የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ሥርዓትም ተፈፃሚነት ሉኖረው የሚገባ አቶ አይሸሽም ገብሬ እና የፋድራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሺን
No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኸሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጤቻ አመልካች፡- አቶ አይሸሽም ገብሬ - ጉዲዩ ተከታታይ ቤተሰብ ቀረበች ተጠሪ፡- የፋዳራል የሥነ - ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀጽ 1በዋና ወንጀል ሰሪነትና በግብረአበርነት አንድ የወንጀል ድርጊት መፈፀማቸው በፍርድ ተረጋግጦ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ባየው ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት /ይግባኝ ሰሚ ችልት/ተመሣሣይ ፍርድና የቅጣት ውሣኔ የተሰጠባቸው ሰዎች በተለያየ መዝገብ የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበው•የአንደኛው የሰበር አቤቱታ አቅራቢ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም ተብል በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቅጽ 22 መሰረት ቢዘጋና የላላኛው የሰበር አቤቱታ አቅራቢ የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት ቀርቦ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ወይም ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፊተኝነት ወይም የቅጣት ውሣኔ ቢሻሻልና የሰበር ችልት በማሻሻል የሰጠው ፍርድ ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልት ለሰበር የሚያስቀርብ ነጥብ የለውም ተብል የተዘጋበትን አቤቱታ አቅራቢ የሚጠቅመው ሆኖ ቢገኝ• የሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም?የሚለውን አከራካሪ የህግ ጭብጥ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች አንደኛ ተከሳሽ በሰበር መዝገብ አመልካች የነበረው አክሉለብርሃን አባቡ ሁለተኛ ተከሳሽ ሆነው በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)ሀ እና አንቀጽ 408 ንዐስ አንቀጽ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ግብር ከፊዮች ቅርንዛፍ ጽ/ቤት ኦዱተሮች ሆነው ሲሰሩ ኦዱት እንዱያደርጉ ከተመደቡበት ኦትራክን/ ጄኔራል ኢትዮጵያ ሰርቪስ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቆዲና ላጦ ፊብሪካ ግብይት አቅራቢ ድርጅት ሂሳቡ አምስት ሚሉዮን ብር ብር / 5000,000/ጉድለት ያሳያል በማለት ከድርጅቱ ሥራ አሰኪያጅ ጋር በአካልና በስልክ በመደራደር ብር 600,000 /ስድስት መቶ ሺህ እንዱከፍላቸው በመስማማት ሰኔ 26 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ አስራ ሁለት ሰዓት ከድርጅቱሥራ አሰኪያጅ ጋር ቀጠሮ በያዙበት ቦታ ተገኝተውና ከድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መኪና ውስጥ ገብተው በተደራደሩበት ገንዘብ ውስጥ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ አንደኛ ተከሳሽ የአሁኑት አመልካች በጥቁር ፋሰታል እንደተጠቀለለ ተቀብል ሲወርድ ሁለተኛ ተከሳሽ /በሰበር መዝገብ /አመልካች የነበረው አክሉለብርሃን አባቡ መኪናው ውስጥ ተቀምጦ ቀሪውን ገንዘብ ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ እያለ የፋዳራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመደባቸው የክትትል አባልች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በማረጋገጥ• የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾች የተከሰሱበትን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ ከባድ የጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች ናቸው በማለት በመዝገብ የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቶባቸዋል።
