ፍ/ቤቶች የተከሳሽን የመከላከል መብት የማክበርና የማስከበር ህገመንግስታዊ ኃላፉነትና ግዳታ ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ህገ መንግስት አንቀፅ 13(1)፣13(2)፣20(4) የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 142(1) ዓለም አቀፍ የማህበራዊና ፖለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀፅ 14(3)(ረ)
No summary available.
ሐምል 15 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ፊንቱ ጉቼ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ዐቃቢ ሕግ - ወ/ት ፍጹም ደጉ ቀርበዋል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለው የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ. 61059 ላይ በ18/06/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ በማለት በ22/07/2006 ዓ.ም የተጻፈ አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪ / የሥር ከሳሽ/ የዲራ ወረዲ ዐቃቢ ሕግ በዲራ ወረዲ ፍ/ቤት በቀረበው የማታለል ወንጀል ክስ የአሁን አመልካች /የሥር ተከሳሽ/ አቶ ፊንቱ ቡቼ የ/ወ/ሕ/ቁ. 692/1/ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ የግል ተበዲይ አቶ ቾቼ ላሚሶ በፍ/ቤት ላለው የመሬት ክስ ዳኞችን ይዤ ነገርን አስጨርሼልሃለሁ በማለት ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በአጠቃላይ ብር 25,000/ ሃያ አምስት ሺህ/ በማታለል በመውሰድ ተከሷል የሚል ነው ። ተከሳሽ አቶ ፊንቱ ቡቼ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለት በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል “ወንጀለን አልፈጸምኩም በማለት ክድ ቃለን ሰጥቷል” ። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግል ተበዲይን ጨምሮ የዐቃቢ ህግ ሶስት የሰው ምስክሮች ተሰምተዋል ። በመቀጠልም ፍ/ቤቱ ተከሳሹን ተከላከል ማለቱን ክሱን ተከላከል ብል ከሆነ የመከላከያ ምስክሮች ለምን ቀርቦ እንዲልተሰሙ በምን ምክንያት እንደታለፈ በውሳኔው ላይ የጠቀሰው ነገር የለም። ነገር ግን የወረዲው ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 11973 በ22/12/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት የዐቃቢ ህግ ምስክሮችን ቃል በመመዘን እንደክሱ አረጋግጧል በማለት ተከሳሹን በወ/ሕግ አንቀጽ 692/1/ ሥር ጥፊተኛ በማድረግ የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት በመቀበል የወንጀለን ደረጃ 5 አድርጎና የቅጣት እርከን 14 በመያዝ በ3 ዓመት እስራት እና 1000 ብር እንዱቀጣ ወስኗል ።
የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታውን ለሶዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረቡ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በመዝገብ ቁጥር. 30133 በ30/01/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195 /2/ለ-2/ መሰረት የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ የሥር ውሳኔን በማጽናት ወስኗል ። አመልካች አሁንም ይህን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታውን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም፣ ችልቱ በመዝገብ ቁ. 61059 በ18/06/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለላለ አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት አያስቀርብም በማለት ወስኗል ። አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ሉያቀርብ የቻለው ይህ ውሳኔ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በ22/072006 ዓ.