ደረጃ እና እርከን ላልወጣላቸው ወንጀልች ቅጣት ስላት ሲሰራ በወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል ስር ያለት አንቀጽ 106/1/ እና 109/1/ ድንጋጌዎች ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለባቸው ስለመሆኑ፣ አንድ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ የተባለ ሰው ወንጀለን ስለመፈጸሙ ሙለ በሙለ ባላመነበት ሁኔታ በከፉል ማመኑ ብቻ ራሱን ችል እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ሉወሰድለት የማይችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ቁ 82/ ዱቦ ገልግል ቴራ እና የፋ/ን/ስ/ላ ዐ/ሕግ
No summary available.
ቀን 14/11/2007 ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ዱቦ ገልገል ቴራ ጠበቃ ትዕግስት ጫንያለው ተጠሪ፡- የፋ/ን/ስ/ላ/ዐቃቤ ሕግ ተወካይ ሕይወት አዲና መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ 2/2006 ደረጃና እርከን ላልወጣላቸው ወንጀልች የሚደረገውን ስላት እና የቅጣት ማቅለያ ምክንያትን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው ፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው “ተከሳሽ የወ/ሕ/ቁ.676(2) (ሀ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በስራ አስኪጅነት ተቀጥሮ ሲሰራ ከነበረበት ፍቅር ለሕፃናት በጎ አድርጎት ድርጀት ለስራ የተሰጠውን 1ኛ ቶሺባ ላፕቶፕ 2ኛ አሴሰር ላፕቶፕ 3ኛ.
ለሲዱ መግዣ የተሰጠውን ብር 3000 አጠቃላይ ግምቱ ብር 24,000 (ሀያ አራት ሺህ ብር) የሚገመት ንብረት በስራው ሃላፉነት ምክንያት እጁ የገባ ንብረት ይዞ በመሰወሩ በፈፀመው ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ነው።” ተከሳሹ (የአሁኑ አመልካች) ላፕቶፖቹን እህቱ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ምክንያት ገንዘብ ቸግሮት የወሰደ መሆኑን ብቻ ያመነ ሲሆን የፍ/ቤቱ እንደ ክሱ ሙለ በሙለ አላመነም በማለት መዝግቦ የዓ/ሕግ ማስረጃ ከሰማ በኃላ ተከሳሽ በተከሰሰበት አንቀጽ እንዱከላከል ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የጥፊተኛነት ውሳኔ ሰጥቶ ክስ በተመሰረተበትና የጥፊተኛነት ውሳኔ በተሰጠበት የወ/ሕ/አ 676(2) (ሀ) ስር የፅኑ እስራት አማራጭ በመውሰድ የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ከግምት በማስገባት ተከሳሽ በ3 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ለፋ/ከፍ/ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ በማቅረቡ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙ ካከራከረ በኃላ የስር ፍ/ቤት ደረጃውን መካከለኛ ማለቱንና ተከሳሽ በፈፀመው አድራጎት የተመለከተውን የገንዘብ መጠን አንፃር የፅኑ እስራት አማራጭ መውሰድ ተገቢ አለመሆኑን በማተት የቀላል እስራት አማራጭን ወስድ ደረጃውን ዝቅተኛ ብሎል። ተከሳሽ ወንጀለን ያመነ እና በቅጣት ማቅለያነት ሉያዝለት የሚገባ ቢሆንም በወ/ሕ/አ. 663(2) እና 82(1) (ሰ) መሰረት ተከሳሽ የወሰደው ንብረት ስለተመለሰ ብል የስር ፍ/ቤት ቅጣት ማቅለያ የተቀበለ በመሆኑ በአንድ የቅጣት ማቅለያ አንቀጽ 82(1) ሰ ተጨማሪ ቅጣት ማቅለያ ሉወሰድ አይገባም በማለት መነሻ ቅጣት 3 ዓመት ከ6 ወር እስራት ወስድ የተከሳሽን የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ከግምት በማስገባት ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ7 ወር እስራት እንዱቀጣ ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን፤የሰበር አቤቱታው ይዘትም “ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የእስራት ቅጣት አማራጭን ከያዘ በኃላ ቅጣቱን ሲያሰላ በልዩ ሕጉ የተደነገገውን የ1 ዓመት እስራት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 106 የተመለከተውን የእስራት ቅጣት መድረሻ ጣራ ያለአግባብ በማለፍ 15 ዓመት መያዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ላላው በስር ፍ/ቤት ወንጀለን ማመኔን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤቱ ተቀብል በወ/ህ/ቁ. 82(1) ሰ ስር በድጋሚ በቅጣት ማቅለያነት ሉያዝ አይገባውም ማለቱ ሉታረም ይገባዋል በሚል ነው።” የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በወ/ሕ/አ. 676(2)(ሀ) የቀላል እስራት አማራጭን ከወሰደ በወ/ህ/ቁ 106 ቀላል እስራት ከ10 ቀን እስከ 3 ዓመት ነው ተብል ተደንግጎ እያለ የመድረሻ ቅጣቱን 3 ዓመት በመያዙ ማክበጃና ማቅለያ ምክንያት ከግምት በማስገባት ቅጣቱን ማስላት ሲገባው መነሻ ቅጣት 3 ዓመት ከስድስት ወር ማለቱ ከወ/ህ/ቁ. 106(1)፣ ከተከሰሰበት አንቀጽ እንዱሁም ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንፃር የቅጣት አወሳሰኑን አግባብነት ግራ ቀኙ ባለበት ለማየት ሲባል የቀረበ የሰበር ጉዲይ ነው።
ተጠሪም ከስር ዓ/ሕ ቀርቦ ለሰበር አቤቱታው በሰጡት መልስ የስር ፍ/ቤት የቀላል እስራት አማራጭ ወስድ አመልካችን ሲቀጣው በወ/ሕጉ አንቀጽ 106(1) መሰረት መሆን እንዲለበት እናምናለን። የወ/ሕጉ አንቀጽ 106(1) ቀላል እስራት መነሻ 10 ቀናት መድረሻው 3 ዓመት ነው።
ስለሆነም በዚህ ረገድ የተነሳው ይታረምልኝ ጥያቄ ላይ ተቃውሞ የለንም።
የስር ፍ/ቤት የወ/ሕጉ አንቀጽ 663(2) እና 82(1) (ሰ)ን በመጥቀስ አመልካች ድርጊቱን ማመኑን እንደአንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሉያዝለት አይገባም ማለቱ ተገቢ ነው። የስር ፍ/ቤቶች ተከሳሽ እንደመነሻ አድርገው ቢወሰድም የወ/ሕጉ አንቀጽ 663(2) እና 82(1) (ሰ) ተጣምረው ሲታዩ አመልካች በስር ፍ/ቤት በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት ሙለ በሙለ ማመን እንዲለበት ያስቀምጣል። ተከሳሽ ሙለ በሙለ ባለማመኑ ዐ/ሕግ ማስረጃ አሰምቶ ተከሳሽ እንዱከላከል ብይን ተሰጥቶ ባለመከላከለ ጥፊተኛ የተባለ በመሆኑ አመልካች በወ/ሕጉ አንቀጽ 82(1) (ሰ) ስር ተጠቃሚ ላሆን አይገባም። በወ/ሕጉ አንቀጽ 663 (2) መሰረት የወሰደውን ዕቃ ሙለ በሙለ ያልመለሰና የተከሰሰበትን ወንጀል ሙለ በሙለ ያላመነ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ቅጣት ሲጣል ከግምት ሉያስገባው የሚችል በመሆኑና ፍ/ቤቱ ሲያምንበት ብቻ እንደሆነ መረዲት የሚቻል በመሆኑ በዚህ ረገድ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም በማለት በፅሐፍ መልሱን አቅርቧል። እኛም የአመልካችን አቤቱታ አግባብነት ካለው የወ/ሕጉ ድንጋጌ እና ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 እንዱሁም ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጋር ከዚህ በላይ ሰበር ችልቱ ከያዘው ጭብጥ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። እንደመረመርነውም፤
የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ተቀብል የአመልካችን የወንጀል አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ በአመልካች ላይ ሉወሰን የሚገባው በቀላል እስራት ቅጣት ነው ብል ካመነበት አመልካቹ ጥፊተኛ የተባለበት የወ/ሕግ አንቀጽ 676(2) (ሀ) ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ከ15 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ የተመለከተ በመሆኑ፣ቀላል እስራትን አስመልክቶ በወ/ሕጉ አንቀጽ 106(1) ከ10 ቀን እስከ 3 ዓመት እንደሆነ የተመለከተ ስለሆነ እና የወ/ህጉ አንቀጽ 676(2)(ሀ) ደረጃ ያልወጣለት በመሆኑ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 19(6) መሰረት ከአንድ ዓመት እስከ ሦስት ዓመት ያለውን እስራት ለአራት እኩል በመክፈል የቅጣት እርከኑን በመለየት መነሻ ቅጣት መወሰን ሲገባው የስር ፍ/ቤት (ፋ/ከፍ/ፍ/ቤት) መነሻ ቅጣቱን ስለቀላል እስራት በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጽ 106(1) ከተመለከተው 3 ዓመት ጣሪያ አልፍ መነሻ ቅጣቱ 3 ዓመት ከ6 ወር መያዙ የወንጀል ሕጉን እና የቅጣት አወሳሰን መመሪያውን መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም።
