አንድ የወንጀል ድርጊት ሉወድቅ የሚችልበት የህግ ድንጋጌ የተለያዩ የማክበጃ ነጥቦች በያዘ ጊዜ እና ተከሳሹ ጥፊተኛ በተባለበት አንቀጽ /ድንጋጌ/ ስር ያለት ንዐስ ድንጋጌዎች የሚደነግጉት የቅጣት መጠን ተመሳሳይ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቶች በዚያው የህግ ድንጋጌ ስር ድርጊቱ በይበልጥ ያሟላቸውን የማክበጃ ነጥቦች ወደ ያዘው ንዐስ ድንጋጌ መለወጥ የሚችለ አቶ አህመድ ሰይድ መሀመድ እና የፍደራል ዐ/ህግ
No summary available.
ሐምል 1 ቀን 2007ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አህመድ ሰይድ መሐመድ ጠበቃ መሳይ ተድላ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ክርክሩ በተጀመረበት ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ከነበሩት ላልች ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን ከባድ የስርቆት ወንጀል መዋል በማለት ተጠሪ ያቀረበባቸውን የወንጀል ክስ የተመለከተው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠባቸው እና በይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔ የጸናው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡-አመልካች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ከመስከረም ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት ወር 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ቀናት ሰዓቱ ተለይቶ ባልታወቀበት የምሽት የጊዜ ክፍል በን/ላ/ክ/ከተማ በቀበላ 13 ክልል ልዩ ቦታው የኔታ አካዲሚ በሚባል አካባቢ የግል ተበዲይ መሐመድ አብደላ በሆነ መጋዘን ተቀጥረው ይሰሩ በነበረበት ጊዜ ስማቸው በክሱ የተዘረዘረውን እና በካርቶኖች ታሽገው ተቀምጠው የነበሩትን አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው ብር 373,080 (ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ሰማንያ) የሆነ የተለያዩ ቧንቧ ዕቃዎችን ከመጋዘን እያወጡ 2ኛ ተከሳሽ ለሆነው ግለሰብ የሰጡ በመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 669 (2) (መ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ሲሆን አመልካች ተጠይቀው በክሱ የተመለከተውን ወንጀል አላደረግሁም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ በሶስቱም ተከሳሾች ላይ የግል ተበዲይን ጨምሮ ተጠሪ ያቀረባቸውን አራት ምስክሮች ምስክርነት ከሰማ እና አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 27 መሰረት ለምርመራ ክፍል የሰጡትን ቃል ጨምሮ ተጠሪው ያቀረበውን የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ዐቃቤ ሕግ በክሱ መሰረት ያስረዲባቸው መሆኑን ገልጾ አመልካች በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር መከላከያቸውን ማሰማት እንዱጀምሩ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142 መሰረት ትዕዛዝ በመስጠቱ አመልካች ለምርመራ ክፍል ቃላቸውን የሰጡት በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት ተገደው መሆኑን ያውቁልኛል በማለት ሁለት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተዋል።ወንጀለን ያልፈጸምኩ መሆኑን ያስረዲልኛል በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 35 መሰረት ለፍርድ ቤት የሰጡትን ቃል እና የየኔታ አካዲሚ የጥበቃ ሰራተኛ እንጂ የግል ተበዲይ ሰራተኛ አለመሆኔን ያስረዲልኛል በማለት ይህንኑ የሚያስረዲ ማስረጃ በመከላከያነት አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም ቀሪዎቹ ሁለት ተከሳሾችም እንዱከላከለ ትዕዛዝ ከሰጠ እና መከላከያቸውን ከሰማ በኃላ በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካቹ ባሰሟቸው የመከላከያ ምስክሮች እና ባቀረቡት የሰነድ መከላከያ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰከረተባቸውን ፍሬ ነገር ለማስተባበል አልቻለም በማለት ደንጋጌውን ግን ለውጦ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 669 (3) (ለ) ድንጋጌ ስር የጥፊተኝነት ውሳኔ ከሰጠባቸው በኃላ የቅጣት አወሳሰኑ ወንጀለ ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ በስራ ላይ በነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት እንዱመራ በአመልካቹ ጠበቃ የቀረበውን ጥያቄ ባለመቀበል የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ውሳኔው በተሰጠበት ጊዜ በስራ ላይ በሚገኘው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ተቀብል አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ የሚያስቀጣው ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እስራት ወይም እስከ አስራ አምስት ዓመት ሉደርስ በሚችል ጽኑ እስራት መሆኑን፣ወንጀለ በመመሪያ ቁጥር 2/2006 ደረጃ የወጣለት መሆኑን፣በወንጀለ የተወሰደው ንብረት ግምት ከብር 100,000 በላይ በመሆኑ እና አንድ ማክበጃ የተገኘ በመሆኑ የሚወድቀው በደረጃ 7 በእርከን 26 ስር መሆኑን፣በእርከን 26 ስር ከተመለከተው ፍቅድ ስልጣን ውስጥ መነሻ ተደርጎ የተያዘው የስምንት ዓመት ጽኑ እስራት መሆኑን፣የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ያልተገኘ ሲሆን ተቀባይነት ባገኙት ሶስት የማቅለያ ምክንያቶች የፍቅድ ስልጣኑ እርከን ከ26 ወደ 23 ዝቅ የሚል መሆኑን በዝርዝር ገልጾ በዚሁ እርከን ስር አመልካቹ በስድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 669 (2) (መ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ እንዱጠብቅ በኃላፉነት የተሰጠውን ንብረት ሰርቋል ተብል ክስ ተመስርቶበት አመልካች የግል ተበዲይ ተቀጣሪ አይደለሁም፣ወንጀለንም አላደረግሁም በማለት ክድ በመከራከሩ የግል ተበዲይ ተቀጣሪ አለመሆኑን፣ብቸኛውን የተጠሪ ማስረጃ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 27 መሰረት የተሰጠ ቃል እና የደረጃ ምስክሮችን የምስክርነት ቃል ለመከላከል አመልካቹ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 35 መሰረት የሰጠውን ቃል እና የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቶ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች በክሱ የተመለከተውን ድንጋጌ ወደ አንቀጽ 669 (3) (ለ) በመቀየር የጥፊተኝት እና የቅጣት ውሳኔ የመስጠታቸውን አግባብነት ከማስረጃ ምዘና መርህ እና ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 113 (2) ድንጋጌ አፈጻጸም አንጻር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡- 3. በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
የሚለትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች ወንጀለን አላደረግሁም በማለት የተከራከሩ ቢሆንም በክሱ የተዘረዘሩት የዋጋ ግምታቸው ብር 373,080 የሆነ የተለያዩ የቧንቧ ዕቃዎች ከግል ተበዲዩ የተሰረቁ መሆኑ እና የተሰረቁትም ከሚቀመጡበት መጋዘን ውስጥ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ እየተወሰደ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።የዚህ ዓይነት የስርቆት ወንጀል የተፈጸመባቸው ስለመሆኑም የግል ተበዲይ ለአካባቢው ፖሉስ በወቅቱ ሪፖርት ያደረጉ መሆኑም ተረጋግጧል።
የወንጀለ ፈጻሚዎች ማንነት ለጊዜው ሳይታወቅ የቆየ ቢሆንም የስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመሳሳይ ላላ ወንጀል ተጠርጥረው የግል ተበዲይ የወንጀል አቤቱታ ባላቀረቡለት በአዱስ አበባ ከተማ ፖሉስ በኩል በቁጥጥር ስር በነበሩበት ጊዜ የግል ተበዲይን የቧንቧ ዕቃዎችም ከአሁኑ አመልካች ጋር በመተባበር መስረቃቸውን በመግለጻቸው ምክንያት አመልካቹ ጭምር ተይዘው ተጠያቂ መደረጋቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካቹ የግል ተበዲዩ ሰራተኛ ባይሆኑም መጋዘኑ በሚገኝበት ግቢ ከግል ተበዲይ ቤት ተከራይቶ ስራውን ለሚያከናውነው የትምህርት ተቋም በጥበቃ ስራ ሲያገለግለ የነበሩ መሆናቸውን አልካደም።ከስር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ጋር የስርቆት ወንጀለን የፈጸሙ ስለመሆኑም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 27 መሰረት ለምርመራ ክፍል በሰጡት የእምነት ቃል አረጋግጠዋል።ይህንን የእምነት ቃል የሰጡት በፈቃዲቸው መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካቹ በልላ ጊዜ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 35 መሰረት ለፍርድ ቤት ባስመዘገቡት ቃል የፈጸሙት ወንጀል አለመኖሩን መግለጻቸው ብቻውን የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ እንደገለጸው ቀደም ሲል በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 27 መሰረት ለምርመራ ክፍል የሰጡትን የእምነት ቃል ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል አይደለም። አመልካች ለምርመራ ክፍለ የእምነት ቃል የሰጠሁት ተገድጄ ነው በማለት ያስያዙትን የመከላከያ ጭብጥ በምስክሮቻቸው ማስረዲት አለመቻላቸውን ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው ሁለቱ የስር ፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በውሳኔያቸው ላይ ገልጸዋል።