ም በተጻፈው አቤቱታ የዐ/ሕግ የሰው ምስክሮች እንደክሱ ጭብጥ የአስረደት ነገር የለም ። ክሱ ራሱ በሰዎች ቅንብር በውሸት የቀረበብኝን ነው። እኔ ይህን ገለሰብ አምስት ጊዜ ወደ ቤት በመጥራት የተጠቀሰውን ገንዘብ ስቀበል ምንም አይነት ውል ወይም ተጨባጭ ማስረጃ በላለበት ይህን ብር ሰጥቼዋለሁ ያለው አግባብነት የለውም። ዐ/ህግ የማስረዲት ሃላፉነቱን አልተወጣም ። የዐ/ህግ ምስክሮች ከጥርጣሬ ውጭ ስላላስረደ በነጻ መሰናበት ነበረብኝ። እኔ የተከሰስኩበት ወንጀል የዋስትና መብት የማያስከለክለኝ ቢሆንም የወረዲው ፍ/ቤት አሳስሮኝ መከላከያዬን እንዲላቀርብ ስላደረገኝ በሕገ መንግስት አንቀጽ 19-20 የተደነገገውን የመከላከል መብቴን ያጣበበብኝ በመሆኑ በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ግድፈት ተፈጽሟል በማለት በዝርዝር አቅርቧል ። ስለዚህ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን ተመልክቶ የሥር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻር በነጻ እንዱያሰናብተኝ በማለት አመልክቷል ።
ከዚህ በኋላ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በመመርመር አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል በማለት ተጠሪው መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት በ07/11/2006 ዓ.ም በተጻፈ መልስ አመልካች ከግል ተበዲይ በማታለል በተለያየ ጊዜ መውሰደን የዐ/ህግ ማስረጃዎች በተገቢ ሁኔታ ከጥርጣሬ በላይ መስክረዋል የመከላከል መብት በተመለከተ የወረዲ ፍ/ቤት ሕገ መንግስትና የወንጀል ህግ ስነ ስርዓትን መሰረት በማድረግ የዐ/ህግ ማስረጃዎች በ15/12/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ከሰማ በኋላ ፣ ከጥርጣሬ በላይ ስለተመሰከረበት ተከሳሹ እንዱከላከል ትእዛዝ በመስጠት የመከላከያ ምስክሮች ስም ዝርዝር አቅርቦ በ16/12/2005 ዓ.ም ቀርቦ እንዱከላከል ወስኖ በእለቱ በዋለው በወንጀል ችልት መከላከያዎቹን ባለማቅረቡ በድጋሚ እድል በመስጠት በ20/12/2005 ዓ.ም አቅርቦ እንዱከላከል ህገ መንግስታዊ የመከላከል መብቱ ቢጠበቅለትም በራሱ ፈቃድ መብቱን አለመጠቀሙ ፍ/ቤቱ መብቱን አጣቧል ለማለት አይቻልም።
ስለዚህ አመልካች የህግ ስህተት አለባቸው ብል ያቀረባቸው ነገሮች የህግ ስህተት የላለበትና ተገቢ የሆነ ውሳኔ የተሰጠበት ነው በማለት በዝርዝር የተለያዩ ነጥቦችን በማንሳት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱጸና በማለት ተከራክሯል ።
አመልካች በ02/04/2006 ዓ.ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል ።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ አመልካች የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ የመከላከል መብት የታለፈው በህግ አግባብ ነው? ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው ምርምረናል ።
ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው የዲራ ወረዲ ዐ/ህግ በዲራ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች የማታለል ወንጀል ፈጽሟል በማለት የወ/ሕ/ቁ. 692/1/ በመጥቀስ የቀረበውን ክስ በተመለከተ አመልካች ፍ/ቤት ቀርቦ በሰጠው ቃል የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈጸምኩት በማለት ክድ ተከራክሯል ። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግል ተበዲይን ጨምሮ ሶስት ምስክሮችን መስማቱን በውሳኔው ላይ ጠቅሷል። ነገር ግን ፍ/ቤቱ የዐ/ህግ ምስክሮች እንደክሱ ስላረጋገጡ አመልካችን ተከላከል ማለቱን አመልካች በምን ምክንያት የመከላከያ ማስረጃውን እንዲላቀረበና እንደታለፈ በውሳኔው ላይ የጠቀሰው ነገር የለም የወረዲው ፍ/ቤት የውሳኔ አጻጻፍ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ፍ/ቤቱ ለዚህ መብት ተገቢ ግምት ሰጥቷል ወይ? የሚል የሕግ ጥያቄ የሚያነሳ ነው።
