በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብትን ከባለይዞታው ጋር የስጋ ዝምድና ለላለው ሰው ማስተላለፍ የማይቻል ስለመሆኑ የስጦታ አደራረግን አስመልክቶ በፍትሐ ብሓር የተመለከቱ ድንጋጌዎች በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም፣የማስተላለፍ እና አስተዲደር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ክርክሮች ተፈፃሚነት የላላቸው ስለመሆኑ፡የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀፅ 6 የፋድራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደር አጠቃቀም አዋጅ.ቁ 456/19 XXII
No summary available.
መገቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- መድሕን ኪሮስ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ብርሃኑ ከበደ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኢብራሂም ሹካ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ በገጠር የእርሻ ይዞታ ላይ የተነሳ የውርስ ይገባኛል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በአርሲ ዞን በዱገለና ጢጆ ወረዲ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።ከሳሽ በ08/11/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ በ2001 ዓ.ም በሞት የተለዩት የከሳሽ አባት አቶ ሹካ ቃለ በሕይወት እያለ በኪራይ ለተከሳሽ ሰጥተው የነበረውን እና በውርስ ለከሳሽ ሉተላለፍ የሚገባውን አወሳኞቹ በክስ ማመልከቻው ላይ የተገለጸውን ሶስት ጥማድ የእርሻ ይዞታ ተከሳሽ እንዱለቁ ተጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን የሚገልጽ እና ይህንኑ መሬት ለቀው ለከሳሽ እንዱያስረክቡ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ሲሆን ተከሳሽ በበኩላቸው በ18/11/2005 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ተከሳሽ የከሳሽን እናት እና አባት ሲጦሩ የነበረ መሆኑን ምክንያት በማድረግ የከሳሽ ወላጆች በእርሻ ይዞታው የመጠቀም መብታቸውን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2427 መሰረት በ26/02/1999 ዓ.ም በተደረገ ውል በስጦታ ያስተላፈላቸው መሆኑን፣ተከሳሽም ውለን በሚመለከተው አካል አስመዝግበው የከሳሽ ወላጆች በሕይወት እያለ የባለይዞታነት ስሙን ወደ ራሳቸው አዛውረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑን እና በዚሁ ይዞታ ጉዲይ የከሳሽ ወንድሞች በተከሳሽ ላይ በልላ መዝገብ ክስ መስርተው መዝገቡ በዕርቅ የተዘጋ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ አንዱደረግ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን በግራ ቀኙ ማስረጃ እና ከሚመለከተው አካል ማጣራቱን፣የከሳሽ ወላጆች በእርሻ ይዞታው የመጠቀም መብታቸውን በ26/02/1999 ዓ.ም በተደረገ ውል በስጦታ ለተከሳሽ ማስተላለፊቸው እና ተከሳሽም የባለይዞታነት ስሙን ወደራሳቸው አዛውረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ በክርክሩ መረጋገጡን ገልጾ ሟቾች በሕይወት እያለ ለተከሳሽ ያስተላለፈት በይዞታው የመጠቀም መብት የውርስ ንብረት ላሆን የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎ ተከሳሽ ይዞታውን እንዱለቁ አይገደደም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ከሳሽ ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን ያጸና ሲሆን ጉዲዩን በመጨረሻ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በበኩለ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብትን ከባለይዞታው ጋር የስጋ ዝምድና ለላለው ሰው ማስተላለፍ የማይቻል ስለመሆኑ በክልለ የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 6 ስር ተደንግጎ የሚገኝ መሆኑን በምክንያትነት ጠቅሶ የሁለቱን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር አመልካች ክስ ያስነሳውን ይዞታ ለተጠሪ ሉለቁ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች አከራካሪውን መሬት በተመለከተ ህዲር 28 ቀን 1999 ዓ.ም ሕጋዊነቱ የተረጋገጠላቸው መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ እያላቸው የክልለ ሰበር ችልት በሀምላ ወር 1999 ዓ.ም የወጣውን የገጠር መሬት አዋጅ ወደ ኃላ ወስድ አመልካች የቤተሰብ አባል ስላልሆኑ መሬት በስጦታ የማግኘት መብት የላቸውም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔን ሽሮ አመልካች ክስ ያስነሳውን ይዞታ ለተጠሪ ሉለቁ ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የተጠሪው ወላጆች ክርክር ባስነሳው የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብታቸውን በ26/02/1999 ዓ.ም በተደረገ ውል በስጦታ ለአመልካቹ ማስተላለፊቸው፣ አመልካችም የባለይዞታነት ስሙን ወደ ራሳቸው አዛውረው እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ እና አመልካች ለስጦታ አድራጊዎቹ ተወላጅም ሆነ በመሬቱ ገቢ የሚተዲደሩ የቤተሰብ አባል አለመሆናቸው ያልተካደ እና በክርክሩም የተረጋገጠ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔን በመሻር ስጦታው ሕጋዊ ውጤት ያለው አይደለም ከሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰው በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብትን ለተወላጅ ወይም ከመሬቱ በሚገኝ ገቢ ለሚተዲደር የቤተሰብ አባል ካልሆነ በቀር በስጦታ ማስተላለፍን የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አይፈቅድም በማለት ነው።አመልካችም ቢሆኑ የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት የሚከራከሩት ስለ ስጦታ ውል አደራረግ እና ስለሕጋዊ ውጤቱ በፍትሐብሕር ሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት አድርገው ከመሆኑ ውጪ ስጦታው በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 “ም” ቢሆን ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር የለም።
በመሰረቱ በገጠር የእርሻ ይዞታ የመጠቀም መብትን በስጦታ የማስተላለፍ ጉዲይን ጨምሮ ከገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ክርክሮች በመሰረታዊነት ተፈጻሚነት የሚኖራቸው የፋዳራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997 እና ይህንን አዋጅ ተከትለው በየክልለ የወጡ አዋጆች እና ደንቦች እንጂ የስጦታ አደራረግን አስመለክቶ በፍትሐብሕር ሕጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ባለመሆናቸው በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው አይደለም። ክርክሩ የተጀመረው የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 በስራ ላይ ባለበት ጊዜ መሆኑ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ ውለ ተደረገ የተባለው አዋጁ ከመጽናቱ ከስምንት ወራት በፉት መሆኑ ለክርክሩ ምክንያት ከሆነው ጉዲይ ልዩ ባህርይ አንጻር ተጠቃሹን አዋጅ ለክርክሩ ተፈጻሚ ከማድረግ የሚያግድ አይደለም።
ሲጠቃለል የሁለቱን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር አመልካች ክስ ያስነሳውን ይዞታ ለተጠሪ ሉለቁ ይገባል በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በዱገለና ጢጆ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ30/01/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ09/04/2006 ዓ.ም. የጸናውን ውሳኔ በመሻር የኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ቸልት በመዝገብ በ19/12/2006 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በዱገለና ጢጆ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተጀመረው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ29/01/2007 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።