የቅጣት ውሣኔውን በተመለከተ• ወንጀለ በዝቅተኛ ደረጃ የሚመደብ ነው በማለትና የቅጣት ደረጃው ከሰባት ዓመት እስከ ዘጠኝ ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት መሆኑን ገልፆ በሁለቱም ላይ የመነሻ ቅጣቱ ስምንት ዓመት ፅኑ እስራትና ብር 4000/አራት ሺህ ብር/ መቀጮ እንደሆነ ወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች አራት ታናናሽ እህቶቹን የሚያስተዲድር መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት እንዱያዝለት ያቀረበውን ጥያቄ አስተዲድራቸዋለው ያልከው ልጆችህን ወይም ሚስትህን አይደለም በሚል ምክንያት ውድቅ ካደረገ በኃላ አመልካች የወንጀል ሪከርድ የላለበት መሆኑንና እና ፀባያቸው መልካም የነበረ መሆኑን አንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያትን በመቀበል በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በእያንዲንደ ማቅለያ ምክንያት አንድ እርከን በመቀነስ ከእርከን ሃያ ስድስት ወደ እርከን ሃያ አምስት ዝቅ በማድረግ ተከሳሾች በስድስት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እሰራትና በብር 3000/ሶስት ሺህ ብር/መቀጮ እንዱቀጡ ውሣኔ ሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነት የቅጣት ውሣኔ በመቃወም የአሁኑ አመልካች የወንጀል ይግባኝ መዝገብ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ•ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ወደ ጉዲዩ የሚያስገባ ምክንያት የለም በማለት የካቲት 2ዐ ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ/ትዕዛዝ/ይግባኙን ሰርዞታል። በሰበር መዝገብ አቤቱታ ያቀረበው የሥር ሁለተኛ ተከሳሽ በበኩለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በመቃወም በወንጀል ይግባኝ መዝገብ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ችልት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ወደ ጉዲዩ የሚያስገባ ምክንያት የለም በማለት የካቲት 25 2006 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ/ ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል።
የአሁን አመልካች የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡትን ውሣኔ በመቃወም ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ በዚህ መዝገብ አቅርቦ፣ የሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታውንና መዝገቡን ከመረመረመ በኃላ በቀረበው ጉዲይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተሰርቷል ማለት አልተቻለም በመሆኑም መዝገቡ ለሰበር አያስቀርብም ብለናል በሚል ትዕዛዝ ቅጥምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶበት ተዘግቷል።
ከአመልካች ጋር በወንጀል ተካፊይነት የተከሰሰውና ጥፊተኛ የተባለው እንደዚሁም ይግባኙ በይግባኝ መዝገብ ይግባኝ ሰሚው ችልት የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ /ውሣኔ/ ውድቅ የተደረገበት አክሉለብርሃን አባቡ በሰበር መዝገብ ግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ፅፍ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ በመመርመር የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የጥፊተኝነት ቅጣቱን የወሰንኩት በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ጭብጥ ተይዞ ለሰበር ችልት በመቅረቡ፣ ይኸ ሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡትን የጥፊተኝነት ውሣኔ አፅንቶ የቅጣት ውሣኔውን በማሻሻል መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል።
