የአንድ የእምነት ተቋም አስተዲደራዊ ስራዎችን ለማከናወን የተሰጠ ሹመትና የሽረት ጉዲይ ከሀይማኖት ተቋሙ መሰረታዊና ተፈጥሯዊ ባህሪ ተነጥለው ለብቻቸው ሉታዩና ሉወሰኑ የማይችለ በመሆናቸው በፍርድ ሉወሰኑ የማይገባቸው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 11 እና 37
No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካችዎች፡- 1. አቶ ኤልያስ አዲሙ ጠበቆች ክፍላ ታደሰና አቶ ጅማ ድልቦ ቀረቡ 2. ሐዋሪያው ዲንኤል መኮነን ተጠሪዎች፡- የኢትዮጵያ ወንጌል ብርሃን ቤቴክርስቲያን - ደረጀ አበበ የቦርድ ተወካይ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 29 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በተጠሪ አንድ አጥቢያ ላይ የተፈጠረ ሁከት እንዱቆምና እንዱወገድ ውሣኔ ይሰጥልን በሚል መንገድ የቀረበን ጥያቄ የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካችዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በጠበቃ ተወክላ ያቀረበችው ክስ ነው። የክሱ ይዘትም፣ ከሳሽ በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የተቋቋመች ናት። ተከሳሾች የካቲት 26 ቀን 2005 ዓ.ም በከሳሽ አንድ አጥቢያ ላይ ሁከት በመፍጠር የከሳሽን ቢሮ ውክልና አለን በማለት አሽገዋል የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት በመምጣት ከላልች ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን የሁከት ተግባር ፈፅመዋል። ሁለተኛ ተከሳሽ /ሁለተኛ አመልካች/ ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን እያወቁት ለላልች ሰራተኞች የሥራ አመራር ትዕዛዝ በመስጠት በከሳሽ ቤተክርስቲያን ላይ ችግር ፈጥረዋል። አንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ አመልካች/ አላግባብ ከሁለተኛ ተከሳሽ ባገኘው ውክልና በከሳሽ ላይ የፈጠረው የሁከት ተግባር እንዱወገድና የውክልና ስልጣኑ እንዱሰረዝልን ሁለተኛ ተከሳሽ ከኃላፉነታቸው ስለተነሡ የሥራ አመራር ተግባር መሣተፊቸው የሁከት ተግባር በመሆኑ ከተግባራቸው እንዱቆጠቡ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
አንደኛ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ባቀረበው የፅሐፍ መልስ ቤተክርስቲያን በመወከል በቤተክርስቲያኗ ስም ክስ ለማቅረብ የሚችለት መስራች ሀዋሪያው ናቸው። የሥራ አመራር ቦርደ ቤቴክርስቲያኗን ወክል ክስ ለማቅረብ አይችልም። ክሱ የቀረበብኝ ቤቴክርስቲያኗን ወክለው ክስ የማቅረብ ሥልጣን በላለው አካል በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት፣ መቃወሚያ አቅርቧል። በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበሩት ሁለተኛ አመልካች መልስ በፅሐፍ ባለማቅረባቸው በፅሐፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኋላ፣ክሱ የቀረበው ቤተክርስቲያኗን ወክል ክስ ለማቅረብ ተገቢው ውክልና ባላቸው ሰው ነው ወይ? ተከሳሾች በቤተክርስቲያን ላይ የፈጠሩት የሁከት ተግባር አለ ወይ? የሚለትን ጭብጦች መሥርቷል።
