የሽርክና ማህበር በህግ አግባብ ተቋቁሞ እየሰራነው ለማለት በጽሁፍ ውል መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተዋዋይ ወገኖች በጋራና በተናጥል በመተባበር በመስራት ከጥቅሙም ይሁን ከእዲው በጋራ ሲጋሩ እንደነበር መረጋገጥ ያለበት ሥለመሆኑ፣ አንድ የሽርክና ማህበር በህጉ አግባብ ተቋቁመ ለማለት የሚቻለው ተዋዋይ ወገኖች ተነጻጻሪ ሣይሆን ተደጋጋፉ የሆነ ግብ ይዘው መዋጮ በማውጣት አብረው በመስራትና በመተባበር ትርፍና ኪሣራም በህጉ አግባብ እየተጋሩ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ማከናወናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 211፣229፣269/1/
No summary available.
ሐምል 01 ቀን/2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሪት ፀሀይነሽ በቀለ ጠበቃ ደረጀ ኢተቻ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ወ/ሪት ንግስት ተክላይ ጠበቃ ላ/ክ/ስንታየሁ ደመቀ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የሽርክና ውል መሰረት በማድረግ የቀረበ ክርክር ሲሆን የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን አመልካች የስር ፍ/ቤቶች በሰጡት ፍርድና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ያቀረቡት አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘት ፡- በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተፈረመ የሽርክና ውል መኖሩን፤ ተጠሪ በሽርክና ውል ስምምነት መሰረት ለትርፍ ክፍፍል እንዱያመች የወጪና ገቢ ሪፖርት የማቅረብ ግዳታ እያላቸው አላቀረቡም ። ተጠሪ በውል የተረከቡትን የንግድ ድርጅት ሽርክና ውለ ጊዜ ያለው በመሆኑ በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 የቤት ቁጥር 014 የሆነው የከሳሽ ድርጅትን እንዱያስረክቡ፤ የድርጅቱ ገቢና ሂሳብ ተሰርቶ በሂሳብ ስራው ውጤት ለአመልካች የሚደርሳቸው ትርፍ ወይም አመልካች በክሳቸው ባቀረቡት ግምት ብር 150,000 ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፈላቸው የጠየቁ መሆኑን የሚሳይ ነው።
ተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የመከላኪያ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ዋና ፍሬ ነገሩ፡- የሽርክና ውል የተባለው በህጉ የተቀመጠው መስፈርት አያሟላም። የንግድ ቤቱ ከሚመለከተው አካል የተከራዮት በመሆኑ አመልካች መጠየቅ አይችለም። የመንግስት ቤት ለ3ኛ ወገን በማከራያታቸው የተወሰደ እርምጃ ህጋዊ ነው። የሽርክና ውለ የማስመሰል ውል ነው።አከራይ የሆኑት አመልካች የጉልበትም ሆነ የገንዘብ አስተዋፆኦ ሳያደርጉ በመንግስት ቤት ብቻ ትርፍ ይክፈለ የሚለው ውል ስለ ኪሳራ ተጠያቂነት የተጠቀሰ ነገር የለም። የሽርክና ማህበር ለማቋቋም የተቀመጡ መሰረታዊ ነጥቦች አልተሟለም ሉጠየቅ አይገባም በማለት የተከራከሩ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው።
የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ የንግድ ማህበር በንግድ ህጉ መሰረት የሚቋቋምበት አግባብ በመለየት የንግድ ማህበር ስለመኖሩ የማስረዲት ግዳታው የሽርክና ማህበር ተመስርቷል። የሚል ወገን መሆኑ በመግለጽ፤ የሽርክና ውል ስምምነት በወረቀት ላይ መፃፍ ብቻውን የሽርክና ማህበር አለ ልባል አይችልም።የግራ ቀኙ ማስረጃዎች እንዱመዘንና የአመልካችም ምስክሮች የሽርክና ማህበር በውል ግንኙነት አለ ቢለም የዚህ አይነት ግንኙነት መመስረት መሟላት አለባቸው የተባለትን ሁኔታዎች በሙለ ባሟላ መልኩ የተመሰረተ ግንኙነት ያላቸው መሆኑ ምስክሮች አላስረደም።አብሮ የመስራትና የመተባበር፣ትርፍ መከፈል የሚለት ሁኔታዎች በግራ ቀኙ ያልነበሩ በመሆናቸው በዚህ የመንግስት ቤት የሚሰሩት ተከሳሽ /ተጠሪ/ ብቻ መሆናቸው ምስክሮች አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ያቀረቡት የሽርክና ውል ስምምነት የተፈረመው ተከሳሽ /ተጠሪ/ቤቱን የተከራዩት በ2003 ዓ/ም ሆኖ እያለ ወደ ኋላ በመመለስ መሆኑን ተጠሪ በዚህ የንግድ ቤት የሚሰሩት የንግድ ቤቱን ተከራይተው መሆኑን የተከሳሹ /ተጠሪ/ ምስክሮች በተሻለ ሚዛን አስረድተዋል ።