አንድ በፋደራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት በክልል ቅርንጫፍ ከፍቶ የንግድ ሥራ መሰራቱና ቅርንጫፍ በክልለ ንግድና ኢንደስትሪ ፅ/ቤት መመዝገቡ በፋደራል መንግስት የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በመሆኑ ላይ የሚያሳድረው ለውጥ የላለ ሥለመሆኑና ድርጅቱ ተካፊይ የሆነበትንም ክርክር በዲኝነት አይቶ ለመወሰን ሥልጣኑ የፍደራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀፅ 6/2/ /3/ /4/ ፣ አንቀፅ 5/2/ አዋጅ ቁጥር 25/1988/6/ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግሥት አንቀፅ 80/2/ /4/ XXI
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ገኣትኮ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል መንገድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ -አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ ታህሳስ 18 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የዲኝነት ሥልጣን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በመቀላ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች/ከሳሽ/ ተከሳሽ /ተጠሪ/ በሚካሄደው ጨረታ ለአንድ ዓመት እንዲልሣተፍ ከህግ ውጭ ዕገዲ ጥልብኛል። ስለዚህ ጉዲዩ በፍርድ ተጣርቶ እገዲው እንዱነሳ ይወሰንልኝ በማለት ለወረዲው ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ አመልካች በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት በመሆኑ ጉዲዩ ላቀርብ የሚገባው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተደራቢ የዲኝነት ሥልጣን ላለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የሚል መቃወሚያና ላልች መከረከሪያዎችን አቅርቧል። የወረዲው ፍርድ ቤት የተጠሪን መቃወሚያ በማለፍ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስራጃ ከመዘነ በኃላ ተጠሪ በሚያካሄደው ጨረታ አመልካች ለአንድ ለአመት ያህል እንዲይሳተፍ የሰጠው ዕገዲ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ይነሳ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ተጠሪ ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት የተጠሪን ይግባኝ ሰርዞታል።
ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ አመልካች በፋዳራል መንግስት ተመዝግቦ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት ነው። በፋዳራል መንግስት ተመዝግቦ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት ተካፊይ የሆነበትን ክርክር በዲኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያለው የፋዳራል ፍርድ ቤት ነው። የወረዲ ፍርድ ቤት የፋዳራል ጉዲይ በዲኝነት አይቶ ለመወሰን የሚያስችለው ተደረቢ ወይም በውክልና የተሰጠው የዲኝነት ሥልጣን የለውም። በማለት የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ ሽሮታል።
አመልካች ጥር 21 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አመልካች ቅርንጫፍ ከፍቶ በሚነግድበት ቦታ እንዱመዘገብ የሚያስገድድ በመሆኑ አመልካች ቅርንጫፍ በከፈትኩበት መቀላ ከተማ ንግድና ኢንደስትሪ ቢሮ በመዝገብ ቁጥር 0041/2003 ተመዝግቤ የንግድ ምዝገባ ማረጋገጫ ፈቃድ የተሰጠኝ በመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት አመልካች በፋዳራል የተቋቋመ የንግድ ድርጅት ነው የሚለውን ብቻ በመመልከት የወረዲው ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዲኝነት የማየት ሥልጣን የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል ተጠሪ በበኩለ አመልካች በመቀላ ቅርንጫፍ ከፍቶ የሚነግድ መሆኑ መመዝገቡ የክልል የንግድ ተቋም አያደርገውም። የክልለ ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የለበትም የሚል ይዘት ያለው መልስ መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ/ም በፅሁፍ አቅርቧል:: አመልካች ሚያዚያ 3 ቀን 2006 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ የቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት ሲቀርብ በሰበር አጣሪ ችልት አመልካች የቀረበውን ክስ የወረዲው ፍርድ ቤት በዲኝነት አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም በማለት የክልለ ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የመመሥረቻ ፅሐፍ መተዲደሪያ ደንብና ላልች በንግድ ሕጉና ላልች አግባብነት ባላቸው የሕግ ማዕቀፍች የተደነገጉትን መስፈርቶች አሟልቶ ለፋዳራል መንግስት በማቅረብ፣ በፋዳራል መንግስት ህጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት የተመዘገበ የንግድ ድርጅት መሆኑን በመካድ ያቀረበው ክርክር የለም።