የሥር ፍርድ ቤት በቤተክርስቲያኑ መተዲደሪያ ደንብና በቤተክርስቲያኗ የመዋቅር መግለጫ ተዋረድ መሰረት ሀዋሪያው ከሥራ አመራር ቦርደ ሥር የተቀመጡ መሆኑንና መሥራች ሀዋሪያው አስተዲደራዊና መንፈሳዊ ሥልጣን በመተዲደሪያ ደንቡ አንቀፅ 18 እንደተሰጣቸው ገልፆ፣ የመስራች ሀዋሪያውን የመንፈሣዊ ሥልጣን በዲኝነት አይቶ ለመወሰን ሥልጣን የለኝም። መሥራች ሀዋሪያው በመተዲደሪያ ደንቡ፣ አንቀፅ 18 ንዐስ አንቀፅ 6 የተሰጠውን አስተዲደራዊ ሥልጣን በተመለከተ በዲኝነት አይቼ መወሰን እችላለሁ። ከዚህ አንፃር መስራች ሀዋሪያው /ሁለተኛ ተከላሽ/ ከአስተዲደራዊ ሥልጣናቸው በሥራ አመራር ቦርደ የተነሱ ስለሆነ በአንደኛ ተከሳሽ የውክልና ሥልጣን መስጠት አይችለም። ስለዚህ ሁለተኛ ተከሳሽ ከአስተዲደራዊ ሥልጣናቸው የተነሱ ስለሆነ በአስተዲደር ሥራ እንዲይሣተፈ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካችዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የአመልካችዎችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካችዎች ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የኢትዮጵያ ወንጌል ብርሀን ቤተክርስቲያን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ሃይማኖት መሰረት የተቋቋመች፣ የራሷን የውስጥ መተዲደሪያ ደንብ አውጥታ የምትተዲደር ቤቴክርስቲያን ነች። ቤተክርስቲያኗ ነሐሴ 2 ቀን 2000 ዓ.ም ያፀደቀችው መተዲደሪያ ደንብ እስካሁንም ድረስ በሥራ ላይ ያለና የምትተዲደርበት ደንብ ነው። የቤቴክርስቲያኗን መተዲደሪያ ደንብ በሚመለከት የሚነሳ ጥያቄና ክርክር ሀይማኖታዊ ባህሪ፣ ይዘት ያለው በመሆኑ በፍርድ ቤት ላታይና ሉወሰን የሚችል አይደለም። ለሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ ይዘትም ጭብጥም የሥራ አመራር ቦርደ ቤተክርስቲያኗ በመተዲደሪያ ደንቡ መሪ አድርጋ የሾመቻቸውን ሁለተኛውን አመልካች ከአስተዲደር ሥልጣናቸው አንስቻለሁ በማለት የሰጠው ውሣኔ በቤተክርስቲያኗ ተፈፃሚነት የሚሰጠው መሆኑን የሚመለከት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የውክልና ስልጣን ሰጥቶኛል የሚለው የቀድሞው የሥራ አመራር ቦርድ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በፈጠራው ረብሻ ምክንያት ጠቅላላ ጉባኤው ተሰብስቦ ከኃላፉነታቸው እንዱነሡ የወሰነባቸውና በልላ ሥራ አመራር ቦርድ የተተካ ቤተክርስቲያኗን ወክል ክርክር ለማቅረብ ህጋዊ ህልውና የላለው አካል ነው። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ታይቶ ሉወሰን የማይችል ጉዲይ በዲኝነት ተቀብል በማየት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 37/1/ እና ስለመንግስትና ኃይማኖት መለያየት በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 11 የተደነገገውንና ይኸ ሰበር ችልት የሰጣቸውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉሞች በመጣስ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ የካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ቤተክርስቲያኗ የምትተዲደረው ግንቦት 2 ቀን 2000 ዓ.ም በወጣው መተዲደሪያ ደንብ መሆኑን ገልፀውና የመተዲደሪያ ደንቡን ድንጋጌዎች በሰፉው ዘርዝረው የሥራ አመራር ቦርደ ከአስተዲደር ሥልጣናቸው ካነሳቸው በኋላ ሁለተኛ አመልካች አንደኛ አመልካችን መወከላቸው የሁከት ተግባር ነው። የሁከት ተግባር መሆኑም የወንጀል ምርመራ ተጣርቶ፣ የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ስለዚህ ሁለተኛ አመልካች ከአስተዲደራዊ ሥልጣኑ ከተወገደ በኋላ ሁከት መፍጠሩን በማስረጃ በማረጋገጥ ሁከቱ እንዱወገድ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉዲዩ በዲኝነት የሚያልቅ መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠው በመሆኑ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተን በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካቾች መጋቢት 29 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራቀኙ በዚህ ሰበር ችልት በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች ሁለተኛ አመልካች ከአስተዲደራዊ ሥልጣናቸው በቤtክርስቲያን መተዲደሪያ ደንብ የተነሱ በመሆኑ፣ የቤተክርስቱያኗ የአስተዲደራዊ ሥራ ውስጥ መግባታቸው የሁከት ተግባር ነው። ስለዚህ ሁለተኛ አመልካች በቤተክርስቲያኗ አስተዲደራዊ ተግባር እንዲይሣተፈ በማለት የሰጡት ውሣኔ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርመረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን አመልካቾችና ተጠሪ የሚከራከሩበት መሰረታዊ ጉዲይ ባህሪና ይዘት ምንድን ነው? ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ መሰረታዊ ይዘት ምንድን ነው የሚለትን ነጥቦች በመመልከቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ለሥር ፍርድ ቤት ክሱ ሲቀርብ ቤተክርስቲያኗን በመወከል ለጠበቃ የወኪልነት ሥልጣን የሰጠው የሥራ አመራር ቦርድ፣ የቤተክርስቲያኗ "መሥራች ሀዋሪያ " መሆናቸው በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በወጣው ደንብ ስማቸው የተገለፀውን ሁለተኛ አመልካች ሁለተኛ ተከሳሽ ቤተክርስቲያኗን የማስተዲደር ሥልጣናቸውን በማንሣት በመንፈሳዊ ሥልጣናቸው ብቻ እንዱገደቡ ውሣኔ ከሰጠ በኋላ በቤተክርስቲያኗ የአስተዲደር ሥራዎች እየገቡ ችግር እየፈጠሩ ነው። ስለዚህ ሁለተኛ አመልካች በልላቸው ስልጣን ቤተክርስቲያኗን እንዱያስተዲድር ለአንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ አመልካች/ የሰጠው ውክልና እንዱሰረዝና ሁለተኛ ተከሳሽ በአስተዲደራዊ ሥራዎች ጣልቃ እንዲይገባ ይወሰንልን የሚል ይዘት ያለው ነው።
አንደኛ አመልካችና በጅምሩ የሥራ አመራር ቦርደ ቤተክርስቲያኗን ወክል ክስ ለማቅረብና ለመከራከር የሚያስችለው ሥልጣን የለውም። በመተዲደሪያ ደንቡ የሥራ አመራር ቦርድ በመሥራች ሀዋሪያው /ሁለተኛ አመልካች/ የሰጠውን ስልጣን መንፈሳዊና አስተዲደራዊ ብል የመክፈልና የመሥራች ሀዋሪያውን ሥልጣን ለመቀነስ ወይም የመስራች ሀዋሪያው ቤተክርስቲያኗን የማስተዲደር ሥልጣኑ የማንሣት ስልጣን የለውም። ስለዚህ የሥራ አመራር ቦርድ መሥራች ሀዋሪያው /ሁለተኛ አመልካች/ በቤተክርስቲያኗ የአስተዲደር ሥራ እንዲይሳተፍ የሰጠው ውሣኔ የቤተክርሰቲያኗን መተዲደሪያ ደንብ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተፈፃሚነት የለውም በማለት አንደኛ አመልካች በፅሐፍና በቃል ባቀረበው ክርክር ሁለተኛ አመልካች የግራቀኙ ክርክር በሚሰማበት ቀን ተገኝቶ በቃል ባቀረበው ክርክር የገለጹ መሆናቸውን፣ ለመረዲት ችለናል።
አንድ ክርክር መሰረታዊ ጭብጦች የሚመሰረቱት ከሳሽና ተከሳሽን የሚካካደበትን የሕግ ነጥብ፣ ከሳሽ በክሱ የገለፀውን ፍሬ ነገር እና በማስረጃነት የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ ይዘት፣ ተከሳሹ በመከላከያ መልሱ የገለፀውን ፍሬ ነገርና በመከላከያ ማስረጃነት የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ ይዘትና ፍርድ ቤቱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 241 መሰረት የግራቀኙን የቃል ክርክር ሲሰማ የተገለፁትን ፍሬ ነገሮች መሰረት በማድረግ መሆን እንዲለበት የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246/1/፤የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 247/1/ እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 248 ድንጋጌዎች ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ሲታይ፣ አመልካችና ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር መሰረታዊ ጭብጦች የስራ አመራር ቦርድ ቤተክርስቲያኗን በመወከል ክስ ለማቅረብ ይችላል ?