አንድ ተከሻሽ የጉሙሩክ አዋጅን በመተላለፍ በፈፀመው ድርጊት ጥፊቱ የመጨረሻ ውሳኔ አስከላገኘ ድረስ ሥራ ላይ ከነበረው የጉሙሩክ አዋጅ ይልቅ አዱሱ የጉሙሩክ አዋጅ ለተከሳሽ ቅጣትን የሚያቀል በሚሆን ጊዜ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ የተሻለው ህግ ተፈፃሚ እንዱሆን ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ የኢፋድሬ ህገመንግስት አንቀጽ 22 /2/ ፣የወ/ህ/ቁ/ 6 የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001፣ አዱሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2007
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 112032 ሐምል 20 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ተክሉት ይመስል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጠታ አመልካች፡- 1ኛ የኑስ አህመድ የቀረበ የለም 2ኛ. ግዛቸው አየለ ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዓቃቤ ህግ ባህር ዲር ቅ/ጽ/ቤት ዓ/ህግ ኤርሚያስ ታደሰ - ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በቤንሻንጉል ጉምዝ የመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁኑ ተጠሪ ከሳሽነት ነው። አመልካቾች ጉዲዩን በየደረጃው የተመለከቱት የስር ፍ/ቤቶች ያስተላለፈት የጥፊተኝነት እና ቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረበው ክስ መሰረታዊ ይዘቱ፡- አመልካቾች ህጋዊ ፈቃድ ከላለ በስተቀር በግለሰብ መያዝም ሆነ ማዘዋወር የተከለከለ በቁጥር 903 /ዘጠኝ መቶ ሶስት / ህገ ወጥ የከሳሽ ጥፊት በሁለት ማዲበሪያዎች ቋጥረው በጉዞ ሻንጣ ውስጥ በመክተት ንብረትነቷ የ2ኛ አመልካች የሆነችው የታርጋ ቁጥር ኮድ 2-0705 ቤጉ በሆነች የሞተር ሳይክል በመጫን ከአል መሃል አቅጣጫ ወደ መንጉሻ አቅጣጫ በማጓጓዝ ላይ ሳለ በቀን 03/11/2006 ዓ/ም ከቀኑ በ11፡30 አካባቢ ማንኩሻ ላይ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 1ኛ ተከሳሽ /አመልካች/ የህገ ወጥ ዕቃ ባለቤት 2ኛ አመልካች የሞተር ሳይክለ አሽከርካሪ በመሆን በፈጸሙት ህገ ወጥ ዕቃ መሆኑን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፊይ በመሆን በፈጸሙት የኮንትሮባንድ ወንጀል የወ/ህ/ቁ/32/1/ሀ/ እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91/2/ የተመለከተውን ወንጀል ተላልፎል የሚል ነው።
አመልካቾች ፍርድ ቤት ቀርበው የተጠሪ ክስ እንዱደርሳቸው ተደርጎ ስለጉዲዩ እምነት ክህደት ተጠይቀው 1ኛ አመልካች እንደ ተጠሪ /ዓቃቤ ህግ/ ክስ አቀራረብ ማመኑ በማስመዝገብ ጥፊተኛ ነኝ ያለ ሲሆን 2ኛ አመልካች መካደ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው ተሰምቷል። የዓቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው በሰጡት የምስክርነት ቃል የ1ኛ አመልካች መሆኑን የተረጋገጠው 903 ጥይት በ2ኛ አመልካችም ሞተር ሳይክል ተጭኖ ሲመጣ ኬላ ላይ መያዙን አስረድቷል። 