ከቤተሰባዊ ቅርርብ የተነሳ ውለታ ላደረገ ሰው አንደኛው ወገን ካለው መሬት ውርስ ቆርሶ በስጦታ መልክ እንዱጠቀም ሰጥቶት በሁለቱ መካከል አለመግባባት ቢፈጠር በሥጦታ ተቀባዩ ወገን በመሬቱ የመብት ክርክር ቢያነሳ የመሬት ይዞታ ስጦታው ሉፀና የሚችለው የክልል የመሬት አዋጅ በሚፈቅደው መሰረት ሥልጣን ባለው አካል ዘንድ ቀርቦ የስጦታ ውለ መመዝገቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። /የኦሮሚያ ክልል የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99
No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ረታ ከበበ ቀረቡ ተጠሪ፡-- ወ/ሮ ቱሬ ደማ ተወካይ ሙልጌታ ከበበ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የመሬት ይዞታ ክርክር የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የወረጃርሶ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረው በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
የአሁኗ ተጠሪ በሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ልጃቸው እንደሆነ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የመሬት ይዞታ በፍርድ ቤት አስወስነው የተረከቡት ከቦቤ ሉበን ቀበላ ውስጥ የሚገኘው በአጠቃላይ 0.9 ሄክታር መሬት በክርክር ላይ እያለ በቀጣይነት ይዘው እየተጠቀሙበት ስለሆነ ከዚህ መሬት ላይ አርሰው ያገኙት አላባ እና ግጦሽ በአጠቃላይ 65ዐዐ የሚያስገኝ ስለሆነ አላባውን ከፍልው መሬቱን እንዱለቅላቸው መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካች በሰጡት መልስ ክስ ከቀረበበት ይዞታ ሁለት ቦታ ላይ የሚገኘው በስጦታ የተሰጣቸው ስለመሆኑ ይኸውም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት በልላ ሰው የተያዘባቸው በመሆኑ ተከራክረው በማስለቀቃቸው መብታቸውን ያስከበሩላቸው በመሆኑ እንደተሰጣቸው በ3ኛ ቦታ የሚገኝ መሬት በተመለከተ ግን የተጠሪ ከብቶች የበለት ስለሆነ ሉጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
የሥር ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራቀኙ ክርክርና እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ለክርክሩ መነሻ ከሆነው ይዞታ ተጠሪ ለአመልካች 3 ገመድ መሬት በስጦታ መስጠታቸው በ22/06/2006 የተፃፈ ስጦታ ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር መያያዙን፣ በመሆኑም ተጠሪ መሬቱን ይዞብኛል በማለት ያቀረቡት በስጦታ የተሰጠውን 3 ገመድ መሬት የአመልካች መሆኑን፤ ላልች ይዞታዎች በተመለከተ ግን ለቀው እንዱያስረክቡ ለግጦሽ አላባ በተመለከተ የተጠሪ ከብቶች የበለት መሆኑ ምስክሮች አረጋግጠዋል በማለት ያለፈው መሆኑን በመጥቀስ ውሳኔ ሰጥተዋል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ቅሬታ ተቀባይነት አላገኘም።
ተጠሪ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት በማግኘቱ ግራቀኙ አከራክሮ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ አጭር ይዘት፡- ግራቀኙ እያከራከረ ያለው የመሬት ይዞታ ውሳኔ አግኝቶ ተጠሪ ከተረከቡት በኋላ አመልካች መያዙን፤
አላባ እና ግጦሽ በተመለከተም አመልካች መሬቱን አርሶ ያመረተበት መሆኑን፤ ግጦሽም በከብቶች መበላቱን በምስክሮች መረጋገጡን በመግለጽ አመልካች ሁለም ክስ የቀረበበት መሬት እንዱለቅ፤ ምርቱ ምን ያህል እንደሆነ፤ የተባለው ግጦሽም ምን ያህል ዋጋ ማውጣት እንደሚችል ተገምቶ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፈል ጉዲዩም በወረጃርሶ ወረዲ ፍርድ ቤት ታይቶ እንዱወሰን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 343(1) የመለሰው መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። ጉዲዩ በሰበር ይታይ በመባለ ምክንያት ግራቀኙ የጽሐፍ ክርክር አድርገዋል። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የሥር ሰበር ሰሚ ችልት የምስክሮች ቃል ቀይሮ መተርጎሙን፤ ለክርክሩ መነሻ ከሆነው መሬት 0.5 ሄክታር መሬት በስጦታ ውል የተሰጣቸው መሆኑን የግጦሽ መሬት የበለት የተጠሪ ከብቶች መሆናቸውን ተረጋግጦ እያለ ይክፈል መባለ በአግባቡ አለመሆኑን መሰረት ተደርጎ የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሽሮ የወረዲው ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱጸና ጠይቋል። ተጠሪ በሰጡት መልስ፡- አመልካች መሬቱን በስጦታ አገኘሁት የሚለት ከሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል ያልተመዘገበ፤የስጦታ ውል የተባለው በራሱ ጊዜ ያዘጋጀው መሆኑን፤ አላባና ግጦሽ በተመለከተ ተጣርቶ እንዱወሰን መመለሱ በአግባቡ ነው የሥር ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ሉጸና