ገቢውን በሚደብቅ ፣አሳንሶ በሚያሳውቅ፣ በሚያጭበረብር ወይም በማናቸውም መንገድ ግብር ሳይከፍል በሚቀር ግብር ከፊይ ላይ በተጨባጭ መረጃ በመደገፍ ሪፖርት ያቀረበ ሰው ከተደበቀው ግብር እስከ 20% ድረስ ግብሩ ሲሰበሰብ ማግኘት የሚገባው ስለመሆኑ፡አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀፅ 84(1) XX
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 15 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን -ዐ/ህግ ኃ/መለኮት አበበ ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
አቶ ቅባቱ ወ/ሰንበት
አቶ ኤልያስ አሰፊ -ጠበቃ ተሻገር ደሳለኝ ቀረቡ።
አቶ አብርሃ ስዩም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ በገቢ ግብር አዋጅ አግባብ የሚቀርበውን የጥቆማ አበል ክፍያ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
ተጠሪዎች ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ.ም ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የተሻሻለ ክሣቸው ቢ.ጂ.አይ የተባለው ማህበር ለደንበኞቹ የሚሸጥላቸውን የድራፍት መጠጥ መጠን ለመንግስት አሣንሶ ስለሚገልጽ ደንበኞቹ ሉከፍለ የሚገባቸውን ግብር እየሰወሩ እንደሚገኙ በጥቆማ መቀበያ ቅጽ ሴሪ ሕዲር 16 ቀን 2002 ዓ.ም ለአመልካች መስሪያ ቤት እንዲቀረቡለት ፣አመልካችም ጥቆማቸውን መሰረት በማድረግ የግብር ስወራው የሚከናወንባቸው ኮምፒውተሮች፣ ፍላሽ ዱስኮች፣ ድክሜንቶች የተግባሩ ፈፃሚ ማንነትና እና የ3ኛ ወገኖች የሽያጭ ሁኔታ የሚያሣዩትን እቃዎች አመልካቹ ባደረገው ምርመራ ፍሬ ግብር ወለድና መቀጮን ጨምሮ በጠቅላላ ብር 72‚467‚971.65 /ሰባ ሁለት ሚሉዮን አራት መቶ ስልሣ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ብር ከስልሣ አምስት ሣንቲም/ መጠን ያለው ገንዘብ እንዱሰወር ያደረገ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ማህበሩም የወንጀለ ክስ አመልካቹ እንዱተውለት በማስደረግ ገንዘቡን ግን እንዱከፍል የተደረገ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 286/1994 እና ሃምላ 1996 ዓ.ም በወጣው መመሪያ ቁጥር 3.3 መሰረት አመልካቹ ካገኘው ፍሬ ግብር 29,433,465.71 /ሃያ ዘጠኝ ሚሉዮን አራት መቶ ሰላሣ ሶስት ሺህ አራት መቶ ስልሣ አምስት ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም/ 20% የጠቋሚ አበል /ሽልማት/ ብር 5‚886‚693.14 /አምስት ሚሉዮን ስምንት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሶስት ብር ከአስራ አራት ሣንቲም/ የሚገባን በመሆኑ እና ከዚሁ ውስጥም አመልካቹ ብር 1‚471‚672.84 /አንድ ሚሉዮን አራት መቶ ሰባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አራት ሣንቲም/ የከፈለን ሲሆን ቀሪው ብር 4‚415‚020.30 /አራት ሚሉዮን አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ ሃያ ብር ከሰላሣ ሣንቲም/ አመልካቹ ይክፈለን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ አመልካች ለተጠሪዎች ክስ ሃምላ 08 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን የሰጠ ሲሆን ዝርዝር ይዘቱም፡-ተጠሪዎቹ ክሣቸውን ከማሻሻላቸው በፉት ያቀረቡት ክስ ቢ.ጂ.አይ ማህበር ግብር ሰውሯል የሚል ቢሆንም ይህ አባባላቸው በመረጃ ያልተደገፈ መሆኑን፣ የ3ኛ ወገኖች ግዢ ማስተላለፉያ ሰነድ የተገኘው በኦዱተሮች እንጂ በተጠሪዎች /ጠቋሚዎቹ/ እንዲልሆነ፣ የተጠሪዎች ጥቆማው ሕጉን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ሽልማቱ እንደማይገባቸው፣ተጠሪዎች በጥቆማቸው ቢ.ጂ.አይ የግብር ስወራ እንደሚያደርግ እንጂ 3ኛ ወገንኖቹ ግብር እንደሚያጭበረብሩ ጥቆማ ያላቀረቡ መሆኑን ዘርዝሮ ተጠሪዎች ሽልማቱ እንማይገባቸው በመግለጽ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። እንዱሁም የተከሳሽ ከሳሽነት ሐምል 19/2003 ዓ.