የግለሰብ ዓለምአቀፍ ህግን / private international law/ የሚመለከቱ ጉዲች ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 25/1988 /እንደተሻሻለ/ አንቀፅ 11/2/ /ሀ/
No summary available.
ሚያዝያ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ መሰረት አለማየሁ - ጠበቃ መላኩ አየነው ተጠሪዎች፡-
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ጋር በአሜሪካን አገር የተፈጸመ ጋብቻ መኖሩን ያስረዲልኛል በማለት ያቀረቡት የጋብቻ ማስረጃ በአዋጅ ቁጥር 334/2004 አንቀጽ 26(1) ድንጋጌ መሰረት በአሜሪካን አገር በሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ያልተረጋገጠ እና ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኃላም ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ መሰረት በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ቀርቦ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካቿ የዚህ ዓይነቱን ሰነድ መሰረት በማድረግ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ መሰረት ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ከጋብቻ እና በጋብቻው የተፈራ ነው ከተባለ ንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ጉዲይ በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ውሳኔ ማሰጠታቸውን፣በጋብቻው ውስጥ የተፈራ ነው ተብል ውሳኔ ካረፈበት ንብረት ውስጥ አንደ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ ባለሶስት ፍቅ ሕንጻ መሆኑን፣የአሁኗ አመልካችም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ መሰረት መቃወሚያ ያቀረቡት በዚሁ ውሳኔ ላይ መሆኑን፣በ20/02/2006 ዓ.ም. አዘጋጅተው ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ አጭር ይዘትም:- ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ጋር በአሜሪካን አገር በ1993 ዓ.ም. ጋብቻ መስርተው አንድ ልጅ እንዲፈሩ፣1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር አብሮ ከመኖር በቀር የፈጸሙት ጋብቻ እንደላለ፣ተጠሪዎቹ በጋብቻ ያፈሩት ነው የተባለው በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ ባለሶስት ፍቅ ሕንጻም የተሰራው በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ የጋራ ገንዘብ እና አመልካች ከአሜሪካን አገር በላኩት ገንዘብ እንደሆነ የሚገልጽ ሆኖ ሕንጻው ለአመልካቿ እና ለ2ኛ ተጠሪ እኩል ከተካፈለ በኃላ 1ኛ ተጠሪ ከፈለጉ ከ2ኛ ተጠሪ ድርሻ እንዱካፈለ እንዱደረግ እና 2ኛ ተጠሪ የልጅ ቀለብ እንዱከፍለ የተጠየቀበት መሆኑን፣1ኛ ተጠሪ በመቃወም አቤቱታው ላይ በሰጡት መልስ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል የተፈጸመ ጋብቻ አለመኖሩን እና የጋብቻ ማስረጃ ነው ተብል የቀረበው ሰነድም በአሜሪካን አገር በሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ያልተረጋገጠ እና ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኃላም በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር ቀርቦ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ አለመሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን፣2ኛ ተጠሪ በመቃወም አቤቱታው ላይ መልስ እንዱሰጡ የተደረገ ስለመሆኑ በብይኑ ላይ የተገለጸ ነገር አለመኖሩን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቿ ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው በመሆኑ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተቀብል የማስተናገድ ስልጣን የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ወይስ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው? የሚለውን ነጥብ ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11 (2) (ሀ) አንጻር እንዱሁም አመልካች በማስረጃነት ያቀረቡትን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የሰጠውን ማረጋገጫ የክልለ ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉት ስለማረጋገጫው ሕጋዊነት ጉዲይ በአግባቡ አጣርተው መሆን አለመሆኑን ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመቃወም አቤቱታውን አስተናግድ ብይን የሰጠው ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን ኖሮት ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከዚሁ ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የስረ ነገር ስልጣን ጉዲይ በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም ማንኛውም ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዲይ አስተናግድ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን ያለው መሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዳታ ያለበት መሆኑ፣ስልጣን የላለው በሆነ ጊዜ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 9(1) እና 231(1)(ለ) እንደተመለከተው ተገቢውን ትዕዛዝ ወይም ብይን ላሰጥበት የሚገባ መሆኑ እና የስረ ነገር ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን የሚያረጋግጠውም በክስ ማመልከቻው ላይ ከተገለጸው ዝርዝር መሆኑ የሚታወቅ ጉዲይ ነው።