2ኛ አመልካች እንዱከላከል ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም የመከላኪያ ማስረጃ እንደ ላለው በመግለጽ ፍ/ቤቱ በቀረበው ማስረጃ እንዱሁም 1ኛ አመልካች ቀድሞ በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት በማድረግ ሁለቱም አመልካቾች በተከሰሱበት የህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 /2/ ስር ጥፊተኛ ናቸው በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት መዝግበዋል። በተጠሪ /የዐቃቤ ህግ/ በኩል የወንጀለ ደረጃ መካከለኛ ሆኖ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባወጣው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በእርከን 28 ስር ቅጣት እንዱወሰን፤ መቀጮም እንዱወሰን፤ ንብረቱ እንዱወርስ ጠይቋል። አመልካቾቹም የቤተሰብ አስተዲዲሪዎች መሆናቸው ግምት ውስጥ እንዱገባ አመልክቷል። የስር ፍርድ ቤትም የወንጀል ድርጊቱ በሀገሪቱና በህዝብ ደህንነት ላይ አደጋ የሚጥል ስለመሆኑ ድርጊቱም ሆን ተብል የተፈጸመ በመሆኑ በከባድ ደረጃ መድቦታል።
የወንጀል ድርጊቱ ሆን ተብል መፈጸሙ፤ አመልካቾች ድርጊቱን በስምምነት መፈጸማቸው ሁለት ማክበጃ ምክንያት እንደሆነ፤ በአመልካቾች በኩል 1ኛ የዘወትር ጸባያቸው መልካም መሆን፤ 2ኛ ድርጊቱ የፈጸሙት ከህግ እውቀት ማነስ መሆኑ 1ኛ አመልካች የወንጀል ድርጊቱ ማመኑ 3ኛ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆናቸውን በቅጣት ማቅለያነት ተይዞላቸዋል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተሰኙበት ወንጀል ከ7 ዓመት እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ እና የወንጀል ድርጊቱም በከባድ ደረጃ በመመደቡ የቅጣቱ መነሻ እና መድረሻ ለአራት እኩል ሲከፈል ከ11 ዓመት -13 ዓመት ጽኑ እስራት ባለው ፍቅድ ስልጣን በማካተት የእስራት ቅጣት መነሻ እርከን 29 እንደሆነ በመለየት ሁለት ማክበጃዎች በመውሰድ እርከን 31 የወደቀ ሲሆን በአመልካቾች በኩል እያንዲንዲቸው ሶስት ሶስት ማቅለያዎች የተያዘላቸው በመሆኑ በእርከን 28 ከተደነገገው ቅጣት 1ኛ አመልካች 10 ዓመት 2ኛ አመልካች 9 ዓመት ጽኑ እስራት፤ እንዱሁም በመቀጮ ረገድ የወ/ህ/ቁ/ 90/2/ መሰረት በማድረግ እያንዲንዲቸው 6670 ብር እንዱቀጡ ወስኗል።
በኢግዚቢትነት የተያዘው ጥይት እንዱሁም የወንጀል መፈጸሚያ የተባለው ሞተር ሳይክል ለመንግስት ውርስ ይሁን በማለት አዟል።
አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቅሬታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። ጉዲዩ በሰበር እንዱመረመር በመቅረቡ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። አመልካቾች የስር ፍ/ቤት ወንጀለ በከባድ ደረጃ መመደቡ እና የቅጣት ማቅለያዎች አያያዝ ላይ የፈጸመው ስህተት እንዱታረምላቸው ሲጠይቁ፤ ተጠሪ በበኩለ የስር ፍርድ ቤት የወንጀል ድርጊት አፈፃጸም መሰረት በማድረግ በከባድ ደረጃ መድቦ ቅጣት መወሰኑ በአግባቡ ነው የሚል መልስ አቅርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥ በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። እንደመረመርነውም በዚህ ችልት ዕልባት የሚያስፈልጋቸው መሰረታዊ ጭብጦች 1ኛ አመልካቾች ጥፊተኛ መሆን ያለባቸው በቀድሞ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91/2/ ነው ወይስ በአዱሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2007 አንቀጽ 168/2/ 2ኛ የስር ፍርድ ቤቶች የወንጀል ድርጊቱ ከባድ በማለት መመደባቸው በህጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? 3ኛ በስር ፍርድ ቤት እንደ ቅጣት ማክበጃ የተወሰደ ነጥቦች የህግ መሰረት አላቸው ወይስ የላቸውም?