በሰበር መዝገብ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም የቅጣት ውሣኔውን ሲያሻሽል የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ሁለት መሰረታዊ የህግ ስህተቶች ሰርተዋል።
የመጀመሪያ የቤተሰብ አስተዲዲሪነት በተለይም እናት አባት ወንድም እህት ማስተዲደርና መርዲት /ልጅና ሚስት/ካልሆነ በስተቀር በወንጀል ህግ አንቀጽ 86 የሚሸፍን ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ላሆን አይችልም በማለት የሰጡት የህግ ትርጉም ስህተት ያለበት መሆኑን በመተንተን• ተከሳሹ እርዲታ የሚያስፈልጋቸው ወንድሞቹን እህቶቹን እናትና አባቱን እየረዲና እያስተዲደረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀረበ በወንጀል ህግ አንቀጽ 86 ሥር የሚሸፈን ልዩ የቅጣት ምክንያት እንደሚሆን ትርጉም ሰጥቷል። ሁለተኛው ቅጣቱ መሰላት ያለበት መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት በማድረግ መሆን እንዲለበት በመተንተን• በመዝገብ አመልካች የነበረው ሰው• እናቱን አባቱን ወንድምና እህቶቹን የሚረዲ መሆኑ በልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት እንዱያዝለትና•በሁለቱ የቅጣት ምክንያቶች በመመሪያ ቁጥር 1/2ዐዐ2 አንቀፅ 17 ንሁስ አንቀፅ 7 መሰረት ሶስት እርከን በአጠቃላይ ስድስት እርከን ሲቀንስ ከእርከን ሃያ ስድስት ወደ እርከን አስራ ዘጠኝ ዝቅ የሚል በመሆኑ አመልካች አክለስብርሃን አባቡ በእርከን አስራ ዘጠኝ ከተቀመጠው የቅጣት ሬንጅ ውስጥ በአራት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 3ዐዐዐ/ሶስት ሺ ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ በማለት የሰበር ችልት በመዝገብ ቁጥር 1ዐ1013 መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል ።
ከዚህ በኋላ አመልካች በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ ከነበረው በሰበር መዝገብ የቅጣት ውሳኔ ከተሻሻለበት አክሉብርሃን አባቡ ጋር ተመሣሣይ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ያቀረቡ መሆኑን ገልፆ እህቶችህን የማስተዲድር መሆኑ ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አይሆንም በማለት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚችልት የሰጡት የህግ ትርጉም ስህተት ያለበት መሆኑ በሰበር ችልት የህግ ትርጉም የተሰጠበት በመሆኑና በጉዲዩም ተፈፃሚነት ሉኖረው የሚገባው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2ዐዐ2 መሆኑ በሰበር ችልት የተወሰነ ሆኖ እያለ• የእኔ የሰበር አቤቱታ የሰበር አጣሪ ችልት ለሰበር የሚቀርብ ነጥብ የለውም በል ስለዘጋው ብቻ የእኩልነትና ፍትህ የማግኘት መብቴ ተገድቦ ሉቀር ስለማይገባው• የሰበር ችልት መዝገብ የሰጠው ፍርድ የሚጠቅመኝ በመሆኑ በፍርድ ተጠቃሚ ላሆንና የቅጣት ውሣኔው ሉሻሻልልኝ ይገባል በማለት አቤቱታውንና ክርክሩን አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች በራሱ መንገድ ይግባኝና የሰበር አቤቱታ አቅርቦ እድለን አሟጥጦ የጨረሰና የሥር ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠበት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በሰበር ማጣሪያ ችልት ያፀናበት በመሆኑ• ይኸ ሰበር ችልት በመዝገብ በሰጠው ውሣኔ የሚጠቀምበት የህግ ሥርዓት የለም። ፡ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀፅ 1 የሰበር አቤቱታ ላላቀረቡ ተከሳሾች እንጅ በአመልካች ጉዲይ ላይ ተፈፅሚነት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል ።
