የገጠር መሬት ወራሽነትን በሚመለከት በአንድ ወቅት በቤተሰብ አባልት መመዝገብ ብቻውን የሟችን የእርሻ መሬት በቀዲሚነት የመውረስ መብትን የማያጎናጽፍ ስለመሆኑ በውርስ ለማግኘት ወራሹ አርሶ አድርና ከእርሻ መሬቱ ከሚገኘው ገቢ የሚተዲደር የቤተሰብ አባል መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ 456/97 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 5 የኦሮሚያ የመሬት አዋጁ 130/99 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 13 እና 16/
No summary available.
ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አበተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኸሉት ይመሰል አመልካችዎች፡- 1- ወ/ሮ ይርጋዓለም ዘውዳ - አልቀረቡም 2- ወ/ሪት ስንቅነሽ ክፍላ 3- ወ/ሪት ወላንሳ ዘውዳ 4- አቶ ኃይለሚካኤል ክፍላ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሰፈ ዘውዳ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የጊምቢቹ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ነሐሴ 8 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 14 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ ህዲር 18 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የእርሻ መሬት ይዞታና የመጠቀም መብት በውርስ የማግኘት ጥያቄን የሚመለከት ነው። ለወረዲው ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
1- የክርክሩ መነሻ ከሳሾች (አመልካቾች)ያቀረቡት ክስ ነው። ከሳሾች የሟች ወ/ሮ ካሰች ዘውዳ ልጆች መሆናቸውን ገልፀው የእናታችን እናት ወ/ሮ የሺ ወልደየስ ታህሣሥ 19 ቀን 2005 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። አያታችን በተለያዩ ስፍራ የእርሻ መሬትና ይዞታ ያላት ሲሆን እኛም በቤተሰብ አባልነት አስመዝግባናለች ። አያታችን በተሰጣት የይዞታ መሬት ማረጋገጫ ደብተር በቤተሰብ አባልነት የተመዘገበ ነው ከሳሾች ስለሆን መሬቱን የመውረስ የቀዲሚነት መብት አለን። ሆኖም ተከሳሽ የሟች ወ/ሮ የሺወልደየስ ወራሽ መሆኑን በፍርድ ቤት አስወስና፣ የያዘች በመሆኑ የተሰጣት የወራሽነት ማስረጃ ተሰርዞ መሬቱን የመውረስ መብት ያለን እኛ መሆናችን ተረጋግጦ ይወሰንልን በማለት ክስ አቅርበዋል።
2- ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርባ ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ ወላጅ እናቴ ናት ተከሳሽ የወላጅ እናቴ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆኔ በማረጋገጥ ማስረጃ ያገኘሁት በሕግ አግባብ ነው። ከሳሾች በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ነው። ከሳሾች የሟችን መሬት በቀዲሚነት የመውረስ መብት የላቸውም በማለት ተከራክራለች። አመልካቾችና ተጠሪ እየተከራከሩ እያለ ፣የወ/ሮ ዘነበች ዘውዳ ልጅ መሆኑን ገልፆ እናቴን ተክቼ የአያቴን የእርሻ መሬት የመውረስ መብት አለኝ በማለት አቶ ሰለሞን መርሻ ጣልቃ ገብቷል።
3- የወረዲው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክር ሰምቷል በአመልካቾች በኩል የቀረቡት ምስክሮች ተጠሪ የሟች የሺ ወልደየስ ልጅ መሆኗን አናውቅም በማለት የመሰከሩ መሆኑንና ተጠሪ የሟች የሺ ወልደየስ ልጅ መሆኗን የሚያውቁ አምስት ምስክሮች በማቅርብ እንዲስመሰከረች ከዚህ በተጨማሪ አንደኛ ከሳሽ ከአምስት ዓመት በፉት አግብታ ከሁለተኛ ከሳሽ ጋር በአዱስ አበባ ከተማ የሚኖሩ መሆኑን ሦስተኛና አራተኛ ተከሳሽም በአዱስ አበባ ከተማ ከአባታቸው ጋር የሚኖሩ መሆኑን ተከሳሽ ባቀረበቻቸው ምስክሮች የተረጋገጠ መሆኑን በውሣኔው ገልፆ የሟች የሺ ወልደየስ መሬት ለሶስት ተከፍል ከሳሾች የእናታቸውን ድርሻ አንድ እጅ እንዱወስደ ጣልቃ ገቡ የእናቱን ድርሻ አንድ እጅ እንዱወስድና ተጠሪ አንድ እጅ ድርሻዋን እንድትወስድ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
4- አመልካችዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል ።የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችዎችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል አመልካችዎች የሰበር አቤቱታ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቅርበው የሰበር አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል ።አመልካችዎች ተጠሪ ከስልሣ አንድ ዓመት በፉት ለላላ ሰው በጉድፈቻ ተሰጥታ ከጉድፈቻ ከተሰጠችበት አደአ አካባቢ አግብታና መሬት ተመርታ እየኖረች ያለች ናት ። ተጠሪ አንድ ቀንም ከወላጅ እናቷ የእርሻ መሬት ተጠቅማ አታውቅም ።በልላ በኩል እኛ የሟች የሺ ወልደየስ የቤተሰብ አባል መሆናችን በመሬትና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሟች አስመዝግባናለች ይህም ሆኖ እያለ ተጠሪ መሬት እንድትወርስ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት ጥር 27 ቀን 2007ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ለዚህ በሰበር ችልት አቅርበዋል።
