ፍርድ ቤቶች በተከሳሽ ላይ በዕምነት ክህደት ላይ በመመስረት የጥፊተኝነት ውሳኔን ከመወሰናቸው በፉት ቃለ ከወንጀለ ዝርዝር እና ከተከሰሱበት የህግ ድንጋጌዎች አነጋገር አንጻር ወንጀለን ማድረጉን ሙለ በሙለ አምኗል የሚያስብል እና ቃለ የእምነት ክህደትን ቃል የሚያቀቋቁም መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባቸው ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 132/1/ እና /3/ XIX
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክሱ በቀረበበት የአደአ ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁኖቹ አመልካቾች እንደቅደም ተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የነበሩ ናቸው። ተጠሪ በ29/01/2007 ዓ.ም አዘጋጅቶ ያቀረበባቸው ክስ ይዘት ባጭሩ፡- ተከሳሾቹ በክልለ የደን አዋጅ ቁጥር 72/1995 በአንቀጽ 13 (1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በ27/01/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ 1ኛ ተከሳሽ የዋጋ ግምቱ ብር 5,400 የሆነ 60 ማዲበሪያ ከሰል፣ 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ የዋጋ ግምቱ ብር 4,590 የሆነ 51 ማዲበሪያ ከሰል በሚያሽከረክሯቸው ሁለት ተሽከርካሪዎች ጭነው በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በመያዛቸው የደን ውጤቶችን ያለፈቃድ የማዘዋወር ወንጀል አድርገዋል የሚል ሲሆን ተከሳሾቹ ተጠይቀው በክሱ ላይ መቃወሚያ እንደላላቸው ከገለጹ በኃላ ድርጊቱን መፈጸማቸውን፣ ከሰለን የጫኑት ለቤተሰቦቻቸው እንጂ ለንግድ አለመሆኑን፣ድርጊቱን መፈጸማቸው በርግጥ ጥፊት መሆኑን አምነው በማስመዝገባቸው ዓቃቤ ህግ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 134 (1) መሰረት በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር የጥፊተኝነት ውሳኔ ከሰጠባቸው በኃላ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብል እያንዲንዲቸው በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል። በውሳኔው ቅር በመሰኘት ተከሳሾቹ ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ በጥፊተኝነት ውሳኔ ላይ የቀረበውን ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የቅጣቱን መጠን ብቻ አሻሽል እያንዲንዲቸው በሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቾቹ አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች የቀረበላቸውን እንደቅደም ተከተለ ይግባኝ እና አቤቱታ ዘግተው በማሰናበታቸው ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካቾቹ እንደክሱ በዝርዝር ወንጀለን የፈጸሙ ስለመሆናቸው ሙለ በሙለ ወይም በከፉል ሳይክደ አምነዋል ተብለው በዚህ መነሻነት በስር ፍርድ ቤቶች የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰጠቱ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አንድ ተከሳሽ በክሱ ማመልከቻ ላይ የተዘረዘረውን ወንጀል ለመስራቱ ሙለ በሙለ ያመነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ጥፊተኛ ነኝ ብሎል ሲል በመዝገብ ከጻፈ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፊተኛነት ውሳኔ የሚሰጥ ስለመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ቁጥር 134(1) ስር የተመለከተ ሲሆን በዚህ አግባብ በእምነት ቃለ መሰረት የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት ተከሳሽ ስለቅጣቱ ልክ ወይም ስለቅጣቱ ህጋዊነት ካልሆነ በቀር በጥፊተኛነት ውሳኔው ላይ ይግባኝ ማለት የማይችል ስለመሆኑም በስነ ስርዓት ሕጉ በቁጥር 185(1) ስር ተመልክቶአል። በተያዘው ጉዲይ የወረዲው ፍርድ ቤት በአመለካቾች ላይ የጥፊተኛነት ውሳኔ የሰጠው የተከሰሱበትን ወንጀል ሙለ በሙለ አምነዋል በማለት ሲሆን ይግባኙን የተመለከተው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾቹ በጥፊተኛነት ውሳኔው ላይ ያቀረቡትን ቅሬታ ሳይቀበል የቅጣት ውሳኔውን ብቻ በማሻሻል ውሳኔ የሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔው የተሰጠው በአመልካቾች የእምነት ቃል መሰረት በመሆኑ በጥፊተኛነት ውሳኔው ላይ ይግባኝ ሉያቀርቡ የሚችለበት የህግ አግባብ አለመኖሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ነው።