መዝገቡ በዚህ ሰበር ችልት የቀረበበት መሰረታዊና አከራካሪ የህግ ጭብጥ አመልካች በዚህ መዝገብ• ከአመልካች ጋር በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከሳሽ የነበረው ሰው በሰበር መዝገብ ያለፈበት ሂደትና የተሰጡ ትዕዛዝና ውሣኔ ይዘት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 196 ንዐስ አንቀፅ 1 በአመልካች ጉዲይ ተፈፃሚነት አለው ወይም የለውም? የሚለውን ጭብጥ ከመወሰናችን በፉት በሰበር መዝገብ የተሰጠው ፍርድ አመልካችን የሚጠቅመው ነው ወይስ አይደለም? የአመልካች ጉዲይ ለሰበር ችልት ቢቀርብ ኖሮ በአመልካች ላይ የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ ሉሻሻልለት ይችል ነበር ወይስ አልነበረም? የሚለትን ነጥቦች መመልከቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካችና በመዝገብ አመልካች የሆነው ሰው በወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና አንቀፅ 408 ንዐስ አንቀፅ 1 በመተላለፍ፣ በዋና ወንጀል ሰሪነት አንድ ላይ ከአንድ ሰው ከባድ ጉቦ የመቀበል ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኛ መሆናቸው እሰከሰበር ችልት ድረስ በተሰጠው ፍርድ ተረጋግጧል። የሥር ፍርድ ቤት ሁለቱም ተከሳሾች ከዚህ በፉት ወንጀል ፈፅመው የማያውቁና የዘወትር ባህሪያቸው መልካም የነበረ መሆኑን አንድ የቅጣት ማቅለያ አድርጎ የያዘላቸው ሲሆን ይህንኑ ይግባኝ ሰሚ ችልትም ተቀብልታል። የሥር ፍርድ ቤት ሁለቱም ተከሳሾች በወንጀል በዝቅተኛ ደረጃ የሚመደብ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የሥር ፍርድ ቤት በሁለቱም ተከሳሾች ለአንድ የቅጣት ማቅለያ አንድ እርከን ብቻ በመቀነስ በእርከን ሃያ አምስት የተመለከተው ሁለቱም ስድስት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራትና በብር 3000/ሶስት ሺ ብር/ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል። ይግባኝ ሰሚው ችልትም ተከሳሾቹ በተናጠል ያስከፈቱትን የይግባኝ መዝገብ መርምሮ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
ይህም የሚያሳየው ከአመልካች ጋር በዋና ወንጀል ተካፊይነት ጥፊተኛ የተባለው በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የነበረው ሰው ለሰበር መዝገብ በአራት ዓመት ፅኑ እስራትና በሶስት ሺ ብር/3000 ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ የተወሰነው፣ ከአመልካች ያነሰ የወንጀል ተሣትፍ ስለነበረው አይደለም። በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ችልትና የሰበር አጣሪ ችልት የሥር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የወሰነውን የቅጣት ውሣኔ ያፀኑት በወንጀል ህግ አንቀፅ 41 በሚደነግገው መሰረት ቅጣቱን በአመልካች ላይ ለይቶ ለመወሰንና ለማፅናት የሚያስችለ የግል ምክንያቶች ያለ መሆናቸውን በማረጋገጥና ይህንንም በሰጡት ውሣኔ ወይም ትዕዛዝ ላይ በግልፅ በማስፈር እንዲልሆነ ተረድተናል።
በአንፃሩ የአሁን አመልካች በሰበር መዝገብ ጉዲዩ ታይቶ የቅጣት ውሳኔው ከተሻሻለለትና በወንጀል ተካፊይነት አብሮት ጥፊተኛ ከተባለው ሰው፣ የተለየ ቅጣት እንዱፀናበት የተደረገው በወንጀል ሕግ አንቀፅ 41 ወይም በወንጀል ሕግ አንቀፅ 88 በተደነገጉና በግልፅ ተለይተው በሚታወቁ ምክንያቶች ሣይሆን፣ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ልጅና ሚስት ካልሆነ በስተቀር ወንድምና እህት እናትና አባት መርዲትና ማስተዲደር በወንጀል ሕግ አንቀፅ 86 የሚሸፈን ልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አይሆንም በማለት በሰጡት የተሣሣተ ትርጉምና ይኽ ሰበር እህትና ወንድም አባትና እናት መርዲትና ማስተዲደር በወንጀል ህግ አንቀፅ 86 የሚሸፈን ልዩ የቅጣት ማቅለያ ይሆናል በማለት በሰጠውና አመልካችን ተጠቃሚ በሚያደርገው ትርጉም ውሳኔ፣ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ባለመቅረቡ ተጠቃሚ ሣይሆን በመቅረቱና