የሚለ ሆነው አግኝተናቸዋል።
ከስር የክርክር ሂደት መረዲት የተቻለው አመልካቾች 1ኛ አመልካች ገደብ የተደረገበት /ህገ ወጥ/ ጥይት ባለቤት፤ 2ኛ አመልካች ንብረቱ የጫነችው ሞተር ሳይክል ባለቤትና ሹፋር በመሆን በ03/11/2006 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት በመንኩሻ ከተማ መግቢያ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ፤ 1ኛ አመልካች ሙለ በሙለ ማመኑ፤ 2ኛ አመልካችም የዐ/ህግ ክስና ማስረጃ አለማስተባበለን የስር ፍርድ ቤት ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ስልጣኑ ከድምዲሜ ላይ የደረሰ ሲሆን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንደተቀበለው ነው። ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የስር ፍ/ቤቶች የፍሬ ነገር ማጣራት እና ማስረጃ ምዘና ስርዓት እንዲለ የሚቀበለው ነው። ምክንያቱም ችልቱ በህግ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዲዮች ማረም ስለመሆኑ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት የምንረዲው ነው።
በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች የፍሬ ነገር ማጣራት እና ማስረጃ ምዘና ድምዲሜ ይዘን ከላይ የተመለከቱት ጭብጦች ከህግ አንጻር እንደሚከተለው መርምረናል የመጀመሪያው ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካቾች ጥፊተኛ የተሰኙት የኮንትሮባንድ ወንጀል በመፈጸም ነው። ይህ ወንጀል በአዋጅ ቁጥር 622/ 2001 አንቀጽ 91/2/ ስር የተመለከተ ሲሆን የሚያስቀጣው በእቃዎቹ ላይ ሉከፍል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር የሚመጣጠን የገንዘብ መቀጫና ከ7 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው። የስር ፍ/ቤትም ይህንን መሰረት በማድረግ 1ኛ አመልካች በ10 አመት 2ኛ አመልካች በ9 አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኗል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለበት አዋጅ ቁጥር 622/2001 ተሽሮ በአዋጅ ቁጥር 859/2007 ተተክቷል። የአመልካቾች የክስ ሂደት እስከ ሰበር ደረጃ ደርሶ ሳይጠናቀቅ አዱስ አዋጅ የወጣ ሲሆን በዚህ አዋጅ ቁጥር 859/2007 አንቀጽ 168/2/ መሰረት የኮንትሮ ባንድ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ ከሶስት ዓመት በማያንስና ከ5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና በብር 50 ሺህ በማያንስና ከብር 100,000 የማይበልጥ መቀጮ ያስቀጣል። በተሻረው እና በአዱሱ አዋጅ በአመልካቾች ላይ በሚጣለው እስራት እና መቀጮ መሰረታዊ ልዩነት እንዲለው ከድንጋጌዎቹ ይዘት መረዲት ይቻላል። ወንጀለ ሲፈጸም ስራ ላይ ከነበረው ህግ ይልቅ የኋላኛው /አዱሱ/ ህግ ቅጣት የሚያቃልለት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ /አመልካቾች/ የተሻለው ህግ ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ከወ/ህ/ቁ/ 6 እና ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 22 /2/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው።በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች የተቀጡት በነባሩ /የቀደም/ አዋጅ ከመሆኑ አንፃር በቅጣት ረገድ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው አዋጅ ቁጥር 859/2007 መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሆኑም አመልካቾች ጥፊተኛ መሆን ያለባቸው አዋጅ ቁጥር 859/2007 አንቀጽ 168/2/ ስር ነው ብለናል።