5- ተጠሪ መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ተጠሪ የሟች ልጅ መሆኔ በርካታ ማስረጃ ያለኝ ቢሆንም አመልካችዎች የሟች እናቴ ወራሽ ስለመሆኔ ተረጋግጦ የተሰጠኝ የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝ ከሕግ ውጭ ጥያቄ አቅርበዋል ። አመልካቿ ለዚህ አሰበር ችልት ተጠሪ በጉዱፈቻ እንዲደኩ አድርገው በሥር ያላነሱትንና እውነትነት የላለውን ክርክር አቅርበዋል፤ክርክራቸውም ውድቅ ላደረግ የሚገባው ነው። ተጠሪ የእርሻ መሬቱን ከዚህ በፉትም ስጠቀምበት የቆየሁ ስሆን አሁንም ድርሻዬን በስሜ አዛውሬ እየተጠቀምኩ እገኛለሁ ። በልላ በኩል የሟችን የእርሻ መሬት የመውረስ መብት የላላቸው አመልካቾች የእኔን ወራሽነት በመቃወም ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ የሰበር አቤቱታቸው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክራለች ።
አመልካችዎች የካቲት 8 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
6- ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ የሟች እናቷን የእርሻ መሬት ከላልች ወራሾች ጋር እንድትካፈል የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል ።
7- ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የግራቀኙን ማስረጃ መዝነው የደረሱበት የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር ማገናዘብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ። ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ፤በሥር ፍ/ቤት ከሳሾች እናት የወ/ሮ ካሰች ዘውዳ ወላጅ እናት መሆኗ ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ የተጠሪ ወላጅ እናት መሆኗ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ የሟች ዘነበች ዘውዳ ወላጅ እናትና በሥር ፍ/ቤት ጣልቃገብ ተከራካሪ የሆነው ሰለሞን መርሻ አያታቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።
8- ከዚህ አንፃር ሲታይ የሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ የእርሻ መሬትና ንብረት አመልካቾች እናታቸውን ወ/ሮ ካሰች ዘውዳ በመተካት ተጠሪ የወላጅ እናቷ አንደኛ ደረጃ ወራሽ በመሆኗና ሰለሞን መርሻ እናቱን ዘነበች ዘውዳን በመተካት የመውረስ መብት ያላቸው መሆኑንን ተረጋግጧል። አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች የሺ ወልደየስ ልጅ አይደለችም በማለት የተከራከሩና ይህንን ክርክራቸውን ለማስረዲት ምስክሮች አቅርበው እንደነበርና አመልካቾች ማስረጃ ታአማኒነት የላለው መሆኑን ተረጋግጧል ።
አመልካቾች በዚህ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የሟች የሺ ወልደየስ የሥጋ ልጅ መሆኗን አምነው ተጠሪ በጉዱፈቻ ላላ ሰው አሳድጓታል የሚል በሥር ፍርድ ቤት ያላነሱትን አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል ሆኖም አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት ተጠሪ በጉድፈቻ ላላ ሰው ነው ያሳደጋት በማለት ያቀረቡት አዱስ የፍሬ ጉዲይ ክርክር የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 329 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ያላገናዘበና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም ።
9- አመልካቾች ተጠሪ የእናቷን ወ/ሮ የሺ ወልደየስ የእርሻ መሬት የመውረስ መብት የላትም ። የእርሻ መሬቱን የመውረስ የቀዲሚነት መብት ያለን እኛ ነን በማለት የሚከራከሩት ሟች ወ/ሮ የሺ በህይወት እያለች እኛን በቤተሰብ አባልነት አስመዝግባናለች በማለት ነው። ሆኖም ሟች ወ/ሮ የሺ አመልካቾችን በቤተሰብ አባልነት ማስመዝገቧ የበታች ፍ/ቤቶች ለማስረጃ ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ መሆኑን ተረድተናል እንደዚሁም ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ አመልካቾችን በአንድ ወቅት በቤተሰብ አባልነት ማስመዝገቧን የሚያሳይ ማስረጃ ቢኖር እንኳን አመልካቾች የሟች የቤተሰብ አባል ሆነው መመዝገባቸው ብቻውን የሟችን የእርሻ መሬት በቀዲሚነት የመውረስ መብት የሚያጎናፅፊቸው አይደለም።
10- ለዚህም ምክንያቱ የእርሻ መሬት በውርስ ለማግኘት ወራሹ አርሶ አደርና ከእርሻ መሬቱ ከሚገኘው ገቢ የሚተዲደር የቤተሰብ አባል መሆን እንዲለበት የፍደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 5 እና የኦሮሚያ ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 13 እና 16 በግልፅ ተደንግጓል።
አመልካቾች ሟች ወ/ሮ የሺ ወልደየስ የእርሻ መሬት ከሚገኘው ገቢ የማይተዲደሩ በአዱስ አበባ ከተማ የየራሳቸውን ኑሮ መሥርተው የሚኖሩ መሆናቸው በማስረጃ ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ አመልካቾች የህጉን መስፈርት የማያሟለ ሆነው እያለ ሟች የሺ ወልደየስ የቤተሰብ አባል ናቸው ብላ ማስመዝገቧ፣አመላከቾች የሟችን የእርሻ መሬት የመውረስ ቀዲሚ መብት አለን በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም ። በአንፃሩ ተጠሪ በእርሻ ሥራ የምትተዲደር አርሶ አደር መሆኗ ተረጋግጧል ። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ተጠሪ የሟች እናቷን የእርሻ መሬት ልትወርስ አይገባም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1- የጊንቢቹ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
2- በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ በየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.