አመልካች እህቶቹን የሚያስተዲድር መሆኑ በልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያትነት ሣይያዝለት በመቅረቱ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ይኽ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 በቅጣት አወሳሰን ሂደት የተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 2/2006 ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር፣ ቅጣት ለመወሰን፣ ተፈፃሚነት ያለው የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ስራ ላይ የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ነው በማለት የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 22 እና የወንጀል ህግን አንቀፅ 5 መሰረት በማድረግና ይኽ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 የሰጠውን አስገዲጅ ትርጉም የስር ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ችልት ባለመከተላቸውና መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመፈፀማቸው ምክንያት ነው።
ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች እህቶቹን የሚያስተዲድር መሆኑ በልዩ የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት፣ ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች ያለት መሆኑንና በመመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 17 ንዐስ አንቀፅ 7 መሰረት ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ሶስት እርከን በድምሩ ስድስት እርከን ሲቀነስ በእርከን አሰራ ዘጠኝ ከተገለፁት የቅጣት ሬንጅ ውስጥ የሚወድቅ መሆኑና በሰበር መዝገብ በተሰጠው ፍርድ የሚጠቀም መሆኑ የሚያከራክር ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች በወንጀል ተካፊይነት አብሮት በተከሰሰውና ጥፊተኛ የተባለው ሰው በሰበር መዝገብ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ፍርድ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ከተረጋገጠ አመልካች በተናጠል በዚህ መዝገብ የቀረበው የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ታይቶ ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉ አመልካች የሰበር አቤቱታ ባያቀርብ ኖሮ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ሉያገኝ የነበረውን ጥቅምና መብት የሚያስቀርበት ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ፣ ጉዲዩ የወንጀል ጉዲይ ከመሆኑ አንፃር በፋዳራል ደረጃ ከተዘረጋው የሰበር ሥርዓት መሰረታዊ ዓላማና ግብ መሰረት በማድረግ መመርመሩ አስፈላጊ ነው።
ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ሀ) የተዘረጋው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥርዓት መሰረታዊ ዓላማ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ በሰበር አይቶ በማረም በአገር ውስጥ ሕጎች ወጥ በሆነ መንገድ እንዱተርጎምና ተፈፃሚ እንዱሆኑ በማድረግ የህግ የበላይነትንና ፍትህን ማስፈን ነው። የሰበር ሥርዓት ከይግባኝ እና ላልች የፍርድ ላይ የሚፈፀሙ ስህተቶች ማረሚያ መንገድች የተለያየና የራሱ የሆነ ባህሪ ያለው በመሆኑ ይህንኑ ባህሪውን ያገናዘበና ዓላማውን ለማሣካት የሚያስችል የሥነ ሥርዓት ላልች አሰራሮች ያስፈልጉታል።