በመሰረቱ ከላይ በተጠቀሰው የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 134 (1) መሰረት በተከሳሹ ላይ የጥፊተኛነት ውሳኔ ላሰጥ የሚችለው ተከሳሹ ያስመዘገበው የእምነት ቃል በክስ ማመልከቻው በተገለፀው የወንጀል ዝርዝር መሰረት ወንጀለን ማድረጉን ሙለ በሙለ ያመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ በሆነ ጊዜ ነው። ተከሳሹ እንደ ሕጉ አነጋገር ወንጀለን መፈፀሙን ሙለ በሙለ ያመነ መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ የሚያስመዘግበው የእምነት ቃል መነፃፀር የሚገባው ከወንጀለ ዝርዝር ጋር ብቻ ሳይሆን በክሱ ተላልፍታል ከተባለው የሕግ ድንጋጌ አነጋገር ጭምር ነው። ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ለይቶ አውቆ መልስ ለመስጠት እንዱችል እያንዲንደ ክስ ወንጀለን እና ሁኔታውን በዝርዝር መግለፅ ያለበት ስለመሆኑ፣ እንዱሁም ስለ ወንጀለ እና ስለ ሁኔታው የሚሰጠው ዝርዝር መግለጫ ተከሳሹ የፈፀመውን ተግባር ወንጀል ከሚያደርገው ሕግ አነጋገር ጋር በጣም የተቀራረበ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ በስነ ስርዓት ሕጉ በቁጥር 112 የተመለከተው ድንጋጌም ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካቾቹ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ አጥብቀው የሚከራከሩት ለወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠነው ቃል በአግባቡ እና በዝርዝር አልተመዘገበም• የመከላከያ ማስረጃ አቅርበን ክሱን እንድንከላከልም ዕድል አልተሰጠንም በማለት መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመላክታል። ተከሳሾቹ ወንጀለን መፈፀማቸውን አምነዋል በሚል መዝግቦ የጥፊተኝነት ውሣኔ ከመስጠቱ በቀር ተከሳሾቹ ተላልፈዋል ተብለው የተከሰሱት የትኛውን ሕግ እና ድንጋጌ እንደሆነ እንኳ የወረዲው ፍርድ ቤት በጥፊተኝነት ውሣኔውም ሆነ በቅጣት ውሣኔው ላይ አላሰፈረም። ተላልፈውታል የተባለው ሕግ እና ድንጋጌ የተጠቀሰው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሣኔ ላይ ነው። ተከሳሾቹ አስመዝግበውታል የተባለው የእምነት ቃል ከተከሰሱበት ድንጋጌ ጋር ተነፃፅሮ በስነ ስርዓት ሕጉ በቁጥር 134(1) ድንጋጌ መሰረት የእምነት ቃልን የሚያቋቁም መሆን አለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተከሳሾቹ ወንጀለን መፈፀማቸውን ሙለ በሙለ አምነዋል በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ መስጠቱ ደግሞ የቁጥር 134 (1)ድንጋጌ ዓላማ እና መንፈስ መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ሲጠቃለል አመልካቾች ያስመዘገቡት ቃል በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ሥርዓተ ቁጥር 134 (1) ድንጋጌ አነጋገር መሰረት የእምነት ቃልን የሚያቋቁም መሆን አለመሆኑን ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ወንጀለን መፈፀማቸውን አምነዋል ተብል በአመልካቾቹ ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
በአደአ ወረዲ ፍ/ቤት በመዝገብ በ29/01/2007 ዓ/ም ተሰጥቶ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ17/03/2007 ዓ/ም በውሳኔ የተሻሻለው እና በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ በ02/04/2007 ዓ/ም እና በመዝገብ በ08/07/2007 ዓ/ም በትእዛዝ የጸናው የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ ተሸሯል።
አመልካቾቹ ያስመዘገቡት ቃል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ቁጥር 134/1/ ድንጋጌ አነጋገር መሰረት የእምነት ቃልን የሚያቋቁም መሆን አለመሆኑ ሳይረጋገጥ የጥፊተኛነት ውሳኔ መሰጠቱ የስነ ስርዓት ህጉን መሰረት ያደረገ አይደለም በማለት ወስነናል።
አመልካቾቹ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 132 /1/ እና /3/ መሰረት ቃላቸውን እንዱያስመዘግቡ ካደረገ በኃላ የሚያስመዘግቡት ቃል ከወንጀለ ዝርዝር እና ከተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ አነጋገር አንጻር ወንጀለን ማድረጋቸውን ሙለ በሙለ አምነዋል የሚያሰኝ መሆን አለመሆኑን መርምሮ እና የሚያስመዘግቡት ቃል የእምነት ቃልን የሚያቋቁም አይደለም የሚል ከሆነም ጉዲዩን በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት በማስረጃ አጣርቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ለአደአ ወረዲ ፍ/ቤት እንዱመለስ ወስነናል።
የወረዲው ፍ/ቤት ጉዲዩን አንቀሳቅሶ መጥሪያ እስኪልክላቸው እና ክርክሩ እንዱቀጥል እስካደርግ ድረስ አመልካቾቹ በማረሚያ ቤት እንዱቆዩ የሚደረግበት ህጋዊ ምክንያት ባለመገኘቱ ከእስር እንዱለቃቸው ለሚገኙበት የምስራቅ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች አስተዲደር ጽ/ቤት ትእዛዝ ይተላለፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለአደአ ወረዲ ፍ/ቤት፣ እንዱያውቁት ደግሞ ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.