ሁለተኛው ጭብጥ በተመለከተ፡- የስር ፍ/ቤት የግራቀኙ የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኃላ የወንጀል ድርጊቱ ክብደትና አፈፃጸም መሰረት በማድረግ ቀላል /ዝቅተኛ/ ተብል እንዱመደብ ይህ የማይሆን ከሆነ ደግሞ ዓቃቤ ህግ እንዲለው በመካከለኛ ደረጃ ሉመደብ እንደሚገባ ተከራክሯል።
በመሰረቱ ደረጃ ያልወጣላቸው ወንጀልች የወንጀል ደረጃ እና የቅጣት መነሻ እርከን በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 19 ስር በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት እንዱሁም ፍ/ቤቱ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 19/5/ የተመለከቱት መመዘኛዎች ብቻ ሳይታጠር ላልች መስፈርቶች ተጠቅሞ የወንጀለ ደረጃ እንደሚመደብ በአንቀጽ 19/6/ ስር ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት የወንጀለ አይነትና ክብደት አፈፃጸም። በፍሬ ነገር ደረጃ መዝኖ ከባድ ነው ማለቱ የሚነቅፍ ሆኖ አልተገኘም ። አመልካቾች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ቅሬታ አልተቀበልነውም።
3ኛ ጭብጥ በተመለከተ ፡- የስር ፍርድ ቤት ቅጣት ሲወሰን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያዎች ከግራ ቀኙ የመዘገበ ሲሆን ዐ/ህግ የወንጀለ ደረጃ መካከለኛ እንዱሆን ከመጠየቅ ውጭ ፍ/ቤቱ እንደ ማክበጃ የወሰዲቸው 1ኛ የወንጀል ድርጊቱ ሆነ ተብል መፈጸሙ፤ 2ኛ የወንጀል ድርጊቱ በህብረት ስምምነት የተፈጸመ ነው በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 84/1/ሀ/ እና /መ/ መሰረት በማድረግ ነው። አመልካቾች ጥፊተኞች የተሰኙበት አዋጅ ቁጥር 168/2/ ስር እንደተመለከተው ድርጊቱ የተፈጸመው እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው በማለት የተደነገገ ሲሆን የስር ፍ/ቤት የወንጀል ህግ አንቀጽ 84/1/ሀ/ በመጥቀስ እንደማክበጃ መውሰደ የድንጋጌው መሰረታዊ ይዘት ያላገናዘበ መሆኑን ተረድተናል። በልላ በኩል የስር ፍርድ ቤት የወንጀል ድርጊቱ በስምምነት የተፈጸመ ነው በሚል እንደ ማክበጃ የወሰደው ቢሆንም በወንጀል ህግ አንቀጽ 37 /1/ እና 84/1/መ/ እንደተመለከተው ወንጀል ለመስራት አስቀድመው በመስማማት /Prior meeting of mind/ የኮንትሮባንድ ወንጀል መፈጸማቸው የሚያሳይ ሳይሆን 1ኛ አመልካች የህገ ወጥ ዕቃ ባለላት 2ኛ አመልካች ደግሞ የሞተር ሳይክል ባለቤት በመሆን የኮንትሮባንድ ዕቃው መጫኑን ከመረጋገጡ ውጭ ወንጀለን ከመጀመሪያው አቅደው ፤ጊዜ እና ሁኔታ አመቻችተው ስለመፈጸማቸው በስር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ እንደ ህጉ አነጋገር ቅጣት የሚያከብደ ሁኔታዎች ሳይኖሩ ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች መውሰደ የህግ መሰረት የለውም ብለናል።