እንደሚገባ ተከራክረዋል። የአመልካች የመልስ መልስም ቀርቧል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ በሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማዛመድ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ጉዲዩ እንደመረመርነው አመልካች ከሥር ፍርድ ቤት አንስተው አጥብቀው የሚከራከሩት ለክርክሩ መነሻ ከሆነው የመሬት ይዞታ 0.3 ሄክታር ከተጠሪ በስጦታ ያገኙት መሆኑ ነው። ተጠሪ በበኩላቸው ለአመልካች የመሬት ይዞታ ስጦታ አለማድረጋቸው፤ የስጦታ ውል የተባለውም እንደማያውቁት በመጥቀስ መከራከራቸውን ተገንዝበናል። ከሥር የክርክር ሂደት መረዲት እንደተቻለው ግራቀኙ እያከራከረ ያለው ይዞታ የተጠሪ ስለመሆኑ የተካሄደ ጉዲይ አይደለም።
ይሁንና አመልካች መሬቱን ከላላ ግለሰብ ተከራክረው ያስመለሱት በመሆኑ እናታቸው /ተጠሪ/ የድካማቸው ዋጋ ይሆን ዘንድ መሬቱን በስጦታ እንደሰጧቸው አፅንኦት በመስጠት መከራከራቸው ከውሳኔ ይዘት መረዲት ችለናል። በሥር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች መሬቱን ከላላ 3ኛ ወገን ማስመለሳቸው የገለጹ ቢሆንም ከማን ጋር ተከራክረው መሬቱን እንዲስመለሱት ያቀረቡት ግልጽ ክርክር የለም። ተጠሪ በአንፃሩ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት ከአሁኑ አመልካች ይሁን ከላላ ሰው ተከራክረው መሬቱ እንዲስመለሱት ግልጽ ባይሆንም በተያዘው ጉዲይ መታየት ያለበት እና መፍትሄ የሚያሻው መሰረታዊ ነጥብ መሬቱን ያስመለሱት ከአሁኑ ተጠሪ አመልካች ይሁን ላላ ሦስተኛ ወገን አመልካች አለኝ የሚለት የስጦታ ውል የኦሮሚያ የመሬት አዋጅ በሚፈቅደው አግባብ ሥልጣን ባለው አካል ቀርቦ ተመዝግቧል ወይስ አልተመዘገበም?
የሚለው ነው።
የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ እንዲረጋገጠው የመሬቱ ባለ ይዞታ ተጠሪ ስለመሆናቸው ተጠሪ ለአመልካች 0.3 ገመድ በስጦታ መስጠታቸው የተገለጸ ቢሆንም በማይንቀሳቀስ ሥልጣን ባለው አካል ቀርቦ የተመዘገበ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር ሕጋዊ ሰነድ የለም። በገጠር የመሬት ይዞታ ተጠቃሚዎች የመሬት ይዞታቸው ለ3ኛ ወገን በስጦታ የማስተላለፍ መብት ያላቸው ቢሆንም ስጦታው በሕግ ፉት የሚጸናው በሚመለከተው አካል ቀርቦ መመዝገቡን ሲረጋገጥ ብቻ ነው። አመልካች አለኝ የሚለት የስጦታ ውል በተጠሪ የተካደ ሲሆን በሕጉ አግባብ የተቋቋመ የስጦታ ውል ስለመሆኑ በሕግ የተደገፈ ክርክር አልቀረበም። የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሻረው ተሰጠ በተባለው ስጦታ ሕጋዊነት መሰረት በማድረግ ሳይሆን ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ ከአመልካች በክርክር አሸንፈው እንደወሰደት መሰረት በማድረግ ነው። ከሥር የወረዲ ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ መረዲት እንደተቻለው መሬት የማስመለስ ክርክሩ በአመልካች እና ተጠሪ መካከል እንደነበር በግልጽ አያሳይም። ከዚህ አንፃር የሥር የኦሮሚያ ክልል ሰበር ሰሚ ችልት የጉዲዩን ክርክር ባሕሪ እና አግባብነት ያለው ጭብጥ ከመመስረት አኳያ ግድፈት ያለበት ቢሆንም በውጤት ደረጃ አመልካች በመሬት ይዞታው መብት እንደላላቸው የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም። ከላይ እንደተመለከተው አመልካች በተጠሪ ተሰጠኝ የሚለት የመሬት ይዞታ ሕጉ በዘረጋው ሥርዓት በሚመለከተው አካል ቀርቦ የተመዘገበ ሆኖ አልተገኘም። በተጠሪ ተሰጠ የተባለው የመሬት ይዞታ ስጦታ በሕጉ አግባብ መቋቋሙ ካልተረጋገጠ በተጠሪ ላይ ሕጋዊ ግዳታ የሚጥል ሆኖ አልተገኘም።
አመልካችም ከተጠሪ የመሬት ይዞታ የመጠየቅ መብት የሚሰጠው አይደለም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የወረጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር አመልካች በመሬት ይዞታው መብት የለውም ብል መወሰኑ በተለየ ምክንያት በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የህግ ስህተተ የተፈጸመበት ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ21/09/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ በተለየ ምክንያት በውጤት ደረጃ በአብላጫ ድምጽ ጸንቷል።
አመልካች ከተጠሪ አገኘሁት የሚለት የመሬት ይዞታ ስጦታ፤ ስጦታ ለመመዝገብ ሥልጣን ባለው የመሬት አስተዲዲር ጽ/ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት ወስነናል። ተጠሪ ለአመልካች 0.3 ገመድ መሬት እንዱያስረክብ አይገደድም ብለናል። የውሳኔ ግልባጭ ለሚመለከተው ይተላለፍ።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከትለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት መጋቢት 8/2007 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት የዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.