ም አሻሽል አቅርቧል። በዚህ ክሱም፡- ተጠሪዎች በስህተት የተሰጣቸውን ገንዘብ ብር 1‚471‚672.84 እንዱመልሱለት ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪዎች በአመልካች በቀረበባቸው ክስ ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልሣቸው አመልካቹ ተጠሪዎች የሰጡትን ጥቆማ መሰረት በማድረግ የተጭበረበረና የተሰወረ ግብር የሰበሰበ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ክሱን እና የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን በመስማት ተጠሪዎች በሰጡት ጥቆማ መነሻነት ብር 72‚467‚971.65 ፍሬ ግብር ወለድና መቀጮ መሰብሰቡን አመልካች የሚክደው ባለመሆኑና ከዚህ ውስጥም ብር 29‚433‚456.71 ፍሬ ግብር ሲሆን አመልካቹ ለተጠሪዎቹ ብር 1‚471‚672..84 የከፈለ በመሆኑ ይህም አመልካች በተጠሪዎቹ ጥቆማ እምነት ያሣደረ መሆኑን እንደሚያሳይ፣ አመልካቹ በጠቋሚዎቹ መረጃ መሰረት ከሚሰበሰበው ግብር 20% ለጠቋሚቹ የመክፈል ግዳታ እንዲለበት ሕግ የሚያስገድደው መሆኑን በምክንያትነት ይዞ አመልካቹ ያቀረበውን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ባለመቀበል ቀሪውን የጥቆማ አበል ገንዘብ ብር 4‚415‚020.30 ለዲኝነት ከከፈለት ከ5% የጠበቃ አበልና ላልች ወጪና ኪሣራ በቁርጥ ብር 5000.00 ጋር አመልካቹ ለተጠሪዎች ሉከፍላቸው ይገባል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፈዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ችልቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በጉዲዩ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ የፍሬ ነገርም ሆነ የህግ ስህተት የለበትም በሚል ድምዲሜ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የስር ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን የክስ እናሻሽል ጥያቄ የተቀበለው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 91 ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማ ውጪ መሆኑን፣የተጠሪዎች ክስ በተገቢው ማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን፣ግብሩ የተሰበሰበው በተጠሪዎች ጥቆማ መነሻ ሳይሆን በአመልካች መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ጥረት መሆኑን፣ተጠሪዎች የሰጡት ጥቆማ በሕጉ አግባብ የጠቋሚ አበል የማያሰጥ መሆኑን ያሳያለ ያላቸውን ምክንያቶችን በሰፉው ዘርዝሮ የተጠሪዎች የጠቋሚ ገንዘብ ይከፈለን ጥያቄ ውድቅ መሆን እና ያላግባብ የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ መወሰን ሲገባ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ከ5% የጠበቃ አበልና ከላልች ወጨዎች ጋር እንዱከፈላቸው መወሰኑ በሕግና በማስረጃ አግባብ ባለመሆኑ ውሳኔው ሉሻር ይገባዋል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪዎች ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆኑት ውሳኔዎች እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። ይህንኑ ጭብጥ ለመመለስም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ የተያዙትን ነጥቦች ተመልክተናል።