አንድ ሰው በላለበት በወንጀል የተፈረደበት እንደሆነ ፍርድን ባወቀ በሰላሳ ቀናት ውሥጥ ፍርደ ወድቅ እንዱደረግለት የማቅረብ መብቱን ሬጄሰትራለ አቤቱታውን አልቀበልም በማለት ሉከለክለው የማይችል ስለመሆኑ፡የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.198፣200 እና 201 የኢፈ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20 XVIII
No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ያረጋል ተስፊ አባተ ጠበቃ አዲነ ታረቀኝ ቀረበ ተጠሪ፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክ/ዐ/ቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለው የአሁን አመልካች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ.03468 በ04/05/2004 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት በጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ በማቅረቡ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በ20/04/2004 ዓ.ም በተጻፈ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ እኔ እና ላልች 5 ሰዎች በተከሰስኩበት በግብረ አበርነት ሰው በግፍ መግደል ወንጀል ተከስሼ ክሱ በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲታይ ቆይቶ ፍ/ቤቱ በመዝገብ ቁ.01597 በግንቦት 3 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ከክሱ ነፃ የተሰናበትኩ መሆኔን እና ከአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት እንድለቀቅ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ የደረሰኝ መጥሪያ ሳይኖር እኔ ቀርቤ ሳልከረከር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በላልች ተከሳሾች ቅጣት ሲጥል በእኔ ላይ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የወሰነብኝ መሆኑን በቅርብ ጊዜ ተነግሮኛል። ስለዚህ እኔ የህግ ታራሚ ስለሆንኩ የፍትህ መጓደል እንዲይደርስብኝ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.191 /3/ መሰረት እኔ በላለሁበት እና ከአቅሜ በላይ በሆነ ምክንያት ማለትም በነጻ ስለቀቅ ወደ ትውልድ ቦታዬ ጎጃም በመሄድ በእርሻ ተሰማርቼ 3 ሕፃናት ልጆቼን በማሳደግ ላይ የቆየሁ መሆኔንና በቲቪ ስሰቃይ፣ በባህርዲር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ስታከም የቆየሁና በስንት መከራ በእግዚአብሓር ፈቃድ ተርፋያለሁ። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ችግሬን ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶልኝ የይግባኝ ማስፈቀጃ ማመልከቻዬን ተቀብል ይግባኝ ተከፍቶልኝ ህጋዊ መብቴ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ክርክሩ እንዱሰማልኝ በማለት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ የነበረ መሆኑን ያስገነዝባል።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የአመልካችን አቤቱታ ከሰማ በኋላ በመዝገብ በ04/05/2004 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የይግባኝ ጊዜ ያለፈባቸው በእውነት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው ወይ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ አመልካች የጠቀሰው ምክንያት ህመም ሲሆን በህክምና ወረቀት ካለመደገፈ በተጨማሪ ለአምስት አመታት ከነበረበት እና ጉዲዩ ከሚታይበት አከባቢ በመሰወር በመጨረሻም በፖሉስ ክትትል መያዙ የምክንያቱን በቂነትና ተቀባይነት ያሳጣዋል። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ጊዜው ያለፈበት እና በበቂ ምክንያት ያልተደገፊ ነው ሲል የይግባኝ ማስፈቀጃውን ሳይቀበል መቅረቱ በህግ አግባብ እንጅ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም በማለት አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቷል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ይህን ትዕዛዝ ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ፡-