በአገራችን የሰበር ሥርዓቱ የሚመራበት ሰበር የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚረዲ የሥነ ሥርዓቱ ህግ የለም። የሰበር ችልት እየሰራ የሚገኘው ጉዲዮችን በመጀመሪያ ደረጃ እና በይግባኝ በሚታዩበት ወቅት እንዱያገለግለ ታስበው ከግማሽ ምዕተዓመት በፉት የወጡና ላልች የሥነ ሥርዓት ሕግ ማዕቀፍችን ነው። ይህም በመሆኑ በሥራ ላይ ያለትንና የሰበር ሥርዓት መሰረታዊ ባህሪና አላማ ግንዛቤ ውስጥ ሣያስገባ ህግ አውጭው የወደዲቸውን የሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ከሰበር ሥርዓቱ መሰረታዊ ባህሪ ጋር በማጣጣምና የሰበርን መሰረታዊ ዓላማ ለመስማት በሚያስችል መንገድ በመተርጎም በማጣጣም ሥራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል።
ለያዝነው ጉዲይ ተፈፃሚነት አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ክርክር ያስነሳው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ 196 ንዐስ አንቀፅ 1 ህግ አውጭው የደነገገውና በሥራ ላይ እንዱውል ያደረገው በአገራችን የሰበር ሥርዓት ባልዘረጋበት ጊዜና የይግባኝ ሥርዓቱ በፍርድ የሚፈጸም የፍሬ ጉዲይ ብቻ ሣይሆን መሰረታዊ የህግ ስህተት ማረሚያ ዋና ሥርዓት ተደርጎ በተዘረጋበት ወቅት መሆኑን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት የታወጀበትን ጥቅምት 23 ቀን 1954 ዓ.ም መመልከቱ ብቻ በቂ ነው።በዚያን የታወጀው የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት አንቀጽ 196 “የተፈረደባቸው ሰዎች ሆነው አንድ ብቻ ይግባኝ ሲያቀርብ” የሚል እርዕስ ያለው ሲሆን የደነገገው ንዐስ አንቀጽ 1 ቃል በቃል ሲነበብ “ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ያቀረበው ይግባኝ ስለተፈረደባቸው ብዙ ሰዎች የሚመለከት ሆኖ ይግባኝ ያለው ግን የተፈረደበት አንድ ሰው ብቻ በሆነ ጊዜ ከዚህ በታች የተመለከተው ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሚሰጠው ፍርድ ይግባኝ ላለትም ሰዎች ይግባኝ እንዲለ ተቆጥሮ ይፈጸምላቸዋል ለማለት የሚችለው /ሀ/ በይግባኝ የተሰጠው ፍርድ ይግባኝ ባዩን የሚጠቅም በሆነ ጊዜና /ለ/ ተከሳሾች ይግባኝ ቢለ ኖሮ በፍርድ እነርሱም ሉጠቀሙ ይችለ ነበር የሚያሰኝ ሆኖ ሲገኝ ነው” የሚል ይሁንታ ያለው ነው።
ይህንን ድንጋጌ አሁን ላለው የሰበር ስርዓት ለመጠቀም ካለው የሰበር ችልት አደራጃጀትና አሰራር ጋር በሚጣጣምና የሰበርን መሰረታዊ ዓላማ ሉያሳካ በሚችል መንገድ መተርጎምና ስራ ላይ ማዋል ይጠይቃል። የመጀመሪያው ብዙ ተከሳሾች አንድ ወንጀል የወንጀል ስራው ተካፊይና ግብረ አበር ሆነዋል ተብለው ክስ ቀርቦባቸውና፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ባየው ፍርድ ቤት እና በይግባኝ ባዩው ፍርድ ቤት ወይም ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አንደኛው ተከሳሽ የሰበር አቤቱታ አቅርቦ፣ አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል በሰበር ችልት ታይቶ፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ወይም በይግባኝ አይቶ ውሳኔ የሰጠው ፍ/ቤት የጥፊተኝነት ወይም የቅጣት ውሳኔ ወይም የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔው መሰረታዊ ህግ ስህተት አለበት ተብል ከተሻረ፣ ከተሻሻለ ወይም ከተለወጠና የሰበር ችልት በመሻር፣ በማሻሻል ወይም በመለወጥ የሰጠው ውሳኔ የሰበር አቤቱታ ያላቀረቡትን ላልቹ በአንድ ጉዲይ የተከሰሱ ሰዎችን የሚጠቅም ሆኖ በተገኘ ጊዜ፣ ሰዎቹ ፍርድን በመቃወም የሰበር አቤቱታ ባያቀርቡም ሰበር ችልት በሰጠው ውሳኔ ወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ተጠቃሚ እንደሆኑ በሚያደርግ አግባብ ድንጋጌው መተርጎምና ስራ ላይ መዋል አለበት የሚለው ነው።