ውለ የሽርክና ውል ተብል መፃፍ ብቻውን ደግሞ ውለ ወደ ኋላ ሳይሰራበት ተጽፍ እያለ በእርግጥ በግራ ቀኙ መካከል የሽርክና ማህበር ውል ተመስርቷል። ልባል አይችልም በማለት የአመልካች ክስ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ/337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ችልት ይቅረብ የተባለ በመሆኑ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር አድርጓል። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ያነሱት መሰረታዊ ነጥብ የሽርክና ውል መቅረብ ባልተካደበት በሰው ምስክር ሰነደን ማስተባበል ህጋዊ አለመሆኑን፣ በሽርክና ውል አብሮ መስራት እንደመስፈርት እንዲልተወሰደ፤ ሽርክና በቀጥታ በስራ ሳይሳተፈ አብሮ በሽርክና መስራት እንደሚችል አመልካች ከመንግስት የተከራዩት ቤት በመዋጮነት በማቅረብ /በመስጠት/ መስራታቸው ህጋዊ ነው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሉሻር ይገባል በማለት መከራከራቸውን ያሳያል።ተጠሪ በበኩላቸው ባቀረቡት መልስ ተደረገ የተባለው የሽርክና ውል ከመንግስት ተጠያቂነት ለማምለጥ የተደረገ ወደ ኋላ ተመልሶ የተፈረመ መሆኑን ተጠሪ ቤቱን በ2000 ብር ተከራይተው 4,000 መክፈላቸው፤ የአስተዲደር አካልም ጉዲዩ በማጣራት የአከራይ ተከራይ ግንኙነት መኖሩን ማረጋገጡን፤ ተዋጣ የተባለው ካፒታል እና የተጠየቀው ትርፍ /300,000 ብር/ የማይገናኝ ፣መሆኑ፤ ቤቱ የመንግስት ሲሆን አመልካችም ውጭ አገር የሚኖሩ፤ የመንግስት ቤት በመዋጮ መስጠት እንደማይቻል፤ ተደረገ የተባለው ውልም የሽርክና ውል በንግድ ህግ ቁጥር 211 የተመለከተው አስገዲጅ መስፈርት እንደማያሟላ በመግለጽ የስር ፍርድ ውሳኔ እንዱጸና ጠይቋል። በአመልካች የቀረበው የመልስ መልስ አቤቱታውን የሚያጠናክር ነው።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የታዘዘ ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም አመልካች ከተጠሪ አደረኩት ያለትን የሽርክና ስምምነት በንግድ ህጉ የተጠቀሱትን መሰረታዊ መመዘኛዎች አያሟለም ተብል በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ መደረጉ በአግባብ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በሽርክና ውል ላይ የተመሰረቱ ስለመሆኑ አጥብቀው የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ግንኙነት አከራይ ተከራይ እንጂ በህግ አግባብ የተቋቋመ የሽርክና ውል የለም የሚል መልስ አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መመዘኑን በውሳኔው ላይ አስፍሯል። የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ አመልካች እና ተጠሪ የነበራቸው ግንኙነት በሽርክና ውል ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን የአከራይ ተከራይ ግንኙነት ነው።በሽርክና ውል መሰረት መተባበርና አብሮ የመስራት፤ ትርፍ መከፈል የሚለት የሽርክና ማህበር ለማቋቋም እንደ መሰረታዊ መመዘኛ የሚወስደት ነጥቦች አልተሟለም። ለክርክሩ ምክንያት በሆነው የንግድ ቤት ተጠሪ ብቻ እንደሚሰሩ አረጋግጧል። የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ስልጣኑ የደረሰበት ድምዲሜ ይዘን ጉዲዩን ከህግ አንፃር መርምረናል።
በመሰረቱ የሽርክና ማህበር በውል የሚቋቋም ሲሆን መሰረታዊ የማህበሩ ባህርያትም በአንቀጽ 211 ስር እንደተመለከተ ህጋዊ ሰውነት ያለው፤ በሽሪኮቹ የውል ስምምነት የሚቋቋም፤ ዓላማው ኢኮኖሚያዊ ተግባር ለማከናወን /ንግድ/፤ ሽሪኮች አብረው ለመስራትና ለመተባበር ተስማሙ፤