አቤቱታው በሕግ የተደገፈ ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ እንደገና አላይም ማለቱ፤ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ስህተቱን አርሞ ጉዲዩ እንደገና እንዱታይ መፍቀድ ሲገባው አቤቱታውን ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ማመልከቻው ተቀባይነት ባያገኝ ደግሞ ማመልከቻው ተቀባይነት ካጣበት ቀን አንስቶ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 197፣198 እና 202/3/ ተደንግጓል። አመልካች ፍርደን እንዲወቅኩኝ በ6 ቀን ውስጥ ሥርዓቱን ጠብቄ ማረሚያ ቤት ሆኜ ተደጋጋሚ አቤቱታ ባቀርብም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ፍርድ የተሰጠበትን ቀን በመቁጠር ሁለንም አቤቱታዎች አልቀበልም በማለቱ በሕጋዊ መብቴ እንዲልጠቀም ከመከልከለም በላይ የሬጅስትራር ክልከላ እንዱወገድልኝ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ባቀርብም የሬጅስትራሩን ድርጊት እንደህጋዊ ተግባር በመቁጠር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማስፈቀጃ አለመቀበለ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባ ነው።
አመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ ማመልከቻ የማቀርብበት ሁኔታ አልተፈጠረም እንጅ ማቅረብ አለበት ቢባል እንኳ ማስፈቀጃው የሚቀርበውም የሚፈቀደውም ሆነ ተቀባይነት ሉያጣ የሚችለው ፍርደን በፈረደው ፍ/ቤት ሬጅስትራር ውሳኔ ሳይሆን ፍርደን በይግባኝ ወይም በሰበር የማየት ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ነው። ሬጅስትራሩ በማይመለከተው የዲኝነት ሥራ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የአመልካች አቤቱታ ለፍ/ቤት ችልት ቀርቦ እንዲይታይ ያደረገው ሕጋዊ ተግባር ፈጽሟል ተብል አቤቱታው ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በ04/05/2004 ዓ.ም የሰጠውን ትዕዛዝ ላይ ቅር በመሰኘት ለይግባኝ ግልባጭ እንዱሰጠኝ በተደጋጋሚ ባመለክትም የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሬጅስትራር በመከልከለ ለሁለት ዓመት መብቴን እንዲልጠቀምና ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ሳላቀርብ ከፍ ያለ በደል ተፈጽሞብኝ መቆየቱ ሕገ መንግስቱ ለተከሰሱ ሰዎች በአንቀጽ 20/6/ የሰጠውን ይግባኝ የማቅረብ መብት የሚጥስ ነው። ሰለዚህ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ትዕዛዝ እንዱሻርልኝ፤ አመልካች የሰበር አቤቱታ ጊዜው ያለፈው በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ችግር ፈጣሪነት ምክንያት ነው ተብል አቤቱታው ለሰበር ቀርቦ እንዱታይ እንዱፈቀድልኝ፤ እኔ በላለሁበት ተገቢውን መከራከርያ ሳላቀርብ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የወሰነብኝ የዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እጅግ ከባድ ቅጣት በመሆኑ ጉዲዩ አመልካች ባለበት እንደገና ታይቶ እንዱወሰን በማለት አመልክቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤት መዝገብ ግልባጭ በማስቀረብ ጉዲዩን በመመርመር "አመልካች በላለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዲወቀ ፍርደ ተነስቶ ባለሁበት እንዱታይልኝ በማለት ያቀረበው አቤቱታ እና የይግባኝ ማስፈቀጃው ተቀባይነት ማጣቱ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? " የሚለውን ለመመርመር ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ታዝዞ፤
ተጠሪ በዚህ ጉዲይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት መጥሪያ ደርሶት መልሱን ይዞ ባለመቀረቡ በጽሁፍ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል። እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገብ እንዱቀርብ ተደርጎአል። ጉዲዩም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን፤ ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማየት አቤቱታው ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ እንደሚከተለው መርምሮታል። ከላይ በዝርዝር እንደተመለከተው እና ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው አመልካችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በግብረ አበርነት በግፍ ሰው መግደል ወንጀል ተከሰው በአሶሳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲከራከሩ ቆይተው ፍ/ቤቱ በግንቦት 3 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ተከሳሾቹን በነጻ ስላሰናበታቸው በዚሁ ዕለት ተከሳሾቹ ከማረሚያ ቤት እንዱወጡ መደረጉን የፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ያመለክታል። ከዚህ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረቡ፤ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ሲያይ ቆይቶ በ17/11/1999 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ መሰረት አመልካች በላለበት የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደበት መዝገቡ ያመለክታል። በዚህ ውሳኔ አግባብነት ፖሉስ አመልካችን በ09/03/2004 ዓ.ም በቁጥጥር ስር በማዋል ማረሚያ ቤት እንዱገባ መደረጉ ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
