሽ ይሁንልኝ በማለት ነው።
ይህ የአመልካች ጥያቄ ህግ አውጭው በንግድ ህግ ቁጥር 416 ንዐስ አንቀፅ 2 የሶስት ወር የይርጋ የጊዜ ገደብ ሲደነግግ ተሳቢ ካደረጋቸው ጉዲዮች ጋር አንድ አይነት ካለመሆኑም በላይ አንድ አክሲዮን ማህበር ባለ አክሲዮኑ ሲሞት የባለአክሲዮኑ ወራሾች ሣይጠራ የሞተውን ባለ አክሲዮን በባለአክሲዮን ጉባኤ ላይ የተገኘ በማስመሰል የወራሾቹን መብትና ጥቅም የሚጎዲ ውሣኔ ቢወሰን ወራሾች የባለአክሲዮን ጉባኤ የተደረገ መሆኑንና የባለአክሲዮኖች ጉባኤ የእነርሱን መብትና ጥቅም የሚጎዲ ውሣኔ መወሰኑና ቃለጉባኤውን ማስመዝገቡን እንዳትና በምን ሁኔታ ያውቃለ? ወራሾች ይህንን ሣያውቁ በንግድ ህግ ቁጥር 416 ንዐስ አንቀፅ 2 የተመለከተው የጊዜ ገደብ ቢያልፍ ሁኔታውን ለማስቀየር በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ክስ ማቅረብ አለባቸው የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሣ ነው።
አንድ ሰው በፍርድ መብቱን ለማስከበር ጥያቄ የሚያቀርበው መብቱ ከተጣሰበት ወይም በመብቱ ሉሰራበት ከሚችልበት ቀን ጀምሮ መሆኑን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1846 ተደንግጓል ። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ያቀረበው ጥያቄ በንግድ ህግ ቁጥር 416 ንዐስ አንቀፅ 2 በተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ ቀሪ የሚሆን አይደለም ። ከዚህ አንፃር አመልካች ጉዲዩን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ባለት አስር ዓመታት ውስጥ የአክሲዮን ማህበሩን ጥያቄውን በማቅረብና በክፈ ልቦና የአክሲዮን ድርሻው ተላልፍላቸዋል የሚላቸውን ሰዎች ላይ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻል መሆኑ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1677 ንዐስ አንቀፅ 1 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1845 በጣምራ በመተርጎም ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ አንፃር አመልካች ጥያቄውን ያቀረበው ከላይ የገለፅነው የአስር ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ሳያልፍበት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ላቀረበው የዲኝነት ጥያቄ አግባብነት የላለውን የንግድ ህግ ቁጥር 416 ንዐስ አንቀፅ 2 በመጥቀስ ጉዲዩ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል ።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ብይንና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ተሸሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በማለት ወስነናል ።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ አመልካችና ተጠሪ በላልች ነጥቦች ያቀረቧቸውን ክርክሮችና የግራቀኙን ማስረጃ በመስማት ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.