ፍርድ ቤቶች በአስተዲደር ክፍል የተሰጠ የቤት ካርታ የተሰጠበት ወይም የተሻረበት ስርዓት እና አስተዲደራዊ ውሳኔው ህግና መመሪያ ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን በማጣራት ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1196፣የ.ኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 32 XXIII
No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ አብረኸት ዱክሪያ ቁምጀን ጠበቃ መስፍን አስፊ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ ወ/ሮ ፊጡማ ጀማል 2ኛ አቶ ያሲን ጀማል 3ኛ አቶ ናስር ጀማል 4ኛ የልደታ ክፍለ ከተማ ማሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ነገረ ፈጅ ንጉስ ከበደ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት ክርክር የተመለከተ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦለት ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማስተናገድ ሥልጣን እንዲለው ትዕዛዝ ከሰጠ በኃላ አመልካች የክስ ላሻሽል ጥያቄ አቅርበው በፍ/ቤት ፉታድ ክሱን ተሻሽል ከቀረበ በኃላ በተመሳሳይ ችልት በመጀመሪያ ውድቅ የተደረገው መቃወሚያ በድጋሚ ቀርቦ ፍ/ቤቱ ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ብይን በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችልት አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በቀረቡት ክስ የአመልካች እና ከ1-3 የተጠቀሱት ተጠሪዎች የጋራ ሀብት የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዲ 2 የቤት ቁጥር 327 ለሆነው ቤት ያለአግባብ 4ኛ ተጠሪን በማሳሳት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስለወሰደ ካርታው ተመላሽ እንዱደረግ ይወሰንልኝ በማለት አመልክቷል። የአሁኑ ተጠሪዎች በሰጡት የመከላከያ መልስ ከ1-3 የተመዘገቡት ተጠሪዎች የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቀወሚያ ሲያቀርቡ 4ኛ ተጠሪዎች የአመልካች ክስ መቅረብ ያለበት ከርታ ለሰጠው አስተዲደር ክፍል እንጂ ለፍርድ ቤት አይደለም በማለት መከራከራቸውን ተመልክተናል።
የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከመረመረ በኃላ ፍርድ ቤቱ ተሰጠ የተባለው ካርታ የተሰጠበት አግባብ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የማጣራት ስልጣን እንዲለው፤ ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት የማን ነው? የሚለው ፍሬ ነገር በማጣራት ሂደት ነጥሮ እንዱመወጣ ይርጋ በተመለከተም የባለቤትነት ክርክር በይርጋ እንደማይታገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በስ/መ/ቁ. 43600 የሰጠው ገዥ ውሳኔ መሰረት በማድረግ ውድቅ እንዲደረገው እና ፍሬ ጉዲዩን ለመስማት ለ25/08/2007 ዓ/ም ቀጠሮ መያዙን የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል።
አመልካች ግን በ7 ቀን 2004 ዓ/ም ክሱን አሻሽል የቀረቡ ሲሆን ይዘቱም ከ1-3 የተመዘገቡ ተጠሪዎች ክስ የማቅረብ መብታቸው በይርጋ ከታገደ በኃላ 4ኛ ተጠሪ ከርታ አዘጋጅቶ መስጠቱ ተገቢ አለመሆኑን፤ በየደረጃው ያለ የአስተዲደር አካላትም አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ መፍታት ስላልቻለ ተጠሪዎች የወሰደት ካርታ ሕገ ወጥ ነው ተብል እንዱመክን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። 