ወይስ አይችልም? የስራ አመራር ቦርድ የመስራች ሐዋሪያውን በቤተክርስቲያኑ መተዲደሪያ ደንብ የተሰጠውን የቤቴክርስቲያን አስተዲደር የመምራት ስልጣን እንዱቀንስ ወይም እንዱሽር የመወሰን ስልጣን አለው ወይስ የለውም? በቤተክርስቲያን አደረጃጀትና የስልጣን ተዋረድ እርከን፣ ከፍተኛ ስልጣን ያለው መስራች ሐዋሪያው ነው ወይስ የስራ አመራር ቦርደ? የስራ አመራር ቦርደ መስራች ሐዋሪያው የቤተክርስቲያን አስተዲደር ስራ እንዲይሰራ በማለት የሰጠው ውሳኔ በቤተክርስቲያን የውስጥ አስተዲደር ጉዲይ ውጤትና ተፈፃሚነት ያለው ውሳኔ ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ናቸው።
ከላይ የተገለፁትንና ግራ ቀኙ የሚከራከሩባቸው መሰረታዊ ጭብጦች በመሰረታዊ ባህሪያቸው 1987 ዓ.ም ህጋዊ ህልውና አግኝታ የተቋቋመችው የኢትዮጵያ የወንጌል ብርሃን ቤተክርስቲያን፣ የተቋቋመችበትን መመስረቻ ፅሁፍ፣ ቤተክርስቲያኗ ኃይማኖታዊ አላማ ለማሳካት፣ የፈጠረቻቸውን መዋቅራዊ አደረጃጀቶች፣ ዓላማዋን ከግብ ለማድረስ ያወጣችውንና በፍትህ ሚኒስቴር ግንቦት 2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ቀርቦ የተመዘገበውን መተዲደሪያ ደንብና የቤተክርስቲያን የተለያዩ አካላት ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፉነት መመርመርና መተርጎም የሚጠይቅ ጉዲይ ነው። በዚህ አይነት መንገድ የተቋቋመ አንድ ሀይማኖታዊ ተቋም፣ የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት የሚያደራጃቸውን አደረጃጀቶች፣ የሚከፍታቸው ቅርንጫፍች፣ የሚፈጥራቸውን መዋቅሮች እንደዚሁም ለተለያዩ የኃይማኖት ተቋሙ አካላት የሚሰጠውን ተግባርና ኃላፉነት፣ በኃይማኖት ተቋም የተለያዩ አካላት መካከል ስለሚኖረው የስልጣን ተዋረድና የእምነት ተቋሙ ኃይማኖታዊ ዓላማውን ለማሳካት ስለሚሰራቸው መንፈሳዊ ተግባራትና የቤተክርስቲያን አስተዲደር ተግባራት እንደዚሁም መንፈሳዊ አስተዲደርና ተግባሩ በየትኛው የኃይማኖች ተቁሙ አካል በኩል መከናወን እንዲለበት የሚነሱ ክርክሮች በመሰረታዊ ይዘታቸውና ባህሪያቸው የኃይማኖት ተቋሙን የተቋቋመበትን መሰረታዊ አላማ የተቋሙን መመስረቻ ፅሁፍ፣ የኃይማኖት ተቋሙ የሚመራባቸውን መሰረታዊ የእምነት ህጎችና ቀኖናዎችና የኃይማኖት ተቁሙን መተዲደሪያ ደንብ በጥልቀት መረዲትና መተርጎምና ተፈፃሚ እንደሆኑ ማድረግ የሚጠይቅ ከኃይማኖት ተቋሙ መሰረታዊና ተፈጥሯዊ ባህሪ ተነጥለው ለየብቻቸው ሉታዩና ሉወሰኑ በፍርድ ሉወሰኑ የሚችለ ጉዲዮች አይደለም። ከዚህ አንፃር ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ጭብጥ በዲኝነት የማያልቅ ከቤተክርስቲያኑ መሰረታዊ ተፈጥሯዊ ባህሪ ተነጥል ላታይ የማይችል ጉዲይ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት የቤተክርስቲያኑን አስተዲደራዊ ስራዎች ለማከናወን የተሰጠ የሹመትና የስርአት ጉዲይ በዲኝነት አይቶ መወሰን የምችለው ጉዲይ ነው።
የቤተክርስቲያኑን መንፈሳዊ ሹመት ስራና ኃላፉነት በተመለከተ በዲኝነት የሚያልቅ ጉዲይ አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 37 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌዎች ይዘት ያላገናዘበ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በዲኝነት አይተው የመወሰን ስልጣን የላቸውም በማለት ወስነናል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.