የወንጀለኛ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 75 (1)ዋስትናን በመፍቀድ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ እንዲያቀርብ ሕጉ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከልክሎል በሚል አግባብ መተርጎም የላለበት ስለመሆኑ ዋስትናን በመፍቀድ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ከሳሽ /ዐቃቤ ህግ/ ይግባኝ የማቅረብ መብት ያለው አቶ ሀብታሙ ደጁ እና የፋዳራል ዐቃቢ ሕግ ጉሙሩክ/
No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ሀብታሙ ደጁ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቢ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ የወንጀል ሆኖ የዋስትና መብት አፈጻጸምን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረውም ተጠሪው በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ አመልካች እና በልላ አንድ ግለሰብ ላይ ባቀረበው ክስ መነሻ ተከሳሾቹ ባቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-ክሱ የቀረበው ተከሳሾቹ በአዋጅ ቁጥር 761/2004 በአንቀጽ 9 (1) (ሀ) እና (ለ) ስር የተደረነገገውን በመተላለፍ የቴላኮም የማጭበርበር ወንጀል አድርገዋል ተብለው ሲሆን የዋስትና መብታቸው እንዱከበር ተከሳሾቹ ባቀረቡት አቤቱታ ሳቢያ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋስትና ጥያቄው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ በክሱ የተጠቀሰው ድንጋጌ የሚያስቀጣው ከ10 እስከ 20 ዓመት ሉደርስ በሚችል ጽኑ እስራት እና በወንጀለ የተገኘውን ሕገወጥ ጥቅም አስር እጥፍ መቀጮ መሆኑን፣ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ድንጋጌ የዋስትና መብትን የሚከለክል አለመሆኑን እና አመልካቹ የተሟላ አድራሻ ያላቸው እና በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በመሆኑ በዋስትና ቢወጡ ግዳታቸውን አክብረው አይቀርቡም በማለት ተጠሪው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67 (ሀ) ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመግለጽ አመልካች ለብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ)፣2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ግለሰብ ደግሞ ለብር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) ዋስትና አቅርበው በዋስ ሆነው እንዱከራከሩ በመዝገብ በ27/05/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት ትዕዛዝ መስጠቱን፣በትዕዛዙ ቅር በመሰኘት ተጠሪው ባቀረበው ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ተከሳሾቹ ከሚጠብቃቸው ቅጣት ከባድነት አንጻር በዋስ ቢወጡ ግዳታቸውን አክብረው አይቀርቡም የሚለው ግምት ሚዛን የሚደፊ ሆኖ ማግኘቱን ገልጾ የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ በመሻር ተከሳሾቹ ጉዲያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዱከታተለ በመዝገብ በ17/06/2007 ዓ.ም. በዋለው ችልት ውሳኔ መስጠቱን፣አመልካች ይህንን የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ለአመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተፈቀደው የዋስትና መብት በተጠሪው ይግባኝ ባይነት በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 75 (1) አንጻር ሲታይ ዐቃቤ ሕግ ለምን ዋስትና ተፈቀደ በሚል ይግባኝ የማለት መብት ያለው መሆን አለመሆኑን ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የዋስትና መብት ቢኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስትም ሆነ በዝርዝር ሕጎች ከተረጋገጡት የተከሳሽ መሰረታዊ መብቶች መካከል አንደ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በማናቸውም ጊዜ እና ሁኔታ የሚረጋገጥ ሳይሆን ይልቁንም በሕግ በተመለከቱት ምክንያቶች ሉገደብ የሚችል ነው።በተያዘው ጉዲይ አመልካቹ የተከሰሱበት ወንጀል በመሰረቱ የዋስትና መብትን የሚፈቅድ ቢሆንም ተጠሪው የአመልካቹን የዋስትና መብት ጥያቄ የተቃወመው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 67 (ሀ) የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ሲሆን የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝን በመሻር አመልካቹ ጉዲያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዱከታተለ ውሳኔ የሰጠው ይህንኑ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ነው።
የዋስትና ጥያቄን ባለመቀበል በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ የሚባልበትን ሁኔታ በተመለከተ በዋስትና ወረቀት ለመለቀቅ የቀረበውን ማመልከቻ ፍርድ ቤቱ ያልተቀበለው እንደሆነ ተከሳሹ በቁጥር 182 (1) ለተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሃያ ቀን ውስጥ ማመልከቻውን ሉያቀርብ የሚችል ስለመሆኑ በወንጀለኛ ሥነ ሥርዓት ሕጉ በቁጥር 75 (1) ስር ተደንግጓል።
ከሳሽ ወገን ዋስትናን በመፍቀድ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ የስነ ስርዓት ሕጉ በተለየ ሁኔታ ያካተተው ድንጋጌ የለም።ይህ መሆኑ ግን የስነ ስርዓት ሕጉን ቁጥር 75 (1) ድንጋጌ አነጋገር ዋስትናን በመፍቀድ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ እንዲያቀርብ ሕጉ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከልክሎል በሚል አግባብ ለመተርጎም የሚያስችል አይደለም።የዚህ ዓይነቱ አተረጓጎም በስነ ስርዓት ሕጉ ከተመለከተው አጠቃላይ ይግባኝ የማቅረብ መብት ጋርም የሚጣጣም አይደለም።ይልቁንም የዋስትና መብት በተከለከለ ጊዜ ተከሳሽ ወገን ይግባኝ የማለት መብት ያለው ስለመሆኑ ሕግ አውጪው በቁጥር 75 (1) ለይቶ የደነገገው የዋስትና መብትን መሰረታዊነት ከግምት በማስገባት ለጉዲዩ አጽንኦት ለማስጠት በማሰብ አንደሆነ ከድንጋጌው ይዘት እና በስነ ስርዓት ሕጉ ከተመለከተው አጠቃላይ የይግባኝ መብት መርህ መገንዘብ ይቻላል።በወንጀል ስነ ስርዓት ሕጉ በቁጥር 75 (1) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ዋስትናን በመፍቀድ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ የከሳሽን ይግባኝ የማቅረብ መብት በተዘዋዋሪ መንገድ እንደሚከለክል ተደርጎ መተርጎም የሚገባው ስላለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቀደም ሲል በቀረበለት ተመሳሳይ ጉዲይ በመዝገብ የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉምም በዚህ መዝገብ በጭብጥነት ተይዞ ለቀረበው ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው መሆኑንም ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ በመሻር የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 75 (2) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ። ለአመልካቹም በማረሚያ ቤት በኩል ይደረስ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.