ከድርጅቱ የሚገኘው ትርፍም ሆነ ከሚመጣው ዕዲ ተከፊፊይ እንደሚሆኑ የሚስማሙበት ውል ስለመሆኑ ከላይ ከተመለከተው የህግ አንቀጽ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው ። የሽርክና ማህበር ሲቋቋም ሽሪኮቹ መዋጮ የማውጣት ግዳታ የተጣለባቸው ሲሆን መዋጮው በገንዘብ፣ በአይነት ወይም በጉልበት ላሆን እንደሚችል በንግድ ህግ አንቀጽ 229 ስር የተመለከተ ሲሆን መዋጮውም ብዛታቸው እኩል እንደሆኑ እና ለማህበሩም የሚስማሙ መሆን እንዲለባቸው የዚህ ድንጋጌ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ /3/ ያመላክታል። ማህበሩ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት ካለው በአይነት /ንብረት/ የተደረገው መዋጮ መልሶ መውሰድ እንደማይችል በንግድ ህግ አንቀጽ 269 /1/ ስር ተደንግጓል። አንድ የሽርክና ማህበር በህጉ አግባብ ተቋቋመ ለማለት የሚቻለው ተዋዋይ ወገኖች ተነፃፃሪ ሳይሆን ተደጋጋፉ የሆነ ግብ ይዘው መዋጮ በማዋጣት አብረው ከመስራትና በመተባበር፤ ትርፍና ኪሳራም በህጉ አግባብ እየተጋሩ ኢኮኖሚያዊ ተግባር ማከናወናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ከተጠሪ ጋር መሰረትኩት በሚለት የሽርክና ማህበር በአዱስ ከተማ ክፍለ ወረዲ 10 የቤት ቁጥር 014 የሆነው የመንግስት ቤት በመዋጮነት በማዋጣት ፤ ተጠሪ ደግሞ በእራሳቸው ገንዘብ የተዘጋጁ ልብሶችና ጫማዎች ገዝቶ በማምጣት በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት የተስማሙ ስለመሆኑ በመዝገቡ ከተያዘው የሽርክና ውል መረዲት ይቻላል። የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ እንዲረጋገጠው ተጠሪ ቤቱን የተከራዩት በ2003 ዓ/ም ሁኖ ሳለ ውለ ወደ ኋላ ተመልሶ 2002 ዓ/ም እንደተደረገ፤ ተጠሪ የንግድ ቤቱን ተከራይተው ተመስርቷል። ልባል እንደማይችል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ያመላክታል።
በአመልካችና ተጠሪ ተፈረመ የተባለው ሽርክና ውል በጽሁፍ ብቻ መሆኑ የሽርክና ማህበር መቋቋሙን የሚያሳይ አይሆንም። የሽርክና ማህበር የንግድ ህግ አንቀጽ 211 እንደደነገገው በህጉ ተለይተው የተቀመጡ መሰረታዊ መስፈርቶች ማለትም አብሮ መስራትና መተባበር፤መዋጮ መኖር የትርፍና ኪሳራ ክፍፍል ስርዓት የተመለከቱ ነጥቦች በመሰረት ላይ በትስስር ሉገኙ ይገባል። የስር ፍርድ ቤት ከላይ የተመለከቱትን መሰረታዊ የሽርክና ውል ማቋቋሚያ ነጥቦች በተግባር አልተረጋገጠም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በድጋሚ የሚመረምር አይሆንም። ምክንያቱም የሰበር ሰሚ ችልቱ በህግ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠባቸው ጉዲዮች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆን ያለመሆኑን ስለመሆኑ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 /3/ /ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው። ከዚህ አንፃር በግራ ቀኙ ተደረገ /ተፈረመ/ የተባለው የሽርክና ውል እና ይህንን ተከትል መሬት ላይ ያለው እውነታ በስር ፍርድ ቤት እንደተጠራው የሽርክና ውል በጽሁፍ ከመደረጉ ውጭ የሽርክና ውል የሚጠይቃቸው መስፈርቶች አሟልተው ሲሰሩ እንደነበር አልተረጋገጠም ። ከላይ እንደተመለከተው የሽርክና ማህበር በህግ አግባብ ተቋቁሞ እየሰራ ነበር ለማለት የሚቻለው የጽሁፍ ውል መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ግራ ቀኙ በጋራና በተናጥል በመተባበር በመስራት ከጥቅሙ ይሁን ዕዲው በጋራ ሲጋሩ እንደነበር በውል መንፈስና ይዘት የሚፈጽሙበት አግባብ የነበረ ስለመሆኑ የሽርክና ማህበሩ የነበረበት ነባራዊ ሁኔታ ይህንን እንደማያሳይ የስር ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን በስልጣናቸው ከድምዲሜ ላይ ደርሰዋል።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተመሰረተ የሽርክና ማህበር ውል የለም ማለታቸው በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን የማያሳይ ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/197575 በ19/07/2005 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/135286 በ30/11/2005 ዓ/ም የሰጠው ትእዛዝ ጸንቷል።
በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተመሰረተ የሽርክና ማህበር ውል የለም ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
ወጪና ኪሳራ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.