አመልካች ከላልች ተባባሪዎቻቸው ጋር የስርቆት ወንጀለን ያደረጉት በላሉት እና ዕቃዎቹ የሚቀመጡበትን መጋዘን ባልታወቀ ሁኔታ ከፍቶ በመግባት በመሆኑ እና እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ ራሳቸውን ችለው በስርቆት ወንጀል ማክበጃነት አመልካቹ ጥፊተኛ በተባለበት አንቀጽ 669 (3) (ለ) ስር የተካተቱ በመሆኑ፣እንዱሁም አመልካቹ የተከሰሱበት እና ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌዎች የሚደነግጉት የቅጣት መጠን ተመሳሳይ በመሆኑ አመልካቹ ጥፊተኛ የተባለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 669 (3) (ለ) ስር መሆኑም በአግባቡ መሆኑን ተገንዝበናል።በመሆኑም በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን ማስረጃ መዝኖ በመከላከያነት የቀረበውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ውድቅ በማድረግ በአመልካቹ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ወንጀል በቀድሞውም ሆነ በአዱሱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ደረጃ ከወጣላቸው ወንጀልች ውስጥ የሚካተት ሲሆን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቅጣቱን የወሰነው በተጠሪው በኩል የቀረበ የማክበጃ ምክንያት አለመኖሩን እና በአመልካቹ በኩል ተቀባይነት ያገኙ ሶስት የማቅለያ ምክንያቶች መገኘታቸውን ገልጾ ቅጣቱን የጥፊተኝነት ውሳኔው በተሰጠበት ጊዜ በስራ ላይ ባለው አዱሱ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማስላት ነው። ግን አመልካቹ ወንጀለን አድርገዋል የተባለት ከመስከረም 2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት ወር 2005 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካች ወንጀለን ባደረጉበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 በቅጣት አወሳሰኑ ረገድ ከተሻሻለው መመሪያ በተለየ ሁኔታ የሚያስከትለው ለውጥ መኖር አለመኖሩ እና ካለም ተፈጻሚ መደረግ የሚገባው የትኛው መመሪያ እንደሆነ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።በመሰረቱ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎቹን ያወጣው በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 88(4) ድንጋጌ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በመሆኑ ምክንያት መመሪያዎቹ እንደ ሕግ የሚቆጠሩ ናቸው።ቀደም ሲል እንደተገለጸው አመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን ወንጀል ያደረጉት መመሪያ ቁጥር 1/2002 ስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ሲሆን ይህ መመሪያ ከጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ተተክቷል። በልላ በኩል አዱሱ የወንጀል ሕግ እንዱጸና ከተደረገ በኃላ አድራጊው ሕጉ ከመጽናቱ በፉት ላደረገው ወንጀል ሲፈረድበት ወንጀለን በፈጸመበት ጊዜ በስራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ አዱሱ ሕግ ቅጣትን የሚያቃልለት በሆነ ጊዜ ተፈጻሚ መደረግ የሚገባው በአዱሱ የወንጀል ሕግ የተመለከተው ቅጣት ስለመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 6 ተደንግጏ ይገኛል።
ለአመልካቹ ቅጣቱን የሚያቃልለው የትኛው መመሪያ ነው? የሚለውን ነጥብ በተመለከተ በቀላል እና በጽኑ እስራት ለሚያስቀጡ ወንጀልች ፍርድ ቤቱ ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት መነሻ ቅጣቱ ከሚያርፍበት የቅጣት እርከን ወደታች የሚቀንሰው አንድ እርከን ብቻ ስለመሆኑ በተሻሻለው መመሪያ አንቀጽ 23 (4) ስር የተመለከተ ሲሆን በአንጻሩ መነሻ ቅጣታቸው ሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወንጀልች ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት መነሻ ቅጣቱ ከሚያርፍበት የቅጣት እርከን የቅጣቱ ፍቅድ ስልጣን ዝቅ የሚደረገው በሶስት እርከን ስለመሆኑ በቀድሞው መመሪያ በአንቀጽ 16 (7) ስር ተመልክቷል።ይህ ብቻ ሳይሆን አመልካቹ ጥፊተኛ የተባለበት ወንጀል በአዱሱ መመሪያ የሚወድቀው በደረጃ 7 በእርከን 26 ስር ሲሆን በቀድሞው መመሪያ ግን በደረጃ 7 በእርከን 21 ስር በመሆኑ ወንጀለ ከሚወድቅበት እርከን አንጻርም ያነሰ ቅጣት የሚደነግገው የቀድሞው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ነው።ወንጀለ የተፈጸመው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ሆኖ የጥፊተኝነት ውሳኔው የተሰጠው ግን የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ
No topics extracted.