የተከሳሽ (አመልካች) ወንጀል አፈፃፀም እና በእምነት ማጉደል ከወሰዲቸው ንብረቶች የመለሰው ንብረት መኖሩን ከግምት በማስገባት አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት የወ/ሕግ አንቀጽ 676(2) (ሀ) የቀላል እስራት አማራጭ መወሰደ ተገቢ ነው። በዚህ አንቀጽ የተመለከተው ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት ሲሆን ከወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጽ 106(1) ጋር በማገናዘብ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 19(6) መሰረት እርከን አንድ ከ1 ዓመት እስከ 1 ዓመት ከ6 ወር ይሆናል የወንጀለን አፈፃፀምና ክብደት መሰረት በማድረግ ቀላል ወንጀል ደረጃ የተሰጠው በመሆኑ በዚህ እርከን አንድ ውስጥ መነሻ ቅጣቱ 1 ዓመት ከ4 ወር እንዱሆን ወስነናል መነሻ ቅጣቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው የቅጣት ሰንጠረዥ እርከን 7 ከ1 ዓመት እስከ 1 ዓመት ከ6 ወር በሚለው ስር ይወድቃል።
በዐ/ሕግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ባለመኖሩ ቅጣቱ የሚከብድ አይሆንም በልላ በኩል አመልካች ለሰበር ችልት እንደ አንድ ቅሬታ ምክንያት በማድረግ ወንጀለን መፈፀሜን ማመኔ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82(1) ሰ በቅጣት ማቅለያነት ሉያዝልኝ ሲገባ በሥር ፍ/ቤቶች ታልፍብኛል በማለት የተከራከረ ቢሆንም፤ አመልካች በስር ፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የወ/ሕጉን አንቀጽ 676(2) (ሀ) በመተላለፍ ከባድ እምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅሟል በሚል በክሱ ዘርዝሮ ከተመለከተው ብር 3000 (ሦስት ሺህ ብር) መውሰደን ሳያምን ላብቶፖቹን ብቻ ወስጃለው በማለት ያመነ በመሆኑ የእምነት ቃለ ከወንጀለ ዝርዝር ጋር ሲታይ ወንጀለን ስለመፈፀሙ ሙለ በሙለ ያመነ ባለመሆኑ በከፉል ማመኑ በቅጣት ፈቅደ ስልጣን ከግምት ሉገባ ከሚችል በቀር ራሱን ችል አንድ ቅጣት ማቅለያ ምክንያት ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባው አይደለም። በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች ይህንን በወ/ህ/አንቀጽ 82(1)(ሰ) እንደ አንድ ቅጣት ማቅለያ ምክንያት አለመውሰዲቸው በአግባቡ ስለሆነ በዚህ ላይ አመልካች ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት ያለው አይደለም።
በስር ፍ/ቤቱ ተከሳሻ (አመልካች) የዘወትር አመለ መልካም እንደነበረ ግምት በመውሰድ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82(1) (ሀ) እና ንብረቶቹ በመመለሳቸው በወ/ህ/አ 663(2) እና 82(1) (ሰ) መሰረት የተያዘለትን ሁለት ቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በመውሰድ መነሻ ቅጣት ካረፈበት እርከን 7 በሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ወደ እርከን 5 ዝቅ ይላል በዚህ እርከን 5 የተመለከተው የቅጣት ፈቅድ ስልጣን ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት እስራት ሲሆን ተከሳሹን ያርማል ለላላው ማስተማሪያ ይሆናል ብለን ባመንበት በ1 ዓመት እስራት እንዱቀጣ ወስነናል።
ው ሣ ኔ
195(2) (ሰ) (2) መሰረት ተሻሽሎል።
No topics extracted.