4ኛ ተጠሪ አመልካች አሻሽለው ላቀረቡት ክስ በሰጠው የመከላከያ መልስ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ የመስጠት ስልጣን የአስተዲደሩ በመሆኑ የመሰረዝ ሥልጣንም የአስተዲደሩ እንጅ የፍርድ ቤት አይደለም በማለት ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም የ4ኛ አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቀብል የባለቤትነት ካርታ የመሰረዝ ሥልጣን የተሰጠው ለአስተዲደር ነው። በመሆኑም ይህ ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.245(2)(መ) መሰረት ብይን ሰጥቷል። አመልካች የዚህ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ያቀረቡት ይግባኝም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይቀበለው ቀርቷል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች ብይን በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ የተባለ በመሆኑ ግራ ቀኙ የፅሐፍ ክርክር ያደረጉ ሲሆን ይህ ችልትም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት ተደርጎ ከተሰጠው ብይን አንፃር የቀረበው የሰበር አቤቱታና መልስ እንደተመለከተው፤ በአመልካች በኩል የቀረበው የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት በብይን ያለፈው ጉዲይ በተመሳሳይ ችልት እንደገና ተቀብል ማስተናገደ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን 4ኛ ተጠሪ በበኩለ የአመልካች አቤቱታ ከተሻሻለ ቀደሞ የተሰጠው ብይንም ሕጋዊ ውጤት አይኖርም የሚል ይዘት ያለው መልስ ሰጥቷል። ከ1-3 የተጠቀሱት ተጠሪዎችም የስር ፍርድ ቤት ብይን እንዱፀና ጠይቋል። የአመልካች የመልስ መልስም የሰበር አቤቱታቸው የሚያጠናክር ነው።
ከሥር የጉዲዩ አመጠጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ብይን አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች በማገናዘብ ጉዲዩን መርምሮታል። እንደመረመረነውም በዚህ ችልት እልባት የሚያሰፈልገው ጭብጥ የሥር ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሥረ ነገር ስልጣን ጋር በተያያዘ የቀረበው መቃወሚያ ውድቅ አድርጎ ጉዲዩን ለመስማት ከተቀጠረ በኃላ ክሱን በድጋሜ ተሻሽል በመቅረቡ ምክንያት በተመሳሳይ ችልትና ፍ/ቤት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ተብል መዘገቡን በብይን መዘጋቱ በሕጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከክርክር ሂደት መረዲት የተቻለው አመልካች ባቀረቡት ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ፍርድ ቤቱም ካርታው የተሰጠበት ትዕዛዝ የማጣራት ስልጣን አለኝ በማለት በብይን ውድቅ አድርጎታል። የፍ/ቤቱ ብይን ተከትል የተጠየቀ ይግባኝ የለም። ይህ በእንዱህ እያለ አመልካች ክሳቸውን ለማሻሻል ያቀረቡት ጥያቄ በፍ/ቤቱ ተቀባይነት በማግኘቱ አሻሽለው አቅርበዋል። የሥር ፍርድ ቤት ካርታ የተሰጠበት አግባብ የማጣራት ስልጣን አለኝ በማለት የሰጠው ብይን በመሻር ካርታ የመስጠትና የመሰረዝ ሥልጣኑ የአስተዲደር ክፍል ነው በማለት በአንድ ጉዲይ ላላ ብይን ሰጥቷል። በአመልካች በኩል የቀረበው የክስ ላሻሽል አቤቱታ የክርክሩ መሰረታዊ ይዘት የለወጠ ሳይሆን የተጠሪዎች መብት በይርጋ የታገደ ነው አስተዲደሩም ውሳኔ ማረም አልቻለም የሚል አዱስ ፍሬ ነገር በማካተት የቀረበ ስለመሆኑ ከስር ፍርድ ቤት የብይን ግልባጭ መረዲት ይቻላል። የሥር ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ4ኛ ተጠሪ መጀመሪያ የቀረበው የፍርድ ቤቱ ሥልጣን ጥያቄ በተመለከተ በብይን ውድቅ ከተደረገ በኃላ አመልካች ክሳቸው በማሻሻላቸው ምክንያት ብቻ የራሱ ብይን መልሶ የሚሽረበት ሥርዓት አይኖርም። የስር ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ውድቅ ካደረገው በኃላ የመቃወሚያው ባሕሪ ዓይነትና ይዘት ሳይለወጥ በተመሳሳይ ጉዲይ የራሱ ብይን መልስ በመሻር ጉዲዩን ለማየት የስር ነገር ሥልጣን የለኝም በማለት የመወሰን ሥልጣን የለውም።