ሁለተኛው በአንድ ወንጀል አድራጎት በወንጀል ህግ ስለወንጀል ተካፊይነት አድራጊነት ወይም ስለግብረአበርነት በተደነገጉት መሰረት በአንድ ላይ ፈጽመዋል ተብለው ክስ ከቀረበባቸው ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ባየውና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው ሰዎች ብዙ ሰዎች ሁለም በግላቸው የሰበር አቤቱታ አቅርበው የሰበር መዝገብ አስከፍተው ከፉልቹ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታና የስከፈቱት የሰበር መዝገብ በሰበር ችልት የሚቀርብ መሰረታዊ የህግ ስህተት ጭብጥ የለውም ተብል በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 22 መሰረት በሰበር አጣሪ ችልት ውድቅ ቢደረግና ቢዘጋ የከፉልቹ ወይም አንደኛው ተከሳሽ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ በሰበር የሚጣራ መሰረታዊ የህግ ጭብጥ አለው ተብል ለሰበር ችልት ቀርቦ የሰበር ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የጥፊተኝነት ውሣኔውን ወይም የቅጣት ውሳኔውን ወይም የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔውን መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር ችልት ከሻረው ካሻሸለው ወይም ከለወጠውና ውሳኔው የሰበር አቤቱታ አቅርበው የሰበር ማጣሪያ ችልት የሚጣራ መሰረታዊ የህግ ስህተት ጭብጥ የለውም ብል አቤቱታውን ውድቅ ያደረገባቸውን ሰዎች የሚጠቅም ሆኖ በተገኘ ጊዜ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ህግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል የሚለው ነው፡፤
ለዚህም ምክንያቱ ለይግባኝ ሥርዓት ታስቦ የተደነገገው የወንጀለኛ መቅጫ ሥርዓት ህግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀፅ 1 አሁን ያለውንና በአዋጅ ቁጥር 25/88 የተደነገገውንና የተዘጋውን የሰበር ችልት አደረጃጀት ጋር በሚጣጣም መንገድ ሥራ ላይ ካልዋለና• አሁን በመዝገቡ ለያዝነው ጉዲይ ተፈፃሚ የማይሆን ከሆነ አንድ የወንጀል ድርጊት በአንድ ላይ ፈፅማችኃል ተብለው ተከሰው ቢኖር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወይም ይግባኝ ሰሚው ችልት ከተመሣሣይ የወንጀል ህግ ድንጋጌ ጥፊተኛ ተብለውና በወንጀለ የነበራቸው ተሣትፍ እና ላልች ግላዊ ሁኔታዎች ተመሣሣይ ሆኖ በመገኘቱ ተመሣሣይ የሆነ የቅጣት ውሣኔ የተላላፈባቸው ሰዎች፣ የአንደኛው የሰበር አቤቱታ የሚጣራ የህግ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ችልት ሰለቀረበና በውሣኔው ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑ ተገልጾ በሚሰጠው ፍርድ ተጠቃሚ የሚሆንበት የላላኛው የሰበር አቤቱታ የሰበር አጣሪ ችልት ለሰበር የሚቀርብ የለውም ተብል ውድቅ ስለተደረገበት ብቻ የፍርደ ተጠቃሚ የማይሆንበትን አግባብ መከተል በህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 እና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 4 የተደነገገውን የእኩልነት መርህ የሚጥስና የሰበርን መሰረታዊ ዓላማ የማያሳካ ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ወንጀል በጋራ ፈፅማችኋል ተብለው የተከሰሱና ጥፊተኛ ተብለው ከተቀጡ ሰዎች መካከል፣ ላልቹ ሰዎች መብታቸውን ለሰበር ችልት ለማቅረብ ዲኛ ሆነው አንደኛው ተከሳሽ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሰበር ችልት በሰጠው ፍርድ ላልቹ ተከሳሾች በሚጠቅሙበት አግባብ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 196 ንዐስ አንቀጽ 1 ጥቅም ላይ የሚውለና የሚፈፀም ከሆነ፣ በአንድ የወንጀል ድርጊት የተከሰሱ ሁለም ሰዎች መብታቸውን ለሰበር ለማቅረብ ተገቢውን ትጋት አሳይተው ለሰበር ችልት በማቅረባቸውና የከፉልቹ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመደረጉና የከፉልቹ ለሰበር የሚቀርብ ነጥብ የለም ተብል በመዘጋቱ•የሰበር ችልት የሰጠው ፍርድ የሰበር አቤቱታቸው ውድቅ የተደረገባቸውን ሰዎች የሚጠቅም ሆኖ እያለ በፍርደ ተጠቃሚ እንዲይሆኑ ማድረግ፣ በአጠቃላይ የሰበር ሥርዓቱን መሰረታዊ አላማና ሕግ አውጭው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 196 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ሉያወጣ የፈለገውን ግብ፣ አሁን ካለው የሰበር አደረጃጀት ጋር በሚጣጣም መንገድ ሥራ ላይ እንዲይውል የሚደረግና ሰዎች ተግተው የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ምክንያት ብቻ የድንጋጌው ቱርፊት እንዲይደርሳቸው የሚያደርግ በመሆኑ፣ ይህንኑ ድንጋጌ ይህንኑ ሁኔታ በሚሰጥበት አግባብ መተርጏም ሥራ ላይ መዋል ያለበት ሆኖ አግኘተነዋል።