በልላ በኩል አንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው መሆኑን አረጋግጦ ጉዲዩን ማስተናገድ በቀጠለበት ጊዜም ሆነ በጉዲዩ ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኃላ ክርክሩ ይመለከተናል ወይም የተሰጠው ውሳኔ መብታችንን የሚነካ ነው በማለት በስነ ስርዓት ሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት እንደ የአግባብነቱ የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ወይም የመቃወም አቤቱታ በሚያቀርቡ ሰዎች ማንነት ወይም በሚያቀርቡት የዲኝነት ጥያቄ ባህርይ ላይ ተመስርቶ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የክርክሩ ተካፊይ ያልነበሩ ሰዎች ወደ ጉዲዩ መግባት ጉዲዩን አስቀድሞ ማየት ከጀመረው ወይም ውሳኔ ከሰጠው ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ውጪ ሉያደርግ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች ሉፈጠሩ ይችላለ።የእንደዚህ ዓይነቶቹ አጋጣሚዎች መፈጠር አንደ መንስዔ አገሪቱ መከተል የጀመረችውን የፋዳራሉዝም ስርዓት መሰረት በማድረግ በአገሪቱ ያለው የዲኝነት ስልጣን በፋዳራል እና በክልል የተከፊፈለ መሆኑ እንደሆነ ይታመናል።
በተያዘው ጉዲይ በአሁኖቹ ተጠሪዎች መካከል የተነሳውን ክርክር የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስተናግድ ውሳኔ የሰጠው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ እንደሆነ የመዝገቡ ግልባጭ የሚያመለክት ሲሆን አመልካች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ ያቀረቡትም ተካፊይ ባልሆንኩበት ክርክር ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት ነው።በመሰረቱ የመቃወም አቤቱታ የሚቀርበው መቃወሚያ የቀረበበትን ፍርድ ለሰጠው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 359(1) ስር ተመልክቷል።ይሁን እንጂ የስነ ስርዓት ሕጉ የወጣው አገሪቱ የፋዳራሉዝም ስርዓት መከተል ከመጀመሯ እና በአገሪቱ ያለው የዲኝነት ስልጣንም በፋዳራል እና በክልል ከመከፊፈለ ከረጅም ዓመታት በፉት በመሆኑ ድንጋጌው መተርጎም የሚገባው የፍርድ ቤቶችን የስረ ነገር ስልጣን አስመልክቶ አዱስ ከወጡት የሕግ ማዕቀፍች ጋር በሚጣጣም ሁኔታ ነው።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ የተደረገው የስረ ነገር ስልጣን ያለውን ፍርድ ቤት ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 11(2)(ሀ) ደንጋጌ አንጻር ለማጣራት ሲሆን የተጠቀሰው የአዋጁ ድንጋጌም የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን(ፕራይቬት ኢንተርናሽናል ልው) የሚመለከቱ ጉዲዮችን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን የሚገልጽ ነው።በዚህ ድንጋጌ መሰረት ጉዲዩ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር እንዱወድቅ የሚያደርገው መሰረታዊ ጉዲይ የተከራካሪ ወገኖች ወይም ከእነዚህ አንደ የውጭ አገር ዜጋ መሆናቸው ሳይሆን ይልቁንም ለክርክር የቀረበው ጉዲይ የተለያዩ ሀገሮች ሕጎችን የተፈጻሚነት ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑ ነው።ከክርክሩ መገንዘብ እንደተቻለው አመልካች የሰዊድን፣2ኛ ተጠሪ ደግሞ የአሜሪካን ዜግነት ያላቸው ሲሆን አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጋብቻ ፈጽመን ስንኖር ነበር የሚለትም በአሜሪካን አገር ነው። በልላ በኩል 1ኛ ተጠሪ ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ ክርክሩ የቀረበውም ለኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ነው።ይህ ብቻ ሳይሆን አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በጋብቻ ያፈራሁት ነው የሚለት የማይንቀሳቀስ ንብረትም የሚገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎችም፡-
ሲጠቃለል የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኗ አመልካች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት ያቀረቡትን የመቃወም አቤቱታ ተቀብል በማስተናገድ የሰጠው ብይን የስረ ነገር ስልጣን ሳይኖረው የተሰጠ እና በዚህም ምክንያት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአሁኗ አመልካች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት ያቀረቡትን የመቃወም አቤቱታ ተቀብል በማስተናገድ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ11/07/2006 ዓ.ም. የሰጠው እና በኦሮሚያ ብ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ25/07/2006 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ብይን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን (ፕራይቬት ኢንተርናሽናል ልው) የሚመለከት በመሆኑ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት የስረ ነገር ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 25/1988 (እንደተሸሻሻለ) አንቀጽ 11(2)(ሀ) ደንጋጌ መሰረት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣በሕገ መንግስቱ በተሰጠው የስልጣን ውክልና መሰረት ደግሞ የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ወስነናል።
ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት በተመለከተው መሰረት አመልካች ተጥሶብኛል የሚለትን መብት ለማስከበር ክሳቸውን ማቅረብ የሚገባቸው ለኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።