በዚህ አግባብ ሲታይ ፍ/ቤት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 142/1/ እንደሚደነግገው የዐ/ህግ ህግና የተበዲይ ማስረጃ እንደክሱ ጭብጥ የመሰከሩ ወይም ያረጋገጡ ከሆነ ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ ማሰማት እንደሚጀምርና መንገር እንደሚችል ነው። ከዚህ ድንጋጌ መረዲት እንደሚቻለው የመከላከያ ማስረጃን አቅርቦ ማሰማት የተከሳሹ መብትና ግዳታ መሆኑን ነው ።
ፍ/ቤቱ ግን ተከሳሽ በዚህ መብቱ እንዱጠቀም የነገረው መሆኑን በውሳኔው ማመልከት ተገቢ ነው። ከዚህ በላይ የተከሰሱ ሰዎች በህገ መንግስቱ ከተከበረላቸው ሰብዓዊ መብቶች መካከል “ የመከላከል መብት” አንደ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20/4/ መገንዘብ ይቻላል።
በዚህ አንቀጽ መሰረት የተከሰሱ ሰዎች “ የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡበትን ምስክሮች የመጠየቅ ፣ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸው ቀርቦ እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው”። ስለዚህ የመከላከል መብት ሕገ መንግስታዊ ጥበቃ ያገኘ መብት መሆኑን ያስገነዝባል።
ከዚህም በላይ ይህ “ የመከላከል መብት “ በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና ዓለም አቀፍ ሰነድች ጥበቃ የተደረገለት መሆኑን መረዲት ተገቢ ነው እ.ኤ.አ በ1976 በጸደቀው ዓለም አቀፍ የማህበራዊ እና የፖለቲካ መብት ስምምነት አንቀጽ 14/3ረ/ እንደሚደነገገው የተከሰሰ ሰው የራሱን ምስክሮች አቅርቦ የመጠየቅ መብት እንዲለው ነው ። ይህ ደግሞ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 13/2/ ሽፊን ያገኘ ጉዲይ ነው።
ይህ “ የመከላከል መብት” በተመለከተ ፍ/ቤት ያላቸው ሚና ሲታይ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 13/1/ መሰረት “ የማክበርና የማስከበር ሃላፉነትና ግዳታ አለባቸው” ከዚህ አኳያ ፍ/ቤት የተከሰሱ ሰዎች የመከላከል መብታቸውን በሚገባ መጠቀም እንዱችለ አስፈላጊውን ሁኔታ ለማመቻቸት በሕግ አግባብ የተቻለውን ሁለ ማድረግ ይጠበቅበታል እንጂ በምንም መልኩ ይህን መብት ለሚገድብ ድርጊት አስተዋጽኦ ማድረግ የለበትም ፍ/ቤት የተቀላጠፍ ፍትህ አሰጣጥን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተከሰሰው ሰው ምስክሮቹን ለማቅረብ ያለው አቅም እና የተመቻቸ ሁኔታ፣ በማረሚያ ቤት መሆኑን እና አለመሆኑን፣ የመከላከያ ማስረጃና ምስክሮችን ለማቅረብ የሚጠይቀውን እገዛ፣ በቂ ነው ልባል የሚችል ጊዜ እና አጠቃላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዚህ መብት ተጠቃሚ እንዱሆን አስፈላጊውን ሁለ ማድረግ ይጠበቅበታል።
ስለዚህ ፍ/ቤት ይህን ሕገ መንግስታዊ ሃላፉነትና ግዳታውን በአግባቡ መወጣት አለበት።
ከዚህ አንጻር አሁን የያዝነው ጉዲይ ስንመለከት የዲራ ወረዲ ፍ/ቤት አመልካች የዐ/ህግ ምስክሮች እንደክሱ ስለመሰከሩበት እንዱከላከል ብይን መስጠቱን አመልካች የመከላከያ ምስክሮቹን ከማቅረብ አንጻር የጠየቀውን መብት የመከላከያ ምስክሮችን ሳይሰማ ለምን እንደታለፈ በውሳኔው ውስጥ የጠቀሰው ነገር የለም። የወረዲው ፍ/ቤት ይህን ያህል በዓለም አቀፍ ሰነድች እና በሕገ መንግስቱ ጥበቃ የተደረገለትን የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ክስ የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ “ የመከላከል መብት “ በውሳኔው አለማካተቱ በሕገ መንግስቱ የተጣለበትን ሃላፉነት በሚገባ ተወጧል ብል ለመናገር የሚያስችል አይደለም። የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የሰበር ሰሚ ችልት የወረዲውን ውሳኔ ማስተካከል ሲገባቸው ውሳኔውን ማጽናታቸው ከዚህ አንጻር የሚጠበቅባቸውን ሚና ተወጥቷል ለማለት አያስደፍርም።
