የሽርክና ውል ስምምነት አለ ለማለት መሟላት ሥለሚገባቸው መስፈርቶች የንግድ ህግ 5፣10(1)፣210(1)፣211፣215 እና 229(2)
No summary available.
ሐምል 01/2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አያላው ወልዳ ዩሐንስ - ጠበቃ ስንታየሁ ባሕሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጀማል ሰማን ኑር - ጠበቃ አማኑል ኩመራ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናለ ።
ጉዲዩ የሽርክና ውል ስምምነት የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ነው። የሥር ፍርድ ቤቶች በአመልካች የቀረበው ክስ ውድቅ በማድረጋቸው ምክንያት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታይልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የንግድ ቤት በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተከሳሽ ከነበረው በአዱስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 1 የቤት ቁጥር 1088 ተከራይተው ሲሰሩ እንደቆዩ፤በዚህ ቤት በሥር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ /የአሁኑ ተጠሪ/ ከነበረው ሰኔ 21 ቀን 2002 ዓ.ም በተፈፀመ የሽርክና ውል የቁርስ ቤት ንግድ ሥራ በጋራ ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን አስተዲደሩ የአከራይ ተከራይ መመሪያው ያለአግባብ በመተርጎም ለተጠሪ አከራይተሃል በማለት የኪራይ ውል ማቋረጡን በአግባቡ አይደለም።ተጠሪም የንግድ መደብሩ ያለአግባብ ይዘው ስለሚገኙ እንዱለቁ፤በተፈፀመው የሽርክና ውል ግዳታ መሰረት ውለን ለማፍረስ የሞከሩ ስለሆነ የገደብ መቀጮ ለአመልካች ብር 10,000.00 ለመንግሥት ብር 5,000 እንዱከፍለ ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት የመከላከያ መልስ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱ ፡በአመልካች እና ተጠሪ ተደረገ የተባለው የሽርክና ውል በንግድ ሕጉ መሰረት የማይታወቅ ነው።
የተደረገ መዋጮ የለም።የንግድ ቤቱን ሰኔ 21 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው ውል መከራየታቸው ፤በየወሩም 2500 ብር እንደሚከፍለ፤የሽርክና ውል የፈረሙት አመልካች ስለአስፈራሩዋቸው በሕጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም ?የሚለው በጭብጥነት ሉያዝ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት የተቻለው አመልካች እና ተጠሪ ተደረገ የተባለው የሽርክና ውል በሕጉ አግባብ የተመሰረቱ ስለመሆኑ ጉዲዩን ለማጣራት የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ የሽርክና ውል የለም ከሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጣቸው መሰረታዊ ነጥቦች የሽርክና ስምምነቱ በጽሐፍ ከመደረጉ በቀር አብሮ የመሥራት የመተባበር እንዱሁም የትርፍና ኪሣራ ክፍፍል ሥርዓት ምን እንደነበር የተገለጸ ነገር የለም ሲል በውሳኔው አስፍሯል። በመሰረቱ አንድ የሽርክና ማህበር የሚቋቋመው በንግድ ሕግ አንቀጽ 10/1/ እንደተመለከተው የንግድ ሥራ ለማከናወን ሲሆን ፣ የንግድ ሥራ ምን እንደሆነም በዚህ ሕግ አንቀጽ /5/ ሥር ተዘርዝሯል። የንግድ ማህበር /ሽርክና/ትርጓሜ መሰረታዊ ባህርያት በንግድ ሕግ አንቀጽ 210/1/ እና 211 በዝርዝር ተመልክቷል። የሸርክና ማህበር ሕጋዊ ሰውነት ያለው በሽርኮቹ ውል የሚቋቋም ዓላማውም ኢኮኖሚያዊ ተግባር ለማከናወን ስለመሆኑ፤ሽርኮቹም አብረው ለመሥራትና ለመተባበር የተስማሙ፤ከሚገኘው ተርፍም ሆነ ከሚመጣው ዕዲ ተከፊይ እንደሚሆኑ ከንግድ ሕግ አንቀጽ 211፣215 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው። ሽሪኮቹ የመዋጮ ዓይነት ልክ መወሰን እንደሚችለ፤መዋጮው በገንዘብ ፣በዓይነት ወይም በጉልበት ላሆን እንደሚችል ፤ይሁንና የመዋጮው ዓይነት ልክ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር መዋጮዎቹ ብዛታቸው እኩል እንደሚሆን፤ለማህበሩ ዓላማ የሚስማሙ እንዱሆኑ እንደሚያስፈልግ የንግድ ሕግ አንቀጽ 229/2/ በግልጽ ደንግጓአል ።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመልስ የሥር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ሥልጣኑ በአመልካች በኩል የቀረቡ ምስክሮች ከተጠሪ ጋር የሽርክና ውል ተፈራርመዋል ያለ ቢሆንም ውለ ሲፈረም የሽርክና ውል ስምምነቱ መዋጮ ምን ያህል እንደሆነ እንደማያውቁ በአንፃሩ በተጠሪ በኩል የቀረቡ ምስክሮች ከ1997 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ ሱቁን ተከራይቶ ይሰራ እንደነበር የሽርክና ውለም ሉዋዋል መሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ ውድቅ እንዱሆን ማመልከታቸውን ያሳያል።
የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በአመልካች እና ተጠሪ መካከል በሕግ አግባብ የተቋቋመ የሽርክና ማህበር የለም ። በተጠሪ የቀረቡ ምስክሮች የግራ ቀኙ ግንኝነት የአከራይ ተከራይ መሆኑን ሚዛን በሚደፊ መልኩ ማስረዲት የቻለ መሆናቸው ችልቱ መገንዘቡን በመግለጽ የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጏታል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም ። ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔን በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ይቅረብ በመባለ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር አድርጓል።አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የግራ ቀኙ ግንኝነት በሽርክና ውል የተመሰረቱ ስለ መሆኑ አመልካች ድርጅቱ ከነ ፉቃድ እና መልካም ስምና ዝናው ሉያዋጡ ተጠሪ ደግሞ የመነገጃ ገንዘብ እንዲቀርቡ ፤የሽርክና ውለ አለመመዝገቡ ውድቅ እንደማይሆን እንደ የእሽሙር ማህበር ሉወሰድ እንደሚገባ፣የ73 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ እና ላላ የገቢ ምንጭ የላላቸው መሆናቸው የአከራይ ተከራይ ግንኙነት መመሪያ ቁጥር 4/2004 ዓመት ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው በመግለጽ ተከራክሯል። ተጠሪ በበኩላቸው በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የነበረው ግንኙነት የአከራይ ተከራይ መሆኑን አስተዲደሩ ማጣራቱ ፤አመልካች የሽርክና ማህበር ለመመስረት የሚያስችል ምንም ያዋጡት ነገር አለመኖሩን ፣የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በማጣራት መወሰኑ ፤የመመሪያ ቁጥር 4/2004 ተጠቃሚነኝ የሚለው ክርክር መቅረብ የነበረበት ለአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች መሆኑን፤የሥር ፍርድ ቤቶች የሽርክና ውል የለም በማለት መወሰናቸው በአግባቡ ነው፣ሉጸና ይገባል በማለት መልስ ያቀረቡ መሆኑን ተረድተናል ።የአመልካች የመልስ መልስም አቤቱታቸውን የሚያጠናክር ነው።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር፤ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመርነውም የሥር ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል ተፈረመ የተባለው የሽርክና ውል በንግድ ሕግ የተመለከቱት መሰረታዊ መመዘኛዎች ያሟላ አይደለም በማለት ውድቅ ሉያደርግ የቻለው ከሳሽ/አመልካች/ ውለን ካልፈረምክ ከሱቁ አስወጣሃለው በሚል አስገድደውት እንደሆነ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት የአከራይ ተከራይ ግንኙነት መሆኑን የሽርክና ስራ እንደማይሰሩ መመስከራቸውን ውሣኔው ማስፈሩን ተረድተናል።የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ያረጋገጠውን ጉዲይ ይዘን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር ስናገናዝበው በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የንግድ ሕጉ በደነገገው አግባብ በጋራ መስራትና መተባበር ፤መዋጮ ስለመኖሩ ፤ከድርጅቱ ከሚገኘው ትርፍ የተደረገ ክፍፍል ስለመኖሩ የቀረበ ክርክር የለም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ በግራ ቀኙ የተደረገው የሽርክና ውል በንግድ ሕግ አንቀጽ 211 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የተመለከቱት አስገዲጅ መመዘኛዎች ስለመሟላታቸው በሕጉ አግባብ የቀረበ ክርክር የለም። በመሆኑም በአመልካች እና ተጠሪ መካከል ተመሰረቱ የተባለው የሽርክና ማህበር በንግድ ሕጉ በተመለከተው የሽርክና ማህበር ማቋቋሚያ መስፈርት ያልተቋቋመ በተግባርም መሬት ላይ የላለ መሆኑ ከአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት መረዲት ይቻላል። ይህ ከሆነ ደግሞ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ግንኙነት በሽርክና ውል ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የሥር ፍርድ ቤት እንዲለው የአከራይ ተከራይ ግንኙነት ነው።
አመልካች በሰበር ቅሬታቸው የተደረገ መዋጮ መኖሩ፣የትርፍ ክፍፍል ሰለመደረጉ እና ሽርክናው በ 3ኛ ወገን አለመታወቁ ውጤቱ የአሽሙር ማህበር የሚመለከት እንደሆነ ፍርድ ቤት ግንዛቤ አለመወሰደን ክርክር አቅርበዋል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ግራ ቀኙ ግንኙነት በሽርክና ውል ላይ የተመሰረቱ ስለመሆኑ ተደረገ የተባለው ስምምነትም አረጋጋጭ በማድረግ አቅርበዋል።የአመልካች የክርክር መስመር ከሥር ፍርድ ቤት ጀምሮ ከተያዘው ጭብጥ የሚጣጣም ካለመሆኑ በተጨማሪ የሽርክና ውል በቀረበበት ሁኔታ ስለመዋጮ እና የትርፍ ክፍፍል ሥርዓት በተመለከተ ግን ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደ እሽሙር ማሕበር ግንዛቤ እንዱወሰድ ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት የለውም።በልላ በኩል አመልካች አቅመ ደካማና የ73 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ በመሆናቸው የመመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 6.1 ተጠቃሚ ሉሆኑ እንደሚገባ በሰበር አቤቱታቸው ገልጸዋል። በመሰረቱ አመልካች ያቀረቡት ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.329(1) ሥር የተመለከተው ፍሬ ሐሳብ ያላገናዘበ ነው።ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የመመሪያው ልዩ ተጠቃሚ መሆን ነበረብኝ በማለት ያቀረቡት ክርክር በግራ ቀኙ ነበረ ከተባለው የሽርክና ውል ስምምነት የማይጣጠም ነው።ጉዲዩም መቅረብ ከነበረበትም ለአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ነው በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ማድረጋቸውን በሕግ አተረጓጏምና አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸማቸውን አያሳይም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.194434 በ12/09/2005 የሰጠው ፍርድ፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.138064 በ 21/02/2006 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ጸንቷል ።
በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተመሰረቱ የሽርክና ማሕበር የለም ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ። የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.