በዚህ ጉዲይ ላላ መታየት ያለበት መሰረታዊ ነጥብ የአሁኑ 4ኛ ተጠሪ ባቀረበው ክርክር ካርታ ከመስጠት እና ከማምከን ጋር የተያያዘ ጉዲይ በፍርድ ቤት የሚታይ አይደለም የሚል ነው።
አስተዲደራዊ ተቋማት በሕግ ተለይቶ የተሰጣቸው ጉዲይ የመወሰን ሥልጣን እንዲላቸው የታወቀ ነው። ይሁንና ለአንድ ባለ ጉዲይ የተሰጠው ከርታ የተሰጠበት እና የተሻረበት አግባብ በሕግ አግባብ መሆን ያለመሆኑን አጠርቶ የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ነው። በዚህ ረገድ ያለ መሆኑን አጣርቶ የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ነው። በዚህ ረገድ የሥር ፍርድ ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታን የመሰረዝ ሥልጣን የአስተዲደሩ ክፍል ነው፣ ፍርድ ቤት ጉዲዬን አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ የጉዲዩ የክርክር ባህሪ እና ይዘት ያላገናዘበ ነው። ፍርድ ቤቶች በአስተዲደር ክፍል የተሰጠው ካርታ የተሰጠበት ወይም የተሸረበት ሥርዓት እና አስተዲደራዊ ውሳኔው ሕግና መመሪያ ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑን በማጣራት ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን እንዲላቸው ከፍ/ህ/ቁ.1196 በህገ መንግስቱ ስለ ንብረት መብት ከአደረገው ድንጋጌና በፍርድ የሚያልቁ ጉዲዮችን በተመለከቱ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘት የምንረዲው ጉዲይ ነው።
በማጠቃላል፡- የሥር ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን እንዲለው መጀመሪያ ብይን መስጠቱ እየታወቀ ክስ ተሻሽል ከቀረበ በኃላ በዚህ ችልት የተሰየሙት ላላ ዲኛ በተመሳሳይ ምክንያት የችልቱ ትዕዛዝ እንደ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመሆን ሽሮታል። ይህ ደግሞ በፍ/ስ/ስ//ሕ/ቁ. 244 እና 245 የተመለከቱት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ብይን አሰጣጥ እና ጉዲይ አመራር ሥርዓት ያላገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች አቤቱታ በማሻሻላቸው ምክንያት ብቻ የክርክሩ ይዘት ሳይለወጥ ብይኑ አጥሮ እንደሚሻር በሚያስቆጥር አግባብ የመጀመሪያ ብይን እንደ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመሆን የሻረው በመሆኑ በሕጉ የተዘረጋው የሙግት አመራር ሥርዓት የተከተለ አይደለም ብለናል። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤት የራሱ የሰጠው ብይን መልሶ መሻሩ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ይህንን ብይን ሳያርም በትዕዛዝ ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ጉዲይ ነው ብለናል።
በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 191377 በ27/05/2005 ዓ/ም የሰጠው ብይን፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 134095 በ13/5/2006 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የስር ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ራሱ የሰጠው ብይን መልሶ የመሻር ስልጣን የለውም ብለናል። ካርታ የተሰጠበት እና የተሻረበት ሁኔታ በሕግ አግባብ መሆን ያለመሆኑን አጣርቶ የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤት ነው በማለት ወስነናል።
የሥር ፍርድ ቤት የተዘጋው መዝገብ በማንቀሳቀስ በተሰጠው ብይን መሰረት ክርክሩን ከቆመበት ቀጥል ተገቢ ሕጋዊ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ይፃፍ ።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ። መዝገቡ ወደ መ/ቤት ተመለስ።
No topics extracted.