በዚህ በኩል ተጠሪ ያቀረበው መልስ ሲታይ ፍ/ቤት በ15/12/2005 ዓ.ም የዐ/ህግ ምስክሮችን እንደሰማ አመልካች በ16/12/2005 ዓ.ም የመከላከያ ምስክሮቹን እንዱያቀርብ መታዘዙን ፣ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ለ20/12/2005 ዓ.ም እንደተሰጠ በመጥቀስ አመልካቹ በራሱ ፈቃድ መከላከል እንዲልፈለገ በመጥቀስ ተከራክሯል ። አመልካች ደግሞ ባቀረበው ክርክር ፍ/ቤቱ በማረሚያ ቤት እንዱታሰር አድርጎኝ በሁለት ቀን ውስጥ እንዱከላከል ትእዛዝ መስጠቱ እንዲልከላከል እንደማድረግ ይቆጠራል። በማለት የመልስ መልሱን ሰጥቷል ። የወረዲው ፍ/ቤት ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮችን እንዱያቀርብ የሰጠው ጊዜ በአጠቃላይ ከ4 ቀናት የሚበልጥ አይደለም ከዚህ ክርክር መረዲት እንደሚቻለው ፍ/ቤቱ አመልካች በማረሚያ ቤት ታስሮ መገኘቱን እያወቀ የመከላከያ ምስክሮቹን አቅርቦ በማሰማት ሕገ መንግስታዊ መብቱን በሚገባ እንዱጠቀምበት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በቂ ነው ልባል የሚያስችል ጊዜ ሰጥቷል ለማለት አይቻልም ። ፍ/ቤቱ አመልካቹ ያለበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ምስክሮቹን እንዱያቀርብ በማዘዝ፣ ምስክሮችን አላቀረብክም በማለት ማለፍ መብቱን እንዲይጠቀም እንደመከልከል የሚቆጠር ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ የስር ፍ/ቤቶች አመልካቹ “የመከላከል መብቱን እንዱጠቀም ተገቢና አስፈላጊ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ በህገ መንግስቱም ሆነ በወንጀል መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ግዳታ በሚገባ ተወጥቷል ለማለት አይቻልም። ስለዚህ የስር ፍ/ቤቶች አመልካች የመከላካ ምስክሮችን አቅር እንዱያሰማ በማድረግ፣ የመከላከል መብቱን ያለ የሕጋዊና በቂ ምክንያት በማለፍ የጥፊተኝነት ውሳኔ እና የቅጣት ውሳኔ ይደነበት አግባብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል ።
የዲራ ወረዲ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 11973 በ22/12/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 30133 በ30/01/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ. 61059 በ18/06/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ተሸሯል ።
የዲራ ወረዲ ፍ/ቤት ይህ ጉዲይ ድጋሚ በማየት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስ በማስገባት በቂ ነው ልባል የሚችል ጊዜ በመስጠት አመልካች የመከላከያ ምስክሮቹን አቅርቦ እንዱያሰማ በማድረግ በሕጉ አግባብ በማጣራትና በመመዘን ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ ይሰጥ ብለናል። ይጻፍ።
የዲራ ወረዲ ፍ/ቤት አመልካች ብር 1000/ አንድ ሺህ/ የሚሆን በቂ ዋስትና ካቀረበ ወይም ይህን ገንዘብ በወረዲው ፊይናንስ በሞዳል ካስያዘ ከማረሚያ ቤት ውጭ ሆኖ እንዱከራር እንዱያደርግ ታዟል ። ይጻፍ ። ጉዲዩን ባለ 5 ዲኛ እንዱታይ ተብሎል ።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ለማረሚያ ቤት እና ለአመልካች ይድረስ ብለናል።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.