በመጨረሻ መታየት ያለበት ጉዲይ ቅጣት ነው። በተጠሪ በኩል በህግ አግባብ ተቀባይነት ያለው የቅጣት ማክበጃ አልቀረበም። በአመልካቾች በኩል ሶስት ሶስት የቅጣት ማቅለያዎች ተቀባይነት አግኝቷል። አመልካቾች ጥፊተኛ የተሰኙበት አዋጅ ቁጥር 859/2007/ አንቀጽ 168/2/ 3-5 ዓመት ጽኑ እስራት በገንዘብ ረገድ ደግሞ ከ50,000-100,000 ብር የሚያስቀጣ ነው። የወንጀለ ደረጃ ከባድ የተባለ በመሆኑ የቅጣት መነሻና መድረሻ ለአራት እኩል ሲከፈል የከባድ ወንጀል ከ4 ዓመት እስከ 4 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው። ይህ ደግሞ በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንቀጽ 26/2/ሐ/ መሰረት መነሻ ቅጣት በሁለት እርከኖች ስር የሚወድቅ ከሆነ ዝቅ ብል ያለው የሚያዝ በመሆኑ በአንቀጽ 19/1/ በመመልከቱ በእርከን 18 ስር ይወድቃል።
ፍ/ቤቱ በተሰጠው ፍቃድ ስልጣን መነሻ ቅጣቱ 4 ዓመት ጽኑ እስራት በመያዝ የቅጣት ማቅለያዎች ተመልክተናል። በእያንዲንደ የቅጣት ማቅሉያ አንድ እርከን ዝቅ የሚል በመሆኑ ቅጣቱ በሶስት እርከን ዝቅ የሚል በመሆኑ በእርከን 15 ይካተታል። መቀጮ በተመለከተ የስር ፍርድ ቤት የወ/ህ/ቁ/90/2/ መሰረት በማድረግ እያንዲንዲቸው ብር 6670 እንዱቀጡ ወስነናል።
ይህ ችልትም አዱሱ አዋጅ በዚህ ረገድ አመልካቾች የማይጠቀም በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የወሰነው መቀጮ እንዲለ ተቀብልታል።
ቅጣት ሲወሰን የወንጀል ህጉ ዓላማ ግብ የሚያሳካ መሆን እንዲለበት በወንጀል ህግ አንቀጽ 1 እና 87 በግልጽ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ በአመልካቾች የተፈጸመው ወንጀል ክብደት በህ/ሰብ/ ሉያደርስ የሚችለው አደጋ በአንድ በኩል፤ የአመልካቾች የመታረም ዕድል በልላ በኩል ግምት ውስጥ በማስገባት አመልካቾች የሚያረምና የሚያስተምር እንዱሁም መሰል ወንጀል ፈፃሚዎች የሚያስጠነቅቅ ነው ብለን ያመንበት በእርከን 15 በተመለከተው ፍቃድ ስልጣን ስር በመሆን እያንዲንዲቸው 2 አመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ የስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ በመለየት እና ሁለቱ ፍርድ ቤት የቅጣት ማክበጃዎች አወሳሰድ ላይ የፈጸሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም ተከታዩን ወስነናል።
የስር መተከል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 10407 በ28/11/2006 ዓ/ም የሰጠው ፍርድና ቅጣት፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ/05758 በ06/05/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 195/2/ለ/2/ መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካቾች ጥፊተኛ መሆን ያለባቸው በአዋጅ ቁጥር 859/2007 አንቀጽ 168 /2/ ስር ነው በማለት ወስነናል።
አመልካቾች በዚህ ጉዲይ የታሰሩበት ካለ በእስራት ቅጣቱ የሚካተት ሆኖ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ እያንዲንዲቸው በ2 አመት ከ9 ወር /ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር/ ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስነናል። አመልካቾች የሚገኙበት ማረሚያ ቤት በተሻሻለው የእስራት ቅጣት መሰረት ያስፈጽሙ ብለናል። የእስራት ቅጣቱ መሻሻለ አመልካቾች ባለበት ማረሚያ ቤት ይድረሳቸው ብለናል።
በስር ፍ/ቤት የተወሰነው መቀጮ እና የንብረት ውርስ የተመለከተ የውሳኔ ክፍል አልተነካም።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.