አመልካች የሰበር አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችልት ውድቅ ባይደረግ ኖሮ ይኸ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ በሰጠው ፍርድ እና ከአመልካቹ ጋር ዋና ወንጀል አድራጊ ሆኖ በተከሰሰው ሰው፣ የቤተሰብ አስተዲዲሪነቱ በልዩ ቅጣት ማቅለያነት እንዲይዝለት ይኸ ሰበር ችልት በሰጠው የህግ ትርጉም ቅጣቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2001 አንቀጽ 17 ፀዐስአንቀጽ 1መሰረት ለአንድ የቅጣት ማቅለያ ሶስት እርከን መቀነስ እንዲለበት ይጭ ሰበር ችልት መሰረታዊ ዓላማ፣ ለማሳካት ፣ በህገ መንግስቱአንቀጽ 80 ፀጉስ አንቀጽ 3ን/ሀ/የተደነገገውን የሰበር ችልት መሰረታዊ ዓላማ፣ ለማሳካት፣ በህገመንግስቱ አንቀጽ 25 እና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 4 የተደነገገውን የእኩልነት መርህ ተግባራዊ ለድረግ፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 196ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ከስር አደረጃጀትና አሰራር ጋር በማጣጣም መተርጏምናአመልካች በሰበር መዝገብ በተሰጠው ፍርድ ተጠቋሚ ማድረግ አስፈላጊ ነው በማለት ወስነናል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች እህቶቹን የሚያስተዲድር መሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 86 ልዩ የቅጣት ማቅለያ ሆኖ ሲያዝለት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ከያዙለት አንድ የቅጣት ማቅለያ ጋር ተደምሮ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ይኖረዋል ። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወሰኑት የቅጣት መነሻ ከሚገኝበት እርከን ሃያ ስድስት እያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ በመመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 17 ንዐስ አንቀፅ 7 መሰረት ሶስት እርከን ሲቀነስ በአመልካች ላይ የሚወሰነው ቅጣት እርከን አስራዘጠኝ ላይ የሚወድቅ ይሆናል ። በመሆኑም በእርከን አስራዘጠኝ ከተቀመጠው የቅጣት ሬንጅ ፈቃደ ስልጣናችንን ተጠቅመን አመልካች በቀሩት ዓመት ፅኑ እስራት እና ብር 3000 /ሶስት ሺ ብር/ መቀጮ ይቀጣል በማለት ወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 196 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት በአመልካች ላይ የተሰጠውን የቅጣት ውሣኔ አሻሽለን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው የቅጣት ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንጀል ይግባኝ መዝገብ የሰጠው ውሣኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/196 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ተሻሽልአል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ማጣሪያ ችልት ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በዚህ ፍርድ ተለውጧል።
አመልካች በዚህ ጉዲይ ተጠርጥሮ እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ አራት ዓመት ፅኑ እስራትና ብር 3000 /ሶስት ሺ ብር/ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል በማለት ወስነናል ።
የቅጣት ውሣኔ የተሻሻለ መሆኑን አውቆ ተከታትል እንዱያስፈፅም ሉክፍለ ማረሚያ ቤት ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።