አመልካች የመመሥረቻ ፅሐፈን መተዲደሪያ ደንቡንና ላልች ህጋዊ ሕልውና ለማግኘት አስፈላጊ የሆነ ፍርማሉቲዎች በማሟላት፣ በፋዳራል መንግስት ህጋዊ ህልውና ያለው የንግድ ድርጅት መሆኑ አከራካሪ ካልሆነ፣ አመልካች በመቀላ ከተማ ቅርንጫፍ በመክፈቱ በአዋጅ አንቀጽ 6 ንዐስ አንቀፅ 4 መሰረት በንግድ መዝገብ መመዝገቡ የአመልካችን የክልል የንግድ ድርጅት ወይም የክልልና የፋዳራል ህጋዊ ሰውነት ያለው የንግድ ድርጅት የሚያደርገው አይደለም።
ማንኛውም ሰው በንግድ መዝገብ የሚመዘገበው ዋና መሥሪያ ቤቱ ባለበት ሥፍራ መሆኑንና ማንኛውም ሰው በተለያዩ ክልልች የተለያየ ንግድ ሥራ በሰራም በንግድ መዝገብ የሚመዘግብ የሚመዘገበው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 686 /2002 አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 3 ተደንግጓል። በአዋጅ አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀጽ 4 የተለያያ ቅርንጫፍ ያለው የንግድ ድርጅት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ስፍራ ላለው መዝጋቢ መሥሪያ ቤት አግባብነት ያለውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላትና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና የንግድ ፈቃድ ፍቶ ኮፒ በማያያዝ የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱን አድረሻና ልዩ የምዝገባ የመለያ ቁጥር የማሳወቅ ግዳታ የተጣለበት ሲሆን፣ አዋጁ በአንቀጽ 6 ንዐስ አንቀጽ 4 ያጣለው ይህ ግዳታ በፋዳራል መንግስት ህጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት የተቋቋመን የንግድ ድርጅት የክልል የንግድ ተቋም ወይም የክልልና የፋዳራል ህጋዊ ሰውነት ያለው የንግድ ድርጅት የማድራግ ህጋዊ ውጤት የለውም፡፤
በአዋጅ አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 4 የተቀመጠውና ቅርንጫፍ የማሳወቅ ግዳታ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከፍቶ የሚነግድ የፋዳራል ወይም የክልል የንግድ ድርጅት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን ከፍቶ የንግድ ሥራ በሚሰራባቸው ክልልች ወይም ከተማ አስተዲደሮች የሚሰራው ሥራ ህጋዊ ህልውናና የንግድ ፈቀድ ካገኘበት የንግድ ሥራ ጋር ተመሣሣይ መሆኑን ለመረጋገጥና ቅርንጫፍቹ ጎጅና ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር መሆኑ የአዋጅን አንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 4 እና የአዋጅን አንቀፅ 3 ድንጋጌዎች በጣምራ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጫማሪ የንግድ ድርጅቱ ቅርንጫፍ በከፈተባቸው ሥፍራ ያለ መዝጋቢ አካለት፣ ቅርንጫፍ የሚመዘግቡት በአዋጅ አንቀጽ 5 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ሚኒስትር በሚሰጣቸው ውክልና መሰረት መሆኑ ተደንግጓል። በመሆኑም አመልካች በመቀላ ከተማ ቅርንጫ ስለከፈትኩና ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ በመቀላ ከተማ ንግድና ኢንደስትሪ ቢሮ ያልተመዘገበ በመሆኑ እንደ አንድ የክልለ የንግድ ድርጅት ስለምቆጠር የወረዲው ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለው በማለት ያቀረበውን ክርክር የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች በመቀላ ከተማ ቅርንጫፍ ከፍቶ የንግድ ሥራ መሥራቱና ቅርንጫፈ በመቀላ ከተማ ንግድና እንደስትሪ ቢሮ የንግድ መዝገብ የተመዘገበና ፈቃድ የተሰጠው መሆኑ አመልካች በፋዳራል መንግስት የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በመሆኑ ላይ የሚያሳድረው ለውጥ የለም ከተባለ በፋዳራል መንግስት ዕውቅና የተቋቋመ የንግድ ድርጅት ተካፊይ የሆነበትን ክርክር በዲኝነት አይቶ የመወሰን ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች መሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀጽ 6 ተደንግጓል። በክልል የዲኝነት ሥልጣናቸው በተደራቢነት የፋዳራል ፍርድ ቤት የዲኝነት ሥልጣን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 4 የተሰጣቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ናቸው።
አመልካች ለወረዲ ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበት ጉዲይ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 4 መሰረት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተደራቢ የዲኝነት ስልጣን ላለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ መወሰን ሲገባው በወረዲው ፍርድ ቤት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎችና የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 (2) የሚጥስ መሆኑን በመረጋገጥ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሻረው በህግ አግባብ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭ ግራቀኙ ለያራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.