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ተለይተው ከተያዙት ጭብጦች አንደ የተጠሪዎች የክስ ማሻሻል ጥያቄ በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 91 ድንጋጌ አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። በመሰረቱ ፍርድ ቤት አንድ ተከራካሪ ያቀረበውን ክስ እንዱያሻሽል ትዕዛዝ የሚሰጥባቸው ምክንያቶች በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 91 ተደንግጓል። ፍርድ ቤቱ ከሣሽ ያቀረበውን ክስ እንዱያሻሽል ትዕዛዝ የሚሰጠው ከሣሽ ያቀረበው ክስ ጉዲዩን ለመወሰን አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እንደሆነ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር አንቀጽ 91 ንኡስ አንቀጽ 1 ስር ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች መጋቢት 12 ቀን 2003 ዓ/ም ያቀረቡትን ክስ አብራርተው ለማቅረብ ይፈቀድላቸው ዘንድ ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም የተጠሪዎችን ጥያቄ በመቀበል ተጠሪዎች ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ/ም ክሳቸውን አሻሽለዋል። ተጠሪዎች አስቀድመው ባቀረቡት ክስ ቢ.ጂ.አይ ግብር እንዱሰወር ያደርጋል በማለት የገለፁትን የክሱን ፍሬ ነገር በተሻሻለው ክስ ደግሞ ይኼው ቢ.ጂ.አይ የተባለው የአክሲዩን ማህበር የቢራና ድራፍት ምርቶችን በሚሸጥበት ወቅት የሽያጭ ዝርዝሩን ለአዱስ አበባ ፊይናንስ ቢሮ ሲያስተላልፍ እውነተኛውን የሽያጭ መጠን ሳይሆን አሳንሶ ስለሚያቀርብ መንግስት ማግኘት ያለበትን ግብር እንዲይሰበስብ ሆኗል የሚለውን የክሱን ፍሬ ነገር በማካተት ክርክራቸውን ማቅረባቸውን የክርክሩ ሑደት ያሳያል። በዚህ አግባብ ክሱ እንዱሻሻል ተደርጎና በአመልካች በኩል ደግሞ ተገቢ ነው የተባለው ተቃውሞ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ያለውን ብይን በመስጠት ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ም ክሱ ሲሰማም ሆነ ሰኔ 29 ቀን 2004 ዓ/ም ምስክሮች ሲሰሙ በተጠሪዎች የተሻሻለ ክስ የተጠቀሰው ፍሬ ነገር መሰረት ተደርጎ ክርክሩ መመራቱንና በማስረጃዎቹ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር መሰረት ተደርጎ ዲኝነት መሰጠቱን ተገንዝበናል። በመሆኑም ተጠሪዎች በሕጉ አግባብ ጥቆማ አድርገናል በማለት ሉከፈላቸው የሚገባውን የጠቋሚ ገንዘብ ተገቢውን የክስ ምክንያትና የክሱ ፍሬ ነገር በክሳቸው ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት በማናቸውም ጊዜ እንዱያቀርቡ ሉፈቀድ እንደሚችልና የክሱ መሻሻል መሰረታዊ አላማም ጉዲዩን ለመወሰን አስፈላጊ ሁኖ መገኘት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 91 ስር የተመለከተ በመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ሁኖ አልተገኘም።
ላላው አመልካች አጥብቆ የሚከራከርበትና በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገው ነጥብ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ተጠሪዎች የጥቆማ አበል እንዱከፈላቸው የሚያስችለ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ባላቀረቡት ክስ አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪዎቹ የግብር መሰወር ተግባር ፈጽሟል በማለት ጥቆማ ያቀረቡት በቢ.ጂ.አይ ላይ እንጂ በ3ኛ ወገኖች ላይ ባለመሆኑ የጥቆማ ፍርሙ ይዘትና የተጠሪዎች ጥቆማ አይስማማም፣ የተሰወረው ገንዘብ የተገኘው በኦዱተሮቹ ጥረት ነው በማለት ቢከራከርም የአመልካች የ"ኢንተለጀንስ" ባልደረቦች የሆኑት እነ ቁምላቸው ሻምበል ስሜነህ ለሥር ፍ/ቤቱ ቀርበው በሰጡት ምስክርነት ተጠሪዎቹ በወቅቱ ያቀረቡት ጥቆማ ቢ.ጂ.አይ ለደንበኞቹ የሚያቀርብላቸውን የመጠጥ መጠን በመቀነስ ለአመልካቹ ሪፖርት ስለሚያደግ የግብር ስወራ እንደተደረገ የሚገልጽ ነው፣ የመጠቆሚያው ፍርም የጥቆማው ይዘት መዘርዘሪያ በጣም አጭር በመሆኑ በአጭሩ በመፃፈ የተጠሪዎቹ ዝርዝር የጥቆማ ይዘት ለማስፈር እንደሚያስቸግር፣ በተጠሪዎች ጥቆማ መሰረት ኦፕሬሽን መካሄደን በግልጽ እንደሚያሳይ ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የስር ፍርድ ቤት አረጋግጧል። በዚህ ረገድ ተመሳሳይ ስልጣን ያለው ይግባኝ ሰሚው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ይህንኑ የፍሬ ነገር ማጣራትና የማስረጃ ምዘና ድምዲሜ ሙለ በሙለ ተቀብልታል። ይህ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ድምዲሜ የሚያስገነዝበውም ተጠሪዎች የሰጡት ጥቆማ በእርግጥም ለምርመራው መነሻ ሁኖ መንግስት ሉሰበስበው የሚገባውን ግብር ለመሰብሰብ ያስቻለ መሆኑን ነው። በመሆኑም የተጭበረበረው ገንዘብ የተገኘው በኦዱተሮች ጥረት ነው በማለት አመልካቹ ያቀረበው ክርክር የተጠሪዎች ጥቆማ ለኦዱት ምርመራ መነሻነቱ ያልተካደ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም።አመልካቹ የተጭበረበረ ግብሩን የሰበሰበው ተጠሪዎቹ ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ ተረጋግጧል።ይህን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ደግሞ ይህ ችልት የማይቀበልበት የህግ አግባብ የላለ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ዱፏብሉክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።የሥር ፍ/ቤቱ የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ውድቅ በማድረግ ተጠሪዎች የጠየቁት ቀሪ የጠቋሚ ገንዘብ እንዱከፈላቸው መወሰኑ ተገቢነት ያለውና የሕጉንም አላማ የሚያበረታታ ሲል ይግባኝ ሰሚ ችልት መደምደሙም በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን ከሕጉ ጋር ያገናዘበ ነው።
ወደ ህጉ ስንመጣም በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 84(1) እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ገቢውን በሚደብቅ፣አሳንሶ በሚያስታውቅ፣በሚያጨበርብር ወይም በማናቸውም መንገድ ግብር ሳይከፍል በሚቀር ግብር ከፊይ ላይ በተጨባጭ መረጃ በመደገፍ ሪፖርት የቀረበ እንደሆነ የተደበቀው ግብር እስከ 20% ድረስ ግብሩ ሲሰበሰብ ሲጠቃለልም በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ ላይ ዲኝነት የሰጡት የግራ ቀኙን ክርክር በሕጉ አግባብ በመምራትና ፍሬ ነገሩን በሚገባ በማጣራት በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችን እንደሚከፈል ተደንግጓል። እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 96 ድንጋጌ ሲታይ ሕግን በመጣስ የሰበሰበውን ግብር ያላሣወቀ ወይም የሚፈለግበትን ግብር ያልከፈለ ወይም መንግስትን ለማጭበርበር በማሰብ የማይገባውን ተመላሸ ታክስ የጠየቀ ማናቸውም ሰው ወንጀል እንደፈፀመ እንደሚቆጠርና የወንጀል ተጠያቂነትንም እንደሚያስከትል ከአዋጁ አንቀፅ 49 ጋር ተዲምሮ ሲነበብ ያስገነዝባል።
ከዚህ አንጻር ሲታይም የተጠሪዎች ጥቆማ ቢ,ጂ.አይ የተባለው አክሲዩን ማህበር በ3ኛ ወገኖች ሉከፈል ይገባ የነበረውን ግብር እንዲይከፈል የሚያደርግ ተግባር መፈጸሙና በተለይም ራሱ አክሲዩን ማህበሩ የወንጀል ክስ እንዱቀርለት ተደርጎ ሳይከፈል ቀርቷል የተባለውን ግብር መክፈለ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ የሚያቀርበውን ክርክር ለመቀበል የሚያስችል የሕግ ምክንያት አላገኘንም።
ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶቹ ፍሬ ነገሩን አጣርተው ማስረጃውን መዝነው የደረሱበት ድምዲሜ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 84 ድንጋጌ ስር የተመለከተውን የህጉን ይዘት፣መንፈስና መሰረታዊ አላማ ያገናዘበ ሁኖ አግኝተናል። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ የካቲት 08/2005 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ለተጠሪዎች ብር 4‚415‚020.30 /አራት ሚሉዮን አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ ሃያ ብር ከሰላሣ ሣንቲም/ ከ5% የጠበቃ አበል ጋር ይክፈል፣ተጠሪዎች ብር 1‚471‚672..84 ለአመልካች ሉመልሱ አይገባም ተብል በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ ብለናል።
ትእዛዝ
No topics extracted.