አመልካች በ14/03/2004 ዓ.ም ጽፍ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበው አቤቱታ እኔ ከተከሰስኩበት የወንጀል ክስ ፍ/ቤት በነፃ ካሰናበተኝ በኋላ ወደ አማራ ክልል በመሄድ ኑሮዬን የመሰረትኩ ሲሆን እኔ በላለሁበት መጥሪያ ሳይደርሰኝ በፍ/ቤቱ የተፈረደብኝ የዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ ፍ/ቤቱ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.199 መሰረት ማመልከቻዬን ተቀብልኝ በቁ.202/1/ መሰረት ፍርደ ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት ማመልከቱን፣ አመልካች እንደገና በድጋሚ በ02/04/2004 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ እርሱ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ውድቅ እንዱደረግለት መጠየቁን፣ ነገር ግን አመልካች አቤቱታው ጊዜው አልፍበታል ተብል ማረሚያ ቤት ስለተመለሰበት ድጋሚ በ02/04/2004 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የይግባኝ መብቱ እንዱጠበቅለት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ማመልከቱን፣ አመልካች አሁንም በ17/04/2004 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የይግባኝ ጊዜው ያለፈው በእኔ ጥፊት ስላልሆነ ክርክሩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱታይለት የመዝገብ ግልባጭ እንዱሰጠው መጠየቁን ከስር ፍርድ ቤት ከመጣው መዝገብ ጋር ተያይዘው የሚገኙ ሰነድች የሚያሳዩ መሆኑን ተገንዝበናል።
ከዚህ በኋላ አመልካች ከላይ እንደተመለከተው በ20/04/2004 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የደረሰበት ከፍተኛ ሰቆቃና ችግር ከግንዛቤ ውስጥ ገብቶ የይግባኝ ጊዜው ያለፈው በእርሱ ጥፊት እንዲልሆነ በመጥቀስ የይግባኝ ማስፈቀጃ ለክልለ ሰበር ችልት አቅርቧል። ይሁን እንጂ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው የይግባኝ ማስፈቀጃ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ በማድረጉ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ምክንያት ሆኗል።
በመሰረቱ አንድ የወንጀል የሚመራው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ነው። በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት የቀረበውን ክርክር ደግሞ መምራትና በሕጉ አግባብ ዲኝነት መስጠት ያለበት በሕግ አግባብ የተቋቋመው ፍርድ ቤት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የክልለ ዐቃቤ ሕግ የቀረበውን የወንጀል ይግባኝ ማመልከቻ ለአመልካችም ሆነ ለላልች መልስ ሰጭዎች እንዱደርሳቸው ማድረግ እንዲለበት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.187/4/ ሥር ተደንግጓል። ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ለአመልካች መጥሪያ እንዱደርሰው ጉዲዩ የሚመለከታቸውን አካላት በመጠቀም ተገቢውን ትጋት አድርጎ ነበር ወይ? የሚለው አሁን የሚታይ ስላልሆነ በዚህ ረገድ ምንም ማለት አይቻልም።
ነገር ግን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች በላለበት የወንጀል ይግባኙን አይቶ በ17/11/99 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዱቀጣ የፈረደበት መሆኑን ከቀረበው ክርክር መረዲት ይቻላል። አመልካች በዚህ ፍርድ አማካይነት በ09/03/2004 ዓ.ም በፖሉስ ተይዞ በማረሚያ ቤት እንዱታሰር ከተደረገ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ በ14/03/2004 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.197 እና በተከታዮቹ ድንጋጌዎች ታይቶ እርሱ በላለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዱነሳለት የጠየቀ ስለሆነ፤ ይህ ጉዲይ በዚህ ድንጋጌ አግባብ የሚታይ ሆኖ ሳለ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሬጅስትራር የይግባኝ ጊዜው አልፍበታል በማለት አቤቱታውን አልቀበልም በማለት ጉዲዩ ለዳኞች ቀርቦ እንዲይታይለት የሚያደርግበት የህግ አግባብ የለውም።
የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.198 እንደሚደነግገው አንድ ሰው በላለበት በወንጀል የተፈረደበት እንደሆነ ፍርደን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ፍርደ ውድቅ እንዱደረግለት ማመልከት እንደሚችል እና በቁ.200 መሰረት የማመልከቻው ግልባጭ ለዐቃቤ ሕግ ደርሶ ለመስማት ቀጠሮ እንደሚያዝ ነው እንጂ ሬጅስትራር ማመልከቻውን አልቀበልም በማለት እንቢ የሚልበት የሕግ መሰረት የለም። ይህ ማመልከቻ ከተሰማ በኋላ የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.201 መሰረት ፍ/ቤት ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው ጉዲይ ነው እንጂ ሬጅስትራር አልቀበልም በማለት ውሳኔ ላሰጥበት በሕግ የተሰጠው ስልጣን የለም። አመልካች የአቀረበው ማመልከቻ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርቦ በዳኞች ታይቶና ክርክሩ በሕግ አግባብ ተሰምቶ ውሳኔ ሉያገኝ የሚገባ ጉዲይ ነው። አመልካች በላለበት የተፈረደበት ቅጣት ነጻነትን የሚያሳጣ ከባድ የእስራት ቅጣት ሆኖ ሳለ አቤቱታው ተቀባይነት ቢያገኝም ቢያጣም ለፍ/ቤት ቀርቦ በዳኞች ውሳኔ ላሰጥበት ሲገባው ሬጅስትራሩ ይህን መብት መገደቡ የህግ መሰረት የለውም። ይህ ድርጊት ደግሞ ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20 መረዲት እንደሚቻለው "የተከሰሱ ሰዎች ክርክራቸው በፍ/ቤት ታይቶ ተሰምቶ ፍርድ ሉያገኙ ይገባል" የሚለውን ሕገ መንግስታዊ መብቱን የሚሸራርፍ ነው።
ይህ በእንዱህ እንዲለ አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ያቀረባቸው አቤቱታዎች የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች የቀረበውን የይግባኝ ማስፈቀጃ ማመልከቻ በማየት ከላይ የተጠቀሱትን አመልካቹ ላይ የደረሰውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት በሬጅስትራሩ ምክንያት የተፈጠረውን የአካሄድ ችግሮችን በማረም፣ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሬጅስትራር አመልካች በላለሁበት የተፈረደብኝ ፍርድ ውድቅ እንዱደረግልኝ በማለት የቀረበው ማመልከቻ ለዳኞች ቀርቦ እንዱታይለት እንዱያደርግ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው የሬጅስትራሩን ድርጊት ሕጋዊ እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጎ መተው ከላይ የተጠቀሱትን የሕግ ድንጋጌዎችን የሚጻረር በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል።
ከዚህም በላይ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ይግባኝ ማስፈቀጃ የጠየቀው እርሱ በላለበት የተሰጠበት ፍርድ ላይ መሆኑ እየታወቀ፣ አመልካች በዚህ ላይ ምን ዓይነት የይግባኝ ጥያቄ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሉያቀርብ እንደሚችል ሳይጣራ፣ እንዳትስ ከዚህ ዓይነት ፍርድ ይግባኝ ማለት እንደሚቻል ሳይመረመር፣ በላለበት ፍርድ የተሰጠበት ሰው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.197 እና ተከታይ ድንጋጌዎች አግባብነት መብቱን መጠየቅ እንደሚችል መገንዘብ ሲገባው፣ የሬጅስትራሩን ከሕግ ውጭ የሆነ ድርጊት ሕጋዊ ሽፊን በመስጠት የሰጠው ትዕዛዝ የሕግ ድጋፍ የለውም።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተፈጠረውን የአካሄድ ችግር ተገቢውን ማስተካከያ ሳያደርግ ከመቅረቱም በላይ አመልካቹ የጠቀሰው " ምክንያት ህመም ሲሆን በህክምና የምስክር ወረቀት ካለመደገፈ በተጨማሪ ከአምስት ዓመታት በላይ ከነበረበት እና ጉዲዩ ከሚታይበት አካባቢ በመሰወር በመጨረሻም በፖሉስ ክትትል መያዙ የምክንያቱን በቂና ተቀባይነት ያሳጣዋል" በማለት የደረሰበት ድምዲሜ፣ አመልካቹ አቤቱታው በፍ/ቤት/በዳኞች/ ታይቶ ተሰምቶ ተገቢ ማጣሪያ ተደርጎ ፍርድ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብቱን የሚያጣብብ በመሆኑ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም። ስለዚህ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሬጅስትራር የፈጠረውን የአካሄድ ችግር ማስተካከል ሲገባው አመልካች በላለሁበት የተፈረደብኝ ፍርድ ውድቅ እንዱሆንልኝ በማለት ያመለከተው አቤቱታ በፍ/ቤት ታይቶ ተሰምቶ ውሳኔ ሳይሰጥበት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ሁኖ ስለአገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ቁ.03468 ላይ በ04/05/2004 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች በ14/03/2004 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ማመልከቻ መሰረት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ.197 እና ተከታይ ድንጋጌዎች በላለበት የተፈረደበት ፍርድ ውድቅ ላሆን ይገባል? ወይስ አይገባም? በሚለው ላይ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ብለናል። ይፃፍ።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች፣ አመልካች በታሰረበት ማረሚያ ቤት በኩል ለአመልካች ይድረስ ብለናል።
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቀረበው የመዝገብ ቁ.03488 እና የአቤቱታዎች ግልባጭ በመጣበት አኳኋን ይመለስ ብለናል። ይፃፍ።
መዝገቡ ውሳኔ ስለአገኘ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.